cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

yeteshale ኪዳን (SOLA Scriptura)

Scripture alone (መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ) 2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy) 15፤ የእውነትን ቃል #በቅንነት (#በትክክል፤# ቀጥ አድረጎ)የሚናገር #የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። ይህ የእውነትን ቃል የሚማሩበት ምኅላፍ (ቻናል) ነው። ለጥያቄና አስተያየት፦ 0983657277 0962858609

Show more
Advertising posts
238Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

📌#የእግዚአብሔር_ልጆችም #የሰውን_ሴቶች_ልጆች_አገቡ -------------------------------- ✍️ ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳብ ለማንሳት የፈለግንበት ምክንያት በቅዱሳኖች የሚነሳውን ጥያቄ ለመመለስና ቅዱሳን በእውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት እንዲኖረን በማሰብ ነው። ✍️ዘፍጥረት 6 2፤ የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ። 📌የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው? ✍️ይህ በዘፍጥረት መጽሐፍ በ6ኛው ምዕራፍ የሚገኘው ሀሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ዘንድ ጠንካራ ምንባብ ተብሎ የሚጠቀስና በቅዱሳን መካከል ግራ የሚያጋባ ጥቅስ ሆኖ ይታያል። የመጽሐፍ ቅዱሱን ደራሲ መንፈስ ቅዱስን ታምነን ሀሳቡን ስንመረምር በዚህ ምዕራፍ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው የተጠሩት እነማን እንደሆኑ ማወቅና መረዳት ይቻላል። 📌መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል፦ --------------------------- ✍️የዘፍጥረት መጽሐፍ የተጻፈው በሙሴ በኩል እንደሆነ ግልጥ ነው። ሙሴ በዘመኑ 6 መጽሐፍትን እንደጻፈ ታሪክ ይነግረናል። ከዘፍጥረት -ዘዳግም 5ቱ የህግ መጽሐፍት (Pentateuch's) ተብለው የሚጠሩት ሲሆን በተጨማሪም የኢዮብን መጽሐፍ ሙሴ እንደጻፈው ይገመታል። ✍️ሰለዚህ የዘፍጥረትና የኢዮብ መጽሐፍ በሙሴ በኩል ከተጻፉ ሙሴ የእግዚአብሔር ልጆች በማለት የገለጻቸው ማንነቶችን በቀላሉ መረዳትና ማወቅ ይቻላል። ✍️እንዲሁም የመጀመሪያው ተደራሲያንና የመጽሐፉ ባለአደራዎች የሆኑትን የአይሁዳውያን መምህራንን ብንጠይቃቸው የመጽሐፍ ቅዱሱንም ሆነ የታሪክን መጽሐፍት አጣቅሰው በግልጽ ሊያብራሩልን ይችላሉ። ✍️በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ “የእግዚአብሔር ልጆች” የሚለው አገላለጽ በዘፍጥረት 6:2, 4፣ ኢዮብ 1:6፣ 2:1፣ 38:7, እና መዝሙር 89:6 ላይ ይገኛል። እነዚህ ጥቅሶች “የእግዚአብሔር ልጆች” እነማን እንደሆኑ አንዳች እውነት ይጠቁሙናል። 📌ኢዮብ 1፡6፤ ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፥ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ። በኢዮብ 1:6 ላይ የተጠቀሱት “የእግዚአብሔር ልጆች” በእግዚአብሔር ፊት የተሰበሰቡ መንፈሳዊ ፍጥረታት (መላእክት)እንደሆኑ ግልጽ ነው። በኢዮብ 2:1, 2 እንዲሁም በተመሳሳይ 📌ኢዮብ 38፡6-7፤ አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥ መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር? የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው? እግዚአብሔር የምድርን ‘የማዕዘን ድንጋይ ባቆመ’ ጊዜ ‘የእግዚአብሔር ልጆች እልል እንዳሉ’ ተገልጿል። (ኢዮብ 38:4-7) በዚያ ወቅት የሰው ልጆች ስላልተፈጠሩ እዚህ ላይ የተጠቀሱት ‘የእግዚአብሔር ልጆች’ መላእክት መሆናቸውን ያረጋግጥልናል። ✍️በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በጴጥሮስ መልእክትና በይሁዳ መልእክት ዘፍጥረት 6 ላይ ስለወደቁት መላዕክቶ በቀጥታ ተጽፎ እናገኛለን። -------------------------------- 📌ይሁዳ 1 (Jude) 6፤ መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል። 