cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Michael Z Ethiop

ሃይማኖታዊ፣ አገራዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮቻችን ይቀርቡበታል!

Show more
Advertising posts
2 341
Subscribers
No data24 hours
-117 days
-4430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
በቤተ  ክርስቲያን  ታሪክ  መሠረት  ቅዱስ  ጴጥሮስ  በፍልስጥኤም፣  በሶርያ፣  በጳንጦን፣  በገላትያ፣  በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ሰብኳል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሮሜ አንድ ዓመት ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ካስተማረ በኋላ የሮሜ ክርስቲያኖች እየበዙ ከመምጣታቸውም በላይ የክርስትናው ጉዞ እስከ ሮማ ባለሥልጣናት ደረሰ። የኔሮን የቅርብ ባለሥልጣናት የሆኑት የአልቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች ወደ ክርስትናው ገቡ። በዚህን ጊዜ ኔሮን ንጉሠ ሮማ በቅንዓት ተነሣባቸው። ኔሮን በሮም የነገሠው በ፶፬ ዓ.ም. ነው። በመንግሥቱ መጀመሪያ ደግ ሰው ነበረ። ነገር ግን በነገሠ በዓመቱ የጨካኝነት ዐመሉ ብቅ ማለት ጀመረ እና የአባቱን ልጅ አስገደለ። በ፶፱ ዓ.ም. ደግሞ እናቱን በመርዝ ገደለ። በ፷፫ ዓ.ም. እያስተማረ ያሰደገውን መምህሩን ፣ በ፷፪ ዓ.ም. የልጅነት ሚስቱን አግታሺያን አስገደለ። ከእርስዋ በኋላ ያገባትን ሚስቱንም ፓፒያን በርግጫ ብሎ ገደላት። ኔሮን በ፷፬ ዓ.ም. እርሱ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተቀምጦ የሮማን ከተማ እሳት ለቀቀባት። የሮም ሕዝብ በደረሰው አደጋ እጅጉን ተቆጣ። ኔሮንም በክርስቲያኖች አመካኘ። በዚህም የተነሣ በሮማ ከተማ ሁለት ዓይነት ወሬ መናፈስ ጀመረ። የሮማ አማልክት በክርስቲያኖች ሃይማኖት ስለተቆጡ በከተማዋ እሳት አዘነቡባት የሚለው የመጀመሪያው ሲሆን ክርስቲያኖች ሆን ብለው ከተማዋን አቃጥለዋታል የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ወሬ ነበር። የከተማው መጋየት ያበሳጨው የሮማ ሕዝብ፣ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ እያወጣ መግደሉን ተያያዘው። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ነበርና ተሠይፎ ዐረፈ። ይህን የሰሙት የአግቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች (የሮም ባለሟሎች ነበሩ) «ባይሆን አንተ ትረፍልን» ብለው በከተማዋ ግንብ በገመድ አሥረው በቅርጫት በማውረድ ቅፅረ ሮማን ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉት። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በኦፒየም ጎዳና ጉዞውን ቀጠለ። ሮማን ለቀቀ። እያዘገመ በሸመገለ ጉልበቱ ሲጓዝ አንድ ቀይ ጐልማሳ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ። እየቀረበ ሲመጣ ጌታችን መሆኑን ተረዳ። ወዲያው በፊቱ ተደፋና «ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?» አለና ጠየቀው። «ዳግም በሮም ልሰቀል» አለው። በዚህ ሰዓት ቅዱስ ጴጥሮስ አዘነና እንደገና ወደ ሮማ ተመለሰ። የኔሮን ወታደሮች እየፈለጉት ነበር። «እነሆኝ ስቀሉኝ» አለ ቅዱስ ጴጥሮስ። ያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ይዘው አሠሩት። ከጥቂት ቀናት በኋላም ሮማውያን የመስቀያውን እንጨት አቀረቡለት። ያን ጊዜ «እኔ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም» በማለት ቁልቁል እንዲሰቅሉት ለመነ። ያለውንም አደረጉለት። ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ። ፪. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዘሩ ከዕብራዊያን፣ ከብንያም ነገድ ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው። ጠርሴስ በንግድዋ የታወቀች የኪልቂያ ዋና ከተማ ናት። በከተማዋ እስከ አምስት መቶ ሺህ የሚገመቱ ከየሀገሩ የተሰባሰቡ ሕዝቦች ነበሩባት። ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነትን ይሰጡ ስለነበር፥ የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር። ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል። ቅዱስ  ጳውሎስ  በ፲፭  ዓመት  ዕድሜው  ወደ  ትውልድ  ሀገሩ  በመመለስ  በኢየሩሳሌም  ከነበረው  የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ። በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዓት እየተማረ እስከ ፴ ዓመቱ ቆየ። ገማልያል ፈሪሳዊ ስለነበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ተቀብሎታል። በ፴ ዓመቱ የአይሁድ ሸንጎ አካል ሆኖ ተቆጠረ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ ሁኔታዎቹን ሁሉ ያውቃል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ አባልነት ለሁለት ዓመታት በሠራበት ወቅት ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመሆኑ  ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር። እንዲያውም ሊቀዲያቆናት እስጢፋኖስን በማስተማሩ ምክንያት ተከሶ ለአይሁድ ሸንጎ በቀረበ ጊዜ የተከራከረው እርሱ ነበር። በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብስ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው። ቅዱስ አውግስጢኖስ «በእስጢፋኖስ ጸሎት፣ ቤተ ክርስቲያን የተፋውን ጳውሎስን አገኘች፤» በማለት ተናግሯል። በ፴፪ ዓመት እድሜው ከኢየሩሳሌም ፪፻፳፫ (ሁለት መቶ ሃያ ሦስት) ኪ.ሜ. ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ አገኘ። ከዚህም በኋላ ጭሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ። ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና «ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?» የሚለውን ድምፅ የሰማው። ሐዋርያው ጳውሎስም «ጌታ ሆይ ማን ነህ?» ብሎ ጠየቀ። «አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል» ሲል መድኃኒታችን ተናገረው። ያን ጊዜም በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ «ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?» ሲል ጠየቀ። ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው። (የሐዋ. ፱፥፩) የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም። እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ። ለሦስት ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ። በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራእይ ተገለጠለት። ቅዱስ ጳውሎስም  ያለበትን  አድራሻ  ነገረውና ሄዶ እንዲያጠምቀው  አዘዘው። ሐናንያ አስቀድሞ  የቅዱስ ጳውሎስን  ማንነት ያውቃል። አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል። አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት የመጡ ናቸው። ያን ስደት ያስነሣው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው። በዚህ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር። ይህን የሚያውቀው ሐናንያ በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር ጀምሮ ነበር። እግዚአብሔር አያውቀው ይመስል ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ማስረዳት ጀመረ። በመጨረሻ ግን «ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተ ዋለሁና» በማለት እግዚአብሔር ሐናንያን ላከው። ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረው በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሀገር መሄዱን ራሱ ተናግሮአል። (ገላ ፩፥፲፯) ለ፫ ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ። በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ። ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰበክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት። በዚህም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት። ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የገጠመው ሁለት ችግር ነበር። በቅድሚያ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሡ። በሌላ በኲል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ፓውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም። በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኲል ወደ ትውልድ ሀገሩ ጠርሴስ ተመለሰ።
Show all...
