cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከአሪፎች ሀድራ የሙሀባዉ ዙላል

የተለያዩ አላህን (ሱብሀነሁ ወተአላን)የሚዘክሩና ረሱላችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን ) የሚያወድሱ የመንዙማ ግጥሞች እና የደጋግ ሰዋች(የወልዮች) ታሪክ(ቂሳዎች) ን እንታደማለን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
200
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰዪዲ ኢማም አን-ነወዊ'ይ « ሷሊሖችን በመውደድ የሚገኘውን ጥቅም ለማግኘት ስራቸውን መስራት መስፈርት አይደለም .. ስራቸውን ከሰራማ ከነሱና እንደነሱ ሆነ ማለት ነው ..» 📗 ሸርሕ ሶሒሕ ሙስሊም : 16/186 https://t.me/mededulhabib
Show all...
ኢብኑ ረጀብ አል-ሐንበሊ'ይ ረሒመሁሏህ : «በትዕግስት ከጭንቀት መውጣትን መጠበቅ እራሱ አላህን መገዛት ነው .. መከራ ዘውታሪ አይደለምና» https://t.me/mededulhabib
Show all...
«ሱልጧኑል ዑለማእ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ዓሊም ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም (አል-ዒዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም) ዲመሽቅ በነበሩበት ጊዜ በጣም ከባድ የኑሮ ውድነት ተከስቶ ነበር ። ነገራቶች ከመወደዳቸው የተነሳ ትናንሽ እርሻ ቦታዎችና ጋርደኖች በርካሽ ይሸጡ ነበር ። የሰዪዲ ዒዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም ባለቤትም አንድ የነበራትን ጌጥ አውጥታ " እስኪ አንድ የሆነ እርሻ መናፈሻ ነገር ግዛልን በበጋ ሙቀት ግዜ አረፍ የምንልበት ብላ ትሰጣቸዋለች" እሳቸውም ወስደው ይሸጡትና ገንዘቡንም ሰደቃ ሰጥተውት ይመጣሉ። ገዛህ ወይ ብላ ስትጠይቃቸው : " አዎ ገዝቻለው .. ጀነት ውስጥ ። ሰዎች በጣም ጥበት ውስጥ ሆነው ሳያቸው ገንዘቡን ሰደቃ አደረግኩት " አሏት እሷም : " ጀዛከሏሁ ኸይረን " አለቻቸው ..»☺️ 📗 ጦበቃት አሽ-ሻፊዒየቱል ኩብሯ : 8/214 https://t.me/mededulhabib
Show all...
አል ሓፊዝ አልሚዝዚ'ይ (742 አ.ሂ.) ረሒመሑሏህ : « የማያውቅ ዝም ቢል ኖሮ እራሱም አርፎ ሌላውንም ያሳርፍ ነበር .. ስህተትም አንሶ እውነት ይበዛ ነበር » https://t.me/mededulhabib
Show all...
Photo unavailable
«ቤታችን ውስጥ ካምፕም ሆነ መሳርያ የለንም... ከአላህ ጋር የመተሳሰር ፣ አላህን የመተማመን ፣ አላህ ላይ የመመካት ፣ አላህን የማስታወስና ሰይዳችንን ሙሀመድ ቢን ዐብዲላህን ﷺ የመከተል መሳርያ ቢሆን እንጂ ! ይሄ ነው መሳርያችን ! በዱንያም በአኼራም የትኛው መሳሪያ እንደሚያሸንፍ እስኪ እናያለን ! » 🟢 ሰይዲ ሀቢብ ዑመር ቢን መሀመድ ቢን ሳሊም https://t.me/mededulhabib
Show all...
ዛሂዱ ተቂዩ ሙጃሂዱ የምርጡ ሰለፎች ዘመን ምርጥ ሰዪዲ ዐብዱሏህ ኢብኑል ሙባረክ ተጠየቁ .. «ሰዎች ማለት እነማን ናቸው ? » እሳቸውም : «ዑለማዎች» አሏቸው «ወራዳዎችስ ?» ተብለው ሲጠየቁ «እነዛ ዱንያን በዲን ስም የሚበሉ» ብለው መለሱ 📗 ኢማሙል ጓዛሊ'ይ - ኢሕያእ ዑሉሙዲን : (1/7) ፡=========================== https://t.me/mededulhabib
Show all...
