cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው!!

እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። ኢያሱ 24 : 15 For any discussion, comment, Question..✍☞ https://t.me/joinchat/Jl58xJ5s1etiMDE0

Show more
Ethiopia12 023The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
172Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰቆ ኤርምያስ 3 (Lamentations) 22፤ ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። 23፤ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። 24፤ ነፍሴ፡— እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ፡ አለች። 25፤ ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው። 26፤ ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
Show all...
@salivationInChristJisus እግዚአብሔር በሚሰራበት ጊዜ ገንዘቡ ባለፈው መልዕክት እግዚአብሔር የሚሰራበት እራሱን የሚገልጥበት ጊዜ እንደሚመጣ አሁን ዓለም ሁሉ እያለፈበት ባለው እርሱ ሳያውቀውና ሳይመለከተው ተሰውሮ ያለ ነገር እንደሌለ ይልቁንም እርሱ ባሰበው በማዳን ክብሩ ዓለም ሁሉ የምትሞላበት ጊዜ እንደሚመጣ ልባችን በዚህ ተስፉ እንዲሞላ ተምረናል። ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር በሚሰራበት ጊዜ ገንዘቡ ሆነን እንድንገኝ የሚያስፈልጉ ነገሮችን አንማራለን። በትንቢተ ሚልክያስ 3 : 17 ላይ እንዲህ ይለናል "እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ " ይህን ከማለቱ በፊት አነዚህ እኔ በምሰራበት ጊዜ ገንዘቤ ይሆናሉ ያላቸው ሰዎች ስላደረጉት አስፈላጊ ነገር ይናገራል እርሱም በቁጥር 16 ላይ ያለው ነው " የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።" ሰለዚህ የመጀመሪያው አስፈላጊ መለኮት በእኛ የሚፈልገው ንጥረ ነገር እግዚአብሔርን መፍራት ነው። በሚመጣው ጊዜ እግዚአብሔር የሚሰራበት ገንዘቡ ለመሆን የመጀመሪያ አስፈላጊ ነገር 1-እግዚብሔርን በመፍራት መነጋገር ሚልክያስ በዚያን ጊዜ የሚለው የመጀመሪያው እግዚአብሔርን ባለመፍራት ሰዎች የተነጋገሩበትን ጊዜ የሚያመለክት ነው በቁ 13 ላይ ቃላቸው ( ንግግራቸው ) በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት የሆነበት ጊዜ እንደነበረ ያሳያል ። አንግዲህ በዚህ ጊዜ ነው እግዚአብሔር ለእርሱ ገንዘብ የሚሆኑ ሰዎችን ከሕዝቡ መሐል ለመምረጥ የሚመለከተው ሰዎች አያለፉበት ስላለው ነገር ፣ በዙሪያቸው ሰለሚታየው ሁኔታ..... የሚናገሩት የሚሉት አለቸው በዚህ ጊዜ ምን እንዴት አንደምንናገር እንጠንቀቅ፦ እግዚአብሔርን በመፉራት መነጋገር እና መመላለስ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው ወቅቱ ሰለዚህ እግዚአብሔር ሊገልጠው የሚፈልገውን ክብሩን በሚገልጥበት ጊዜ ገንዘቡ ለመሆን አሁን ላይ ምርጫችን እግዚአብሔርን ስለምንም ነገር አርሱን በመፍራት እንነጋገር ። ተጨማሪ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ከዚህ በመቀጠል አስቀምጣለሁ ይኸውም ካነበብኩት በ1904 የዌልስ ሪቫይቫል ታሪክ ያገኘሁት ነው። በወቅቱ ይህን ሪቫይቫል ለማስነሳት ለተጠቀመበት ሰው ከእርሱ ጋር ያሉትን ሰዎች እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ያዘዘውን አና አነርሱም ያን ተግባራዊ በማድረጋቸው ያ ታላቅ ሪቫይቫል ተከሰተ ። እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ያዘዛቸው 1- ከማናቸውም ከሚታወቅ ሐጢአት ሀሉ ነስሐ መግባት።( Repent from every known sin) 2- ከማናቸውም አጠያያቂ ነገሮች ሁሉ መለየት ።