cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ልብ አንጠልጣይ ታሪኮች

For Any Comment Contact @tarikoachBot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
132
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Watch "ትረካ" on YouTube https://youtu.be/pgSJlbwNtAI
Show all...
ትረካ

🔅🔅🔅🔅🔅ባንዳ🔅🔅🔅🔅🔅 .......ክፍል ሃያ ስምንት....... ፀሃፊ-ንፍታሌም 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 ‹‹ለምን እዚ ቆምን?››ሚሊያርድ ሳሮን ላይ አፈጠጠችባት ‹‹ዶ/ር ብሩክ ጋር ነዋ›› ሳሮን ሳቅ እንደማለት እያለች ‹‹ዶ/ር ብሩክ ዶ/ር ብሩክ ማነው?›› ግራ ተጋብታለች በዚ ሰአት የሳሮን መሳቅ ደግሞ ብሽቅ እያደረጋት ነው ‹‹ምሳ የጋበዘሽ ሰው ቤት ነዋ አሁን ስላረፈድን በፍጥነት ውረጂ ማርፈድ የለብኝም ስትይ አልነበር እንዴ?›› ኮስተር ብላ ስታያት ‹‹ሳሮን ምን ሆነሻል እዩኤል እኮ የመኪና አደጋ ደርሶበታል እባክሽ እሱ ጋር ውሰጂኝ…››እንባዎቿ ዝርግፍግፍ ብለው በአንዴ ተዝረከረኩ ‹‹እንደዚ አይነት ፍቅር አይቼ አላውቅም ታስቀናላችሁ …እዩኤል እዚ ነው ያለው …›› እያወራች ነበር ሚሊያርድ ግን የመኪናውን በር ከፍታ ስትወርድ እና ስትሮጥ የከፈተችውን በር እንኳን ሳትዘጋው ነው ‹‹ሚሊ ኸረ ሚሊያርድ ወይኔ እቺ ልጅ ሰርፕራይዙን አበላሸችው›› እየተከተለቻት እየተጯጯሁ ሲገቡ ጊቢ ውስጥ አንድም ኮሽታ የለም አንድም ነፍስ ያለው ፍጥረት ማለቴ ከታሰረው ውሻ ውጪ  ተንደርድራ ሄዳ የሳሎኑን በር ስትበረግደው የብዙ ሰዎች አስደናቂ ጩኸት እና የፌሽታ ኡኡታ ‹‹ሰርፕራይዝ›› የሚል በአንድነት የተዜመ የሚመስል ዜማ ነገር ጩኸት ነገር ደስ የሚል ፣የሚያስደነግጥ ግን ደስ የሚል፣የሚያስበረግግ ግን የእውነትም የሚያስደንቅ የብዙ ሰዎች ጥርቅም በአንድ ሳሎን ውስጥ የተዘጋጀ የልደት ዝግጅት ከዛ በኋላማ ትርምስምሱ ወጣ አንዱ የልደት ኮፍያ ሲያደርግላት አንዱ ቆይ የተገዛላትን ቀሚሷን ትልበስ እያለ ወደ መኝታ ቤት ሲወሰወዳት ሌላው ፀጉሯን እንዴት እናድርገው እያለ ሲጠያየቅ እስከዛ ሰአት ድረስ በትክክል የማን ልደት እንደሆነ አልገባትም ነበር ውጥንቅጡ የወጣ ነገር ሁሉንም ትታ በቤት ውስጥ ያለውን ሰው መመልከት ጀመረች በመጀመሪያ እዩኤልን በአይኗ መፈለግ ጀመረች ልታገኘው ግን አልቻለችም ዮናስን አየችው ከእህቱ ጋር ሰላም እየተባባለ ነው ዶ/ር ብሩክ መቶ ሰላም አላት እና ‹‹ወደ ቤቴ እንኳን ደና መጣሽ እና መልካም ልደት›› ብሎ እቅፍ አደረጋት ንፁህ አባታዊ ፍቅር ነበር እቅፉ ውስጥ ቀጥላ ሚስቱ መጣች እርጉዝ ናት ግራ የሚያጋባ ነገር ‹‹እንኳን ደና መጣሽልን ልጄን ከሞት የታደግሽ መልአክ ነሽ ለኔ›› ብላ እቅፍ ስታደርጋት አልቻለችም አይኖቿ እንባ አቀረሩ ፍቅር መታ እንቅ አድርጋ አቅፋ ደጋግማ ጉንጮቿን ሳመቻት የእዩኤልን እናት እራሷ ሄዳ ሰላም አለቻት ሌሎችም የማታውቃቸው እሷ ግን ያውቁኛል ብላ የምትገምታቸው ሰዎች በቤቱ ውስጥ ነበሩ ወደ መኝታ ቤት ይዘዋት ገቡ የሚያምር አበባማ ሮዝ ቀሚስ አለበሷት ፀጉሯን አስተካክለው ኳሏት የቀኑ ልእልት መስላለች በትክክል ዛሬ ልደቷ መሆኑን እንደሁል ጊዜው እረስታው ነበር ማስታወሻ ላይ በፃፈችው ቀን መሰረት ይሄንን ድግስ ለማዘጋጀት ሁሉም ቤተሰብ ስለተስማማ ዶ/ር ብሩክ ቀድሞ ቤቴን እይልኝ ብሎ ስለቀጠራት እንዳጠራጠር እሱ ቤት እንዲሆን ወሰኑ ‹‹እዩኤል እዚ ነው አላልሽኝም ነበር›› ልቧ አሁንም እዩኤል ደና መሆኑን አላመነላትም እሷን ወደዚህ ለማስመጣት የተጠቀሙበት ዘዴ መሆኑን ማመን አልቻለችም እስክታየው ልቧ ቸኩሏል ‹‹ይመጣል ምነው ናፈቀሽ›› ብላ ሳሮን ሳቀችባት ‹‹ሳሮን አትቀልጂ በአውነት እንደዚ አይነት ቀልድ በጣም ነው የሚደብረው ያንን ወንድምሽን ደሞ ላግኘው›› ዛቻዋ የቀልድ እንደሆነ ያስታውቃል ‹‹እንዴ እዚው እኮ ነው ለምን ሄደሽ አትቀጠቅጪውም ወንድሜን ሁለት ፍቅረኛሞች ቀጥቅጠው