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለዘጠኝ ዓመታት ቆይቷል። ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ። ከኢየሩሳሌም የተሰደዱት ክርስቲያኖች የአንጾኪያን ሕዝብ ተግተው በማስተማራቸው ዝናው እስከ ኢየሩሳሌም ደረሰ። በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም የነበሩት አበው በርናባስን ወደ አንጾኪያ ላኩት። በርናባስ የግሪክ ቋንቋ ችሎታ ያለውን፣ ከማንኛውም ሰው ጋር መግባብ የሚችለውን፣ ደግሞም እግዚአብሔር ለአሕዛብ ሐዋርያ እንዲሆን የመረጠውን ቅዱስ ጳውሎስን ከጠርሴስ በማምጣት በአንጾኪያ ሥራቸውን ጀመሩ። በገላትያ መልእክቱ ምዕራፍ ፪ ላይ ራሱ እንደገለጠው ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ርዳታ ይዞ ወጣ። በዚህም በአይሁድና በአሕዛብ መካከል የነበረውን መለያየት ክርስትና አንድ እንዳደረገው አስመሰክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያው ጉዞ ያደረገው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ። በዚህ ጉዞአቸው በጠቅላላ ወደ ፪፼ (ሁለት ሺህ) ኪሎ ሜትር የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል። ይህም ጉዞ የተከናወነው በ፵፮ ዓ.ም. አካባቢ ነው። የተሸፈኑትም ሀገሮች ሲሊንውቂያ፣ ቆጵሮስ፣ ስልማን፣ ጳፋ፣ ጰርጌን፣ ገላትያ፣ ጵስድያ፣ ኢቆንዮን፣ ሊቃኦንያ፣ ልስጥራ፣ደርቤን፣ጵንፍልያ፣አታልያና አንጾኪያ ናቸው። ሁለተኛው ጉዞ የተከናወነው በ፶ ዓ.ም. ገደማ ነው። በመጀመሪያው ጉዞ ማርቆስ አብሮ ተጉዞ ነበር። ነገር ግን ጵንፍልያ ከተማ ሲደርስ እናቱ ስለናፈቀችው መመለስ በመፈለጉ በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት መጣ። ስለዚህም በሁለተኛው ጉዞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ወደ ኪልቂያ ሶርያ ሲጓዝ በርናባስ ደግሞ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። በዚህ ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ግሪክ ደርሶአል። የተጓዘባቸውና ያስተማረባቸው ከተሞችም፦ ደርብያ፣ ልስጥራ፣ፍርግያ፣ ገላትያ፣ ሚስያ፣ጢሮአዳ፣ ሳሞትራቄ፣ ናፑሊ፣ ፊልጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ፣  በርያ፣አቴና፣ ቆሮንቶስ፣ አንክራኦስ፣ አፌሶን፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌምና አንጾኪያ ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚሁ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ነው። ሦስተኛው ጉዞ የተከናወነው በ፶፬ ዓ.ም. ሲሆን የተሸፈኑትም ሀገሮች የሚከተሉት ነበሩ። ገላትያ፣ ፍርግያ፣ ኤፌሶን፣ መቄዶንያ፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆሮንቶስ፣ ጢሮአዳ፣ አሶን፣ ሚልጢኒን፣ አንጠቀከስዩ፣ ትሮጊሊዩም፣ መስጡ፣ ቆስ፣ ሩድ፣ ጳጥራ፣ ጢሮስ፣ ጵቶልማይስ፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌም ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከልዩ ልዩ ሀገሮች ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በመያዝ ሦስተኛውን ጉዞ አጠናቅቆ ኢየሩሳሌም ገባ። ነገር ግን ኢየሩሳሌም የገባበት ጊዜ የፋሲካ በዓል ስለነበር ከልዩ ልዩ ሀገሮች የተሰበሰቡ አይሁድ በከተማዋ ነበሩ። እነዚህ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን በየሀገራቸው በትምህርቱ የተነሣ ሲቃወሙት የነበሩ ናቸው። እኒህ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን በኢየሩሳሌም ሲያዩት ታላቅ ተቃውሞ አነሡበት። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ተቃውሞ አነሡበት። ሐዋርያው  ቅዱስ ጳውሎስም  ተቃውሞአቸውን ለመግታት እንደ አይሁድ  ሕግ በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ጀመረ። ነገር ግን ከኤፌሶን የተከተለውን ጥሮፊሞስን ወደ መቅደስ ያስገባው ስለመሰላቸው ተቃውሞአቸው በረታ። ከተማውንም አወኩት፤ ይህ ቅዱስ ጳውሎስን በ፶፰ ዓ.ም. ለሮም እሥር የዳረገው። ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ታስሮ ሮም ገባ። በዚያም በቁም እሥር ለሁለት ዓመታት ያህል ወንጌልን ሰበከ። የሁለቱን ዓመት የቁም እሥር እንደጨረሰ ወደ ኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ። ይህም በ፷ዎቹ ዓ.ም. ነው። በፍርድ ቤቱ በተደረገው ምርመራ የሮሜን ሕግ የሚቃወም  ምንም ወንጀል ስላልተገኘበት በነፃ ተለቀቀ፤ ከዚህ በኋላ  ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አራተኛውንና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያልመዘገበውን ጉዞውን ያደረገው። ይህ ጉዞው በመታሠሩ አዝነው ተክዘው የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት የጀመራቸውን ሥራዎች ፍጻሜ ለማየት የተደረገ ጉዞ ነው። በዚህም ጉዞው ኢየሩሳሌምን፣ ኤፌሶንን፣ ሎዶቅያን፣ መቄዶንያን፣ ቀርጤስን፣ ጢሮአዳን፣ ድልማጥያን፣ እልዋሪቆን፣ ኒቆጵልዮን፣ ብረንዲስን፣ ጎብኝቷል። በዚህ የመጨረሻ የስብከት ጉዞው ለአራት ዓመታት ያህል ቆይቷል። በመጨረሻ በ፷፬ ዓ.ም. ኔሮን በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ፷፭ ዓ.ም. ተይዞ ወደ ወኅኒ ገባ። ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ፸፬ ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሰይፎ በ፷፯ ዓ.ም. ሐምሌ ፭ ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ዐስራ አራት መልእክታትን ጽፈዋል። የቅዱሳኑ ሐዋርያት ረድኤትና በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን። ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ ፭፤ መጽሐፍ ቅዱስ-ሐዲስ ኪዳን፣ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ ቁጥር ፩፤ በማኅበረ ቅዱሳን © ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም የተከተበ
Show all...