ምን አለበት ከሚባሉት ነገሮች መለየት ( Separate yourself from every questionable habits ) 3- ከእቶቻችሁ እና ከወንድሞቻችሁ ጋር ሁሉን ነገር ማስተካከል ( Make every things right with your brothers and sisters ) እነዚህን አደረጉ እግዚአብሔርም ሪቫይቫሉን ላከላቸው ። ዛሬ እኛ ከዚህ የምንማረው አለ -- ምን የንስሐ ፍሬ ያላደረኩበት የሚታወቅ ሐጢኣት አለ በሕይወቴ ? ብሎ እራስን መመርመር እና ንስሐ መግባት -- ምን አጠያያቂ የሆነ ልማድ በሕወቴ አለ ? ሐአጢኣት ነው አይደለም የሚል አወዛጋቢ የሆነ ነገር ? ምን አለበት ? የሚባል ነገር። እንደ እግዚአብሔር ሰው የእርሱ መጠቀሚያ ዕቃው ለመሆን እንደሚፈልግ ሰው እራሳችንን ከምንአለበት መለየት ያስፈልገናል ። -- ከወንድሞቻችን እና ከእህቶቻችን ጋር ሁሉን ማስተካከል ።ነገሮችን ሁሉ ትክክል straight እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግ መማር እንችላለን ። ለማጠቃለል ወገኖች ሆይ እግዚአብሔር የሚሰራበት ጊዜ በደጅ ነውና እርሱን በመፍራት ከሚታወቅ ሐጢአት ሁሉ ንስሐ በመግባት ፣ አጠያያቂ ከሆኑ ልማዶች ሁሉ በመለየት ከፍቅር በሰተቀር ለማንም ዕዳ ሳይኖርብን ከወንድም እህቶቻችን ጋር ነገሮችን ትክክል አያደረግን ጌታን አነጠብቅ። እርሱ ይገለጣል! @salivationInChristJisus
Show all...
@salivationInChristJisus 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼   🌻 🌻🌻🌻   🌻🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻   🌻🌻🌻🌻🌻🌻   🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼🌼   🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻  🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻   🌼 🌼🌼🌼   🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼   🌼🌼🌼🌼🌼🌼   🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼  🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 @salivationInChristJisus
Show all...
@salivationInChristJisus ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። እንድሁም ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን ጌታችን ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፡— አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል። @salivationInChristJisus
Show all...
@salivationInChristJisus ምሳሌ 16:1-11 1 የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው የምላስ መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። 2 የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ንጹሕ ነው እግዚአብሔር ግን መንፈስን ይመዝናል። 3 ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች። 4 እግዚአብሔር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ፥ ኀጥእን ደግሞ ለክፉ ቀን። 5 በልቡ የታበየ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው፥ እጅ በእጅም ሳይቀጣ አይቀርም። 6 በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋት ይመለሳል። 7 የሰው አካሄድ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘው እንደ ሆነ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል። 8 በጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር በዓመፅ ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል። 9 የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል። 10 የእግዚአብሔር ብይን በንጉሥ አፍ ነው፥ አፉም በፍርድ አይስትም። 11 እውነተኛ ሚዛንና መመዘኛ የእግዚአብሔር ናቸው የከረጢት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ሥራ ናቸው። @salivationInChristJisus