ሊገሉት ነው ብዬ ለፖሊስ አመለክታለው ›› ብላ ሳቋን ለቀቀችው ‹‹ሂጂ ሞዛዛ ››ብላ የቀልዷን እየመታቻት ሲቃለዱ ቆይተው ‹‹አልመጣችም ››የሚል የወንድ ድምፅ ሰሙ በሹክሹክታ ‹‹እዩኤል ነው ዝም በይ ››አለቻት ሳሮን ‹‹እማ አልመጣችም›› ፊቱን ክፍት እንዳለው መላ ሳሎኑን አማትሮ ደግሞ አየ ‹‹አልመጣም አለች ዮኒ ብሞትም ግድ የላትም ይሄንን ያህል ጠልታኛለች ››ንግግሩ ትንሽ ቢቆይ እንደሚያለቅስ ያስታውቅ ነበር እናቱ ከተቀመጡበት ብድግ ብለው ‹‹መታለች የኔ ልጅ እኔ ልከፋልክ ››እቅፍ አደረጉት ሚሊያርድም ከዚ በላይ መደበቅ አልቻለችም ስትወጣ እቅፍ ሙሉ አበባ ‹‹ይቅርታ ›› የሚል ፖስት ካርድ ይዞ ቆሟል አጠገቡ እቴቴ እና ፍላጎት ቆመዋል እሱ ያለበት መድረስ ፈራች ባለችበት ቆማ እያየችው የእንባ ዘለላ በጉንጮቿ ላይ መውረድ ጀመሩ ተጠጋ እና እግሯ ስር ተንበርክኮ ‹‹ይቅርታ አድርጊልኝ ሚሊ የኔ ፍቅር ይቅርታ ይቅር በይይኝ›› አብራው ተንበርክካ አቀፈችው አለባበሱ የተዋጣለት ቢሆንም በጣም ከስቶ ጠቋቁሯል ጭራሽ ያ! ሁሉ ሞገስ እና ግርማ ያለው እዩኤል አይመስልም ፊቱን እየደባበሰች ትኩር ብላ አየችው እስኪበቃው ድረስ እንቅ አድርጎ አቀፋት ፀጉሯን ግንባሯን ጎንጮቿን ደጋግሞ ሳማት በየተራ ሁሉም ሳሮንን ጨምሮ ዮናስ የእዩኤል እናት እና የዮናስ እናት ይቅርታ ጠየቋት፡፡ የልደት በአሏን ከብዙ ሰዎች ጋር እጅግ አምሮባት ተውባ አከበረች ድግሱ አልቆ ተሰነባብተው ሲወጡ ሚሊያርድን እዩኤል አቅፏት በብርድ እየተንዘፈዘፈች ስለነበር ጃኬቱን አውልቆ አልብሷት፣ዮናስ እልም ብሎ ሰክሮ ‹‹እዩኤልን ፍቅር ያስተማርክ አምላክ እኔንስ መቼ ነው የምታስተምረኝ?›› እያለ አምላኩን እየጠየቀ፣ሳሮን በሱ መስከርና መለፋደድ ተናዳ የስድብ ናዳ እያወረደችበት ነበር በመሀል መኪና ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ‹‹እዩኤል እባክህ አንዴ ሚስትን ላናግራት›› ሲል ፍቃድ ጠየቀ ‹‹ይቻላል ዶክተር ግን ገና እያገኘዋት ነው ቶሎ ቶሎ ነው የምትናፍቀኝ›› ብሎ ጥሏቸው መኪና ውስጥ ገባ ‹‹ደስ አለሽ ›› አላት ፊቷን በጥሞና እየተመለከተው ‹‹ከመቼውም ጊዜ በላይ በጣም አመሰግናለው ዶ/ር›› ብላ አቀፈችው መልሶ አቀፋት ‹‹ባለፈው አንድ ጥያቄ ጠይቀሽኝ ያልመለስኩልሽ ጥያቄ ነበር ›› ለማስታወስ ሞከረች ግን ምንም አልመጣላትም ‹‹አሁን በሂወትህ ደስተኛ ነህ ወይ ብለሽ ቤተሰቤን አየሽ ›› አላት ፊቱ በደስታ ፈገግ እያለ ‹‹ቆይ ቆይ ዶ/ር ሚስትህ እርጉዝ ናት ›› አለችው እሷም ፈገግታው የተጋባባት ይመስላል በአዎንታ አንገቱን ወዘወዘ ‹‹እንዴት ›› ኮስተር አለች መልሳ ‹‹የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል ይባል የለ ሚስቴ ሁለተኛ ልጅ ልትሰጠኝ ነው ›› በግርምት እየተመለከተችወ ‹‹አሁንም…›› ተናግራ ሳትጨርስ ‹‹አይ አይ የኔ ልጅ ነው ሁሉም ነገር በህክምን ተፈቷል ፍቅር የመጀመሪያ ልጄ አሁን ደግሞ ሁለተኛውን ልንቀበል ነው›› አቤት እርጋታው ‹‹በጣም ደስ ይላል በጣም ደስ ብሎኛል ብላ ደና እደር አመሰግናለው..›› መኪና ውስጥ ገባች፡፡ ‹‹የአባትሽን አድራሻ ሰጥሻለው ይሄ ያንቺ ውሳኔ ነው ልታውቂው ከፈለግሽ ሄደሽ እይው ግን ቀድመሽ እንድታውቂው ያህል ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነው›› አለቻት እቴቴ በወረቀት ላይ የተፃፈ አድራሻ እየሰጠቻት ለብዙ ሰአት አሰበችበት እና ለሳሮን ደወለችላት ‹‹ሳሪ ዛሬ ከቻልሽ አንድ ቦታ አብረሽኝ እንደትሄጂ ነበር በጣም አስፈላጊ ነው›› ፍቃድ ሞልታ እንደምትመጣ ነግራት ስልኩን ከአጉ በኋላ ልብሷን ለባብሳ በፍጥነት ወጣች እንደተገናኙ ‹‹የት ነው የምንሄደው ›› ሳሮን የሚሊያርደ ሁኔታ ምንም ደስ አላላትም ‹‹አባቴን ላገኘው ነው ግን በጣም ፈርቻለው›› ከፊቷ ፍርሀቷ በግልፅ ስለሚነበብ ይሄንን ለመረዳት አልከበዳትም ‹‹እርግጠኛ ካልሆንሽ ሌላ ጊዜ ማድረግ እንችላለን ›› ትከሻዋን አሸት አሸት አደረገቻት‹‹አይ ዛሬ ነው ማድረግ የምፈልገው ›› ከመኪና
Show all...
