cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

┇ወዳጄ አሲፍ┇✍®

TELEGRAM LINK: http://t.me/seudkemal አስተያየት ካለዎት በዚህ ይላኩልን! 👉 http://t.me/wedajeasif

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
2 111
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Watch "Tewfiq Yusuf – Temsalte || ተውፊቅ ዩሱፍ ተምሳሌቴ || New Official Music Vedio #Ramadan" on YouTube https://youtu.be/IRgP4AbMKlE
Show all...
Tewfiq Yusuf – Temsalte || ተውፊቅ ዩሱፍ ተምሳሌቴ || New Official Music Vedio #Ramadan

#Ramadan #TewfiqYusuf #NeshidaShare Share Share⤵️⤵️⤵️➖➖➖➖⤵️⤵️ ቻናሌንን Subscribe ያድርጉYOUTUBE-

https://www.youtube.com/tewfiqyusufFacebook-https://www.facebook.co...

ባለ ታሪክ #2 As wr wb ለቤተሰቦቼ ሁለተኛ ልጅ እና ብቸኛ ሴት ልጅ ነኝ ከሁሉም ጋር ጥሩ የሆነ ቅርበት አለን ነገር ግን አባቴ በባህሪው በጣም ቁጡ እና ተናዳጅ ሲበዛ ችኩል ነው በዚህም የተነሳ ከኔጋ ብዙ ጊዜ አንስማማም እናቴ ደግሞ የሱ ተቃራኒ ናት ለኔ የማትሆነው የለም ለኔ ሲሆን ሁኚ ያልዋትን ሁሉ ትሆናለች ብቻ ወንድሞቼ ደግሞ ሁሉም ማለት ይቻላላል ጥሩ የሚባል ሁኔታ ላይ አይደሉም ግማቹ በራሱ ሀጃ ግማሹ በተለያየ ሱስ የተጠመዱ ናቸው እናቴ በነሱ ሁሌ እንዳዘነች እንዳለቀሰች ነው ለልጆቹ አላስፈላጊ ባህሪ አባቴ ሁልጊዜ እናቴን ነው ተወቃሽ የሚያደርጋት በዚህም ምክኒያት ብዙ ጊዜ እኔና አባቴን የሚያጣላን ሰበብ ይሄ ነው እናቴ አልፎ አልፎ ልቧን ያማታል ታዲያ አንድም ቀን በሌላ ምክኒያት ታማ አታውቅም በዚው ቤተሰብ ጉዳይ እንጂ እኔ በመሀል ቤት አንዴም በአባቴ አንዴም በወንድሞቼ በእናቴም ስቃይ እየታመምኩ ነው ወንድሞቼንም በኡስታዞቻቸው በጓደኞቻቸው ብዙ ጊዜ አስመክሬያቸዋለሁ ግን ለውጥ የለም እኔ አሁን ደክሞኛል ማግባት አልፈልግም ሁሉን ትቼ ልጠፋም አስብና የእናቴ ስቃይ ትዝ ሲለኝ አተወዋለሁ ብዙም ከሰዎች ጋር አልግባባም አንድም የውስጤን ህመም የምነግረው ጓደኛ የለኝም ውድ የኢስላም ልጆች እናንተ እኔን ብትሆኑ ኖሮ ምንታደርጉ ነበር፡፡ ሀሳቦቻችሁን በ 👇👇👇 @Alkewserbot ላይ አድርሱን
Show all...