📌2 ጴጥሮስ 2 (2 Peter) 4፤ እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥ 5፤ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥ ✍️በጴጥሮስና በይሁዳ መልዕክት ተጨማሪ አንድ ነገር እናገኛለን እነዚህ መላዕክቶች አሁን በዚህ ምድር እንደሌሉ ይልቅስ በጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ታስረው ለታላቁ የፍርድ ቀን እየተጠበቁ እንደሆነ ይነግረናል። ✍️እንደዛ ከሆነ አሁን የአዳምን ግዛት ማለትም አየሩን ምድሩንና የውሃ አካላቱን ተቆጣጥረው ካሉት ከሰይጣንና ከአጋንንቶቹ የተለዩ መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባናል።በዚህ መሰረት መላእክቶች በሁለት ዙር እንደወደቁ መረዳት እንችላለን። 📌1)በመጀመሪያ ዙር የወደቁት መላእክት(አጋንንቶች) =መሪያቸው #ሰይጣን ወይም #ዲያቢሎስ ነው =የወደቁት ሰው ከመፈጠሩ በፊት ነው። ዘፍ 1:2 = የወደቁበት ምክንያት እንደ እግዚአብሔር ለመሆን(በልዑሉ መመሰል) ሲፈልጉ ። ኢሳ 14:12-15, ሕዝ 28 :13-17 📌2)ሁለተኛ ዙሮችን ብዙ ጊዜ ሰው አያስተውላቸውም ዘፍ 6:2 , ኢዮብ 1:6, 38:6-7 = መሪያቸው #አብዶን ወይም #አጶልዮን ይባላል።ራዕ 9:11 = ሰው ከተፈጠረ በኃላ የወደቁ ናቸው። ዘፍ 6:2 = የወደቁበት ምክንያት የክብር ቦታቸውን ሳይጠብቁ ከሰው ሴቶች ልጆች ጋር ዝሙት በመፈፀማቸው ነው። ዘፍ 6:2 , ይሁዳ 1:6, 2 ጴጥ 2:4 = አሁን በምድር ላይ የሉም በጨለማ ጉድጓድ(በጥልቁ) ውስጥ ታስረው ይገኛሉ 2 ጴጥ2:4 ,ይሁዳ 1:6 ቅዱሳን ማስተዋል ያለብን ነገር ------------------------- 📌አሁን ላይ ካላመኑ ሰዎች የሚወጡት ሰይጣን(ዲያቢሎስ) የሚመራቸው አጋንንቶች መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባናል። ✍️ ካላመኑ ሰዎች በሚወጡ ጊዜ ምንም ወደሌለበት ምድረበዳ ይሄዳሉ እንጂ ወደ ጥልቁ አይሄዱም እስከዛሬ ድረስ ወደ ጥልቁ ውረዱ ተብሎ የተፀለየው ፀሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። አንድ ወንጌላዊ ሰይጣንን ከነተከታዮቹ ወደ ገሀነም የማስገባት ስልጣን የለው። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ሰይጣንን ከነ ተከታዮቹ ወደ ገሀነም እንደሚያስገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። 📌 ኢየሱስ በምድር የአገልግሎት ዘመኑ እንኳ አጋንንትን ሲያስወጣ ወደ ጥልቁ ውረዱ አላለም ምክንያቱም ወደ ጥልቁ የሚወርዱበት ጊዜያቸው ገና አልደረሰም ነበርና ወደ አሳማዎች እንዲገቡ አደረገ። ማቴ 8:29-31... 📌እንዲሁም ኢየሱስ ሲያስተምር ርኩስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ ምንም ወደሌለበት ምድረበዳ ይሄዳል ነው ያለው። ማቴ 12:43-45...እንጅ ወደ ጥልቁ ይወርዳል አላለም ምክንያቱም ጊዜያቸው ገና አልደረሰምና። 📌በመጨረሻ ግን ሰይጣንን ከነተከታዮቹ ወደ ገሀነም የሚልካቸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ✍️ይሁዳ 1 (Jude) 17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ ✍️ 2 ቆሮንቶስ 13፡14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
Show all...