4
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የቅዱሳን ሐዋርያት ታሪክ ገድልና ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሙሉ አልሰፈረም። አርባዕቱ ወንጌላት ሐዋርያት እንዴት እንደተጠሩና እስከ ዕርገት ድረስ የነበራቸውን ሁኔታ ሲጽፉ፤ ወንጌላዊው ሉቃስ ደግሞ የሐዋርያትን ታሪክ እስከ ፷ዎቹ መጀመሪያ ያለውን ጽፏል። ከዚህ በመለስ ያለውን የሐዋርያት ታሪክ ለማወቅ ግን ዋናው ምንጩ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት ናቸው። የሐዋርያት ደቀመዛሙርት እነ ፓፒያስ፣ ፖሊካርፐስ፣ አግናጥዮስ፣ ቀሌምንጦስ ዘሮም ወዘተ. የአባቶቻቸውን ታሪክ ጽፈው አቆይተውልናል። ከዚህበኋላ ጊዜም  በ፪ኛውና በ፫ኛው መቶ ክፍለ  ዘመን  የተነሱት የቤተ ክርስቲያን  ታሪክ  ጸሐፍት እነ አውሳብዮስ፣ ሩፊኖስ፣ ጄሮም፣ ወዘተ. በትውፊት የተቀበሉትን መዝግበው አልፈዋል። ቅዱሳን ሐዋርያት ገድላቸው የተጻፈላቸው፣ በዓላቸው የተከበረላቸው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው። በቤተ ክርስቲያናችን በሐምሌ ፭ ቀን በታላቅ ድምቀት በዓላቸው ከሚከበረው ሐዋርያት መካከል የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስና የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ፩. ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ነው። የአባቱ ስም ዮና ይባላል። ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ ማሥገር ጀመረ። ለደቀመዛሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው ፶፭ ዓመት እንደነበረ ይነገራ፤ ወደ ጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ በርናባስና ወንጌላዊው ማርቆስ ቤተ ዘመድ ናቸው። የማርቆስ አባት አርስጦቡሎስና በርናባስ በእናት የሚገናኙ ወንድማማች ናቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ ያገባው የበርናባስና የአርስጦቡሎስን እኅት ስለነበር በጋብቻ ይዛመዳሉ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው። የቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያ ስሙን ስምዖን ብላ እናቱ የጠራችው በነገዿ ስም እንደሆነ ይነገራል። በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ማን ትሉኛላችሁ?» ብሎ በጠየቀ ጊዜ «አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረውን ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን «አንተ ጴጥሮስ ነህ» ብሎታል ይህም በላቲን ቋንቋ ዐለት ማለት ነው፤ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል። ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ ወይንም የምሥጢር ሐዋርያት ከእነ ዮሐንስ እና ያዕቆብ ጋር የሚቆጠር ነው። ከሐዋርያት ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ ነበረው። ጌታ በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ሌሊት በእግሩ ሲመጣ ቢመለከት ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ በማለት ካስፈቀደ በኋላ ወደ ጌታ ለመምጣት መንገድ ጀምሮ በመሐል ቤት ጥርጣሬ ገባውና መስጠም ስለጀመረ ጌታችን «ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን» ብሎ ገስፆ ከመስጠም አድኖታል። (ማቴ ፲፬፥፳፪-፴፫) በቅፍርናሆም ጉባኤ ጌታን ምሥጢረ ቁርባንን ሲያስተምር፣ አይሁድ ስላልገባቸው ወደ ኋላ አፈገፈጉ። ከደቀ መዛሙርቱም «ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ» በዚህን ጊዜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁ?» ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው። በዚህ ሰዓት «ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም የሕይወት ቃል አለህ። እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ እናምናለን» በማለት ሐዋርያትን ወክሎ የመለሰ እርሱ ነው። (ዮሐ ፮፥፷፮-፷፰) ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር። ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለበት በመሆኑ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል። (ማቴ ፲፮፥፳፫) በኋላም «ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም» ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር። ጌታችን «ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» እያለው እንኳን «ከአንተ ጋር መሞት እንኳን የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም» በማለት የተናገረ ሰው ነው። (ማቴ ፳፮፥፴፬) ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የተናገረውን ቃል ለመጠበቅ ሞክሮ ነበር። ጌታ ዛሬ «የሰው ልጅ አሳልፎ ይሰጣል» ብሎ አስተምሮአቸው ነበርና መከላከያ ይሆነኛል ብሎ ሠይፍ ደብቆ ይዞ ነበር። የሮም ጭፎሮችም ጌታን ለመያዝ ሲጠጉ የሊቀ ካህናቱን ባርያ (ማልኰስን) በሠይፍ ጆሮውን ቆረጠው። ጌታችን ግን ሞቱ በፍቃዱ ለድኅነተ ዓለም ነውና «ሠይፍህን ወደ ሰገባው» መልስ ሲል ገሠፀው። ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሐው ነው። ጌታው የነገረው መድረሱን፣ ቃል የገባለትን አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለያቸው ጊዜ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሳ ወደ ማሥገሩ ተሠማራ። ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢክደው እንኳን  በንስሐ  በመመለሱ  ንስሐውን  መቀበሉን፤  ዛሬም  እንደሚወደው  ይገልጽለትም  ዘንድ  በጥብርያዶስ  ባሕር ተገለጠለት። (ዮሐ ፲፰፥፲) ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው። አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው ዐውቆአልና «ትወደኛለህን?» ተብሎ ሲጠየቅ «አንተ ታውቃለህ» ነበረ መልሱ። የራሱ ዕውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኅዳጌ በቀል (በቀልን የሚተው) ነውና ዛሬም እንደሚወደው፣ በንስሐ ተመልሶአልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐድልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጐቼን አሠማራ» በማለት አደራውን አስረከበው። ከዚያም በሞቱ እንደምን አድርጐ እግዚአብሔርን አንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማያት ዐረገ። (ዮሐ ፳፩፥፲፭-፲፯) ቅዱስ ጴጥሮስ በአራቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። ይህም፦ ፩. በሽምግልና አባትነቱ፣ ፪. ጌታ በቂሳርያ በሰጠው ቃል ኪዳን፣ ፫. የሐዋርያት አፈ ጉባዔ ሆኖ ይናገር ስለነበር፣፬. በጥብርያዶስ ባሕር በተሰጠው ቃል መሠረት ነው። በዚህም የተነሣ በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ እንዲመረጥ ሐሳብ ያቀረበ እርሱ ነበር። በበዓለ ሃምሳም ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ለተሰበሰቡት አይሁድ አፈ ጉባዔ ሆኖ ወንጌልን የሰበከ ፫፼ (ሦስት ሺህ) ምእመናንንም አሳምኖ የመጀመሪያዋን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የመሠረተ እርሱ ነው። (የሐዋ. ፩፥፲፮-፳፫፣ ፪፥፲፬-፴) አስቀድሞ ፈሪ የነበረውና በሊቀ ካህናት ቀያፋ ግቢ ጌታውን የካደው ቅዱስ ጴጥሮስ፣ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ካገኘ በኋላ ግን በአይሁድ ሸንጐ ድውይ ፈወስክ ተብሎ በተከሰሰ ጊዜ በድፍረት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሰከረ። የሐዋ ቆርነሌዎስን በማጥመቅ ወንጌልን ለአሕዛብ አስቀድሞ የሰበከው ሐዋርያ ነው። ይህ ሐዋርያ ልዑል እግዚአብሔር ባደለው  ጸጋ ጥላው እንኳን ድውያንን ይፈውስ ነበር። የሐዋ ፭፥፲፭። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፭ ላይ በ፶ ዓ.ም. አካባቢ በኢየሩሳሌም በተደረገው የሐዋርያት ሲኖዶስ ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች ለቀረበው ጥያቄ የመጀመሪያውን መልስ የሰጠው እርሱ ነበር። ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ መልክና ቁመና ጥንታዊያን መዛግብት እንደሚከተለው ያቀርቡታል። «ፊቱ ሰፋ ያለ ሲሆን ሪዛምና መካከለኛ ቁመት የነበረው ራሰ በራ ሰው ነው። በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ ነበር።»
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