Show all...
@salivationInChristJisus የዕብራዊያን መልዕክት እኛ ባለንበት ዘመን ነገሮች እጅግ በፍጥነት እየተለዋወጡ የምናይበት ለመተንተን እንኳን በቂ ጊዜ ማናገኝበት እንዲያውም አሞካሽተንም ሆነ ተቃውመን ሳንጨረስ ነገሮች መልካቸው ተለውጡ እናገኛለን፡፡ ከፍ ያደረግናቸው ዝቅ ሲሉ ዝቅ ያደረግናቸው ከፍ ሲሉ ማየት የተለመደ ሲሆን አንዳንዶች ምነው አፌን በቆረጠው ብለው እስኪያፍሩ ያደርሳቸዋል የነገሮች መለዋወጥ፡፡ የመለዋወጣቸውን ያክል ወደክርስቲያኑ ማህበረሰብ ስንመለከት ደግሞ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነገር እየሰማን እንዳለን አሌ የማይባል ነገር ነው፡፡ በአንዳንዶች ዘንድ ራሳቸውን በአማኞች ልቦና ላይ ለመቅረጽ/ለመሳል የሚያደርጉት ጥረት፣ በመታየት እንጂ መታየት የተገባውን በማሳየት ያልተጠመዱ አገልጋዮችን መመልከት፣ አማኞችን እስከማሰገድ የደረሱ የምናይበት እና ይህ ያልተሳካላቸው ደግሞ ስርዓትና ወጎቻቸውን አጥብቀው አማኒያኑን በእስራት እንዲመላለሱ ሲያደርጉ እንመለከታለን፡፡ እውነታው የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ፣ የሃያላን ሃያል፣ የሁሉ የበላይ የሆነው ክርስቶስ ዳግም የሚገለጥበት ቀን በደጅ እንደሆነ መረዳት ላይ የተመሰረተ ብቻ ነው፡፡ ይህን እውነት የዘመናችን ቤተክርስቲያን በደመቀ ጽሑፍ በአካሉ ብልቶች ላይ ልትጽፍ ይገባታል፡፡ ዳግም ክርስቶስን በሰዎች ልብ የመሳል ብርቱ ስራ ከፊት ለፊታችን አለ፡፡ ስለዚህም ይህን ደማቅ እውነት እንደገና በአማኙ ሕይወት የመሳል ስራን ሊያቃኑልን ከሚችሉ ቅዱሳት መጽሓፍት ውስጥ የዕብራዊያን መልዕክት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል ብንል የተሳሳትን አይመስለኝም ምክንያቱም መጽሐፉ የክርስቶስ ኢየሱስን ከሁሉ የበላይነት እና የበለጠ መሆኑ በብዙ ማሥረጃዎች በማስቀመጥ በጊዜው ወደኋላ በማፈግፈግ ላይ የነበሩትን አማኞች ለመመለስ ጸሐፊው በስፋት ማረጋገጫ የሰጠበት መሆኑን ነው። በመሆኑም በዚህ ጥልቅ ትንታኔ በምናገኝበት የዚህ መጽሐፍ ጥናት ላይ አብረን እንድንጓዝ ብሎም ለብዙዎች በማዳረስ ክርስቶስን የሚያልቅ ሕይወት በመያዝ በምድራችን ላይ እርሱን የምናገንበት አገልግሎት እና ሕይወት እንዲሰጠን ባለ ምኞት ጥናታችንን እንድንቀጥል በታላቅ ትህትና እንጋብዛችኋለን፡፡ ለዚህም የምዕራፍ በምዕራፍ ጥልቅ ጥናት ይረዳን ዘንድ አስቀድመን ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሓፍት ስናጠና ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮችን በማስተዋወቅ እና በዛም መሰረት በዕብራዊያን መጽሐፍ ላይ ያለውን ቅደመ ግንዛቤ እናስቀምጣለን ከዛም በዛ መሰረት የምዕራፍ በምዕራፍ ጥናታችንን እንቀጥላለን ማለት ነው፡፡ ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሓፍት ስናጠና በተቻለ መጠን የሚከተሉትን መሰረታዊ እውነታዎች በመረዳት ሊሆን ይገባል ምክንያቱም እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች በመጽሐፉ ውስጥ ብሎም በየምዕራፉ ያለውን የጸሐፊውን መልዕክት ሳናዛባ እንድንረዳ እንድንተረጉምና ከሕይወታችን ጋር እንድናዛምድ ይረዱናልና ነው፡፡ እነዚህም፡- 1. የጸሓፊውን ማንነት መረዳት፡ ብዙ ጊዜ በፊት ለፊት የተጠቀሰ ላይሆን ቢችልም ደጋግሞ ምዕራፎቹን በማንበብ ተጓዳኝ ማመሳከሪያ መጽሓፍትን ከቅዱስ ቃሉ በመመልከት እንዲሁም ከተለያዩ አጋዥ መጽሓፍት በማንበብ ማወቅ እንችላለን፡፡ ይህን ማወቅ ከጸሐፊው ማንነት አንጻር ጽሑፉን መረዳት ያስችለናልና ነው፡፡ 2. የተጻፈበት ወቅትን መረዳት፡ መቼና ምን ሁኔታ በነበረበት ወቅት ነው መልዕክቱ የተጻፈው የሚለውን ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ ለምሳሌ በኃይለስላሴ ጊዜ፣ በደርግ ጊዜ ወይም በአሁን ጊዜ ያሉ ጽሑፎችን እንደወቅታቸው ስንረዳቸውና አመሳቅለን ለመረዳት ስንሞክር ምን ያህል የትርጉም መዛባት እንደምናመጣ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ 3. የተጻፈላቸውን ሰዎች ማንነት መረዳት፡ መቼም አንድ ጽሑፍ ከጸሐፊውና ከተጻፈላቸው ሰዎች ማንነት ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዳለው መገንዘብ አያዳግትም። ለምሳሌ:- ለአይሁድ የተጻፈና ለአህዛብ የተጻፈ መሆኑን መረዳት ጥናት ላይ ምን ያህል ለትርጉም እንደሚረዳን መገመት አይቸግርም፡፡ 4. የተጻፈበትን ዓላማ መረዳት፦ ይህ ማለት አንድ ጸሐፊ ጽሑፉን የሚጽፍበት የራሱ የሆነ ዓላማ አለው ፡ ያንን የፀሐፊውን ዓላማ መረዳት አንባቢውን በጸሐፊው ዓላማ ፍሬም ወርኩ ውስጥ ንግግሮቹን ሁሉ እንዲረዳ ያግዘዋል ማለት ነው፡፡ ይህም በጥቂት ቁጥር ላይ ያሻንን እንዳንል ያግዘናል፡፡ 5. በመጨረሻም አሁን ላለን አንባቢያን ምን አይነት ትምህርት እንዳለው መረዳት፡ መቼም መጽሐፍ እንደሚል ቅዱሳት መጽሐፍ የተጻፉልን ለትምህርታችን ልብንም ለማቅናት ስለሆነ ምን ያስተምረናል የሚለውን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን መሰረታዊ መጠይቆች በልቦናችን አድርገን መጽሓፍትን እንድንመረምር እያበረታታሁ ለአሁኑ በዚህ የዕብራዊያን መልዕክት ጥናታችን ላይ እንደመግቢያ እነዚህን መሰረታዊ መጠይቆች በመዳሰስ ወደጥልቅ ጥናታችን እንሄዳለን፡፡ መልካም ጥናት!!! ✓ መግቢያ ይህ መልዕክት ከአዲስ ኪዳን መጽሓፍት መካከል ከየትኞችም በተሻለ መልኩ ከብሉይ ኪዳን ጋር ቅርበት ያለው መጽሐፍ እንደሆነ እንወቅ ይህም መጽሐፍን በበቂ ሁኔታ ለመረዳት ከብሉይ ኪዳን መጽሓፍት ጋር በተለይ ከዘሌዋዊያን መጽሐፍ ጋር አገናኝተን ብናጠና የተሻለ ግንዛቤ ልንጨብጥ እንችላለን። ምክንያቱም በዛ መጽሐፍ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላትን በተደጋጋሚ ሁኔታ ስለሚያነሳ ነው (ለምሳሌ - ሊቀ ካህን፣ ደም መርጨት፣ ቅድስተ ቅዱሳን…)። በተጨማሪም ይህ መልዕክት እስከ አሁን ድረስ በእርግጠኝነት በማን እንደተጻፈ የማይታወቅ መጽሐፍ ነው። ✓ ጸሐፊ የዚህ መልዕክት ጸሐፊ በግልጽ አይታወቅም። ነገር ግን በተለያየ ዘመን የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኝዎች ጳውሎስ፣ በርናባስ፣ ሲላስ፣ ሉቃስ፣ ፊሊጶስ፣ ጵሪስቂላ፣ አቂላ፣ ወይንም የሮም ጳጳስ መልዕክቱን ሳይጽፉት አይቀሩም የሚል ግምታቸውን ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ የመልዕክቱ የቃላት አጠቃቀም፣ ዘዬው፣ እና ስነጽሁፋዊ ባህራያቱ በማናቸውም ግለሰቦች ላይ እምነታችንን እንዳናደርግ ያደርገናል። በተለይ ደግሞ ጸሀፊው ራሱ ወንጌልን ከሌላ ሰው ከሰሙት መካከል አንዱ እንደሆነ መጠቆሙ የተለያዩ መላ ምቶች እንዲኖሩ አድርጎታል (2፡3)። ምናልባት ይህን ጸሐፊው ራሱ መጥቀሱ ወንጌልን ከራሱ ከኢየሱስ በመገለጥ እንደተቀበለው የገለጸው ጳውሎስ (ገላ.1፡12) ይህን መልዕክት አልጻፈውም የሚለውን የሚያጠናክር ይመስላል። ለማንኛውም ማንም ይጻፈው ማን ጸሐፊው ብሉይ ኪዳንን ሲጠቀም የሚታየው በግሪክ ቋንቋ (LXX) ከተጻፈው እንደሆነ እና በዕብራይስጥ የተጻፈውን አለመምረጡን ግን ልንመለከት እንችላለን። ለማንኛውም ማን እንደጻፈው ለማወቅ አዳጋችነቱ መልዕክቱን ከመንፈስ ቅዱስ እንዳመጣው ግን የሚያጠራጥረን ነገር የለም። ✓ የተጻፈበት ወቅት ጸሐፊው የአሁን ጊዜን የተጠቀመባቸውን ክፍሎች 5:1–4; 7:21, 23, 27–28; 8:3–5, 13; 9:6–9, 13, 25; 10:1, 3–4, 8, 11; እና 13:10–11 ስንመለከት ጸሐፊው መልዕክቱን በሚጽፍበት ወቅት የካህናት አገልግሎትና የመስዋዕት መሰዋት ልምድ በወቅቱ እንደነበር ሲያመላክቱን መልዕክቱ የተጻፈበት ጊዜ ቤተመቅደሱ ከመፍረሱ በፊት ነው (ማለትም ቤተመቅደሱ የፈረሰው በ70ዓ.ም. ስለሆነ ከ70ዓ.ም በፊት መልዕክቱ ተጽፏል ማለት ነው)። በተጨማሪም ጢሞቴዎስ ከእስር የተፈታበት ወቅት (13፡23) መሆኑና ከዛ በኋላ ስደቱ እጅግ በጣም የከፋበት መሆኑን ስንመለከት (10፡32-39፣ 12፡4፣
Show all...
