cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወንጌል ይለዉጣል📖

ወንጌል ይለዉጣል ትምህርቶች የእግዚአብሔር ቃል የዝማሬ ግብዣ እና ሌሎችም እራሳችንን እንድናይ የሚያደርጉ ፅሁፎች የሚቀርቡበት gospel channel contact us @kalu_hayal_new @enchanted_nuha

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
201
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ያልኖርክበት ዘመን የለም ካንተ በፊት ዘመን አልነበረም አምላካችን እግዚአብሔር 😇🙏
Show all...
ራእይ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ። ¹⁰ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥ ¹¹ እንዲሁም፦ የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ። ¹² የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፥ ¹³ በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። ¹⁴ ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ ¹⁵ እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ። ¹⁶ በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። ¹⁹ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ። ²⁰ በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፥ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
Show all...
ስራችን የተገለጠ ነው በዚህ ክፍል ላይ ስለ 2 ሀሳቦች ይናገራል ስለ ጨለማ ስራ እና ስለ ብርሃን ስራ እነዚህ 2ቱ በምንኖረው ህይወታችን የሚገለጡ ናቸው ነገር ግን የቱኛውም ስራችን በሰው ፊት ያለውም በድብቅ ያለውም ከ እግዚአብሔር እይታ የተሸሸጉ አይደሉም ነገር ግን ወገናችንን ይናገራሉ የጨለማ ስራ ብርሃን የሌለበትና መንገዱም የማይታይ ነገር ግን ሁል ጊዜ በተራመድን ቁጥር ለመሰናክልና ለመጥፎ አወዳደቅ የሚያሰናዳን ነው፤ ከነገሮች እየሸሸን የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የህሊናችን ተወቃሽ የኃጢያት ደግሞ እስረኛ ያደርገናል በጨለማ ለመከለል ያበቃን ይህ ድርጊታችን የማያኮራና ልክ ያልሆነ ከመሆኑም ባሻገር ህይወታችንን የሚያሳጣ መሆኑ ይበልጥ የከፋ ያረገዋል፤ ይህ የጨለማ ስራ የሰይጣን ተጎታች ጋሪ ያረጋል ከእግዚአብሔር መንግስት እርቀን ተቅበዝብዘን ያለ ሀሴትና እረፍት እንድንጠፋ ያደርጋል ክፉ ስለሆነም ብርሃንን ጠልተን ከህልሞቻችን ሁሉ አርቆ ያስቀምጠናል ም/ም የጨለማ ተጓዥ ትርፉ የአውሬ እራትነት ነው በብርሃን የሚኖር ግን መንገዱን ያያል የቆመበትንም የሚመጣውንም ያስተውላል በቀኑ ብርሃን የህይወትን እሩጫ ያሸንፋል ስራውም መልካም ስለሆነ በሁሉ ፊት ይገለጣል ያስመሰግነዋልም የሚያሳፍር ነገር እንደሚሸሸግ የሚያኮራ ነገር ልክ እንደ ፀሀይ ይታያል ይህም ስራ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስመሰግናል ይህ መንገድ, የእውነት, የፅድቅ, የልክ, የብርሃን, የደስታ, የሰላምና እአፍት መንገድ ነው ሰዎች በዚህ ስራ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉት እውነተኛ የዓለም ብርሃን ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ በመምጣት ነዉ ከመሰናከልና ያለ ተስፋ ከመጥፋት ማምለጫ ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ነው፤ በእርሱ ያለም የህይወት መንፈስ ሁለንተናችንን ለውጦ በፅድቅ እንድንኖር በፀጋው ያበረታናል በራሳችን ይህን ሁሉ ማድረግ አንችልም በህይወታችን ግን መንፈስ ቅዱስ ሲኖር ሁለንተናችንን ለውጦ በቅድስና ያኖረናል እዚህ ጋር አንድ መመርመር ያለብን ነገር ስራችንን ነው በብርሃን ነን የተገለጠ ነው ወይስ በጨለማ ተደብቀናል🤔 ማንም ይህን የብርሃን ይህወት ቢፈልግ እና ከውድቀቱ መነሳት ቢሽ ከልቡ አንድ ነገር ይበል አምላኬ የኔ ፍላጎት ይቅርና አንተ በህይወቴ ላይ ዋና ሁን በብርሃንም መንገድ ምራኝ እጆቼን ለታመኑ እጆችህ አሳልፌ ሰጥቻለው ተቀበለኝ ይበል እግዚአብሔርም ለዘለዓለም አይጥለውም @kalu_hayal_new @kalu_hayal_new
Show all...