" ከአሁን ጀምሮ ግብረሰዶማዊነት እና ተዛማጅ ድርጊቶች ሁሉ የተከለከሉ ናቸው " - የቡርኪናፋሶ ሁንታ ቡርኪናፋሶ ግብረ ሰዶማውያንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አወጣች። ረቂቁ ሕጉ ስራ ላይ እንዲውል በፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ይሰጥበታል። ትላንትና የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት በሰጠው መግለጫ ፥ የተሻሻለ የቤተሰብ ህግ ረቂቅ አዋጅ በወታደራዊው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ በሚመራ ሳምንታዊ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ተቀባይነት አግኝቷል። የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፍትህ ሚኒስቴር ፥ " ከአሁን ጀምሮ ግብረሰዶማዊነት እና ሌሎች ተዛማጅ ድርጊቶች ሁሉ የተከለከሉ እና በህግ የሚያስቀጡ ናቸው " ብሏል። ሕጉ ወደ ትግበራ  ፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ሊሰጥበት ይገባል ፤ በተጨማሪ ትራኦሬ ማወጅ እንዳለባቸው ሮይተርስ ዘግቧል። ሀገሪቱ በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት በወታደራዊ አገዛዝ ስር የምትገኝ ሲሆን በተመሳሳይ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዙት ጎረቤቶቿ #ኒጀር እና #ማሊ ወታደራዊ መንግስታት ጋር በኮንፌዴሬሽን #ለመዋሀድ ከቀናት በፊት ነው የተስማማቸው። @tikvahethiopia
Show all...
👏 7
06:19
Video unavailableShow in Telegram
ሦስቱ አደገኛ ኦሮሙማዎች
Show all...
7.56 MB
🥰 2
የግፍ ግፍ...! ግለሰቡ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪ ነው። ለ15 አመት የጋሪ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት በዝቅተኛ ስራ የሚተዳደር በአካባቢው ነዋሪ ታማኝና ታታሪ የሚባል ሰው ነበር። ክርስትና ላስነሳ ብሎ 'ቆላ' ወደሚባለው ስፍራ የዛሬ ወር ገደማ ግንቦት 27/2016 ከተወሰኑ ቤተሰቦቹ ጋር ሲጓዝ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ይይዟቸውን እና ከሌሎች ቀድመው ከታገቱ ሰዎች ጋር ይቀላቅሏቸዋል፣ ለመልቀቅም ግማሽ ሚልዮን ብር ይጠይቃሉ። ካዛም ወንድሞቹ ፌስታል ይዘው እየለመኑ እና ያላቸውን ጥሪት በሙሉ አሟጠው ሸጠው ገንዘቡ ይሰበስቡና እሱን ሰጥተው ወንድማቸውን ለማስለቀቅ ጉዞ ሲጀምሩ የአካባቢው ሚሊሺያዎች ያገኟቸው እና ከተዋጣው ብር ላይ 90,000 ብር ይወስዳሉ። የቀረውን ብር ይዘው መንገድ ሲቀጥሉ ደግሞ 'ልዩ ሀይል' ተብለው የሚጠሩ አካላት እጅ ይወቁ እና ሙሉውን ቀሪ ብር ይወስዱባቸዋል። ገንዘቡ ያልደረሳቸው አጋቾች ታድያ ይህን ታታሪ ግለሰብ ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን ገድለው፣ የተቀሩትን ደግሞ ይዘው ሸሽተዋል። ቤተሰብ ሀዘን ተቀምጦ ሰንብቷል፣ የአካባቢው ህዝብም ሆነ በስፍራው ያሉ የመንግስት አካላት ጉዳዩን በደንብ ያውቁታል (የግለሰቡን ስም እና ይኖርበት የነበረውን ከተማ አስቀርቼዋለሁ)። የግፍ ግፍ! EliasMeseret
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ትናንት አስመርቃለች። በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) በትናናው አልተ ተማሪዎቹን ያመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ መካከልም በአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎቹ ይገኙበታል። በቻይና የኢትዮጵያ ኤማባሲ ተወካዮች ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ምርቃት ላይ መሳተፋቸውንም ኤምባሲው አስታውቋል። “በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU በቻይና ውስጥ ብቸኛው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል የሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ ትናንት ከተመረቁት መካከል የመጀመሪያው ዙር የአማርኛ ተማሪዎች ይገኙበታልብሏል ኤምባሲው ባወጣው መረጃ። ኤምባሲው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠቱን አመስግኖ፤ “ይህ የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያጠናክራል” ብሏል። የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ መማሪያ መጽሃፍትን ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ማስተማር መጀመሩን ይፋ ያደረገው በፈረንጆቹ 2022 ላይ ነበር። ዩኒቨርስቲው ከቀዳሚ የቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ነው።ሃይዲያን በተሰኘው የቤጂንግ አካባቢ የሚገኝም ሲሆን ምስራቅና ምዕራብ ብለው የተከፈሉ ሁለት ካምፓሶች አሉት። ተጠሪነቱ በቀጥታ ለሃገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር የሆነው ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰዓት አማርኛን ጨምሮ በ101 የውጭ ሃገራት ቋንቋዎች በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ያስተምራል ሲል አልዓይን ዘግቧል።