🔅🔅🔅🔅🔅ባንዳ 🔅🔅🔅🔅🔅 .......ክፍል ሃያ ሰባት....... ፀሃፊ-ንፍታሌም 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 ሀይቅ ጋር ሄዳለች ማንንም ማየትም ሆነ ማናገር አትፈልግም የሰማችውን ነገር ለመቀበል ገና እረጅም ጊዜ እንደሚወስድባት ተሰምቷታል እዛው አከባቢ የሚጠበሰው የአሳ ሽታ ሆዷን አላወሰው እዚ ከመጣች ሰአታት እንዳስቆጠረች እና ከነጋ ምንም እንዳልበላች የታወሳት የእራብ ስሜት ሲሰማት ነው መብላት ፈልጋለች ግን ደግሞ የሆነ የሚያስጠላ የብቸኝነት አባዜ መብላት እንዳትችል ቆልፏታል ልብላ አልብላ በሚሉ ሁለት ስሜቶች ተወጥራ ሳለች ከፊት ለፊቷ ሳሮን ስትመጣ አየቻት ዛሬስ በመምጣቷ አልተከፋችም የምታወራው ስው ፈልጋ ነበር   ‹‹ ስላንቺ ተጨንቄ እቤታችሁ መጥቼ ነበር እናትሽ ናበት እዚ እንደማገኝሽ የነገረችኝ አብሬሽ መሆን እችላለው?›› ወንበሩ ላይ መቀመጥ እንደምትችል ጠየቀች በአዎንታ አንገቷን ነቀነቀች ‹‹እናትሽ ነው ያልሽው?›› ‹‹አዎ ሁሉንም ነገር ነግራኛለች….›› በረጅሙ ተነፈሰች እና ቀጠለች ‹‹ወዳ አይደለም ይሄንን ለመቀበል ስሜቱ ከባድ እንደሆነ አውቃለው ግን እሷም በጣም ተከፍታለች እባክሽ ከባድ ጊዜ እያሳለፈች ነው ለመረዳት ሞክሪ›› ‹‹ለእረጅም ጊዜ ሰው ስፈልግ ነበር ግን አሁን ….›.እንባዋ ቀደማት መናገር ሲያቅታት አቀፈቻት እና ፀጉሯን ደባበሰቻት ‹‹መቀበል አልቻልኩም በሂወቴ አንድም ቀላል ነገር የለም ሁሉም ነገር እንደከበደ ነው ›› ‹‹ይገባኛል አንቺ ግን ጠንካራ ነሽ ሁሉንም አልፈሽዋል አሁንም አያቅትሸም ጠንከር በይ›› በእቅፏ ውስጥ ተመቻቸች እንደዚ ያለ ሰላም ከተሰማት እረጅም ጊዜ ሆኗታል ‹‹ስለመጣሽ አመሰግናለው ›› አለቻት ከተረጋጋች በኋላ ‹‹ይቅር የምትይኝ አልመሰለኝም ነበር በጣም በራሴ አፍሬያለው የሰራውት ስራ ትልቅ ስህተት ነበር ›› ተከፍታለች ‹‹ይቅር ብዬሻለው የተገናኘን ቀን ከእዩኤል ሴቶች አንደኛዋ ነበር የመሰልሽኝ ›› ሁኔታውን እስታወሰች ፈገግ አለች ‹‹ገምቻለው ግን እዩኤል ካንቺ ጋር ከተገናኘ በኋላ ስለሴት ያለው አመለካከት ተቀይሯል ›› በእርግጠኝነት ነበር የምትናገረው ‹‹ እሱን እንኳን መገመት ይከብዳል እርቦኛል ምሳ እየበላን እናውራ›› ‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው እንደውም እኔ ነኝ የምጋብዝሽ›› ተያይዘው ተነሱ ‹‹እዩኤል ያለበት ሁኔታ ጥሩ አይደለም ልታይው አትፈልጊም እርግጠኛ ነሽ?›› ትኩር ብላ ስሜቷን አጤነችው ፊቷ ተረባበሸ ‹‹እንደ ጓደኛ እውነቱን ልንገርሽ በጣም ይናፍቀኛል በአለም ላይ ካለ ነገር በሙሉ አስበልጨ ስለእሱ ነው የማስበው ግን በቃ አላውቅም ልቤን ሰብሮታል ይቅር ልለው አልቻልኩም›› አቀረቀረች እና እንዳታያት እንባዎቿን ጠረገች ‹‹ አውቃለው ይገባኛል በቃ ዛሬ ፕሮግራም ከሌለሽ አብረን መዋል እንችላለን ›› ስትላት እጇላይ ያሰረችውን ሰአት በፍጥነት ተመለከተችው ‹‹ወይኔ እረስቼው ነው ስምንት ሰአት ላይ አንድ ፕሮግራም አለኝ  በጣም ይቅርታ ማርፈድ የለብኝም ›› ‹‹ስምንት ሰአት አኮ ገና ነው ምሳ እንብላ እና መኪና ስለያዝኩ እኔ ሸኝሻለው ›› ፈገግ ብላ በሀሳቧ ከተስማማች በኋላ ምሳ የሚበሉበት ቤት ገቡ፡፡ ‹‹ችግር ያጠነክራል በችግር የተገኘ ፍሬ በልፋት በድካም የተገኘ ውጤት ጣፋጭ ነው አንድ ቀን እንደ ወርቅ ተፈትኖ ነጥሮ መውጣት አይቀርም ዛሬ አንድ ደስ የሚል ቀን ነው አዲስ ቀን እንደልሙጥ ወረቀት ነው የየራሳችንን ታሪክ በአዲሱ ቀናችን የምንፅፈው እኛው እራሳችን ነን ስለዚ አዲስ ቀንሽን እንዳታበላሺው ሁሉም ነገር ለመልካም ነው ብለሽ አስቢ እና ተቀበይው›› አለቻት ትኩር አድርጋ እየተመለከተቻት ‹‹እዩኤል እርግጠኛ ነኝ ዛሬ አንቺን እንደዚ በማድረጉ በጣም ይፀፀታል አንቺ ግን እሱን ይቅር ብትይው ምንም የሚጎልብሽ ነገር የለም በዛ ላይ አብራችሁ ደስተኛ መሆን የምትችሉ ከሆነ… ›› ቀና ብላ ስትመለከታት ልታጎርሳት የነበረውን ምግብ ቁጭ አደረገች እና ‹‹ስለ ሌላ ነገር እናውራ እባክሽ ከሁሉም ነገር መሸሽ ነው ፍላጎቴ›› በሚያሳዝን አስተያየት ተመለከተቻት ‹‹አዎ አውቃለው ግን ፍቅር እኮ ሸሽተሸ የምታመልጪው ነገር አይደለም ተጋፈጪው ከዛ ልብሽ እና ጭንቅላትሽን አስተባብሪያቸው ›› ጉርሻዋን ተቀበለች ‹‹መጋፈጥ አልችልም አልፈልግምም በቃ ነፃ ሕይወት እንዲኖረኝ  ነው የምፈልገው›› ስልችት እንዳላት ከንግግሯ መረዳት ይቻላል ‹‹አትችይም ከፍቅር መሸሽ አትችይም ብትፈልጊም እንኳን ›› ስልኳ ጠራ የማታውቀው ቁጥር ነው አንስታ ማናገር ጀመረች ‹‹ዮናስ እባክህ ሂወቴን እየረበሽክ ነው  ደሞ ምንድነው የሚያንተባትብህ?