cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

👑Ethio pic

የ ኢትዮ pic አባል በመሆን በፎቶ ውድድር ይሸለሙ ለማንኛውም አስተያየት @yowbizz or @tteda @naniboy1 ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ታላቅ የ pic Competition Telegram ላይ ታዋቂ famous ለመሆን ከፈለጉ የእርስዎን አሪፍ pic ይላኩ👌 👇👇 Join us👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAESVJQasdYJg0blmXQ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
289
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ትምህርት ተከፍቶ የዜግነት ክብር ሲባል ═══••🇪🇹••═══ የኮሮና ፍርሃት በኢትዮጵያችን ፀንቶ ታየ ቤት መቀመጥ ዳር እስከ ዳር ብርቶ ለሰላም ለፍቅር ለህዝቦች ነፃነት እጃችንን ታጥበን ቆመናል በርቀት መሰረቱ ፅኑ በሽታ መጥቶብን ህዝቦች ነን ከስራ ከስራ የራቅን ድንቅ ገዳይ በሽታ የሞትም ባለቤት የተፈጥሮ እርግማን የበሽታዎች ሁሉ እናት እንርቅሃለን አለብን አደራ ኮሮና ጥፋልን እኛም ስራ እንስራ የምን አንብቦ ማለፍ ነው ገባ ገባ በሉ እንጂ @ethiopicc01
Show all...
AUD-20200425-WA0005.opus2.52 KB
ኮቪድ -19፡ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ መንፈሳዊ መዝሙር ለቀቁ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓለም እየተሸበረበት ያለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በማድረግ ፈጣሪን የሚማፀን ‘ማረን’ የሚል መንፈሳዊ መዝሙር አወጡ። መዝሙሩ በቀጥታ ቫይረሱን የተመለከተ ባይሆንም “ዓለም በመጥፎ ዜናዎች እየተሸበረ ባለበት በዚህ ጊዜ አትተወን” ሲሉ በመዝሙራቸው አምላካቸውን ለምነዋል። ‘ማረን’ የሚል ርዕስ ያለው ይህ መንፈሳዊ መዝሙር በዩቱብ የተለቀቀው ትናንት ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጋርተውታል። በቪዲዮ ላይ ቀዳማዊት እመቤቷ ፈጣሪ ሕዝቦቹን እንዲጠብቅላቸው ተንበርክከው ሲፀልዩ ይታያል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሰው በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው መጋቢት 3/2012 ዓ. ም ነበር። እስካሁን 55 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። [BBC]
Show all...
ማረን.mp442.36 MB
#ኮቪድ19 በዓለም አቀፍ ደረጃ በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያስከትለውን የጫና ክብደት በመገንዘብ፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለፉት ሳምንታት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል ሲዘጋጅና ርምጃዎችን ሲተገብር ቆይቷል፡፡ እስካሁን ሊከሰቱ የሚችሉትን ፈታኝ ሁኔታዎች ያለማቋረጥ በመገምገም፣ ከሁኔታዎቹ ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ ርምጃዎች ሲወሰዱ ቆይቷል፡፡ የኮቪድ19 ወረርሽኝ በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር ደረጃ መስፋፋቱን በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስቴሮች ምክር ቤት፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 በተደነገገው መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ደንግጓል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንዲያደርግ እና የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን ቫይረሱን የመከላከል መመሪያ በጥብቅ እንዲተገብር ይጠይቃሉ፡፡
Show all...
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ #Ethiopia declares state of emergency to fight #COVID19
Show all...
እናሆ ምስጋና፤ ሰባራ ባቡር አካባቢ የሚገኘው ዕድገት በህብረት ህንጻ ባለቤቶች 150 ለሚሆኑ ተከራዪቻቸው ለሁለት ወር በነፃ እንዲገለገሉበት ፈቅደውላቸዋል። ለአከራዮች ያቀረብነውን ጥሪ ተከትሎ ይሄንን ውሳኔ በመወሰናቸው አክብሮቴን መግለጽ እፈልጋለሁ። ሌሎች አከራዮችም የእነሱን ፈለግ እንደሚከተሉ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። [Takele Uma Banti]
Show all...
ቻይና የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዎቹን ሁለት የህመም ደረጃዎች ለማከም የተጠቀመችባቸውን የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ልትሰጥ ነው፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር ከቻይና የባህል ሃኪሞችና ተመራማሪዎች ጋር ቫይረሱን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡ ቻይና የባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም ስኬታማ በሆነ መልኩ የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር የቻለችባቸው መንገዶችን ለኢትዮጵያ ለማጋራት ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡ በተለይ የቫይረሱ ህመም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ለማከም የተጠቀመችባቸውን ሁለት የመድሃኒቶች ዓይነቶች ለኢትዮጵያ በድጎማ መልክ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡ ረጅም እድሜ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ የባህል ህክምና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረትም በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ እና በሙያም እደግፋለሁ ብላለች፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ ሀገር ከተጀመሩ ስራዎች ጎንለጎን የቻይና ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባህላዊ መድሃኒቶችም ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት እንዲሳካም የቻይናን ልምድ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡ [Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia]
Show all...
ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ 3 ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ፡፡ ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል። ዛሬ የተገለጸውን ጨምሮ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ከፍ ብሏል ነው። ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው፡፡ አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው። ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ የተደረገለት ነው፡፡ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ ገብቷል፤ ይህም በጽኑ ህሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር ሁለት ሆኗል፡፡ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ጤና ሚኒስቴር ያሳስባል፡፡ ህብረተሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እናድርግ፡፡ በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አራቱ ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።
Show all...
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ #Ethiopia declares state of emergency to fight #COVID19 [Ministry of Health,Ethiopia]
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.