Photo unavailable
{ وَمَا جَعَلْنَا لِبَشَرٍ مِّن قَبْلِكَ الْخُلْدَ أَفَإِن مِّتَّ فَهُمُ الْخَالِدُونَ * كُلُّ نَفْسٍ ذَآئِقَةُ الْمَوْتِ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ } سورة الأنبياء «(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም ፡፡ ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን ?! ..ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ » ፡========================== እዚች ዱንያ ላይ አንዳች ነገር ዘውታሪ እንዲሆንልህ አትጠብቅ .. እራሷ ዱንያም ጊዜያዊ ናት ! አላህ በወደዳቸውና ባከበራቸው ባርያዎቹ በረካ ኻቲማችንን ያሳምርልን ። ሸይኻችን ሰዪዲ አል-ሐቢብ አቡበክር አል-መሽሁር አል-ዐደኒ'ይንም አስደሳች ነገር ሁሉ ዘውታሪ በሆነባት የጀነት ሀገር ድጋሚ አይናቸውን የማየትና እግራቸው ስር የመቀመጥን እድል አላህ በረሕመቱ ይስጠን https://t.me/mededulhabib
Show all...
Photo unavailable
" ዚክር የሚያበዛ ልቡ ሁሌም ወደ ጌታው ተሳፋሪ ነው ፤ ፍቅርና ውዴታ ይሞላዋል ፤ የተለያየ ጉዳዮችና ስራዎች ቢመጡበትም አካሉ እንዳለ ሆኖ ልቡ ግን የውዴታና የእርጋታ ሰማይ ውስጥ ይበራል ፤ በማንኛውም እንቅስቃሴም ሆነ እርጋታ ከጌታው ጋር ነው " ሰለዋት በማብዛት ጉዳዮቻችን ይፈቱ ፣ ቀልባችንም ይፅዳ ፣ ወደ ጌታችንም እንቃረብ https://t.me/mededulhabib
Show all...
Photo unavailable
💚አለይከ ረበና ቢሁስነል ሂታሚ 💚ያ ረበና ቢሁስነል ሂታሚ 💚ቢጃሂ ሰይዲ ሰይዲል አንአሚ 💚ኢንደ ተወፊቅና ሊሁሰለነል ሂታሚ 💚ያ ረበና አለይሂ ሰላሚ 💚አለይከረበና ቢሁስነል ሂታሚ 💚ያ ረበና ቢሁስነል ሂታሚ.....
Show all...
ተፃፈ በ Kedir Taju አንተ-ሆየ፥ አዳምጠኝ፦ አንድ! (“Shock-Therapy/አስደንግጦ ማከም”) መዳረሻውን ቀድሞ ያቀደው አካል፣ በዕቅዱ መሠረት፣ ዛሬ ካቀደው 'ቦታ' ላይ ደርሷል። ህልሙን አፍሷል። አንተ የዕቅዱ አካል ወይም አባል አልነበርኽም። አንተ አሁን ያለህበት ሁኔታ፣ ወደፊትም የሚገጥምህ እክልታ፣ የእርሱ 'ቁብ' አይደለም። እንዲሆንም አይፈልግም። ቢሆንም አይመኝም። ምናልባትም ሁኔታህ፣ የዕቅዱ ክፍል አለመሆኑንም አስረጋጭ ኃይል የለም። አሏሁ የዕለም። አንተ ግን አሁን ቁም! ‹‹ምንድር ነው የተደረገው/የተፈጠረው? እኔ የሆንኹት ምንድር ነው?›› በል። የባህር-ማዶ ልሂቃን “Shock-Therapy(አስደንግጦ ማከም)” የሚሉት ንድፈ-ሀሳብ(Theaory) አላቸው። አንድን ተረጋግቶ የቆየ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት በሌላ ለመተካት የሚታገዙበት ዘዴ ነው። ባለቤቱ Milton Friedman(d-2006) ናቸው። የቺካጎ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነበሩ። “የShock-Therapy የጥበብ አባት” ተሰኝተዋል። በንፁሀን የሕይዎት ግብር፣ ስኬታማ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሪፎርም ፈጥረዋል። ንድፈ-ሀሳባዊ ቀመራቸው በ1973 ተፈትሾ መፅናቱ ይነገራል። ለቺሊው ለGeneral Augusto Pinochet አማካሪ ሆነው፣ በሀገሪቱ የ150 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ያልተስተዋለ መፈንቅለ-መንግሥት አስፈፅመዋል። በወቅቱ የቺሊ መንግሥት የነበሩት Salvador Allende(d-1973) ከነሚስቴሮቻቸው እቤተ-መንግሥት ውስጥ ተገደሉ። በስቁቅ ሆኔታ ተቀጠፉ። በድናቸው በአደባባይ ተሰጣ። ሕዝቡ ፈራ። 13,000 ደጋፊዎች በአንድ ቀን ታሰሩ። ቺሊ ገላጋይ አጥታ አበደች። ቀዎሰች። ልሳነ-ብእሲ ሆነች፣ ተራቆተች። ሂደቱ አምስት ቁልፎች ነበሩት፦ ፩ኛ.ሕዝቡ - ከአንድ አስደንጋጭ እርምጃ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ - ተደናበረ። ትጥቅ እንዲያወርድም ሆነ። ፪ኛ.የዚህ ዓላማ - ሕዝቡ ሁኔታውን ለመቀልበስ ዓቅሙን እንዳያሰባስብ፣ የወረደበትን መዓት ባህርይና ምንነት በቅጡ እንዳይረዳ ማድረግ ነው። ፫ኛ.በሕዝብ ተመርጦ የነበረው ፕሬዝዳንት - ‹የሶቭየት ሰላይ› ተብሎ ተረገመ። ከሀዲ፣ ሀይማኖት የለሽ፣ አረመኔ ተደርጎ ተወገዘ። ተቋማትም እንዲወድሙ ተደረገ። ፬ኛ.የዚህ ዓላማ - ሕዝቡ መሪና አኗሪ አጥቶ፣ በመኖርና ባለመኖር መካከል እንዲዋልል ማድረግ ነበር። ፭ኛ.የአስደንግጦ ማከም ዋና ግብ ይኸኛው ነው!ፔኖሼ፦ ድምርምር ሁኔታዎችን ተጠቅሞ፣ በተረጋጋ ጊዜ የማይታሰቡ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን አፀደቀ። የኒዮሊብራል ሥርዓት በቅፅበት ሰፈነ። የመንግሥት ይዞታ ለውጭ ባለሀብት ሲሳይ ሆነ። ያልተገራ የነፃ ንግድ ገበያ ሥራ ላይ ዋለ። የማሕበራዊ አገልግሎት በጀት ተቋረጠ።....ወዘተ ሆነ። እያዳመጥኸኝ ነው?፣ መልካም! ከዚህ በኋላ አስደንግጦ ማከምን፣ ፈልሳፊውን፣ የቺሊን ሁኔታ አታላምጠው። ወደ'ራስህ ተጨባጭ ሁኔታ ተመለስ። ግና ፈፅሞ ወደኋላ አትመልከት። ወደፊትም አትጓዝ። በቅድሚያ ቁም። "ደንግጠህ አትታከም"። ካደፈጠብህ የእንዝህላልነት-መደብ ተነስ። ስሜትህን፣ እልክኽን፣ ቁጣህን፣ ቂምኽን፣ ጥላቻህን፣...አስወግድ ወይም በጣም ቀንስ። ትናንት ከማማህ ያወረደህን፣ ዛሬም መልሶ የሚጥልህን ማንነት አትልበስ! ለዛሬ እዚህ ላይ አበቃለሁ። ሲያመኝ-ሲያመኝ መጤጥፌን እቀጥላለሁ። ‹‹ማን ነህና?›› አትበለኝ። መልዕክት እንደለጠፈ እንጨት፣ ሀሳብ እንደሰቀለ ብረት ቁጠረኝ። ሳታኮርፍ፣ የቻልኸውን ሀሳብ/መልዕክት ብቻ ውሰድ!!! ሸርር https://t.me/sudayisyeharyifochu https://t.me/sudayisyeharyifochu
Show all...
የአሪፎች ሀድራ ኢሽቅ || ѕυ∂α ує αяуιfσ¢н

suda tube አሪፍ ቻናል🔉 👉 አዳዲስ ነሽዳና መንዙማወች‍🎤 👉አሪፍ ፕሮፋይል ፒክቸሮች🎨 👉ያልታዩ ሀላል ሚሚወች 😂 👉አዳዲስና ትኩስ መረጃወች &🕛 👉ኢስላሚክ የዲን ትምርቶችን☑️ ለማግኘት አሪፍ ቻናል ለ አስተያየት 👉 @Suda245 Watch "suda YE aryifoch" on YouTube

https://youtube.com/channel/UCVofeUY0CIHsjotUTHDc3IQ

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.