cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✍ ከማስታወሻ ገፃችን 🗓

ስለ ህይወት ብዙ እላለሁ ! በቂ እውቀት ባይኖረኝም ....እታዘባታለሁ። . . . . life is like war . . . . Always be ur self . . . 👉 መገኛዬ @ItsEtafrharg 👉 @itsEtaferharg

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከተነበበው ላይ እንካፈል #አለማወቅ "በጣም የምወደው ጓደኛ ነበረኝ እና የሆነ ግዜ ላይ ይህንን ብሎኝ ነበር ! 'የምታየው ሁሉ እያየኸው የሚጠፋ ነው ።' እውነቱን ነው እያየሁትም ጠፋ ። 'የወፍ ድምፅ የማትሰማበት ግዜ ይመጣል' ። ይለኝም ነበር ። ይኸው የወፍ ድምፅ ከሰማሁ ቆየሁ ። እዚህ መጥቼ ቁጭ ስል በሩቁ ከሰማይ ላይ አንድ ወፍ ሲበር ሳይ ደስ ይለኛል ፣ አስታውሰዋለሁ ። ጥቂት ቆይቶ እንባ በዝርግ ፊቱ ላይ ፈሰሰ ። የአፍ ትራፊ መቀበያውን እራፊ ጨርቅ ከጭኖቹ ላይ በማንሳት ፊቱን ሞዠቀ ። በዝምታዬ ፀናሁ ለመስማት ሳይሆን የምለው ስላልነበረኝ ። "እዚያ ሻይ ቤት የማልሄደው አንሶብኝ እንዳይመስልሽ ብዙ ትዝታ አለኝ ያለ አስታዋሽ የማስታውሰው የሚናፍቀኝ፣ የሚቆጨኝ፣ ከጓደኛዬ ጋር አሁን እንደምታያቸው ወጣት ሀኪሞች ገንዘብ አጋጭተን የበላነው፣ የጠጣነው፣ እኔም እሱም ፍቅርን አግኝተን ያጣነው..." ብሎ በዝምታ እንባውን ማርገፍ ቀጠለ ። "ስለዚህ እዚህ የምመጣው ለሽሽት ነው" የኔ ልጅ አለኝ ። አባባሉ አሳሰበኝ ግን አልጠየኩትም ። "ሽሽት ከትዝታ፣ ከሰቀቀን ከራስ ሽሽት እዚህ መጥቼ ወዳጄን እፈልገዋለሁ ። የሚያየኝ፣ የሚሰማኝ ይመስለኛል ። አየዋለሁ፣ መፀፀቴን እዘረግፍለታለሁ" ። ብሎ ሲቀዳለት ያላስተዋልኩትን ውስኪ ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ በአንድ ትንፋሽ ከአፉ ውስጥ ወረወረው ። "አሁን የት ነው ያለው ?" ብዬ ጠየኩት ፣ ፈገግ ብሎ አየኝ ። "የለም! እንደወፎቹ ድምፅ ይጠፋል ብዬ ባላሰኩት ሰዓት ጠፋ! ሄደ" አለኝ ። "የምወደውም ሁሉ ነገር ከሱ ጋር አብሮ ጠፋ " ጨነቀኝ ፣ "ለምንድነው ይህንን ሁሉ የምትነግረኝ" ? "ጓደኛዬ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ?" የምትችዪ ይመስልሻል? አለኝ ። "ለምን"? አልኩት "ለብቸኝነቴ ማስረሻ፣ የወዳጅነት ማስታወሻ እንድትሆኚኝ እፈልጋለሁ " አለ። "ትዕዛዝ አይደለም ግን አስቢበትና ሌላ ግዜ ትነግሪኛለሽ ። በጣም ጥሩ ጓደኛሞች የምንሆን ይመስለኛል" ። #አለማወቅ .... ዳዊት ወንድማገኝ እንደፃፈው !
Show all...
"ራስን ለመፈለግ የሚደረግ ሁሉም መንገድ ወደ ልጅነት የሚደረግ ጉዞ ነው ። ፣ በልጅነት ገና ስንወለድ ምንም ነገር ሳናውቅ ፣ ሁሉም ነገራችን አለማወቅ በነበረበት ጊዜ ... አንድ የምናውቀው ነገር እራሳችንን ብቻ ነው ። "ስለራሳችን ደግሞ አንድ ሳይገባን የምናውቀው ፣ ሲገባን ግን የምንረሳው ወይም እንደማናውቅ የምንሆነው ጉዳይ ፣ በህይወት ለመኖር ሌላ ሰው ማስፈለጉ ግዴታ መሆኑን ነው ። አንድና መሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት ቢኖር ይሄው ነው ። የሌላ ሰው መኖር አስፈላጊነት ሳናውቅ የምናውቀው ስናውቅ ፣ የምንፈራው ስናቀው የምንፈራውና የምንከዳው መሰረታዊ ፍላጎት ነው ። #አለማወቅ ፣ በዳዊት ወንድማገኝ ገጽ 208
Show all...
በህይወት ሊደርስብን የሚችለው የመጨረሻው ክፉ ነገር ቀድሞ ደርሶብናል ። የህይወት ትውውቅ የሚጀምረው "ከሌለ ነገር ነው" ለምን የሌለን ነገር ማሰብ ግድ ይላል ? ሰዎች ሲኖረን ያለንን አናስብን ። - 'የሌለን ነገር' ሲመጣ ነው ማሰብ የምንጀምረው ። ጡት መኖሩን ያወቅኩት ጡት ስጠባ ሳይሆን ጡት ሲቀርብኝ ነው ። በመጀመሪያ ጡት ይቅርና እናት እንደነበረኝ እንኳን አላውቅም ። መርሳት ብዙ ችግር ያለው አይመስለኝም ። ይሄው እኔ ብዙ ነገር እረስቼ እየኖርኩ ነው ። በጣም ለመረዳት የሚቸግረው ነገር ባደግንበት ዘመን ሰው ሰውነቱን መርሳት መቻሉ ነው ። ሰው ይገርማል ! ያልነበረ ፣ የሚኖር 'ሰው' ምድርን እና ሞላዋን በእውቀቱ ፣ በብልሀቱ በተለይ ደግሞ በጉልበቱ ተቆጣጥሮ የገዛ ። #አለማወቅ ገጽ 182-183
Show all...
" ሰው አንድን ነገር የሚያደርገው በምክንያት ነው ። ሁሉም ሰው ያጠፋል ፣ ሁሉም ሰው ደግሞ በጎ ይሰራል ። ከሰው ጋር የምንኖረው በጎ ስለሆንን ሳይሆን ፣ ከክፋታችን ይልቅ በጎነታችን ስለሚበዛ ነው " ። #አለማወቅ ገጽ 178
Show all...
የውስጤን ፍርሀት የትኛዉ ቃል ይገልፅልኝ ይሆን... 😔
Show all...
አጥብቀው ከያዙት ለካስ ፍቅር ሞት ነው
Show all...
መሄድህ ሳይሆን አለመምጣትህ ነዉ ሚረብሸኝ
Show all...
ለካ ለመኖር መጓጓትም መታደል ነዉ
Show all...
...እስካሁን ድረስ ያወራናቸዉን እያንዳንዱን ቃል አስታዉሰዋለሁ ሁሉንም... ቃል በቃል... እሱ ደግሞ ዉስጤን እየገደለዉ ነዉ ቀስ በቀስ እየሞትኩ ነዉ...
Show all...
"አንዳንዴ ለመኖር ስትል ያለፈ ታሪክህ እና ማንነትህን መግደል አለብህ" ግድ ይልሀል !
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.