›› ተናግራ ከመጨረሷ ‹‹ምን!....አሁን የት ናችሁ…?››እጇመንቀጥቀጥ ጀመረ ፊቷ ግርጥት ብሎ ከመቅፅበት ልውጥውጥ አለ ‹‹እዩኤል ደና ነው? በናትህ ንገረኝ›› መልሱን ሳትሰማ ስልኩ ከጇ አምልጧት ወደቀ ‹‹ምንድነው? ማነው እሱ? ምን ሆነሽ ነው?›› መልሷ ሲዘገይባት በፍጥነት ሳሮን የወደቀውን ስልክ አንስታ ማናገር ጀመረች ‹‹ዮኒ ተረጋጋና እና የተፈጠረውን  በትክል ንገረኝ›› አለችው ሚሊያርድ በተቀመጠችበት ትንቀጠቀጣለች ስታወራው ቆየች እና ‹‹የመኪና አደጋ ነው የደረሰበት ›› አለቻት የደነገጠች ትመስላለች ‹‹እራስሽን አረጋጊ መረጋጋት አለብሽ ››ትከሻዋን ይዛ ለማረጋጋት ሞከረች እና እጇን ይዛ ወደ መኪናዋ... በፍጥነት መኪናዋን እያሽከረከረች አስፓልቱን እየሰነጠቀች በክላክስ የሰው ጆሮ እየበሳች ነዳችው በየመሀሉ ‹፣አይዞሽ በእራስሽን አረጋጊ›› እያለች ሚሊያርድን ታረጋጋታለች በመጨረሻ የሆነ ሰፈር ሲደርሱ አንድ ሰው ቤት በር ላይ መኪናውን ሲጢጢጢ…. አድርጋ አቆመችው      የመጨረሻው ክፍል ነገ ይለቀቃል 👍 ሲገባ ውድ አንባቢዎቻችን ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #አድ አና #ሼር አንድታረጉ በትህትና አንጠይቃለን አንዲሁም አስተያየታቹ አይለየን @tarikoachbot
Show all...
👍 7
🔅🔅🔅🔅🔅ባንዳ🔅🔅🔅🔅🔅 .......ክፍል ሃያ ስድስት....... ፀሃፊ-ንፍታሌም 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 ቀኑ እሁድ ነው እሁድ ማለዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ ሚሊያርድ ፣እቴቴ እና ፍላጎት ለባብሰው ሲወጡ ስልኳ ጠራ የማታውቀው ስልክ ነው አነሳቸው ‹‹ሄለው ›› ‹‹እንደምን አደርሽ ሚሊያርድ ዶ/ር ብሩክ ነኝ›› ሰላም የሚሰጥ እርግት ያለ አባታዊ ፍቅር ያለው ድምፅ ‹‹እንደምነህ ዶ/ር ጠፋህ እኮ ›› ልቧን ደስ ብሎታል አስታውሶ መደወሉም ይመስላል ያስደሰታት ‹‹አዎ ልክ ነሽ ዛሬ ግን ይኸው ተገኝቻለው እንዴት ነሽ ›› ኡፍፍ እርጋታው ሲያስቀና ‹‹በጣም ደና ነኝ ዶ/ር አንተስ ቤተሰብ ሰላም ነው›› ‹ይኸው ልታያቸው አይደል  ዛሬ  ስምንት ሰአት እኔ ቤት ነሽ እርግጠኛ ነኝ ሌላ ፕሮግራም የለሽም ›› ‹‹አይ የለኝም ዶክተር አቅጣጫውን ብቻ ላክልኝ እመጣለው በዛውም ፍቅር ምን እንደምትወድ ብትነግረኝ ›› በረጅሙ ሳቀ እና ‹‹ፍቅርማ የምትወደው አንቺን ነው በይ አትቀልጂ አርፋጅ ሰው ደግሞ አልወድም እሺ›› ስልኩን ተሰነባብተው ሲዘጉ ፍላጎት እና እቴት በጥያቄ እየተመለከቷት ነው የሰሞኑ ሁኔታዋ ምንም ደስ አላላቸውም ‹‹ ያከመኝ ዶ/ር ነው ምንድነው የምታፈጡብኝ›› አለቻቸው ‹‹አዎ እሱማ መቀጣጠራችሁ ነው እንጂ ያልገባን›› እቴት በእዩኤል ምክያት በጣም ስሜቷ  ስለተጎዳ አይሆኑ አኳኋን እንዳትሆን ፈርታላች ‹‹ውይ እቴት የመኪና አደጋ ደርሶባት ሆስፒታል ወሰድኳት ያልኩሽ ልጅ አባት እሱ ነው ፍቅር ትባላለች ልጁ:: ቤቱ ወስዶ ቤተሰቡን ሊያስተዋውቀኝ ፈልጎ ነው በቃ›› ቀለል አድርገው እንዲያስቡት ስለፈለገች ይመስላ አነጋገሯ ቤተ ክርስቲያን ከደረሱ በኋላ ፍላጎት ለመቁረብ ወደ ቤተ መቅደስ ስለተጠጋች ብቻቸውን መውጫው አከባቢ ቆሙ እቴት ያለ ወትሮዋ መቁነጥነጥ አበዛች ፊቷ መረባበሽ እና አለመረጋጋት ይታይባታል ‹‹እቴት ዛሬ ምን ሆነሻል ቆይ አመመሽ እንዴ?›› ሚሊያርድ አተኩራ አየቻት ‹‹ስላንቺ ተጨንቄ ነው የኔ ልጅ›› ፊቷ በፍርሀት ስትርድ በግልፅ ያስታውቃል ‹‹ስለ ዶክተሩ ከሆነ…›› ተናግራ ሳትጨርስ ‹‹ አይ አይ አይደለም የኔ ልጅ ›› ዛሬ ደግሞ የኔ ልጅ ማለት አበዛች ቅዳሴው አልቆ ፀበል እየተሰጠ ነው ‹‹ምንድነው እሱ ችግር አለ እንዴ እቴት?