ባለ ታሪክ #2 As wr wb ለቤተሰቦቼ ሁለተኛ ልጅ እና ብቸኛ ሴት ልጅ ነኝ ከሁሉም ጋር ጥሩ የሆነ ቅርበት አለን ነገር ግን አባቴ በባህሪው በጣም ቁጡ እና ተናዳጅ ሲበዛ ችኩል ነው በዚህም የተነሳ ከኔጋ ብዙ ጊዜ አንስማማም እናቴ ደግሞ የሱ ተቃራኒ ናት ለኔ የማትሆነው የለም ለኔ ሲሆን ሁኚ ያልዋትን ሁሉ ትሆናለች ብቻ ወንድሞቼ ደግሞ ሁሉም ማለት ይቻላላል ጥሩ የሚባል ሁኔታ ላይ አይደሉም ግማቹ በራሱ ሀጃ ግማሹ በተለያየ ሱስ የተጠመዱ ናቸው እናቴ በነሱ ሁሌ እንዳዘነች እንዳለቀሰች ነው ለልጆቹ አላስፈላጊ ባህሪ አባቴ ሁልጊዜ እናቴን ነው ተወቃሽ የሚያደርጋት በዚህም ምክኒያት ብዙ ጊዜ እኔና አባቴን የሚያጣላን ሰበብ ይሄ ነው እናቴ አልፎ አልፎ ልቧን ያማታል ታዲያ አንድም ቀን በሌላ ምክኒያት ታማ አታውቅም በዚው ቤተሰብ ጉዳይ እንጂ እኔ በመሀል ቤት አንዴም በአባቴ አንዴም በወንድሞቼ በእናቴም ስቃይ እየታመምኩ ነው ወንድሞቼንም በኡስታዞቻቸው በጓደኞቻቸው ብዙ ጊዜ አስመክሬያቸዋለሁ ግን ለውጥ የለም እኔ አሁን ደክሞኛል ማግባት አልፈልግም ሁሉን ትቼ ልጠፋም አስብና የእናቴ ስቃይ ትዝ ሲለኝ አተወዋለሁ ብዙም ከሰዎች ጋር አልግባባም አንድም የውስጤን ህመም የምነግረው ጓደኛ የለኝም ውድ የኢስላም ልጆች እናንተ እኔን ብትሆኑ ኖሮ ምንታደርጉ ነበር፡፡ ሀሳቦቻችሁን በ 👇👇👇 @Alkewserbot ላይ አድርሱን
Show all...
አንድን ሰው መጥቀም ባትችል አትጎዳው!! • ማስደሰት ባትችል በአንተ ምክንያት እዲያዝን አታድርገው!! በችግር ጊዜ ከጎኑ መቆም ባትችል በመቸገሩ አትደሠት!! መልካም ነገር በማግኘቱ ባትደሠት ምቀኛ አትሁነው!! መልካም ስራውን ለሠወች ማወደስ ባትችል አታጠጥለው!! መልካም ቀን @Alkewser
Show all...
አቡበክር (ረ.ዐ) ከሞት አፋፍ ላይ በሆኑ ጊዜ ዑመርን ጠሩና እንዲህ ሲሉ መከሯቸው፡- ‌ “ዑመር ሆይ! አላህን ፍራ። አላህ በቀን ካልሆነ በሌሊት የማይቀበለው ስራ አለው። ፈርድን እስክትወጣ ድረስ ሱናን አይቀበልም። በእለተ ቂያማ ሚዛናቸው የሚከብድላቸው ሰዎች ይህን እድል ያገኙት በዚህች ዓለም ሐቅን በመከተላቸው ነው። ሐቅ የስራ ሚዛናቸውን አከበደው። ነገ ሐቅ የሚቀመጥበት ሚዛን ሊከብድ ተገባው። ‌ በእለተ ቂያማ ሚዛናቸው የሚቀልባቸው ሰዎች ይህ የሆነባቸው በዚህች ዓለም ሐሰትን በመከተላቸው ነው። ሐሰት ስራቸውን አቀለለው። ነገ ሐሰት የሚቀመጥበት ሚዛን ሊቀል ተገባው። አላህ የጀነት ሰዎችን ሲያወሳ ከስራዎቻቸው መካከል ይበልጥ መልካሙን አወሳ። ግድፈቶቻቸውንም አለፈ። እነርሱን ሳስታውስ፡- ‘ከነርሱ ሳልሆን እንዳልቀር’ የሚል ስጋት ያድርብኛል። የእሳት ሰዎችን ሲያወሳም ከስራዎቻቸው መሐል ይበልጥ ክፉውን አብሮ አወሳ። ጥሩውን ስራቸውን መለሰባቸው። ‌ እነዚህንም ሳሰታውስ፡- ‘ከነርሱ እንደማልሆን ተስፋ አደርጋለሁ’ እላለሁ። በፍርሃትና በተስፋ መሐል መሆን ተገቢ ነው፤ በአላህ ላይ መመጻደቅም ከእዝነቱ ተስፋ መቁረጥም ተገቢ አይደለም። ይህን ምክሬን ከሰራህበት ወዳንተ መምጣቱ አይቀሬ ከሆነው ሞት ይበልጥ ተወዳጅ ሩቅ እንግዳ አይኑርህ። ካልሰራህበት ደግሞ ከሞት ይበልጥ የምትጠላው ሩቅ እንግዳ አይኑርህ።” (አልሁልየህ 1/36) •════•••🍃🌺🍃•••════• Join us ➤➤ @Alkewser
Show all...