ህያው አምላክ ነህ አዜብ ኃይሉ ቁ~6 አዲስ አልበም | 6 MB | @ZELALEMAWI sʜᴀʀᴇ ◈JOIN◈sʜᴀʀᴇ
Show all...
👏 1
❤#ኢየሱስ_መማጸኛ_ከተማችን❤ ============================= ✍️ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ " እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም #ስለ_እኔ_የሚመሰክሩ_ናቸው፤" (የዮሐንስ ወንጌል 5: 39) ✍️ ሉቃስ 24 (ኢየሱስም).... 27፤ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን #ተረጐመላቸው። ✍️መጽሐፍት ሁሉ ስለ ኢየሱስ ይናገራሉ! ✍️የመማጸኛ ከተሞች ብሉይ ኪዳን ዋና አገልግሎታቸውና የአዲስ ኪዳን ትርጓሜያቸው። ዘዳ 4:41-43, ዘዳ 19:1-13, ኢያሱ 20:1-9 ✍️በብሉይ ዘመን የትኛውም እስራኤላዊ ወይም እንግዳ በተለያዬ መንገድ በስህተት ነብስ ቢያጠፋ ወንጀለኛ ስለሆነ የሟች ዘመድ እንዳይገድለው እና እንዳይበቀለው እግዚአብሔር ወዳዘጋጀው መማጸኛ ከተማ በመሸሽ ከመጣበት የሞት አደጋ ማምለጥ ይችል ነበር። ዘዳ19:5-6 ✍️ይህ ነብሰ ገዳይ (ኃጢያተኛ) ከመጣበት የሞት ፍርድ ማምለጥና መዳን የሚችለው መልካም ስራን በመስራትና ሀይማኖታዊ ስርዓት በመፈጸም ሳይሆን እግዚአብሔር ወዳዘጋጀው የመማጸኛ ከተማ ከገባ ብቻና ብቻ ነው። ✍️በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ከመማጸኛው ከተማ መውጣት የለበትም፡፡ምክንያቱም ተበቃዮቹ ከመማጸኛው ከተማ ወጥቶ ካገኙት ሊገድሉቶ ይችላሉ። የኃጥያተኛው ዋስትናም በሊቀካህናቱ መኖር ላይ ይመሠረታል። በመማጸኛ ከተማ ገብቶ የሚኖር ሀጥያተኛ ሊቀካህናቱ በሕይወት እስካለ ድረስ እገዳላለሁ ብሎ አይሰጋም አይሳቀቅም ነበር። ዘኃ 35:25-29,ዕብ 7:24-26 📌 ልክ እንደዚህ እኛም በኃጢአታችን እና በበደላችን የሚጠብቀን ዘላለማዊ የሞት ፍርድ ነበረብን ነገር ግን በምህረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ እናመልጥበት ዘንድ አማናዊ መማጸኛ ከተማችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አዘጋጀልን። 📌 እኛም በአዲስ ኪዳን ዘመን የምንገኝ ከዘላለም ሞት ፍርድ ማምለጥ የምንችለው መልካም ስራ በመስራት ሀይማኖታዊ ስርዓቶችን በመፈጸም ሳይሆን እግዚአብሔር ለሀጥያተኞች ሁሉ ያዘጋጀውን የአዲስ ኪዳን መማጸኛ ከተማ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን በጸጋው ብቻና ብቻ ነው። ኤፌ 2:8-9, ሮሜ 3:21-23, ሮሜ 4:3-6 📌ኢየሱስ ክርስቶስን በማመናችሁ በጸጋው ድናችኋል ይህም እናንተ በራሳችሁ ያገኛችሁትን ሳይሆ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መዳን ለምናደርገው መልካም ተግባር የሚሰጥ ዋጋ አይደለም "ማንም ሰው ደህንነትና ያገኘሁትበበጎ ስራዬ ነው ሊል አይገባም"። (ሕያው ቃል) ኤፌ 2:8-9 📌 እንዲሁ እኛም በአዲስ ኪዳን የተገለጠ ታላቅ ሊቀካህናት ኢየሱስ ክርሰቶስ አለን። ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን እንደነበረው ሊቀካህናት የሚሞት ሳይሆን ለዘላለም ሕያው የሆነ የማይሞት ሊቀካህን ነውና ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናኛችን ነው። ከመማጸኛ ከተማችንና ከማይሞተው ሊቀ ካህናችን ከኢየሱስ የተነሳ ለዘላለም አምልጠናል ሞት በእኛ ላይ ስልጣን የለውም ዘላለማዊ የሕይወት ዋስትና አለን። 📌ዮሐንስ 6:37፤ አብ የሚሰጠኝ ሁሉ #ወደ_እኔ_ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን #ከቶ_ወደ_ውጭ_አላወጣውም፤ 38፤ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። 39፤ ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው። ✍️ዕብራውያን 7 (Hebrews) 24፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ..... 26፤ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤ ✍️ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ሰላም ብዙ ምህረት ለሁላችንም ይብዛ። አሜን።
Show all...