›› ፍዝዝ ብላ አየቻት ‹‹ሚሊያርድ አንድ ልነግርሽ የምፈልገው ነገር አለ ተቀመጭ ››እጇን ይዛ አስቀመጠቻት ክፉ ዜና እንዳይሆን ሚሊያርድ በልቧ ፀለየች ‹‹ይህንን ታሪክ መቼም እንዳልነግርሽ እማማ አስምላኛለች ከዚ በላይ ግን እንዲህ በብቸኝነት ስትሰቃይ ማየት አልችልም ›› አለች እና እንባዋ በመንታ መውረድ ጀመረ ‹‹ምንድነው እቴት ንገሪኝ?››  ሁሉ ነገርዋ ወሬውን ለመስማት አቆበቆበ‹ም ‹እንዴት እንደምነግርሽ አላውቅ ››እጆቿነ በጭንቀት አፍተለተለቻቸው ‹‹እኔንም እያስጨነቅሽኝ ነው እቴት››ድንገት ቀና አለች እና ‹‹ትክክለኛ እናትሽ እኔ ነኝ እኔ ነኝ እናትሽ የኔ ልጅ›› ብላ እያለቀሰች ስትጠመጠምባት አናቷን በትልቅ ፍልጥ እንደተባለ ሰው ድርቅ ብላ ቀረች እስከዛሬ እያወቀች እንዳላወቀች እያስመሰለቸ መኖሩን እንዴት ቻለችበት? የእናትነት ፍቅሯ ሌላ ሰው ‹‹እማ ›› ብዬ ስጠራ መስማት እንዴት አስቻላት? ለምን ጣለችኝ? እና ሌላም ሌላም  ብዙ ጥያቆዎች በጭንቅላቷ ሲመላለስ  በእቅፏ ውስጥ እንዳለች እንባዎቿ መዘርገፍ ጀመሩ ‹‹ለምን ለምን ጣልሽኝ ግን?›› ስቅቅ ብላ ስታለቅስ እቴቴም በለቅሶ አጀበቻት ‹‹በጣም አዝናለው ይቅር በይኝ የኔ ልጅ ፈልጌ ያደረኩት ምንም ነገር የለም አማራጭ ስላጣሁ ነው አንቺን ማሳደግ አልችልም ነበር ›› እቅፏን መንጭቃ ወጣች እና ‹‹እና ለምን ወለድሽኝ አባት አለኝ? አባቴ ማነው?›› አይኗን ማየት አሳፍሯት መሬት መሬቱን እያየች ጠየቀቻት  ከዚ በኋላ ከእሷ ጋር እንዴት የእናት እና ልጅ ግንኙነት መመስረት  እንዳለባት እያሰበች ግራ ተጋብታለች ‹‹አባትሽ በጣም የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ነው እነሱ ቤት ተቀጥሬ ስሰራ ነው ይሄ የተፈጠረው ፍቅር ይዞኝ ነበር ከሱ ጋር ቤተሰቦቹ ግን ስለክብራቸው ሟች ነበሩ እና እንዳረገዝኩ እንዳወኩ ሆዴ ሳያስታውቅ ከዛ ቤት ወጣሁ ላሶርድሽ አልፈለኩም ነበር አንቺን ለማሳደግ ያላየሁት ፈተና እና ስቃይ የለም የኔ ልጅ ዘጠኝ ወር ተሸክሜ አምጬ የወለድኩሽ እኔ ነኝ››   ‹‹ለምን ጣል ሺኝ››  ‹‹ሌላ አማራጭ አልነበረኝም የኔ ልጅ ግን ሁሉንም  ነገር አቅጄ ነበር ያደረኩት የእማማን ደግነት ስሰማ እሷ በር ላይ ልጄን ጣልኩ እና በሁለተኛው ቀን ያንቺ ሞግዚት ሆኜ ተቀጠርኩ ›› ፍላጎት ፀበል ይዛ ስትመጣ ከርቀት ትታያለች ‹‹እና አባቴ አባት መሆኑን አያውቅም ማለት ነው?›› አንገቷን በመነቅነቅ አዎንታዋን አረጋገጠችላት ‹‹እናትም አባትም እያለኝ ለምን እንዲህ በብቸኝነት እንድሰቃይ ይህንን ሁሉ መከራና ስቃይ እንዳሳልፍ ሆንኩ? ለምን ምን አጠፋሁ? እቴት ለምን ለምን ጣልሽኝ? የተጣልኩ ልጅ ማንም የማይፈልገኝ ነኝ ብዬ ሳምን የት ነበርሽ?›› ሳግ እንቅ እንቅ አደረጋት ‹‹ ለእማማ ቃል ገብቼላት ነበር ልጄ መሆንሽን እንዳልናገር ›› ‹‹ታዲያ አሁን ቃልሽን ለምን አፈረሽ ምን ተገኘ? አሁን እናቴ መሆን ለምን ፈለግሽ?›› ‹‹እራስሽን ለማጥፋት የሞከርሽ እለት መፈጠሬን እስክጠላ ድረስ እራሴን ወቀስኩ የዛን ቀን አንድ ነገር ሆነሽ ቢሆን ኖሮ መቼም እራሴን ይቅር አልልም ነበር ለዛ ነው ልነግርሽ የወሰንኩት በቃ የእኔ ልጅ ነሽ ›› ልታቅፋ ስትል ‹‹አይ ይሄንን ነገር እውነት ነው ብሎ አምኖ መቀበል ከብዶኛል ትንሽ ጊዜ ያስፈልገኛል›› ተነስታ ስትሄድ ፍላጎት አጠገባቸው ደርሳ ነበር ፡፡ አንዳንዴ ወይም ብዙ ጊዜ በሂወት ወጥመድ እንጠለፍ እና መውጫው ቀዳዳ ጠፍቶብን ወይም እያወቅነው እንኳን በፍርሀት መድፈር አቅቶን እዛው ስንደነቃቀፍ እረመጥ በእረመጥ እያድበሰበስነው እንደታመቀ እንኖራለን የታመቀ ነገር አንድ ቀን መፈንዳቱን የምናውቅ አይመስላኝም የሂወት ድርና ማግ ተተብትቦ ውሉ ይጠፋብናል ሂወት የባለቤቱ ውሳኔዎች ጥርቅም መሆኑን እንዘነጋው እና ውጥንቅጥ ውስጥ እንገባለን ብዙዎቻችን የሚያስደስተን ነገር የቱጋር እንዳለ እናውቃለን ግን ይቅር ማለት ያለብንን ይቅር ብለን ወደፊት ለመራመድ ሳንችል ቀርተን የወደፊቱንም ደስታችንን በባለፈው እናጨልመዋለን ለዚህ ነው ደስተኛ መሆን ያልቻልነው የእውነት ደስተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ምንም እንደማያውቅ ጨቅላ ልባችሁን ከቂም እና ከክፋት አርቁ ቀጣይ ክፍል ቶሎ እንዲለቀቅ ❤️ @tarikoach @tarikoach
Show all...