✨Aha Moment ( አሃ የምንልባት ክስተት.... ) ✍በ ደምስ ሰይፉ 💧“What I always want is to have several little ‘aha’ moments where your brain is very happy.” – Scott Kim 💦ከመቶ ዓመት በፊት በአንዱ ዕለት ነው… ሰውየው የሚያማምሩ አበቦች ባሉበት የቤቱ የአትክልት ስፍራ ላይ ተቀምጦ የዕለቱን ጋዜጦች ያገላብጣል… ድንገት… ‘በሞት የተለዩ ሰዎች’ በሚለው አምድ ላይ የአንድን ሰው ዜና እረፍት አየና ክው ብሎ ደነገጠ… ጽሑፉን ሲያነብ ጋዜጣው እንደ መርዶ ነጋሪ ሹክክ ብሎ ቤቱ የተገኘ ጥላቢስ እንጂ ተራ ወረቀት አልመስልህ አለው… ክውታና ድንዛዜ… ደርሶ ጭውውውውው አለበት… 💦ብንን ብሎ ጋዜጣውን በድጋሚ ተመለከተው… አልተሳሳተም… በትክክል የሚያነበው የራሱን ዜና እረፍት ነው… Dynamite king dies ይላል… ‘የድማሚቱ ንጉስ አረፈ…’ ያ.. ተራራውን ገምሶ.. ቋጥኙን ፈልፍሎ.. አለታቱን ነድሎ መንገድ የሚተልመውን ድማሚት የፈጠረው ሰው አረፈ እያለ ነው… ሰውየው ራሱን ጠየቀ… ‘ይህን ዜና የማነበው በእውኔ ነው በሕልሜ?’ … መልስ የለም… 💦ዜናው በዚህ ቢያበቃ ጥሩ አይደል… ስለ ‘ሟቹ’ ሌላም ነገር ይላል… And he was the merchant of death…(የሞት ነጋዴ እንደማለት ነው) ሳይሞት ሞተሃል ከመባሉ በላይ እንደ ሙት የሚታሰብበት መንገድ ሰውየውን የበለጠ አስደነገጠው… ተንቀጠቀጠ… ሰበበ ሞት ተደርጎ ነዋ የተገለጸው… የጅምላ ፍጅት ምክንያት ተደርጎ ነው የተሳለው… ‘እውነት ሞቼ ቢሆን ሰዎች የሚያስታውሱኝ እንደዚህ እያሉ ነው?’ ሲል ጠየቀ… ‘በፍጹም!!!… ይህ ቅጽል መፋቅ አለበት!!’ 💦ይህ ሰው አልፍሬድ ኖቤል ነው… ኖቤል ድማሚትን ‘በመፍጠሩ’ ይታወቃል… ግኝቱ ለመንገድ ስራ ያለው አስተዋጽዎ ጎልቶ የሚነገርለት ቢሆንም ኖቤልን ‘ነፍሰ ገዳይ’ ከሚል ስም አላስጣለውም… የፈረንሳይ ጋዜጦች “Le marchand de la mort est mort” (“The merchant of death is dead.”) ብለው ሲዘግቡ ዜናውን በዚያው ወቅት ፈረንሳይ ውስጥ ከሞተው የአልፍሬድ ኖቤል ወንድም ሉድቪግ ጋር አምታተውት ኖሯል… ሆኖም አጋጣሚው ኖቤልን ከጥልቅ እንቅልፉ የሚያነቃው ነበር… እናም ይህን ስም ለውጦ ማለፍ እንዳለበት የወሰነው እዚያው ነበር… 💦በፈጠራው ምክንያት ያገኘውን ሳንቲም ሰብስቦ ለበጎ ተግባር እንዲውል ሰጠ… በደህናው ዘመን ስለ ድንቅ ጥበቡ የተበረከተች ሳንቲም በችግሩ ጊዜ ስለ ስሙ መታደስ ወጣች… ያቺ ሳንቲም በዝታና በርክታ በዓለም ዙሪያ በሳይንስ፣ በስነጽሑፍ፣ በሰላም፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በፊዚክስና በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ከፍ ያለ አስተዋጽዎ ለሚያደርጉ ግለሰቦች ሽልማት ሆና የምትቀርብ ሆነች… ዛሬ ዛሬ የ Nobel Prize Winner መሆን የልዕልና መግለጫ ሆኗል… ‘እከሌ የኖቤል ተሸላሚ ነው’ የሚለው ስያሜ ትልቅ ማዕረግ ሆኗል.. ብዙ የምናደንቃቸው የዓለማችን ሰዎች የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል… አዎን… ዛሬ ኖቤልን ከሞት ጋር አያይዞ ስሙን የሚያነሳ… ከውድመት ጋር አቆራኝቶ ስራውን የሚያወሳ አንድ ስው እንኳ የለም… 💦ከ’ሞት’ በኋላ በበጎ መታወስ የሚል ቅዥት ሰከንዶችን ተጋርቶኝ አያውቅም… ግና ሰው በኑረት ብቻ ሳይሆን በእልፈቱም ለሌሎች መኖር ከቻለ ድንቅነቱ ይገባኛል… ያም ሆኖ የበለጠ የሚመስጠው የተረኩ ክፍል ‘በሌሎች ዘንድ የጠለሸን ስም’ ለማደስ የመቁረጡ ጉዳይ ነው… ✨አስባችሁታል… መንግስት ‘ለካ ሕዝብ የሚረዳኝ እንዲህ ነው?’ ብሎ ስሙን ለማደስ ሲተጋ… ባል በጸጸት ውስጥ ሆኖ ‘ለካ በሚስቴ ዓይን የምመስለው ይህን ነው?’ ብሎ እንከኑን ሲነቅስ… አባት ‘ለካስ ለልጆቼ ጥሩ ወላጅ አልነበርኩም’ ብሎ መንገዱን ለመቀየር ሲወስን… ተቋማት ‘በደንበኞቻችን ዘንድ ያለን ገጽታ ጥሩ አይደለም ለካ’ ብለው ለምርትም ሆነ አገልግሎት መሻሻል ሲሰሩ… ትራፊኮች በአሽከርካሪ ዓይን፣ አሽከርካሪዎች በተሳፋሪ ዓይን… አለቆች በሰራተኛ፣ መምህራን በተማሪ… ብቻ ሁሉም በየአንፃራቸው ቦታ ራሳቸውን አስቀምጠው ‘አሃ…’ ሲሉ… 💫አንዳንዴ በሌሎች መስታወት ውስጥ ካላየነው በቀር የማይገለጥ ቁሸት አያጣንም… በወዳጅ ምክር ውስጥ ካልሆነ የማይቀና ጉብጠትም እንዲሁ… ✨‘ለሌሎች’ ሲባል ሁሉ ይፍረስ አይባልም መቼም… ሁሉን ማስደሰት አለመቻል ብቻ ሳይሆን ‘የራስ ጣዕም’ ማጣትም ልክ አይሆንምና… ግን አለ አይደል… ‘በልክ ነኝ’ ካብ ውስጥ ያደፈጠች ክፋት፣ በማናለብኝ ጎሬ ውስጥ የተሸጎጠች ትዕቢት፣ የሌላውን ምቾት የምትነሳ ክርፋት… ምናል.. ‘አሃ…’ እያልን ብናስወግዳት… ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!🙏 👌 አንብበን ብቻ ከማለፍ ይልቅ ቅርባችን ላሉት ወዳጆች ብናጋራ ሰናይ እሁድ #Join_share 👇👇👇 @Alkewser
Show all...
ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) ከተቡክ ሻም ላይ ለሚገኙ ወንድሞቹ መልእክት ፃፈላቸው፦ ይህም (መልእክት) በእውነቱ ወደ ጌታው ተሰዳጅ ለሆነ እውነተኛ ስንቅ ነው። (የመልእክቱ) መጨረሻ አካባቢ እንዲህ አሉ፦ «ከዚህ ሁሉ የረዘመ (መልእክት) ሶስት ንግግሮች ያብቃቁ ነበር። ሰለፎች (ቀደምት ምርጥ ህዝቦች) እርስ በርሳቸው ይፃፃፉትም ነበር። አንድ ባሪያ የልቡ ወለል ላይ ቢነቀሰውና ልክ እንደ እስትንፋሱ ቢያነበው እንኳ (ለዚህ ንግግር) ከሚሰጠው ደረጃ ከፊሉ ብቻ በሆነ ነበር። እርሱም ይህ ነው፦                                                1 ውስጡን ያጠራ አላህ ላዩን ያጠራለታል። 2 በእርሱና በአላህ መካከል ያለውን ነገር ያሳመረ አላህ በእርሱና በሰዎች መካከል ያለውን ነገር ያሳምርለታል። 3 ለአኼራው የሰራ አላህ ለዱንያ ጣጣ በቂው ይሆነዋል።» @Alkewser
Show all...