አልልም! አልወድቅም አልልም ፤ በእርግጥም እወድቃለሁ ፤ ግን እንደምነሳ አምናለሁ። አልስትም አልልም ፤ አዎ እስታለሁ ፤ ቢሆንም እንደምመለስ አውቃለሁ። አልጥልም አልልም ፤ ጥዬ አይቻለሁ ፤ ነገር ግን የጣልኩትን እንደማነሳ አምናለሁ ። አልበድልም አልልም ፤ ብዙ እንደምበድል አያለሁ ፤ ቢሆንም ልቤን ለንሰሐ ላዘጋጅ እወዳለሁ ። ብዙ አጥፍቼ ፣ ወድቄ ፣ በድዬና ስቼ አውቃለሁ ። ለመመለስ ያስቻለኝ የእግዚአብሔር ምህረትና ርኅራኄ ብቻ መሆኑን አውቃለሁ ። አንድ አባቴ " አለመውደቅ በማይቻልበት ዓለም ወድቆ መነሳት ክብር ነው።" በማለት ይናገራሉ ፤ አዎ እግዚአብሔር ከመውደቃችን ጋር ሳይሆን ከመነሳታችን ጋር ጉዳይ አለው። ብዙዎቻችን ላለመውደቅ እንጂ ወድቆ ለመነሳት ጥረት አናደርግም ፤ "እግዚአብሔር ግን ባለመውደቃችን የሚከብረውን ያህል ወድቀን በመነሳታችን ይከብራል።" ስለዚህ ሁሌ በዚህ እንበረታታ ፤ ዛሬ ብንወድቅ ነገ ለመነሳት እንጣር ፤ ላለመውደቅ የምንጥረውን ያህል ስንወድቅ ለመነሳት እንትጋ። ወዳጆቼ ሆይ ከዚህ ቀደም ብዙ ወድቄ አውቃለሁ ፤ ከዚህ በኃላም ብዙ ልወድቅ እችላለሁና ብዙ አትታዘቡኝ። ነገር ግን አንድ እውነት ይገባኛል ፤ ትላንት የመለሰኝ የምህረት እጁ ለነገም ዋስትናዬ ነው። ጸሎት ጌታዬና መድኀኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በጸጋህ ደግፈህ ኑር ስላልከኝ አመሰግናለሁ። ብዙ ምህረትህ ስላነሳኝ ፣ እንደገና ቁም ስላለኝ ከፍ አደርግሃለሁ። አንዳንዴ በራሱ እንደቆመ ለሚያስበው ልቤ ያቆምከኝ አንተ እንደሆንክ አስተምረው ፤ ለነገም በመታበይ ከመውደቅ ታደገው። ልዑል ሆይ ሰው ብዙ ሊናገር ተፈጥሯል ፤ ሰው ምን ይለኛል ብሎ ከደጅህ ከመራቅ ጠብቀኝ። ሁሌም ብስትና ባጠፋ ሮጬ በፊት መመልስ እንዲሆንልኝ እለምንሃለሁ። የዓለሙ ቤዛ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም። አሜን! ተጻፈ በቦዔዝ ታምሬ ሰኔ-16-2013 ዓ.ም አዲስአበባ , ኢትዮጵያ በ" " ያሉት ሀሳቦች የዲ/ን አሸናፊ መኮንን ናቸው።
Show all...
እንደራሱ አሳብና ፀጋ እንጂ እንደ ስራችን አይደለም ደግሞ #ከዘላለም #ዘመናት ከመፈጠራችን በፊት የታቀደ በክርስቶስ የሆነ ድነት ነው ወይም ፀጋ ነው
Show all...