❤️ 7
Letefetere chigr betam ykrta enteykalen 🙏🙏
Show all...
🔅🔅🔅🔅🔅ባንዳ🔅🔅🔅🔅🔅 .......ክፍል ሃያ አራት....... ፀሃፊ-ንፍታሌም 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 ‹‹ከእኔ ምንድነው የመትፈልጉት እሺ ምንድነው ማድረግ የምትፈልጊው ከልጅሽ እንድርቅ ከሆነ የምትፈልጊው አስቀድሜ አድርጌዋለው አታስቢ ›› ግንባሯ ላይ የሚገኙት ደምስሮቿ ተገታተሩ ‹‹ሚሊያርድ ባንቺና በእዩኤል መካከል በትክክል ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ግን ከነገሮች ሁለት ነገር ተረድቻለው አንደኛው ልጄ ከምታስቢው በላይ ያፈቅርሻል እዩኤል እንደዚ ሆኖ አንድም ቀን ቢሆን አየዋለው የሚል ግምት ኖሮኝ አያውቅም ፣ሁለተኛው ግን የልጄ ጥፋት በቸልተኝነት ያጠፋው ይሄ ይመስለኛል ›› የእራሷን ማሰታወሻ አውጥታ ስትሰጣት በውል ያልታወቀ ትርምስምስ ያለ ስሜት ተሰማት ደብተሩ ተንገላቷል ተገንጥሎ እንደተለበደ ያስታውቃል ‹‹ አሁን በቃችሁ? ተቀባብላቸሁ አንብባችሁ ጨረሳችሁ? ልጇ የሰረቀውን ደብተር እናት ልትመልስ መምጣቷ ጥሩ ነገር ነው ›› ፍዝዝ ባላ ታያታለች ‹‹ከጨረስን አሁን ልሂድ ››ደብተሩን ይዛ ተነሳች ‹‹እሱ አንቺን ማፍቀሩ ምንም ስሜት አይሰጥሽም?›› በመገረም የምታያት መሰላት ‹‹እኔ እንጃ አሁን ላይ ምን እንደሚሰማኝ እንጃ በፊት ግን….ምን ነበር ያለምኩት እንኳን አዎን በእያንዳንዱ ደቂቃ ውስጥ ደጋግሜ የመተንፈስ ያክል አስበው አልመው ነበር ጠዋት እና ማታ እሱን ብቻ በልቤ እመኘው ነበር አሁን ግን አበቃ አልቋል ›› ‹‹እና ልጄን ይቅር አትይውም ማለት ነው›› እናት ልቧ ክፉኛ ታመመ ‹‹አይ ይቅር ብዬዋለው ለእሱም ይቅር እንዳልኩት ንገሪው ይቅር ማለት ባህሪዬ ነው ያደረገውን ግን መቼም እንደማልረሳለት እና ድጋሚ አይኑን ማየት እንደማልፈልግም ጭምር ንገሪልኝ አንቺ ደግሞ እባክሽ ድጋሚ እኔን ለማግኘት እንዳትመጪ›› ጥላት ስትሄድ ከወራት በፊት የተዋወቁበትን ቀን እረገመችው ነበር ሰው አንዳንዴ ፍላጎቱን ባያውቀው ይሻላል ማወቅ መታመም ነው እውቀት መድሀኒት የሆነውን ያህል በሽታም ነው ፣እውነትን አውቆ ምንም ማድረግ አለቻል አዎ መታመም ነው፣ሊጋፈጡት የማይችሉት ባላወኩት ብለው የሚመኙትን ነገር ማወቅ አዎ መታመም ነው ያውም የማያባራ ለዘመናት ውስጥን የሚጠዘጥዝ ህመም፡፡ የዮናስ እናት ወደ እቤት ስትመለስ በር በሩን በጉጉት እያየ የጠበቃት እዩኤል ገና እንዳያት ከፊቷ  የተፈጠረውን ተረዳ ‹‹ ጠልታኛለች ዮናስ ጠልታኛለች መቼም ዳግም አታፈቅረኝም ›› ፊቱን ክፍት አለው ‹‹እዩኤል እባክህ በመጀመሪያ የተፈጠረውን እንስማ›› ዮናስ ሊያጋጋው ሞከረ ‹‹እማ ዝም ብለሽ እኮ ነው የደከምሽው አይኑን ማየት አልፈልግም አለችሽ አይደል ይቅር አትለኝም አይደል ብዙ በድያታለው አውቃለው ግን እኮ ልመልስላት ፈልጌ ነበር አሁን ግን ሁሉ ነገር እረፈደ›› ‹‹ልጄ ምን ላድርግልህ እንግዲህ በጣም ልቧ ተሰብሯል በጣም አዝናለች›› ‹‹ይሄ ያንተ ብቻ ጥፋት አይደለም የተፈጠረውን ሁሉንም ነገር እኔና ሳሮን እናስተካክለዋለን የተፈጠረውን ሁሉንም እውነቱን እንነግራታለን›› ዮናስ የእዩኤልን ጭንቀት ለማስታገስ ሞከረ ‹‹አትችልም ዮናስ አትችሉም እማማን ሁላችሁም እንዳትደርሱብኝ ብላ አባራታለች ›› ‹‹በድጋሚ አይኑን ማየት አልፈልግም ብቻ ይቅር እንዳልኩት ንገሪው ብላኛለች ላንተ ቀላል እንዳልሆነ አውቃለው ልጄ ግን ትንሽ እራሷን እስክታረጋጋ ጊዜ ስጣት ›› ‹‹አልችልማ እማ አልችልም …አልቻልኩም ›› ሳያስበው እንባዎቹ ዝርግፍ ዝርግፍ አሉበት ‹‹                            ‹‹                            ‹‹ ሚሊያርድ እቤት እንደደረሰች ማስታወሻዋን እየቀደደች በክብሪት ማቃጠል ጀመረች በዚህ ማስታወሻ በእያንዳንዱ ሉክ በጣም ብዙ እንባ ፣ብዙ ስቃይ ፣ትንሽ ደስታ በጣም ትንሽ ፌሽታ ተፅፎበታል እያንዳንዱ ሉክ ላይ የፃፈቻቸውን እያነበበች ሁኔታዎችን እያስታወሰች አነባች