cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

AddisWalta - AW

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel. For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Show more
Advertising posts
45 260
Subscribers
+1424 hours
+677 days
+42730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቡርክና ፋሶ ኦጋዱጉ በየዕለቱ መብረር ሊጀምር ነው ግንቦት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቡርኪና ፋሶ ኦጋዱጉ የሚያደርገውን በረራ ማሳደጉን አስታውቋል። ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ በረራውን ዕለታዊ በማድረግ ቀልጣፋ የበረራ አማራጭ መፍጠሩን አየር መንገዱ ገልጿል።
Show all...
👍 7
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ጋር ተወያዩ ግንቦት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አምባሳደር ምስጋኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው ውይይት የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና የመልሶ ማቋቋም ሂደት እንዲሁም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
Show all...
👍 4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግብርናው ዘርፍ የታየውን ዕድገት ከባለፈው ዓመት ጋር በማነጸጸር በዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ከተናገሩት… #አዲስ_ዋልታ
Show all...
👏 12👍 3
አያት ሪል እስቴት ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ለ #ጽዱኢትዮጵያ፡- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄውን ይቀላቀሉ፡፡
Show all...
👏 7👎 1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግብርናው ዘርፍ የታየውን ዕድገት ከባለፈው ዓመት ጋር በማነጸጸር በጎርጎራ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ከተናገሩት…
Show all...
👏 7👍 2🙏 1
ሆሣዕና #ከተሞቻችን ሆሣዕና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክላስተር ከተሞች አንዷ ስትሆን የሀዲያ ዞን አስተዳደር ዋና መቀመጫም ናት፡፡ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በደቡብ አቅጣጫ 230 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። ሆሳዕና ከባህር ጠለል በላይ 2 ሺሕ 217 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝና ወይናደጋ የአየር ንብረት ያላት ሜዳማ እና ተዳፋታማ ተፍጥሯዊ የመሬት ገፅታን ተላብሳለች፡፡ በ1888 ዓ.ም እንደተቆረቆረች የምነገርላት ሆሳዕና የከተማዋ የቀድሞ መጠሪያ ዋቸሞ እንደነበርና ወደ ሆሳዕና የቀየሩት ራስ አባተ ቧያለው ሲሆኑ ተሹምው ወደ ስፍራው ባመሩበት ዕለት እየተከበረ የነበረውን የሆሳዕና በዓል ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ይነገራል። ሆሣዕና በስድስት ቀበሌዎች የተዋቀረች ከተማ ስትሆን ኬንተሪ፣ ገብረፃዲቅ፣ የአብስራ፣ ማሪያም፣ ሞቢል፣ ቁጭራ፣ አራዳ እና ካናል/መሳለሚያ በሚል የሚጠሩ የሰፈር ስያሜዎችም አሏት። በከተማዋ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሆነውን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጨምሮ፣ ሆሣዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ሆሳዕና መምህራን ኮሌጅ እንዲሁም ቅድስት ስላሴ፣ ዋቸሞ 1ኛ ደረጃ፣ አለሙ ወልደሀና 2ኛ ደረጃ እና ሌሎችም ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ሆሣዕና ምቹ የሆቴል እና ቱሪዝም እንቅስቃሴ የሚታይባት ከተማ ስትሆን ቪክትሪ፣ አዲላ፣ ዋኣኔ መላይ፣ ዎዜ ስታር፣ በረከት እና የመሳሰሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች እና ሌሎች ይጠቀሳሉ። 👇👇 https://shorturl.at/ghpFR
Show all...
👍 16
በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመረቀ ግንቦት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ተመርቆ ስራ ጀምሯል። በ250 ሚሊየን ብር ካፒታል የተከፈተው ፋብሪካው በቀን እስከ 10 መኪኖችን የመገጣጠም አቅም እንዳለው ተገልጿል። ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ፋብሪካውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ይገኛል። ፋብሪካው ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ መንግስትም ለግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል። ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር ቅርንጫፍ)
Show all...
👍 14👏 1
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ ግንቦት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባ አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡ የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ የረቂቅ አዋጁን መሻሻል አስፈላጊነት እና በምርመራው ሂደት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ የአርሶና አርብቶ አደሩን እና ከፊል አርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ አገሪቱ ከደረሰችበት ዘርፈ ብዙ እድገት ጋር እኩል ለማራመድ እንዲቻል፣ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማደራጀትና ለተጠቃሚው በአግባቡ ለማሰራጨት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር መንግስት እና የመሬት ተጠቃሚዎች አስተማማኝ የሆነ መረጃ የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ነውም ብለዋል፡፡ 👇👇 https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02tV3vu3WTvCBbHF8reioe2mX9UbcWpTWpkKfkqgJ594be7tXg97TBi3uUGRbamPvNl
Show all...
👍 9
የኢትዮጵያ ታምርት አንደኛው ዓላማ ዘርፉ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረጉ ማነቆዎችን በቅንጅት ለመፍታት መቻል ነው - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ግንቦት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ታምርት አንደኛው ዓላማ ዘርፉ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረጉ ማነቆዎችን በቅንጅት ለመፍታት መቻል መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ትላንት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠናቀቂያ ሥነ ሥርዓት ላይ መታደማቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ታምርት ደግሞም ትጠቀም ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዓላማው ሁለት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የመጀመሪያው እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ዕድሎች እጅግ በተሻለ መንገድ መጠቀም ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ዘርፉ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረጉ ማነቆዎችን በቅንጅት ለመፍታት መቻል ነው ብለዋል። መንግስት ለዘርፉ ዕድገት ልዩ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀምም ትልቅ ትኩረት መስጠቱን አመልክተዋል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህልን እንዲያጎለብት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖው 2016 ከግንቦት 1 ጀምሮ ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
Show all...
👍 9🙏 3
በጎርጎራ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠ/ ሚ ዐቢይ አሕመድ የሰጡት ገለጻ 👇👇 https://www.youtube.com/watch?v=S7Ei0OYN3yk
Show all...
👍 16🙏 1