cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፊርማ art

ወደፊት ከኛ ጋር በመስራት ህልሞን ይወቁ። ምን መሆን ይፈልጋሉ...........? 🎬የፊልም አክተር ለመሆን 🎶ሲንገር ለመሆን ግጥም እና ዜማ ከፈለጉ እና 🎬 ፕሮዳክሺኖችን እናገኛችኋለን ስለ Art በሞላው እዚ ይወራል Join @abibalageru Contact @antensl

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
185
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 @ethiogreat 🌻 @ethiogreat
Show all...
❤️'ማ_ይንገርሽ'❤️ ♡ ♡ ♡ ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ ግና ገና ሳይሽ ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር ጉልበቴም ይዝላል አካሌም ይደክማል ልሳኔም ይዘጋል ልቤም ያው ይፈራል ታዲያ የኔ ፍቅር የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ 🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹 @ethiogreat @ethiogreat
Show all...
❤️❤️ #ፍራፍሬዉ ፍቅሬ ገና ሳይሽ ድንግጥ ያለዉ ልቤ በሀሳብ ተጓዘ አንችን እያለመ በቀንም በማታም ሁነሽኝ ሀሳቤ #ሰበቤ...... ማየት የናፈቀው አይኔ መንገድ ላይ ስቀር አልወጣ ብለሽ ከቤትሽ ስቀር መባዘኑን ቀጠለ ልቤ መንገድ በመንገድ ስያሰኘዉ የቆየ ፍቅር ና መዉደድ #ገና..... ገና ይቀጥላል ናፍቆት ትዝታዬ መዉደድና ማፍቀሬ እስክትሆኝ የኔ መብሰል ላይ የነበርሽ ዉዷ ብርቱካኔ #ብርቱካኔ.... ስትበስይ አይቀርም ሁሌም መላጥሽ እኔዉ ልላጥሽ አቅፌ ተንከባክቤሽ በእቅፌ ሙቀሽ ያልጎደለዉ ፍቅሬን ከእጄ ጎርሰሽ ሁነሽ ከአጠገቤ ሁኜ ከአጠገብሽ ጥፍጥናሽ ልዩ ነዉ መዓዛ ዉበትሽ ...ለዉዷ ሚስቴ.... . . ✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍ 👉 @JONELOVER 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ❤ @ethiogreat ❤ ❤ @ethiogreat
Show all...
#ሁለት_ነጥብ [በመንጌ] ፡ ፡ የእግዜር ቤት ጠቋቁሮ ደመናን ሲቋጥር በዐይኖቼ ወደ ላይ በጥልቀት ሲማትር ፡ ጠቋቁሮ ከሚታይ ከደመናው መሃል ትወደኛለህ፡ወይ የሚል ፅሁፍ ይታያል። ፡ ፡ #ታዲያ...... ትወደኛለህ፡ወይ ከሚለው ፅሁፍ መሃል እንባሽን ሚመስለ ሁለት ነጥብ ቁሟል። ፡ እናልሽም ወዴ ፍርሃት ፍርሃት ብሎ የልብሽን ሚስጥር ከደመናው ስሎ ፡ ፍቅርሽ ስያሳየኝ የውስጥሽን እውነት ልቤ ተሳሰረ በፍቅርሽ ሰንሰለት። ፡ ፡ #እናልሽም_ውዴ........ ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ትወጣለች ጠሀይ አንድዬን ስማፀን አንቺ ሰጠኝ ከላይ የሚል ፀሁፍ ይፃፋል ከእንግዲህ በሰማይ ፡ ፡ #ግና አንዳንደዚህ ይህ ፍቅርሽ አይሎ ምስልሽን ስያሳየኝ በፊቴ ላይ ስሎ ፡ ፍቅርሽ በፈርሆን ተመስሎ ድንገት እንደ ሙሴ ደፋር ሆናለሁ በቅፅበት። ፡ እንዲህ ነው አለሜ ላንቺ ያለኝ ፍቅር ሙሴን ያስጠራኛል ልቆ ከዚች ምድር። ፡ ፡ #እናልሽም_ውዴ............. ዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ትወጣለች ጠሀይ አንድዬን ስማፀን አንቻን ሰጠኝ ከላይ የሚል ፅሁፍ ይፃፋል ከእንግዲህ በሰማይ። ፡
Show all...
🎬 YARED CASTING 🎬 🎬 ኦድሽን ማድረግ ጀምረናል 🎬 ሰላም 🎬 YARED CASTING 🎬ቤተሰቦች በምን ሰራው ፊልሙ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በምንሰራቸው ፊልሞች ላይ በድጋሜ ካስት ጀምረናል ቤተሰባችን ይሁኑ 🎬 በአክቲንግ ዘርፍ 🎬 በሞዴሊንግ ዘርፍ 🎬 በሙዚቃው ዘርፍ ለጥበብ አፍቃሪያን የቀረበ ድንቅ ቻናል። ለጀማሪያን ቅድሚያ እንሰጣለን @yared_Casting Join በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ። 🎞🎥🎞🎥🎞🎥🎞🎥🎞🎥 @yared_Casting 🎞🎥🎞🎥🎞🎥🎞🎥🎞🎥 🔊ኑ አብረን የራሳችንን የፊልም መንደር እንመስርት @yared_Casting 🎬 SIQE FILM PRODUCTION 🎬 🎬 YARED CASTING 🎬 አሁኑ ኑ ፈጥነው ፈጥነው ይመዝገቡ !!! 📞📞📞 0900014950 ተስሚ ህንፃ 4 ኪሎ ብርሀን ሽሮ ሶስተኛ ፎቅ ሰኔ 20 / 10 / 2013 እሁድ ቀን ከጠዋቱ 3•00 ጀምሮ 📞📞📞 0900014950 📞 ስልክ ቁጥር 0900014950 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡ 📞☎️📞☎️📞☎️📞☎️ 🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬🎬
Show all...
ስለ ነፃነት አንድ ተናጋሪ ተነሳና "እስቲ ደግሞ ስለነፃነት ንገረን" አለ እሱም መለሰ ፦ በአምባገነን ገዢያቸው ፊት ራሳቸውን አሳንሰው እንደሚሽቆጠቆጡትና አጋድሞ ሲያርዳቸው ጭምር እንደሚያወድሱት ባሪያዎች በከተማይቱ መግቢያና በየጓዳችሁ ተደፍታችሁ ለገፃ ነፃነታችሁ ስትሰግዱ አይቻለሁ ። አዎ! በየመቅደሱ ጓዳና በየምግቡ ጥላ ስር ሆነው ከእናንተ መሃል በጣም ነፃ የሚባሉት ሰዎች ጭምር ነፃነታቸውን እንደቀንበር ተሸክመውና እንደ እግር ብረት አጥልቀውት አይቻለሁ ። ልቤም በውስጤ ደምቷል ። ነፃ የምትሆኑት ነፃነትን የመፈለግ ሃሳብ እንኳን የማያፈናፍን ጭነት ማሰርያ ሲሆንባችሁና እንደ አላማና ግብ ቆጥራችሁ ስለ ነፃነት መናገር ስታቆሙ ብቻ ነውና ። ነፃ የምትሆኑት ቀኖቻችሁ ደንታ ቢስ ፣ ሌሊቶቻችሁ ደግሞ ፍላጎትና ችግር የሌለባቸው ሲሆኑ አይደለም ። እነዚህ ነገሮች ሕይወታችሁን ሲከቡትና እናንተ ግን ተገላልጣችሁ እርቃናችሁን ሆናችሁ ከበባውን በጣጥሳችሁ ከእነሱ በላይ ከፍ በምትሉበት ግዜ ነው ። ነፃ ለመውጣት ከላያችሁ አራግፋችሁ የምትጥሉት ነገር የገዛ ራሳችሁን ማንነት ስብርባሪዎች እንጂ ሌላ ምንድንነው? የምታስወግዱት ኢ-ፍትሃዊ የሆነን ሕግ ከሆነ ያ ሕግ በየግንባራችሁ ላይ የተፃፈው በእናንተው በራሳችሁ እጅ ነው ። የሕግ መጽሐፍቶቻችሁን በሙሉ ብታቃጥሉ እንኳ ልታስወግዱት አትችሉም ። ባሕር ሙሉ ውሃ እያንቆራቆራችሁ የዳኞቻችሁን ግንባር ብታጥቡ እንኳ ልትፍቁት አትችሉም ። ከዙፋን ላይ የምታስወግዱት አምባገነንነትን ከሆነ በቅድሚያ በራሳችሁ ውስጥ የተተከለው(ያለው) ዙፋን መውረዱን አረጋግጡ ።ምክንያቱም አምባገነን መሪ የሚያስተዳድረው በራሳቸው ነፃነት ላይ አምባገነን የሆኑትን በገዛ ክብራቸው ላይም ሃፍረት የሆኑትን ነውና ። ነፃዎቹንና ክብራቸውን የሚጠብቁትንማ ሊመራቸው (ሊያስተዳድራቸው) አይችልም ። የምታስወግዱት ደንታ-ቢስነትን ከሆነ ያ ደንታ-ቢስነት እናንተው ያመጣችሁት እንጂ በእናንተ ላይ የተጫነባችሁ አይደለም ። የምታስወግዱት ፍርሃትን ከሆነ የዚያ ፍርሃት መኖርያ በእናንተው ልብ ውስጥ እንጂ በምትፈሯቸው ሰዎች እጅ ውስጥ አይደለም ። በእውነቱ ነገሮች ሁሉ የምትፈልጉትንና የምትፈሩትን ፣ የምትጠሉትንና የምትወዱትን የምታሳድዱትንና የምትሸሹትን ሁሉ በከፊል ይዘው ያለማቋረጥ የሚንቀሳቀሱት በእናንተነታችሁ ውስጥ ነው። እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ የሚንቀሳቀሱት እንደ ብርሃንና እንደ ጥላ አብረው ሆነው ነው ። ጥላው እየደበዘዘ ሲጠፋ ከኋላ የሚንቀረፈፈው ብርሃን ለሌላኛው አዲስ ብርሃን ይሆናል ። በተመሳሳይ ሁኔታም የእናንተ ነፃነት ማሰሪያውን ሲፈታ ለሌላኛውና ከፍ ላለው ነፃነት ማሰሪያ ይሆናል ። ✍️የካህሊል ጂብራን @Zephilosophy @Zephilosophy
Show all...
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @ethiogreat @ethiogreat
Show all...
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ❗️ 1. በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሰኔ 19 እና ሰኔ 20 2013 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣ - ብርድልብስና አንሶላ፣ - የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ - የስፖርት ትጥቅ - አራት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡ ➢ በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡ ➢ ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡ ➢ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን 2. ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡ 3. ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ በ http://portal.aau.edu.et በመጠቀም የኦንላየን ምዝገባ ማካሄድ ይጠበቅባችኋል፡፡ 4. የገጽ ለገጽ ትምህርት የሚጀመረው ረቡእ ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 5. ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ 6. በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች ከዘንድሮ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2013 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡ ©የአ.አ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር @Academic_learn
Show all...