ፊቷ እስኪግል ድረስ ዳግም እነዚህን መጥፎ ትዝታዎች ላታስታውሳቸው ተሰናበተቻቸው የመጨረሻውን ሉክ ላይ ስትደርስ ግን ማንበብ ጀመረች፡፡ ኤልሻዳይ ውዴ አሁን መላ ዙሪያዬን ሰላም እና ደስታ ይሰማኛል አሁን ሂወቴን እንዳዲስ እየጀመርኩ ነው ፍሬ ስራ የምትጀምርበት ብር እንዳበድራት ስትጠይቀኝ ፣ሚኪ እስር ቤት ደጋግሜ ሄጄ ስጠይቀው የሚሰማው ስሜት እና የሚመክረኝ ምክሮች እቴት እና ፍላጎት የሚሰጡኝ የማያልቅ ፍቅር ሁሉም ነገር እንደገና እንደጀመረ እንደበፊቱ ደስተኛ ወጣት መሆን እንደምችል ተረዳው ያቋረጥኩትን ትምህርት ጀመርኩ ጊዜ ጊዜን ሲረታ ቀናት ቀናትን ሲወልዱ ሁሌም በሂወት አዲስ ነገር መፈጠሩ የማይቀር ነው ይሄም የሚጠበቅ ነው በሂወት ኡደት ውስጥ የማግኘት እና የማጣት ውጣ ውረድ የተለመደ ነው ያገኙትን ማጣት ህመሙ ከባድ ነው የዛን ያህል ደግሞ ያጡትን ማግኘት ደስታው ወደር የለውም አሁን ቤተሰብ አለኝ የእኔ ትእግስት እና ሰላምን መሻት የፈጠረው ሰላማዊ ቤተሰብ እናም ደስተኛ ነኝ ማንም ሰው ነገ ምን እንደሚፈጠር በእርግጠኝነት መናገር አይችልም የምን ነገ ኸረ አሁን በዚህች ቅፅበት እንኳን ምን እንደሚፈጠር ማን ያውቃል ነገን ፍሩ ስለነገ መልካም እንሁን ስስታም ድሎት የለውም ብዬ በእርግጠኝነት መናገር እችላለው ምክንያቱም እድሜ ልኩን ሲሰስት ነው የሚኖረውቀናተኛም ደስታ የለውም ውሸታምም እምነት የለውም እውነትን እምነትን እወዳለው ለስህተት ግን ይቅርታ አደርጋለው ይቅር ብያቸዋለው ፡፡ ይላል ይሄንን የመጨረሻ ሉክ ስታቃጥል ‹‹እዩኤል አንተ ግን ከማንም በላይ ሳምንህ ከዳኸኝ ›› እንባዋን መቆጣጠር ፈልጋ ነበር ከማስታወሻዋ ጋር አብራ ትውስታዋንም ስለሱ የሚሰማትንም ስሜት አብራ ያቃጠለችው፣ የቀበረችው መስሏት ነበር ግን ስለእሱ አለማሰብ አልቻለችም ውስጧን ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት እየተሰማት ዞር ስትል እዩኤል ፊት ለፊቷ ቆሟል፡፡ ይቀጥላል
Show all...
👍 5
🔅🔅🔅🔅🔅ባንዳ🔅🔅🔅🔅🔅 .......ክፍል ሃያ አምስት....... ፀሃፊ-ንፍታሌም 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 ‹‹ገና ያየውሽ ቀን ነው ስላንቺ የተለየ ስሜት የተሰማኝ ይሄንን አለመቀበል ትችያለሽ ግን እውነት ነው›› ‹‹ለዛ ነው ማስታወሻ ደብተሬን የሰረቅከው እስቲ ንገረኝ ስላፈቀርከኝ ነው ሚስጥሬን አደባባይ ላይ ያወጣኸው?››  ቀድሞ ሲሰማት የነበረው ሀዘን ወደ ቁጣ ተቀየረ ‹‹አስቤ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ሁሉም ነገር ያጋጣሚ ውጤት ነው እምልልሻለው›› ‹‹አጋጣሚ አልከው ስንት ጊዜ ነው አይኔን እያየህ የካድከኝ? ስንት ጊዜ ነው እንደልጅ ያታለልከኝ ሁሉም ይቅር ተሳስቶ ቦርሳህ ውስጥ ገብቶ ከሆነ ፈልግልኝ ብዬ አልጠየቅኩህም? አንተ ግን ደጋግመህ ዋሸኸኝ ›› ‹‹የዛኔ ደብተሩ ዮናስ ጋር ነበር በነጋታው አምጥቼ ልሰጥሽ ፈልጌ ነበር ግን ጠፋ አለኝ እኔስ ደውዬ ልመልስልሽ ስል ደግመህ እንዳትደውል አላልሽኝም ›› ‹‹አሁን ስለዚ ጉዳይ ማውራት ምን ይረባል በቃ አሁን ከዚ ሂድ›› ‹‹ይቅር በይኝ እባክሽ ሚሊ አጥፍቻለው አሺ አውቃለው በጣም እንደጎዳውሽ አንድ እድል ስጪኝ›› እየተጠጋ ነው ‹‹አልገባህም እንዴ እዩኤል ለእናትህ እኮ ነግሬያታለው ይቅር ብዬሀለው ዳግም ግን አይንህን አይንህን ማየት አልፈልግም አብቅቷል በቃ ›› ‹‹ተይ እንደዚ አታድርጊኝ ተይ ገና እኮ መጀመራችን ነው ሚሊያርድ ለምን እንደዚ ጨከንሽብኝ ደጋግሜ እኮ ልነግርሽ ሞክሬ ነበር ፖሊሶች መተው የወሰዱኝ ቀን ልነግርሽ ነበር የመጣውት›› እጇን ያዛት አልቧታል ልቧ ሲንሸራተት እየተሰማት ነው እዩኤል እየሸነገላት ያለ መሰላት ትኩር ብላ አየችው እና ‹‹አዝናለው ግን አንተን ይቅር ማለት አልችልም ዳግም ላምንህ አልችልም እዩኤል ››እንዲሄድ የመውጫውን በር ከፍታ ቆመች ደክሟታል በቃ ይሄ ሁሉ ውጥንቅጡ የወጣ አንድም ደስ የሚያሰኝ ነገር የሌለበት ኑሮ አድክሟታል ያለ አንዳች ቃል