11 (<<አሕዛብ የነበራችሁ>>፤ <<የተገረዙ በተባሉት>>___<<ያልተገረዙ የተባላችሁ>>) ማለትም እስራኤላዊ ያልሆኑ/ አይሁድ ያልሆኑ እስራኤላዊያን እግዚአብሔርን ከጥንት ያመለኩ የነበሩ እና በእ/ር የተመረጡ ወገኖች ናቸው ተስፋ ያላቸዉና እ/ር ለዛ ኪዳን ምልክት ግዝረትን የሰጣቸው በህግ የሚኖሩ ናቸው ከ እነርሱ ዉጭ ያሉት አሕዛብ(ሕዝብ) እ/ር የማያመልኩ ወይም ህግ የሌላቸው ናቸው ስለዚህ አይሁድ አሕዛብን ይንቋቸዋል ኃጢአተኛም አርገው ይቆጥሯቸዋል የተስፋውም ባለቤት አድርገው አያዩአቸውም። ስለዚህ በእነሱ ያሌተገረዙ የተባላችሁ 12 ፀጋው ባልተገለጠበት ዘመን ከእስራኤል ወገን ሳትሆኑ ለተስፋውም እንግዶች ሆናችሁና ተስፋ አታችሁ ኖራቹ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ አዳኝ ነበራችሁ 13 አሁን ግን በክርስቶስ ደም ወደ እ/ር ቀርባችኋል 14 ክርስቶስ ሰላም ነው፤ ሕግንም ሽሮ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ/ልዩነት በስጋው ሞት ያፈረሰ፡ አይሁዳዊም አህዛብም ሳይባል ሁሉንም አንድ አዲስ ፍጥረት ፈጠረ ሰላምንም አደረገ 16 ጥልንም ገድሎ ሁለቱንም አይሁድንም አሕዛብንም ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ 17 ኋላም ከተስፋው ለራቁት አሕዛብ ከእ/ር መንግስት ጋር ሰላምን ያሰፈነ፡ ለተስፋው ለቀረቡትም አይሁዳዊ የተጠባበቁትን ተስፋ መገለጥ የምስራች አበሰረ 18 በክርስቶስ ስራ ወደ አብ ገባን 19 ስለዚህ ሁላችንም ለመንግስቱ እንግዶች ሳንሆን ወራሾች ነን
Show all...
11 (<<አሕዛብ የነበራችሁ>>፤ <<የተገረዙ በተባሉት>>___<<ያልተገረዙ የተባላችሁ>>) ማለትም እስራኤላዊ ያልሆኑ/ አይሁድ ያልሆኑ እስራኤላዊያን እግዚአብሔርን ከጥንት ያመለኩ የነበሩ እና በእ/ር የተመረጡ ወገኖች ናቸው ተስፋ ያላቸዉና እ/ር ለዛ ኪዳን ምልክት ግዝረትን የሰጣቸው በህግ የሚኖሩ ናቸው ከ እነርሱ ዉጭ ያሉት አሕዛብ(ሕዝብ) እ/ር የማያመልኩ ወይም ህግ የሌላቸው ናቸው ስለዚህ አይሁድ አሕዛብን ይንቋቸዋል ኃጢአተኛም አርገው ይቆጥሯቸዋል የተስፋውም ባለቤት አድርገው አያዩአቸውም። ስለዚህ በእነሱ ያሌተገረዙ የተባላችሁ 12 ፀጋው ባልተገለጠበት ዘመን ከእስራኤል ወገን ሳትሆኑ ለተስፋውም እንግዶች ሆናችሁና ተስፋ አታችሁ ኖራቹ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ አዳኝ ነበራችሁ 13 አሁን ግን በክርስቶስ ደም ወደ እ/ር ቀርባችኋል 14 ክርስቶስ ሰላም ነው፤ ሕግንም ሽሮ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ/ልዩነት በስጋው ሞት ያፈረሰ፡ አይሁዳዊም አህዛብም ሳይባል ሁሉንም አንድ አዲስ ፍጥረት ፈጠረ ሰላምንም አደረገ 16 ጥልንም ገድሎ ሁለቱንም አይሁድንም አሕዛብንም ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ 17 ኋላም ከተስፋው ለራቁት አሕዛብ ከእ/ር መንግስት ጋር ሰላምን ያሰፈነ፡ ለተስፋው ለቀረቡትም አይሁዳዊ የተጠባበቁትን ተስፋ መገለጥ የምስራች አበሰረ 18 በክርስቶስ ስራ ወደ አብ ገባን 19 ስለዚህ ሁላችንም ለመንግስቱ እንግዶች ሳንሆን ወራሾች ነን
Show all...
6-7 በትንሳኤው ኃይል ከክርስቶስ ጋር አስነሳን መነሳት ብቻ አይደለም በሰማያዊ ስፍራ ከሱ ጋር አስቀመጠር ባለ እርስት ነን 8 ይህ ፀጋ በእምነት አዳነን ይህም ስጦታ ነው 9 ነገር ግን በክርስቶስ በማመን የሚገኝ ድነት እንጂ ከእኛ የፅድቅ ስራ አይደለም 10 መጀመሪያ ለፅድቅ ስራ ፈጠረን ነገር ግን ኃጢአትን አድርግን አሁን ግን መልካሙን ስራ ዳግም እንድናደርግ በክርስቶስ ዳግም በሞቱና በእምነት ተባብረን ለዓለም ሞተን በትንሳኤውም አምነን ተባብረን አዲስ ፍጥረት አርግ በክርስቶስ የመስቀል ስራ ፈጠረን
Show all...