13፡3) ጊዜው ከ64 እስከ 68 ዓ.ም @salivationInChristJisus
Show all...
@salivationInChristJisus By Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ # አምስቱ_የፍርዶች_አይነቶች # ክፍል_አራት ፬ ===================== NB ቅዱሳን ልብ ሊሉት እና ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር ከ 5ቱ የፍርድ አይነቶች ከዚህ በኃላ ያሉት ሁለቱ 4ኛው እና 5ኛው የፍርድ አይነቶች በክርስቶስ አምነው የዳኑትን እውነተኛ አማኞች አይመለከታቸውም 2 ጢሞቴዎስ 2:15 የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። 4) # ባልተነጠቁ_በምድር_በሚኖሩ # ላይ_ነው ። # ምክንያት፦ የመንግስት ወንጌልን ባለማመን እና እስራኤላውያንን የማጥፋት ሙከራ # ጊዜ ፦ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በክብር ሲገለጥ ማቴ 25:31-33, ዘካ 14:5 # ቦታ፦ በኢዮሳፍጥ ሸለቆ ( አርማጌዶን) ኢዮኤል 3:2,12...,ራዕ 16:16 # ውጤት ፦ የመንግስት ወንጌልን ያመኑ ወደ ሺው አመት በረከት ይገባሉ ። ማቴ 25:31-32 የመንግስት ወንጌልን አናምንም እስራኤላውያንን እናጠፍለን የሚሉት ፍርድ ይቀበላሉ = ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ ። ራዕ 19:21, ዘካ14 :12-13 ይህ ፍርድ ከአማኞች ጋር ግንኙነት የሌለው እና አማኞች ከተነጠቁ ከ ሰባት(7) አመት በኃላ የሚፈፀም ፍርድ ነው። ፍርዱ በዋናነት ባልተነጠቁ እና የመንግስት ወንጌል አናምንም እስራኤልንም እናጠፋለን በሚሉት አህዛብ (የአውሬው= የአውሮፓ ህብረት እና ጦር) ላይ የሚፈፀም ነው። NB ይህ አራተኛው ፍርድ ከ አምስተኛው(5) የነጬ ዙፋን ፍርድ እንደሚለይ ልብ ልንል ይገባል። ማቴዎስ 25:31-33 31፤ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ 32፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ 33፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። መዝሙር 96፡13 ይመጣልና፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል። ዘካርያስ 14:5 = ማቴ 25:31-33 የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፤ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል። ዘካርያስ 14 :12-13 = ራዕ 19:17-21 ፤ እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። 13፤ በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፤ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል። ራእይ 1፡7 እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። ዳንኤል 2 (Daniel) 34፤ እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና ሲፈጭ አየህ። 35፤ የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፥ በመከርም ጊዜ በአውድማ ላይ እንዳለ እብቅ ሆነ፤ ነፋስም ወሰደው፥ ቦታውም አልታወቀም፤ ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ። ዳንኤል 2 (Daniel) 45፤ ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል፤ ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው። 1 ተሰሎንቄ 5:9 ፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ። ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ይቀጥላል........ የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma @salivationInChristJisus
Show all...