cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ምርጥ ትውልድ ቲቪ (CGF'TV)

"It's finished" Jesus Christ ▪︎Evangelism and ▪︎Discipleship are our main targets. አላማችን:- ወንጌልን(ኢየሱስን) ለፍጥረታት ሁሉ መስበክ እና ዳግም የተወለዱትን ሁሉ በተለያየ መንገድ ማስተማር ለሰርጉ ማብቃት።ግብ:- ክርስቶስን በህይወቱ፣ በኑሮው፣ የሚመስልና የሚኖረው ትውልድ ማፍራት ለአስተያየትዎ @Goldua ይፃፉልን •ኢየሱስ ያድናል! ማራናታ!

Show more
Advertising posts
267
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አመጸኛ ስለበዛ ጻድቅ ሆይ ነፍስህን አድን! አሁን እያደረጋችሁት ያለው ነገር መሆን የምትገልጉት አይነት ሰው እንድትሆኑ ግብዓት የማይሆናችሁ ከሆነ አሁኑኑ አቅጣጫ መለወጥ ይኖርባችኋል። እናንተ እኮ አሁን ካላችሁበት ከየትኛውም ሁኔታ ትበልጣላችሁ። ለህይወታችሁ በቂ የሆነ ነገር ከፊት ለፊታችሁ ስላለ ምናልባትም ማልቀስ አቁማችሁ እንደ አጋር ምንጩን መመልከት ይኖርባችሁ ይሆናል። እልፍ ስትሉ እልፍ በረከት ይጠብቃችኋል። ውድቀታችሁን ሲጠባበቁ የነበሩ ጠላቶቻችሁ በትንሳዔአችሁ ቀን አንዳቸውም አይኖሩም። አሁንም የሉም። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው። እግዚአብሔር አሁን እያለፋችሁበት ባለው ነገር እንድታልፉ ሲፈቅድ ልብ በሉ የተሻለ ስላሰበላችሁ ነው። ውስጣችሁ ያለውን እንቁ ያን ውድ ወርቅ አንጥሮ ሊያወጣው ሲፈልግ ከላዪ ላይ ያለውን አዋራ የሚያስወግድበት አንዱ መንገድ ያ ነው። ክፉዎች ተሳካላቸው እኔ ግን ዘገየብኝ አትበሉ። ክፉዎች ኖሩም ክፉ ናቸው አለፉም ፍጻሜያቸው ጉድጓድ ነው። ልዩነቱ ፍሬጋ ነው። የጻድቅን ነፍስ ለማስጨነቅ ብለው ይኳትናሉ። ረገጥ ሲል "የሚነሳብህ ወገቡ ይወጋ" እንዲል የሚነሱባችሁ ወገባቸው ይወጋ! #የተረገሙ ናቸው። ምቀኛ ሲያልፍለት አይታችሁ ታውቃላችሁ? ሰበበኛ ሲከናወን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? "ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፤ አጥርን የሚያፈርስ እፉኝት ይነድፈዋል" አዎ ልክ እንደዛ። በተፈጥሮ ህግ መሰረት መዝራትና ማጨድ ይቀጥላል። መክበር እና መዋረድ እንደዚሁ። ማንም ባያይህ ጌታ አይቶሃል። ማንም ባይሰማህ ልዑል ሰምቶሃል። ማንም ባይረዳህ እርሱ ይረዳሃል። ይሄ ከገባህ ዝም ብለህ መንገድህን ጠብጥብ። በነገርህ ላይ የአለም ፍጻሜ ከመሆኑ በፊት ከኮሮና የከፋ ወረርሽኝ እና የረቀቀ የአውሬው አሰራር ከፊትህ አለ። ብዙ ንጹሃን ነፍሳት ይሞታሉ። ለምን? አትበል። የተጻፈው ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ጻድቅ ሆይ ነፍስህን አድን! የአውሬው ተላላኪዎች ምን እንዳቀዱ ቢገባህ ትኩረትህ አንዱ ላይ ብቻ ይሆናል። ኢየሱስ ላይ። የአንተ መገኘት የሚያስጨንቃቸው ባላንጣዎችህ ዞር ስትል በጨለማቸው ምድርን ያጥለቀልቋታል። ለዚህ ነው ባለህበት ሁሉ ብርሃንህ ያስፈለገው። ዝም ብለህ አብራ። ብርሃንህ በሰው ፊት ሁሉ ይብራ። የትም ብትሄድ አንድ አይነት ሰው መሆን አለብህ። ወጥነት መለያህ ይሁን። አንተ እኮ ለአፍታ መስራት ትተህ ተመልካች ብትሆን መራራ ሬታቸው ምድርን ከብቦ የባሰ ከድጡ ወደ ማጡ እንድትወርድ ያደርጓታል። አሁን ምስጢሩ እዚህ ጋር ነው ያለው። ትለያለህ። አንተ የአለም ብርሃን እና ጨው ነህ። የአለምን ጦርነት በአልማዊ ስልት በተመሳሳይ ጦርነት መዋጋት አቁም! ... ይቀጥላል... ጻድቅ ሆይ ነፍስህን አድን! #ኢየሱስ--> #በመጀመሪያ--> #አሜን--> #ኢየሱስ ምርጥ ትውልድ የቴሌግራም ጣቢያ
Show all...