1
♥️#በኢየሱስ_መታዘዝ_ጸድቀናል♥️ ===================== ✍️ዳግም የተወለድን ሁላችንም አንዱን የክርስቶስ ን ጽድቅ እኩል ተካፍለናል። ✍️<<በአንዱ አዳም አለመታዘዘ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ (በኢየሱስ) መታዘዝ ጻድቃን ይሆናሉ፡፡>> (ሮሜ 5፥ 19) ✍️ኃጢአተኞች #የተባልነው በሰራነው ሳይሆን# አዳም በሰራው እንደ ሆነ #ጻድቃን የተባልነውም በሰራነው ሳይሆን በክርስቶስ ሥራ ነው፡፡ ✍️ሰው ሀጥያተኛ የተባለው የድርጊት ሀጥያቶችን ስለሰራ ሳይሆን ከአዳም በተቀበለው የሀጥያት# ተፈጥሮ ምክንያት ሀጥያተኛ ሆኗል እንደዚሁም አንድ ሰው(አማኝ) በሚሰራቸው የጽድቅ ስራዎቹ ሳይሆን #በክርስቶስ ስራ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆኗል። ✍️ሥራችን ኀጢአተኞች# ካላደረገን ሥራችን# ጻድቃን ሊያደርገን አይችልም ፡፡ ስለዚህ በአንዱ አዳም ሃጢያተኞች ሆነናል ብለን ለመናገር ካላፈርን በአንዱ በክርስቶስ ጻድቅ ነን ማለት እውነት እንጅ ከንቱ ድፍረት አይደለም ፡፡ (ሮሜ 5፡12-21) በክርስቶስ ላላችሁ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ። https://t.me/yeshalekidan https://t.me/yeshalekidan https://t.me/yeshalekidan https://t.me/yeshalekidan
Show all...
yeteshale ኪዳን (SOLA Scriptura)

Scripture alone (መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ) 2 ጢሞቴዎስ 2 (2 Timothy) 15፤ የእውነትን ቃል #በቅንነት (#በትክክል፤# ቀጥ አድረጎ)የሚናገር #የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። ይህ የእውነትን ቃል የሚማሩበት ምኅላፍ (ቻናል) ነው። ለጥያቄና አስተያየት፦ 0983657277 0962858609

❤️ #የሕይወት_እንጀራ_እኔ_ነኝ❤️ =========================== 📌📌ዮሐንስ 6 (John) 35፤ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡— የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፡ በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም። ✍️ ስለ መብል ስናነሳ የመጀመሪያው አዳም እናስታውሳለን አትብላ የተባለውን እንጨት ላይ የተንጠለጠለ ፍሬ በልቶ ሀጥያተኞችና ሙታን አድርጎን ነበር። ዘፍ 2:16-17, ኤፌ 2:1-3 📌 ኢየሱስ ግን አዳም ያልፈለገው በኤደን ገነት የነበረው የህይወት ዛፍ እርሱ ነበር። ሀጥያተኛና ሙት የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲያገኝ ከሰማይ የወረድኩ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ በማለት ለሀጥያተኞች መስቀል ላይ ራሱን አሳልፎ በመስጠት ብሉኝ ያለ የህይወት እንጀራችን ኢየሱስ ነው። 📌 ይህን የህይወት እንጀራ የሚበላ ከቶ አይራብም ከቶም አይጠማምና እኛም በእርሱ በማመናችን ለዘላለም እንዳንራብና እንዳንጠማ የህይወት ጥጋብና እርካታ የሆነልን ከአብ ዘንድ የተሰጠን የህይወት እንጀራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችንም ይሁን።
Show all...