Show all...
👍 2🥰 1
01:09
Video unavailableShow in Telegram
ይሄው ነው
Show all...
5.74 MB
👍 8
#የኢሰመኮ_ሪፖርት #በአማራ_ክልል_አገዛዙ_ስለፈፀመው_ግፍ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢነትና ሥጋቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት አውጥቷል። በሪፖርቱ ፦ - ከሕግ ውጭ ግድያ (በድሮን ጨምሮ) ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፤ - የዘፈቀደ፣ ሕገወጥ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፤ - እገታ - አስገድዶ መሰወር እና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ አስሮ ማቆየት - የሀገር ውስጥ መፈናቀል ... ተዳሰዋል። ° በጸጥታ መደፍረስ፣ ° ከመንግሥት አካላት ተገቢውን ምላሽና ትብብር በወቅቱ ባለማግኘት ° በሌሎች ምክንያቶች ምርመራቸውና ክትትላቸው የዘገዩና የተጓተቱ በርካታ ጉዳዮችን መኖራቸው ተገልጿል። እነዚህን ጉዳዮች በመርመርና ክትትል በማድረግ በተገቢው ጊዜ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኮሚሽኑ የተላከለትን ዝርዝር ሪፖርት ከላይ አያይዟል፤ በጥሞና ያንብቡት። ኢሰመኮ በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከዐውድ ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆም ይገባል ብሏል። የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝቧል። #EHRC #Ethiopia #TikvahEthiopia ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016 በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ላይ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ #ውጡ ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ #በ11_ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችንም ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል። በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች አስረድተዋል። - መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ/ም በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር #በኤፍራታና_ግድም እና #ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እና የቀንድ ከብቶችና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል። - መጋቢት 6 ቀን 2016 በአማራ ክልል፣ በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል ፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ " ኑ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ " በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 በባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ #የፊጥኝ_እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል። - በባሕር ዳር ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል። - ሚያዝያ 7/2016 ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና ቀበሌ ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች (#ፋኖ ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ #የመንግሥት_የጸጥታ_ኃይሎች ወደ ቦታው በመግባት 7 (1 ሴትና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ ፈጽመዋል። ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ገልጸዋል። - ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከቀኑ ከ7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል። @tikvahethiopia #Amhara #EHRC @tikvahethiopia
Show all...
👍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.