በከፈተችለት በር እዝን ክፍት እንዳለው ወጥቶ ሲሄድ እየተጎተተ ደጋግሞ ዞሮ እየተመለከታት ነበር እሱን ላለማየት ፊቷን ወደ ቤታቸው አዙራ እንባዋን ትጠርጋለች ፡፡ ወደ እቤት ከገባች በኋላ ስቅስቅ ብላ ሀዘኗን በእንባዋ አጠበችው ከመላ አካሏ አንዳች ትልቅ አካል ተነጥሎ እንደተወሰደ ነገር ውስጧ ባዶ ሆነባት ምንም ብታደርግ ልትሞላው እንደማትችል ታውቋታል ይሄንን ሁኔታ ግን መላመድ እንዳለባት አስቀድማ ወስናለች በብዙ ነገሮች እራሷን ለመጥመድ ስለፈለገች እሱን ላለማሰብ ብዙ ስራዎችን ስትሰራ ትውላለች ባልተለመደ ሁኔታ ግን በጣም ነጭናጫ ሆነች በእያንዳንዱ ነገር ጥል እና ቁጣ የቀናታል ወደ እራሷ ስትመለስ ደግሞ መልሳ በሰራችው ስራ አፍራ ይቅርታ ትጠይቃለች ትምህርት ቤት ትሄዳለች እንጂ ምን እንደተማረች እንኳን ሳታስተውል ትመለሳለች ለመዋል ያህል ትሄዳለች አንድ እለት ከትምህርት ቤት ስትመለስ  ‹‹ሚሊያርድ! ሚሊያርድ›› ተደጋግሞ ስሟ ሲጠራ ዞራ አየች ‹‹አቤት ›› ግራ ተጋብታለች  ‹‹ዮናስ እባላለሁ ›› ‹‹እሺ ዮናስ ምን ልርዳህ?›› ‹‹አውቀሽኛል?›› አስተያየቱን አሎደደውም ‹‹በአንድ ማስታወሻ ምክንያት አሁን ታዋቂ ሆኛለው አንተ ካወከኝ አይበቃም የእዩኤል የልብ ጓደኛ ዮናስ! ›› አለችው ኮራ ብላ ‹‹በትክክል! ትንሽ ደቂቃ ይኖርሻል ››ፀጉሩን አከክ አከክ አደረገ ‹‹ፍቃዴን እየጠየቅከኝ ከሆነ አለማውራት እመርጣለው›› እንደማይተዋት አስቀድሞ ገብቷታል ‹‹እባክሽ ብዙ ሰአት አልወስድብሽም ቢያንስ የተፈጠረውን እንዳስረዳሽ እድል ስጪኝ ›› ‹‹ያው ነው አንተም የእዩኤል ድምፅ ነህ እሱ መናገር ያልቻለውን ነው አንተ የምትናገርለት››   ‹‹እዩኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ካንቺ ጋር ተገናኝቶ ሲመጣ ‹ቀና ልበ መልካም ሴት ተዋወቅኩኝ› ብሎ ነበር የነገረኝ ታምኛለሽ ስለ አንድም ሴት እዩኤል እንደዚ አስቦ አያውቅም ገና ሳገኘው ፊቱ በፈገግታ ያበራ ነበር ያየሽ ቀን ነው የወደደሽ ›› ‹‹ሊሆን ይችላል ሰውን መውደድ ጥሩ ነው ይሄንን ማወቄ ግን አሁን ለውጥ የለውም  የእኔ እና የእሱ ነገር አሁን አብቅቷል›› ትከሻዋን ሰበቀች በከንቱ አትድከም አይነት ይመስላል ‹‹አይንሽ ውስጥ ግን የማየው ሌላ ነው አሁንም ፍቅርሽ አላለቀም ደጋግመሽ ይቅር ስለማለት ማስታወሻሽ ላይ እኮ ፅፈሻል የማታደርጊውን ነው እንዴ የፃፍሽው?›› ‹‹በቃ አሁን ልሂድ ›› ፊቷ መረበሽዋን ይናገራል ‹‹ስለምንም ነገር ማወቅ አትፈልጊም ለምሳሌ እዩኤል ለምን እንደታሰረ?›› ‹‹እሱን ማወቄ ለውጥ ያመጣል ብለህ ታምናለህ?›› ‹‹ምን አልባት… ባንቺ ምክንያት ነው ›› ‹‹ምን!... በእኔ ምክንያት?›› ‹‹አዎ ላንቺ ሲከራከር፤ማስታወሻሽን በመጣሌ ተናዶ እኔን በቦቅስ መቶኝ ጥርሴን ስላወለቀ ነው የታሰረው›› ‹‹አሁን ገና የሚጠቅም ነገር አወራህ እስካሁን ከሰማውት ይሄ የተለየ ነው ›› ‹‹ገና አልጨረስንም እኮ›› እጆቹን እያወናጨፈ ‹‹ሌላ ጊዜ እንቀጥላለን ›› ብላ ጥላው ሄደች ሊያልቅ 2 ክፍል ብቻ ቀረው እንደ 👍 ብዛት አይቼ ነገ 26 ይለቀቃል 🙏መልካም አዳር🙏                       @tarikoach
Show all...
👍 4
ከ ገጣሚ መድብል ከተመቻችሁ 👍 ካልተመቻችሁ 👎
Show all...
👍 2
👎
🗞🗞ከገጣሚያን መድብል🗞🗞 📜" ደጄ ሰላም"📜 🖌 እንዳለ ወርቁ 〰〰〰〰〰〰〰 በዚያቅጥር ግቢ-ሁካታ ሲጠፋ የመቻቻል ጥበብ እጅጉን ሲስፋፋ ከዋይታ ግርግር አለም ነጻ ወጥታ ሲሰፍን ጸጥታ ክፉና በጎውን ሁሉን ቢቀበሉ ከፉን ደላን ባይሉ የመንደሩ ሰዎች እንግዳ ቢወዱ ቁም ቢሉት አልቆመም ይነጉዳል ትውልዱ 🇪🇹ጣፋጭ ትረካዎች🇪🇹 ✏️5
Show all...
🗞🗞ከገጣሚያን መድብል🗞🗞 📜" ፀፀት_ያሸንፋል"📜 🖌 በርናባስ ከበደ 〰〰〰〰〰〰〰 ፍቅር ሲሰጥ ኖሮ ለቀረበው ሁሉ ሳይሰስት መንዝሮ - ያ የእምነት ማማ አምድ ሆኖ የኖረ በንፋስ ሽውታ ወድቆ ተሰበረ! - አያ ፀፀት ብርቁ፤ እርሙን ሰው ቢያስቀይም ጥይት ጎርሶ እልም !!!! 🇪🇹ጣፋጭ ትረካዎች🇪🇹 ✏️6
Show all...