1
❤️#አጋፔ= #የእግዚአብሔር_ፍቅር❤️ ============================ ✍️ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጽሐፍት በተጻፉበት በመጀመሪያው የግሪክ ቋንቋ ፍቅርን በ4 ይከፍለዋል፦ 1ኛ. አጋፔ ይባላል 2ኛ. ሄሮስ (ኢሮስ) ይባላል 3ኛ. ፍሊኦ(ፊሊያ) ይባላል 4ኛ. ስቶርጅ ይባላል 👉ሄሮስ የሚባለው ፍቅር የፆታ ፍቅር ሲሆን፤ 👉ፍሊኦ የሚባለው የፍቅር አይነት ደግሞ የጓደኝ ፍቅር ነው፤ 👉ስቶርጅ ደግሞ የቤተሰብ የፍቅር አይነት ነው። ሄሮስ፣ፍሊኦ፣ስቶርጅ የሚባሉት የፍቅር አይነቶች በባህሪያቸው ሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ አንዱ የሌላኛውን እጅ በመጠበቅ ጥቅምን መሠረት ያደረጉ የፍቅር አይነቶች ናቸው።እንደውም አንድ አባባል አለ ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው ይባላል።እንዚህ ሦስቱ የፍቅር አይነቶች ሰቶ በመቀበል ላይ የተመሰረቱ የፍቅር አይነቶች ናቸው። ✍️አጋፔ ግን ከእነዚህ ይለያል፤ ============== ❤️አጋፔ ሰቶ በመቀበል ላይ የተመሠረተ አይደለም። ❤️አጋፔ እግዚአብሔር ሰውን ፍፁም ለዘላለም የወደደበት የፍቅር አይነት ነው። ❤️አጋፔ፦ ያለምንም ጥቅም ፣ያለምን ቅድመ ሁኔታ እንዲሁ ዝም ብሎ ሰውን መውደድ ነው። ❤️አጋፔ ፦ የሚባለው የፍቅር አይነት ዘር፣ቀለም፣ብሔር፣ሃይማኖት፣ሀብታም፣ደሃ፣የተማረ፣ያልተማረ፣ያመነ፣ያላመነ፣ አውሮፓዊ፣ኢትዮጵያዊ እያለ ሰዎችን አይመርጥም ዝም ብሎ ከራሱ ፍፁም ጥልቅ ከሆነ ፍቅር በመነሳት ሰዎችን ይወዳል።ስለ ሰዎች ፍቅር ሲል ራሱን አሳልፎ ለሞት የሚሰጥ የፍቅር አይነት ነው። ✍️ፍቅርም እንደዚህ ነው ፣እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።1ኛ ዮሐ. 4፥10 ✍️ኃጢአተኞች ፣በደለኞች ምንም የማንጠቅም ጠላቶች በነበርንበት ጊዜ በፍፁም ፍቅሩ የወደደን ቅዱስ እግዚአብሔር ነው ሕይቱንም አሳልፎ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማን ነው ለጠላቱ ህይወቱን የሚሰጥ ???? ጠላቱንስ የሚወድ ማን ነው ???? መገረፍ፣መሰቃየት፣መሞት የሚገባን እኛ ሆነን ሳለ የማይገባው ኢየሱስ የእኛን ሞት ሞተ እኛን ለማዳን በእኛ ፈንታ ምራቅ ተተፋበት፣ተገረፈ፣ተሰቃየ፣በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተ፤ኃጢአታችንን፣ እርግማናችንን፣ነውራችንን ሁሉ አስወገደልን። ኢየሱስ ክርስቶስ ንጽህ ደሙን አፍስሶ፣ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ ውድ ሕይወቱን ስለእኛ ፍቅር አሳልፎ በመስጠት መውደዱን፣ፍቅሩን በቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሲገልጥልን ጭራሽ በእግዚአብሔር እንደተቀሰፈ፣እንደተቸገር ፣እንደተመታ ተቆጠረ። እርሱ አብዝቶ ቀረበን ፤ምንም የሚወደድ ነገር ሳይኖረን እርሱ በቸርነቱ ወደደን።በሰማይ ያለውን የክብሩን ዙፋን ትቶ ስለእኛ ፍቅር ሲል እንደ ኃጢአተኛ፣እንደ ወንበዴ፣እንደ ምናምንቴ ተቆጠረ።በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የገለጠው ፍቅር ከአዕምሮ ያልፋል። ✍️1 ዮሐንስ 4 (1 John) 19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። ✍️1 ዮሐንስ 4 (1 John) 10፤ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ✍️ኤፌሶን 2 (Ephesians) 4፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ 5፤ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ✍️ሮሜ 5 (Romans) 8፤ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ✍️ዮሐንስ 15 (John) 13፤ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ✍️ዮሐንስ 17 (John) 23፤... እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። ✍️ዮሐንስ 13 (John) 1... በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። ✍️ዮሐንስ 15 (John) 13፤ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ✍️ይሁዳ 1 (Jude)33q 1111 1፤ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ 2፤ ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።
Show all...