👆4 <<ባለጠጋ>> በሀብታም እና ባለጠጋ መካከል ያለው ልዩነት ሀብታም ሲሰጥ ያልቅበታል ውስንነት አለበት ባለጠጋ ግን እየሰጠ ሚሞላለት ነው የተትረፈረፈለት ነው የእ/ርም ምህረት እንደዚህ ነው ዛሬ አጥፍተህ ይቅር ብሎክ ነገ አልቆብኛል አበዛኸው አይልም ሁሌም የምህረት እጆቹ ለልጆቹ ይዘረጋሉ ከልብ እንፀፀት እንጂ ሰዎች አንዴ ሲስቱ እ/ር ፊት ደግመው መቅረብ ይፈሩና በዛው ይሰምጡበታል ግን የማመልከው አምላክ ምህረት ማያልቅበት ነው ዳግም አቅፎ ያስገባል 5 ይሄም ፍቅሩ በድለነው መጨረሻችን መጥፋት ተነበረ ሰዓት እንኳን ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን ይሄ ፀጋ ነው ያዳነን
Show all...
ፀጋ ለሰው የተገለጠው ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሳ እንጂ ማንም ሰው የሚገባው ሆኖ አይደለም 👆ተስፋ የነበረው መሲህ ጊዜው ደርሶ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአል ለፃዲቅ ሰው ነፍሱን በድፍረት የሚሰዋ ይኖር ይሆናል ለ ደግ ሰውም የሚሞት ይኖራል ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን በድለነው ተጣልተን ባለን ሰዓት ስለኛ እሱ ሞት መልካም ላደረገስ ይሁን ለበደለው ግን የሚሞት ለዛውም በአንዴ ሳይሆን ተሰቃይቆ ልብሶቹ እስኪቀደድ አጥንት ባለው ጅራፍ ተገርፎ ተተፍቶበት መስቀል ተሸክሞ ተራራ ወቶ ኦምጣጤ አጠጥተውት ጎኑን በጦር ወግተውት ልብሱን ቀዳደው ተካፍለውት የእሾህ የተሰራ አክሊል አድርገውለት ለበደለው ሰው ይሄን ስቃይ አይቆ የሚሞት አይገኝም ክርስቶስ ግን አድርጎታል ይሄ እ/ር የሰውን ልጅ ለማዳን ያለውን ፍቅር ያሳያል
Show all...
4 ሰራተኛ ሲሰራ ይከፈለዋል ካልሰራ ግን ባለ እዳ ነው አሰሪው ላይ ሰው ደግሞ በሕግ ስራ አይፀድቅም ስለዚህ ባለ እዳ ይሆናል 5 ነገር ግን ሰራተኛ ካልሆነ ደሞዝም እዳም አይኖርበትም ግን ገንዘቡ ከባለቤቱ በነፃ ሚሰጠው ስጦታ ከሆነ በነፃነት ይኖራል ፀጋም ልክ እንደዚህ የእ/ር ነፃ ስጦታ ነው በስራችን አይደለም ኃጢአተኛውን በሚያፀድቅ ለሚያምን ይላል ማፅደቅም መኮነንም የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ነው በሱ ለሚያምን ደግሞ ስራው ሳይሆን እምነቱ ነው ሚያፀድቀው
Show all...
ስለዚህ ይህ ፀጋ እግዚአብሕር ለሰው ልጆች ያለው መልካም አስተያየትና የሚያፈልቀው #ፍፁም #ፍቅር ነው 👆 ሰዎችን #የሚያድን የእ/ር ፀጋ ተገልጧል ፀጋው የአለምን ኃጢአትና ምኞት እንድትክድ ያደርጋል፤ በፅድቅም የክርስቶስን መገለጥ(ምፅአት) ያስጠብቃል፤ ወደ እርሱ እስክንሄድ ደግሞ በፅድቅ እራሳችንን ገግተን እንደ እ/ር ፈቃድ እንድንኖር ያደርገናል። በምድር ፅድቅን በሰማይ ተስፋን ይሰጣል
Show all...
የዘለዓለም ሕይወት የፀጋ ስጦታ ነው 23👆 22 ከኃጢአት ባርነት በክርስቶስ ነፃ መውጣታችንና ለእግዚአብሔር መገዛታችን& መቀደሳችን ጅማሬ ብቻ ሳይሆን መጨረሻም አለው እሱም የዘላለም ሕይወት ነው፤ 23ኃጢያትን ለሚያደርጉ ግን ሞት ነው ደሞዛቸው የእ/ር ፀጋ ስጦታ << በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን" የዘላለም ሕይወት ነው።>> ስለዚ በክርስቶስ ሕይወት አለ እሱም ከኛ የሆነ ሳይሆን የእ/ር የፀጋ ስጦታ ነው
Show all...