የቁርአን ቁጥራዊ ተዐምር (math miracle ) ቁርአንን ባወቅከውና በተረዳኸው ቁጥር ተዐምሩ እየሰፋብህ ይሄዳል፡፡ የአላህን ታላቅ ጥበብ ትረዳበታለህ፡፡ ለብዙ ክፍለዘመናት ይዘቱን ጠብቆ መቆየቱ በራሱ የአላህ ታላቅ ችሮታ ነው ብለህ እንድታስብ ያደርግሀል፡፡ በቁርአን ውስጥ ፈልገህ የምታጣው ጉዳይ አይኖርህም ሁሉም ነገር ተጠቅሶበታል፡፡ ታሪክ ብትፈልግ ባማረ አገላለፅ ቁልጭ ብሎ ታገኘዋለህ፡፡ ስለ ሂሳብ ፣ አስትሮኖሚ ፣ ፊዚክስ.... ሁሉንም አቅፏል፡፡ እስቲ ከገረሙኝ የቁርአን ቁጥራዊ ተዐምሮች ትንሽ ልበላችሁ "ውሀ" የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ 63 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ "ሰው"(የሰው ልጅ) የሚለው ደግሞ 90 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ እስኪ የ90 63% ሲሰላ ስንት ይመጣል?? 70 ይሆናል ... ሱብሀነላህ ከሰውልጅ የሰውነት ክብደቱ 70ፐርሰንቱ ውሀ እንደሆነ ያውቃሉ!!! ያአላህ ጥበብህ ብዙ ሚስጥር አለው!!! እርሶ ጋር እንዲቀር አይፍቀዱ ቢያንስ ለ5 ሰው ሼር ያድርጉ #Join_share 👇👇👇 @Alkewser
Show all...
ባለታሪክ #1 ብዙ እህቶች አሉኝ፡፡ እህቶቼ በዲናቸው ጠንካራ ስለሆኑ የነሱን መንገድ እየተከተልኩ ነው ያደኩት፡፡ የተወሰኑት አላህ ባዘዘው መልኩ ተዘውጀዋል፡፡ከቀሩት እህቶቼ ጋር ምናወራው እንደነሱ ለመሆን ነው፡፡ ግን አንድ ቀን አንድ የማላውቀው ልጅ ደውሎ ጓደኛ እንድትሆኚኝ እፈልጋለሁ አለኝ፡፡ ለብዙ ጊዜ እምቢ አልኩት፡፡ ግን ማይቀየር ነገር የለምና በልመና ብዛት ተስማማው፡፡ ከዛ ማውራት ጀመርን፡፡ በቴክስት እየደወለም ያዋራኛል፡፡ ከቆይታ በኋላ እንገናኝ ማለት ጀመረ፡፡ እኔ ግን ፈሪ ስለነበርኩ እምቢ አልኩት፡፡ በዚ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተጣላን፡፡ ግን መልሶ ታረቅን፡፡ አሁንም መለመኑን አልተውም ሲለኝ እሺ አልኩት፡፡ ግን ብንገናኝም አንጨባበጥም ለተወሰነ ሰዐት አውርተን እንለያያለን፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልን 4 አመት ሞላን፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን ስለዚ ጉዳይ ከቤተሰቦቼ ማንም የሚያውቅ የለም፡፡ ግን በማላውቀው ምክንያት ለ2 ወር ዘጋኝ፡፡ ስልክ ብደውል አያነሳም ፤ ቴክስት አይመልስም፡፡ በቤተሰብ ደግሞ ብዙ ትዳር ይመጣልኛል፡፡ የኔ መልስ ግን መቆየት እፈልጋለው የሚል ነው፡፡ በጓደኛው በኩል ምክንያቱን ሳጣራ "በጣም ነው የሚወድሽ ግን ሱስ አለበት እና ልጎዳት አልፈልግም ብሎ ነው የራቀሽ" አለኝ፡፡ እኔ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም አላህዬ ቢመልሰው ብዬ ዱዐ አደርጋለው በዱዐዬም እመልሰዋለው ብዬ አስባለው ፡፡ ከሱ ውጪ ማንንም አልፈልግም እናንተ ምን ትመክሩኛላችሁ ሀሳባችሁን አጋሩኝ በዱዐችሁም አትርሱኝ ሀሳባችሁን በ 👇👇👇 @Alkewserbot ላይ አድርሱን
Show all...