👍 1 1
በሉቃስ ወንጌል 1፡5- 13  #ከአብያ# ቤተሰብ የሆነ  ስሙ ዘካርያስ የሚባል ሰው እናገኛለን በ 4ኛው ወር (ታሙዝ) የወሩ ሁለተኛ አጋማሽ ማለት# ከ 16-30 ቀን በክፍሉ ተራ ለማጠን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ይገባል። በመቅደስ ውስጥ እያጠነ #መልአኩ ገብርኤል ተገልጦ ልጅ እንደሚወልድ ይነግረዋል ተራውንም ጨርሶ ወደ ቤቱ ይመለሳል ከዚያም ዩሐንስ መጥምቁ ይፀነሳል። ✍️መጥምቁ ዩሐንስ  በተጸነሰ# በ6ኛው ወር መልአኩ ገብራኤል በናዝሬት አውራጃ ገሊላ በሚባል አካባቢ ወደምትኖር ስሟ ማርያም ወደምትባል ድንግል ሴት ያቀናል ከመንፈስ ቅዱስ እንደምትጸንስና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ ይነግራታል። ሉቃ 1:26   ኢየሱስም# በ 10ኛው ወር (#ቴቬት) ይፀነሳል ቴቬት 10ኛ ወራቸው በኢትዮጵያ አቆጣጠር# በጥር ወር ኢየሱስ ይፀነሳል ከጥር ጀምሮ #9 ወር ስንቆጥር መስከረም (ቴስር) መጨረሻ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ይወለዳል ። #ቃልህ #እውነት ነው።
Show all...
በሉቃስ ወንጌል 1፡5- 13  #ከአብያ# ቤተሰብ የሆነ  ስሙ ዘካርያስ የሚባል ሰው እናገኛለን በ 4ኛው ወር (ታሙዝ) የወሩ ሁለተኛ አጋማሽ ማለት# ከ 16-30 ቀን በክፍሉ ተራ ለማጠን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ይገባል። በመቅደስ ውስጥ እያጠነ #መልአኩ ገብርኤል ተገልጦ ልጅ እንደሚወልድ ይነግረዋል ተራውንም ጨርሶ ወደ ቤቱ ይመለሳል ከዚያም ዩሐንስ መጥምቁ ይፀነሳል። ✍️መጥምቁ ዩሐንስ  በተጸነሰ# በ6ኛው ወር መልአኩ ገብራኤል በናዝሬት አውራጃ ገሊላ በሚባል አካባቢ ወደምትኖር ስሟ ማርያም ወደምትባል ድንግል ሴት ያቀናል ከመንፈስ ቅዱስ እንደምትጸንስና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ ይነግራታል። ሉቃ 1:26   ኢየሱስም# በ 10ኛው ወር (#ቴቬት) ይፀነሳል ቴቬት 10ኛ ወራቸው በኢትዮጵያ አቆጣጠር# በጥር ወር ኢየሱስ ይፀነሳል ከጥር ጀምሮ #9 ወር ስንቆጥር መስከረም (ቴስር) መጨረሻ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ይወለዳል ። #ቃልህ #እውነት ነው።
Show all...