Persist and Resist When people ask where I'm, what I'm doing, how that "situation" is coming along, the answer should be clear: I'm working on it. I'm getting closer. When setbacks come, I respond by working twice as hard. Jesus's Lord! @CGFwow
Show all...
2
ስሙ... ፈተና፣ ህመም፣ ተግዳሮት፣ ችግር መከራ ወይም የኑሮ ውድነት ወዘተ... ሕይወታችሁን አመሰቃቅሎት ይሆን? አልገፋ ብሎ የከበዳችሁ ነገር ኖሮ ይሆን? የተወደዳችሁ ሆይ ድላችሁ ያለው በገጠማችሁ ችግር እዛው በራሱ ላይ ነው። ድላችሁ የሚገኘው እያለፋችሁበት ባለው የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ እዛው ላይ ነውና ጸንታችሁ ቁሙ! በርትታችሁ ተዋጉ! ኢያሪኮ ፈርሶአል አይደል? የእናንተም ተራራ ይናዳል! በፍጹም እጅ አትስጡ! ቀጥሉ! ሰይጣን ሲዋሻችሁ እንደማትችሉ ሹክ ይላችኋል። ጠላቶቻችሁ ሲቀኑባችሁ አፍጠው ይመለከቱዋችኋል። ነገር ግን የማታ ማታ ድሉ የእናንተ ነው! በጌታ በኢየሱስ ስም ኃይል እንዲጨመርላችሁ ጸለይኩ!
Show all...
ስሙ... ፈተና፣ ህመም፣ ተግዳሮት፣ ችግር መከራ ወይም የኑሮ ውድነት ወዘተ... ሕይወታችሁን አመሰቃቅሎት ይሆን? አልገፋ ብሎ የከበዳችሁ ነገር ኖሮ ይሆን? የተወደዳችሁ ሆይ ድላችሁ ያለው በገጠማችሁ ችግር እዛው በራሱ ላይ ነው። ድላችሁ የሚገኘው እያለፋችሁበት ባለው የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ እዛው ላይ ነውና ጸንታችሁ ቁሙ! በርትታችሁ ተዋጉ! ኢያሪኮ ፈርሶአል አይደል? የእናንተም ተራራ ይናዳል! በፍጹም እጅ አትስጡ! ቀጥሉ! ሰይጣን ሲዋሻችሁ እንደማትችሉ ሹክ ይላችኋል። ጠላቶቻችሁ ሲቀኑባችሁ አፍጠው ይመለከቱዋችኋል። ነገር ግን የማታ ማታ ድሉ የእናንተ ነው! በጌታ በኢየሱስ ስም ኃይል እንዲጨመርላችሁ ጸለይኩ!
Show all...
የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤቴ ማርያምን እወዳታለው ደግሞም አከብራታለው💛 በልዑል የተመረጠች ምርጥ ጨዋ እናታችን ናትና ሁሌም ለሴቶች ሁሉ ምሳሌ ሆና ትኖራለች!
Show all...
My friends keep sinning and mocking against the Anointed men of God and keep doing whatsoever seems likely to you before your eyes. You want to march doing things that are dirty and contradictory to the words of God? And guess what happens next? You'll find yourself in the most horrible place- the so called Hell. I'm sorry to say that but the hell is for real and waiting all the sinners who are walking against the commandments and orders of God. If you repent of your sins and come to the throne of God today, right now, he will forgive your sins and you will go to heaven. Accepting Jesus is the only license you have to enter the kingdom of God. Nothing else just acknowledging His deeds on the cross and believing as per the story written in the Holy Bible. Remember this the day of salvation is today. Tomorrow is not yours. Just think of it and return from your wicked life and be planeted in the presence of the Holy Spirit. Turn away from your sins right now. Come to your merciful Father God- the one who createdyou in His likeness and image. He sent His only begotten son 2000 years ago to save us all. And Jesus Christ died instead of you for the remission of your sins. He sheded His blood for you to prove that He loves you unconditionally. His love never fails. Moreover His blood was sheded not for those who rejected him and are going to reject it but to those who accepted it and are going to accept it- the passedgenerationand the coming generations too. Yes the blood of Jesus is enough to save you from eternal punishment. This's your friend Z Anointed Gold If you have any questions please don't hesitate to contact me in my email: [email protected] I'll pray for you. Blessings, Happy day! @CGFwow
Show all...
Every good tree bears good fruit, but a bad tree bears bad fruit. A good tree cannot bear bad fruit, nor can a bad tree bear good fruit.
Show all...
🥰 2
ቅድስና ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለሰው አይደለም። አታስመስሉ! በተሳሳተ ህይወት ውስጥ ተዘፍቃችሁ እየተመላለሳችሁ መንፈስ ቅዱስ አዝኖ መመለሳችሁን በትእግስት እየተጠባበቀ ባለበት ሁኔታ እኔ ጥልቅ ብዬ በርቱ አልላችሁም። እዚጋ መጠርመስ የለም መደርመስ እንጂ። ፈጥናችሁ ተመለሱ። የአመጽ ህይወት ፍጻሜው ሞት ነው። ተቀደሱ! ንጹ! እድፈታችሁ በኢየሱስ ደም ይታጠብ! ኑ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት ቅረቡ! እግዚአብሔር መሐሪ ነው።
Show all...