#ሠርቼ_ሳይሆን_ተቆጥሮልኝ......
❇️ እኔ በራሴ ደካማ ነኝ!
#አልችልም! በመልካም ማንነት በጥንቃቄ ብራመድም ለጥቂት ነው እንጂ ፤ ተመልሼ እወድቃለሁ ፤ እንዲሁም እነሳለሁ። እድሜዬን በሙሉ ጠንካራ ሁኜ ያለምንም ስህተት መኖር አልችልም! ህጉንም ሁሉ መጠበቅም አልችልም! ምክንያቱም ፍጹም አይደለሁም።
✝ በዚህ ሁኔታም ፤ ህግን በመጠበቅ እና በመልካም ሥራ የሚጸድቅ ማንነት የለኝም!....
#ብቁ_አይደለሁም ፤ እራሴን አላምንም! ምክንያቱም እጅግ ደካማ ነኝ [በመንፈስም ደሃ ነኝ]።
#በሥራዬ_ብጸድቅ ፤ ነገ ደግሞ ስደክም ጽድቄን አጣዋለሁ። በእኔ ኃይል እና በሥራዬ ቢሆን ዛሬ ላይ ባልደረስኩ ነበር።
#እንደ_ሥራዬ ቢሆንማ አጠቃላይ ውጤቴ የከፋ ነበር። በሥራዬ ቢሆን ፤ እንኳን በእግዚአብሔር ፊት
#ልጸድቅ ይቅርና ፤ በሰዎች ፊት እንኳን ጻድቅ አልባልም ነበር።
✝ አሁን ግን
#የምጸድቀው_በሥራዬ_አይደለም! 😁 የምጸድቅበት አዲስ ተስፋ መጥቷል ፤ እርሱም
#እምነት ይባላል። ያገኘሁትም
#ጽድቅ የራሴ አይደለም!
#ተቆጥሮልኝ እንጂ። በራሴ በየትኛውም ሥራ
#የእግዚአብሔርን_ጽድቅ ላገኘው ስለማልችል ፤
#እንዲሁ_ተቆጠረልኝ ፤ ያውም የራሱ
#የእግዚአብሔር _ጽድቅ። እኔ መሥራት ስላልቻልኩ
#ልጁ ሥራዬን ሠራልኝ እና ለእኔ ለደካማው
#ተቆጠረልኝ። ልጁ በሠራው እኔ እንዲሁ በእምነት ገባሁ ፤ ልጁ ህጉን በሙሉ መፈጸሙ ለእኔ
#ተቆጠረልኝ ፤ ያለ ኃጢአት መመላለሱ ለእኔ
#ተቆጠረልኝ።
ሮሜ 3÷28፤ [
#ሰው_ያለ_ሕግ_ሥራ_በእምነት_እንዲጸድቅ >>
#እንቆጥራለንና<<። ]
ሮሜ 4 (Romans)
5፤ [
#ነገር_ግን_ለማይሠራ_ኃጢአተኛውንም_በሚያደድቅ_ለሚያምን_ሰው_እምነቱ_ጽድቅ_ሆኖ >>
#ይቆጠርለታል<<።
6፤ [ እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር >>
#ያለ_ሥራ<< ጽድቅን
#ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል። ]
22፤ [ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ >>
#ተቆጠረለት<<።
23፤ ነገር ግን፦ >>
#ተቈጠረለት<< የሚለው ቃል
#ስለ_እርሱ_ብቻ_የተጻፈ_አይደለም፥ >>
#ስለ_እኛም<< ነው እንጂ፤
24-25፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው >>
#ለምናምን_ለእኛ >>
#ይቈጠርልን_ዘንድ<< አለው። ]
ገላትያ 3 (Galatians)
8፤ [
#መጽሐፍም እግዚአብሔር >>
#አሕዛብን_በእምነት_እንዲያጸድቅ >>
#አስቀድሞ_አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። ]
✝ እግዚአብሔር
#በልጁ_ስም በማመኔ ብቻ
#የልጁን_ጽድቅ ለእኔ ለኃጢአተኛው እንዲሁ ከቆጠረልኝ ፤ ታዲያ ኃይማኖት የምን
#ምቀኝነት ነው? ፤ ለምንድነው "
#ለመጽደቅ_መሥራት_አለብህ" የምትለኝ? እህ!!!!!!...... ቆይ መቼም በሥራዬ ፈጽሞ መጽደቅ እንደማልችል ስለሚያውቅ መስሎኝ እግዚአብሔር እንዲሁ
#በነጻ ፤ ማመኔን ጽድቅ አድርጎ
#የቆጠረልኝ። ወይ ሃሳብህን አስተካክለው ፤ "
#ስለጸደክ_መስራት_አለብህ" በለኝ። እንዲህ ስላልከኝም አይደለም ፣ መልካም መስራት የኔ አዲሱ ሰው ማንነት life system ነው።
ሮሜ 8 ÷ 33፤ [
#እግዚአብሔር_የመረጣቸውን_ማን_ይከሳቸዋል? >>
#የሚያጸድቅ_እግዚአብሔር_ነው፥
#የሚኰንንስ_ማን_ነው? ]
ሮሜ 10 (Romans)
3፤ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።
✝ እወድሃለሁ አንተ ወንድሜ! ይህ ጽድቅ ለእኔ ብቻ እኮ አይደለም
#ላንተም ነው! እመን!
#ይቆጠርልሃል! በሥራ ካልክ እውነቱን ልንገርህ መቼም አትጸድቅም! እግዚአብሔር የራሱን ጽድቅ ሊሰጥህ ይፈልጋል ፤ ታዲያ አንተ ለምን የእርሱን ትተህ
#የራስህን_ጽድቅ ለማቆም ትጥራለህ? እርሱ እንዲሁ በነፃ ስለሰጠህ?...... የምትድነው እኮ
#በራስህ_ጽድቅ ሳይሆን በራሱ
#በእግዚአብሔር_ጽድቅ ነው።
@marsilchannel
@marsilchannel
@marsilchannelShow more ...