አንድ ሰው መንፈሳዊ ነገሩ እንዲያድግ በየቀኑ ጂም እየሄደ ስፖርት አይሰራም ወይም ሰውነቱን አጠንክር ጡንቻ ለማውጣት መፀሐፍ ቅዱስ አያነብም ልክ እንደዚህ መንፈሳዊ ነገራችን እንዲያድግ በሚገባን ስፍራ መገኘት አለብን። ኃጢአት ለስጋ ይመቻል ለጊዜው እርካታን ይሰጣል፤ ግን ለመንፈስ ቅድስና ይመቻል ምክንያቱም ግክ አለመሆኑን ልቦናችን ስለሚወቅሰን ስለዚህ ነው ስጋም ለኔ አጉርሰኝ መንፈስም ለኔ አጉርሰኝ ሚሉት ይቃወማሉ፡ ምንወስነው ግን እኛ ነን ቀን ሙሉ ዘፈን የሰማ ሰው ማታ አይዘምርም ቀን ሙሉ የፀለየም ሰው ሲጨርስ አይዘፍንም ጡንቻችን እንዳበላነው ነው ሚያድገው 18 በመንፈስ ብንሆን ያ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ስለሚወቅሰንና ቅድስናን ስለሚያሳየን ሕግ አያስፈልገንም ልክ የሆነን ሰው ልክ ሁን ስለማይባል
Show all...
ይሄ ፀጋ ከጥንት ጀምሮ ለሰው ልጆች እንደሚሰጥ የታወቀ ነበር 12mecheresha lay መላእክት እንኳን ሊያዩት እንደናፈቁ የእ/ር የዘላለም እቅዱ እንደነበር ያሳያል በሕግ ስርአት ውስጥ የነበሩት ነቢያት እንኳን ስለዚሕ ፀጋ ይመረምሩ ነበር ከእ/ር ትንቢትንም ተናግረዋል (ኢሳይያስ 53 የክርስቶስ መከራ) ግን ወደፊት የሚፈጠር ስለነበር አንቀላፍተዋል ስለዛ ነው እናንተን አነፁ ሚለው ያ ፀጋም ድህነትን የሚሰጥ ነው። በሰው ውስጥ የኃጢአት ሕግ አለ ማንም አለማድረግ አይችልም ስለዛ በሕግ ፊት ንፁህ ሆኖ መገኘት አይችልም ኩነኔ ስለሚገኝ ይህ ፀጋ ግን በክርስቶስ የተፈፀመ ስራ ስለሆነ ለመዳናችን የእኛን ስራ አይጠይቅም እምነታችንን እንጂ የኃጢአትን ሕግ ምናሸንፈው በመንፈስ ሕግ ነው ያም በክርስቶስ በማመን የሚገኝ ፅድቅ ነው፤ ያ በውስጣችን የሚኖረው የመንፈስ ሕግ መዳናችንን በመንገር ኃጢአትን እንዳናደርግ ይወቅሰናል። ምሳሌ ፡ሰው አታድርግ የተባለውን ያደርጋል ለ ሌባ ግን እቃ ጠብቅ ካልከው ግን አይነካትም።
Show all...
መጀመሪያ እንዳነበብነው ሕግ በሙሴ ተሰቶ ነበር ያ ሕግ ማለትም በብሉይ ኪዳን የሰዎችን ድርሻ የሚያሳየው ለአዲሱ ኪዳን ጥላ ነበር & ሞግዚትም ተብሏል ምክንያቱም እ/ር ሌላ አዲስ ኪዳን አደርጋለው ብሎ ስለነበር፡ በብሉይ ሕግ እንደተሰጠ በአዲሱ ደግሞ ፀጋ ነው የተሰጠው። ሌላው እዚሕ ክፍል ላይ እውነትንም ያነሳል፡ ሰዎች እውነትን ለማወቅ ዘመናቸውን ይጨርሳሉ ክርስቶስ ግን እኔ (እውነት) (ሕይወት) (መንገድ) ነኝ ማንም በእኔ ካልሆነ በቀር ወደ አብ መሄድ አይችልም ብሏል። ስለዚህ ፀጋ መፀሐፍ እንዲህ ይላል
Show all...