cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖

እናነባለን ያነበብነውን እናጋራለን በመፃህፍት ስለመፃህፍት እናወራለን ✅በዚህ ቻናል ድንቃድንቅ መረጃዎች፣ ጣፋጭ ግጥሞች፣ መጣጥፍና አጫጭር ልቦለዶች፣ የረዥም ልቦለድ ትረካ እና ወጎች ግጥሞች(በድምፅ)፣ ባጠቃላይ ጥበብ እና ጥበብ ነክ ነገሮች ይቀርቡበታል። ይቀላቀሉ! 👇👇👇👇 https://t.me/seido27hurelhub To contact me @seido11

Show more
Advertising posts
1 129
Subscribers
+124 hours
No data7 days
+1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ማርክ ዙከርበርግ የናጠጠ ቢሊየነር ነው። ሚስቱን ለማስደሰት ማንኛውንም በአለም ላይ ውድ የሆነ ቁስ ሊገዛላት ይችላል—ጌጣጌጦች፣ ቤት፣ መኪና፣ አውሮፕላን፣ የመዝናኛ መርከብ yacht ወዘተ። አንድ ደሴት ወይም ትንሽ ሀገር የሚገዛ ገንዘብ ያለው ሰው ነው። ገንዘብ ሊገዛው የሚችለውን ነገር ሁሉ በስጦታ ሊሰጣት ይችላል። ማርክ ግን ገንዘብ የሚገዛውን ትቶ ገንዘብ የማይገዛውን ሰጣት። ምን ይሆን ገንዘብ የማይገዛው?! የማርክ ሚስት ፕሪሲላ ቻን ትባላለች። በትውልዷ ቻይናዊ ናት። በላቧ ሰርታ የምታድር ሜዲካል ዶክተር ነች። ደግሞ በባህሪዋም ገንዘብ የሚያስደንቃት፣ ግድ የሚሰጣት ሴት አይደለችም። ታዲያ ለዚህች ሴት ማርክ ምን ይስጣት? ማርክ ለሚስቱ ሳይነግራት የቋንቋ ትምህርት ቤት ተመዘገበ። ለአመታት ማንዳሪን አጠና። በነገራችን ላይ ማንዳሪን ለመማር በጣም ከባድ ቋንቋ ነው። አይደለም በሁለተኛ እና ሶስተኛ ቋንቋነት አፈ ለፈቱበትም ዳገት ነው። በተለይ ጽሁፉ። አንዴ ስለ ማንዳሪን ሳነብ ከ48 ሺ በላይ ካራክተርስ አሉት ይላል። መሰረታዊ ጽሁፍ ለማወቅ ቢያንስ 3ሺ ካራክተር ማወቅ ይገባል። ምእራባውያን የለመዱት 26 የላቲን ፊደል ነው። ማንዳሪንን ተዉትና የኛ ቋንቋ 231 ፊደላት እንዳለው ሲያውቁ ልባቸው በድንጋጤ ቀጥ ነው የምትለው። አማርኛ ራሱ ለመማር ቀላል ቋንቋ አይደለም። ማንዳሪን የበለጠ ከባድ ነው። ብዙ ትጋት ይጠይቃል። ማርክ ራሱ ቋንቋውን በደንብ ለመካን ብዙ አመት ወስዶበታል። ያውም እሱ ከፍተኛ የአእምሮ ብቃት ስላለው ነው እንጂ ቋንቋው የሊማሊሞ ዳገት ነው። ታዲያ ማርክ በማንዳሪን ሲካን ለሚስቱ በመጀመሪያ እንዲህ ነበር ያላት፦ "我爱汝" ትርጉሙ "አፈቅርሻለሁ" ነው። ከዚህ የሚበልጥ ምን ስጦታ አለ?! በገንዘብ የማይተመን ዋጋ የማይወጣለት ውድ ስጦታ። ፍቅርና ቋንቋ። ቋንቋና ፍቅር። ፍቅር በቋንቋ ይገለጻል። እስኪ አንዳችን የሌሎቻችንን ቋንቋ በፍቅር እንማር። ፍቅራችንን እንገላለጽ። ቋንቋዎቻችን የፍቅር ድልድይ እንጂ የልዩነት ግድግዳ አይሁኑብን። እወዳችኋለሁ!❤❤ Anii sin jaalladha!❤❤ የፍቅረኪ እየ!❤❤ @Tewodros shiwangizaw
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ለ16ኛ ጊዜ የመጻሕፍት አውደርዕይ ትናንት ጀምሮ እያካሄደ ነው። ለሳምንት በሚቆየው በዚህ አውደርዕይ ሥፍራ ሌሎች ተጨማሪ ክንውኖች አሉ። ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን ከሰዓት  በኋላ ዓለማየሁ ገላጋይ ስለ አዲሱ መጽሐፉ ማእበል ጠሪ ወፍና ስለሌሎቹም ሥራዎቹ፣ ፋሲካ ሙሉ ደግሞ ሰለ ያልተገራ ፈረስ መጽሐፏይነግሩናል። ወዳጆቼን ሁሉ በክብር ጋብዣችኋለሁ።
Show all...
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ለ16ኛ ጊዜ የመጻሕፍት አውደርዕይ ትናንት ጀምሮ እያካሄደ ነው። ለሳምንት በሚቆየው በዚህ አውደርዕይ ሥፍራ ሌሎች ተጨማሪ ክንውኖች አሉ። ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን ከሰዓት በኋላ ዓለማየሁ ገላጋይ ስለ አዲሱ መጽሐፉ ማእበል ጠሪ ወፍና ስለሌሎቹም ሥራዎቹ፣ ፋሲካ ሙሉ ደግሞ ሰለ ያልተገራ ፈረስ መጽሐፏይነግሩናል። ወዳጆቼን ሁሉ በክብር ጋብዣችኋለሁ።
Show all...