✍️1ዜና 24፡7-19 ንጉሥ# ዳዊት👉# ካህናትን በተራቸው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ገብተው ያጥኑ ዘንድ# መደባቸው #24 ካህናት ነበሩና# በወር 2 ካህን  ማለትም( ከ 1-15 እና ከ 16-30) በ# 12 ወር 24 ካህናትን አደረገ ። ✍️❤️#በእስራኤላዊያን ቀን# አቆጣጠር መሰረት ደግሞ የመጀመሪያ ወራቸው #ኒሳን (Nisan) ይባላል። አስቴር 3፡7 , 8፡9 የእስራኤል የመጀመሪያ #ወር ኒሳን #በኢትዮጵያውያን ቀን አቆጣጠር   👉#ሚያዚያ መሆኑ ነው። ✍️ በምድቡም መሰረት ===================== 📌በአንደኛው #ወር (ኒሳን)                      ከ 1-15 ቀን== 👉ዮአሪም                     ከ 16-30 ቀን== ዮዳኤ 📌በሁለተኛው ወር# (እያር)                      ከ 1-15 ቀን==ካሪም                     ከ 16-30 ቀን==ሥዖሪም 📌በሶስተኛው ወ#ር (ሲቫን)                     ከ 1-15 ቀን==መልክያ                     ከ 16-30 ቀን==#ሚያሚን ♥️በአራተኛው ወር #( ታሙዝ)                   ከ 1-15 ቀን== አቆስ                  ከ 16-30 ቀን== ♦️አብያ♦️
Show all...
✍❤#ኢየሱስ_ሁሉን_ላስገዛለት_ይገዛል ================================ ✍❤️" #ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን# ላስገዛለት ይገዛል።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:28) 📌 ❤ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳብ እንደሚገባ #ካለማጥናት የተነሳ በብዙ ቅዱሳን ዘንድ ግርታ ይስተዋላል። 1ቆሮ 15 ሙሉ ምዕራፉ ስናጠና ስለ ትንሳኤ ስለ ቤተክርስቲያን መነጠቅና መሲሁ ምድር ላይ ስለሚመሰርተው መንግስት የሚያስተምር ሲሆን። ✍️❤ይህንን ርዕስ ለመረዳት የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ማወቅ ተገቢ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም እስከዘላለም ያለና የሚኖር አምላክ# የመሆኑን ያህል ቃል #ስጋ (ሰው) ከሆነ ጀምሮ የዘላለም #ሰው መሆኑም መዘንጋት የለበትም። የኢየሱስ ሰው መሆን መታሰብ ያለበት ከማህፀን እስከ መቃብር ብቻ ሳይሆን ከትንሣኤ በኋላም እስከዘላለም እንደሆነ ልብ ልንል ያስፈልጋል። ✍️#አንዳንዶች ባረገ ጊዜ ሰው መሆኑን ያቆመ አድርገው የሚያስቡ ሰውነቱን የዘነጉ አሉ። 👉❤# ጌታ ኢየሱስ ካረገ በኋላም "የሰው ልጅ" ተብሎ መጠራቱን ከሐ.ሥ.7፡56 ይመልከቱ። 👉❤# ሊፈርድ የሚመጣውም እንደ ሰው ልጅነቱ መሆኑን ከዮሐ.5፡27 እና ማቴ.25፡31 ያንብቡ። ኢየሱስ የሚፈርደው "በሕያዋንና በሙታን" ላይ መሆኑ ይታወቃል። (የሐ.ሥ.10፡42; 2ጢሞ.4፡1 ይመልከቱ)። በሕያዋን ላይ የሚፈርደው በ"#ክብሩ ዙፋን" በሚቀመጥ ጊዜ ሲሆን በሙታን ላይ የሚፈርደው ደግሞ# "በታላቁ ነጭ ዙፋን" ላይ በሚቀመጥ ጊዜ እንደሆነ ተነግሯል (ማቴ.25፡31; ራእ.20፡11-13)። ✍️❤ #በሕያዋን ስራ ላይ ከፈረደ በኋላ በሙታን ላይ ከመፍረዱ በፊት ጌታ የእርሱ ከሆኑት፥ #መንግሥትና ካህናት ካደረጋቸው ጋር ይነግሣል። ይህም ጊዜ በራእ.20 የተጠቀሰው የሺህ ዓመት መንግሥት ጊዜ ነው (ራእ.20፡4-6)። በ1ቆሮ.15 ውስጥ "#መንግሥቱ" የሚለው ይህንን መንግሥት ነው። በዚህ መንግሥትም ኢየሱስ የሚነግሠው በሰውነቱ መሆኑን ልናስተውል ይገባናል። 📌❤ ዕብራውያን 1፡8-9 ስለ ልጁ ግን፡— #አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9፤ ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ# እግዚአብሔር👉 አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ፥ ይላል። 📌 #በዚህ ጥቅስ ውስጥ የምናስተውለው እውነት እግዚአብሔር አብ ልጁን አምላክ ሆይ ሲለውና ቀጥሎም እግዚአብሔር አምላክህ በደስታ ዘይት ቀባህ ሲለው እንመለከታለን። ኢየሱስ ክርስቶስ# አምላክ ሆይ የተባለው ፍጹም አምላክ ስለሆነ ሲሆን። #እግዚአብሔር #አምላክህ በደስታ ዘይት ቀባህ የተባለው ደግሞ ፍጹም ሰው ስለሆነ ነው። 👉❤ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም #አምላክነትና ፍጹም #ሰውነት መርሳት የለብንም። ✍️❤ #ሺው ዓመት ካበቃ በኋላ ከዚያም ጌታ ከላይ እንደተጠቀሰው# በነጩ ዙፋን ፊት በሙታን ላይ ከፈረደ በኋላ ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ። ይህም ማለት የኋለኛው ጠላት ሞት ይሻራል ማለት ነው። በዚህን ጊዜ አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር የሚያልፉ ሲሆን እንደተስፋ ቃሉ የምንጠብቃቸው አዲስ ሰማይና ምድር ለዘላለም ይመሠረታሉ። ✍️❤ #የሺው ዓመት መንግሥት ካበቃ በኋላ ባለው የዘላለም መንግስት ኢየሱስ መንግሥቱን ለአባቱ# አሳልፎ ይሰጣል። ይህም ማለት በሰውነቱ የነበረው የመንግሥቱን #ባለቤትነት# መለኮት ብቻ በሆነው #በአባቱ ማንነት እና ባለቤትነት እንዲሆን ይተዋል። በዚህ መለኮታዊ የመንግሥት ባለቤትነት ውስጥ ወልድ (ኢየሱስ) በአምላክነቱ ማለትም ከአባቱ ጋር ባለው አንድነት እርሱም ባለቤት እንደሆነ ማስተዋል ተገቢ ነው። ሆኖም #በሰውነት ስፍራው በእርሱ ስም ሲጠራ የነበረውን መንግሥት በእግዚአብሔር ስምና ባለቤትነት እንዲጠራ አሳልፎ ከሰጠ በኋላ በሰውነቱ እርሱ ራሱ በዘላለሙ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ #የተገዢነት ስፍራን ይዞ ይቀጥላል። ✍️❤#ከአባቱ ጋር# በአምላክነቱ የዘላለም #ገዢ የመሆኑን ያህል ከእኛ ጋር በሰውነቱ ለዘላለም ይገዛል። በዕብራውያን 2፡8 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፡ ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም፤ ይህ ቃል አባት ለልጁ ሁሉን የሚያስገዛለት የሺው አመት መንግስ ከፊት ለፊታችን እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ✍️❤"ሁሉን #ላስገዛለት" የሚለው ቃል ኢየሱስ# በሺው አመት መንግስት ጊዜ የሚገዛው በሰውነቱ መሆኑን እንደሚያመለክት ሁሉ "ይገዛል" የሚለውም በዚያው #በከበረው# ሰውነቱ እንደሆነ መረዳት ይገባል። እግዚአብሔር እኛን የሚያየን# በክርስቶስ ስለሆነ ይህ መገዛቱ የእኛን መገዛት እግዚአብሔር በሚፈልገው ልክ ፍጹም ያደርገዋል። የእግዚአብሔርም ገዢነት ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደእኛ ሰው የሆነውን ኢየሱስን ሲጨምር #ያልተገዛለት ምንም እስከማይኖር ድረስ ሁሉ በሁሉ ይሆናል። 📌 2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians) 14፤ የጌታ የኢየሱስ #ክርስቶስ #ጸጋ የእግዚአብሔርም #ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም #ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
Show all...