cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከብዙዎች በጥቂቱ

ዕውቀትን የሚያስጨብጡ ኢስላማዊ፣ሳይኮሎጂን እና ሌሎችንም ማህበራዊ ታሪኮችን ያዘሉ መፅሀፍቶች(pdf) የሚዳሰሱበት እና በልዩ እና ማራኪ ሁኔታ ተሰናድተው የሚቀርቡበት ልዩ Channel join በማድረግ ይቀላቀሉን። https://t.me/joinchat/AAAAAEOw-c-NOpmiL5OPTg For any comment or suggestion contact us

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
206
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Aselamu aleykum werehmetulahi weberekatuh እስቲ በዚ በተከበረው የረመዳን ወር ምን ለማድረግ አስበዋል ምን ኸይር ስራ ለመስራት ይፈልጋሉ ? 👉 የየቲም ልጆችን ለመርዳት አስበዋል? 👉 የሚረዳቸው ላጡ እናት አባቶችን ለመርዳት ይፈልጋሉ 👉 ለሚስኪን ቤተሰቦች ልጆችን ይረዳሉ 👉 የየቲም ልጆች ማልበስ ይፈልጋሉ 👉 የሚያፈጥሩበት ለሌላቸው ወገኖቻችን የማፍጠሪያ ወጪ መሸፈን ይፈልጋሉ በችግር አለንጋ ተገርፈው ጌታቸውን ከመገዛት ያልቦዘኑ የአላህ ባሮችን በታላቁ ረምዷን ማፍጠሪያ በማጣት ብቻ ቀን እና ሌሊት ያለማቋረት ከመፆም እንታደግ። "ከአንዳች ነገር አትለግሱም እርሱ አላህ የሚተካው ቢሆን እንጂ።" (ሰበእ 39) ኑ! ተቀላቀሉን @yeyetimoch
Show all...
ወንድምዬ እህትዬ በእህት ወንድሞቻችሁ፣ በአጠቃላይ በሙስሊሞች ረብ የለሽ አካሄድ ብሎም የሙስሊሞች ሰቆቃና የስቃይ ግርፋት ውስጥህ አቁስሎን ልባችንን አድምቶት ይሆናል። በጉዳዩ ላይ የእውነት ከጌታችሁ ጋር አውርታችሁ ታውቃላችሁ? ዛሬ እጃችሁን በተማፅኖ ዘርጉ ጥያቄዎችህን አዥጎድጉድ ፈጣን ምላሽ ትስሰጣለህ። ምክንያቱም ዛሬጁሙዓ ነው! @keewketadmas
Show all...
ርቀትህን ለካ . በፊትም በኋላም በግራም በቀኝም አስበህ ሞክረህ በነገርህ ሁሉ ጥረህ ካልተሳካ፣ ሙሲባህ ከበዛ ኪሣራህ ካየለ በድርብርብ ችግር ዉስጥህ ከተነካ ፣ እራስህን መርምር ችግሩ ካንተ ነው ከፈጠረህ አምላክ ምን ያህል እንደራቅክ ክፍተትህን ለካ! . @keewketadmas
Show all...
ለሐያት መዳን ምክንያት እንሁን 🙏 *** ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትባላለች:: የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን እድሜዋ 17 ነው። በደረሰባት ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ህመም ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ቆይታለች። አሁን ላይ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ከጥቅም ውጪ ስለሆኑ ወደ ቀድሞ ጤንነቷ እንድትመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ ከሃኪሞች ተነግሯታል። የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጪ ሀገር መሄድ የግድ ይኖርባታል። ለዚህም ህክምና ሁሉንም ሂደት (process) ጨምሮ እስከ 2,000,000 (ሁለት ሚሊየን) ብር ያስፈልጋታል!!! ይህን ገንዘብ ለመሸፈን የሀያት ቤተሰቦች ወገኖቻችን እርዱን አግዙን እያሉ ወደ ህብረተሰቡ ጥሪ ያቀርባሉ። ሐያት ወደ ሞት ስትሄድ እያያችሁ ዝም አትበሉኝ ለመዳኔ ምክንያት ሁኑ ትለናለች! ከተረባረብን 2000( ሁለት ሺህ) ሰው ሆነን 1000 (አንድ ሺህ) ብር ብልነግስ ልጃችን፣እህታችን ድና ህልሟን ታሳካ ዘንድ ምክንያት እንሁናታለን። ሀያት ድና ትምህርቷን መቀጠል ትፈልጋለች። ደግሞ ለመዳኗ ሰብብ እንሆናለን። የቻልነውን በሙሉ እህታችንን በገንዘብ እንርዳት፣ በገንዘብ ያልቻልን በፀሎት አብረናት እንሁን ፣ ሌላው ቢቀር መረጃውን ሼር በማድረግ ሊረዷት ወደሚችሉ ሰዎች አንድ እርምጃ እናቅርባት። በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈ የአካውንት ስም:— ሀያት ኢብራሂም ዑመር የኢትዮጲያን ግድ ባንክ:— 1000353443147 አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ:— 01425853981500 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ :— 1000089014135 የሀያትን ቤተሰቦች በስልክ ለማግኘት ◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈ 0983676776 0920942369 0912823605 ያለችበትን ሁኔታ ማወቅና መከታተል እንዲሁም ከጎናችን መቆም ለምትፈልጉ በሙሉ በፌስቡክ https://m.facebook.com/Help-Hayat-115161023734791/?ref=opera_speed_dial በቴሌግራም https://t.me/helphayat https://t.me/Help_sis_Hayat መጠቀም ተቀላቀሉን፡፡ 🙏🙏🙏🙏
Show all...
Log in to Facebook

Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.

Join👆👆👆👆
Show all...
👉የምግብ ግብዣው የባለቤቷን ቤተሰቦች ማክበር የማይሆንላት አንዲት ባልቴት ነበረች። አንድ ቀን ባለቤቷ እንዲህ አላት "ቤተሰቦቼ፣ ወንድም እህቶቼና ልጆቻቸው እጅግ ናፍቀውኛል። ለነገ የምሳ ማዕድ አዘጋጂና ለምሳ ፕሮግራም እንዲመጡ እጠራቸዋለሁ። ለበርካታ ጊዜያት ሳንገናኝ ከርመናል።" ሚስቲቱም የድካም ስሜት እያንፀባረቀችና በንቀት ዓይን እየተመለከተች " ኢን ሻ አላህ ጥሩ እሺ" አለች። ባል ወዲያው ንግግሯን እንዳበቃች "እንግዲያውስ ቤተሰቦቼን በሙሉ ልብ እጠራቸዋለሁ" አለ። ፊቱ በደስታ የፈካ፣ ልቡም በፈንጠዚያ የተወጠረ ይመስላል። ጊዜ ይተካካልና ትናንት አልፎ ቤተሰቦቹ የተጠሩበት ቀን ደረሰ። ባል በማለዳ ተነስቶና ተጣጥቦ ወደ ስራ ቦታው አቀና። ብዙም ሳይቆይ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለባለቤቱ "የምሳውን ማዕድ አዘጋጅተሻላ? ቤተሰቦቼ ከአንድ ሰዓት በኋላ ብቅ ይላሉ" አላት። ሚስት " አይ! ምንም የተለየ ምግብ አላዘጋጀሁም። ቤተሰቦችህ እንግዳ ስላልሆኑ ቤት ያፈራውን ይመገባሉ። ምንም ችግር የለውም።" አለች ቀለል አድርጋው። ምን ያልነካው ምን አያውቅም አሉ። ባል ድምፁን ንዴት ዋጠው። ትንሽ ዝምም አለና "ፈጣሪ ይቅር ይበልሽ! ትናንት ስንስማማ አላዘጋጅም፣ አልችልም ብለሽ አትነግሪኝም ነበር? አሁን ከ 1 ሰዓት በኋላ እዚህ ይደርሳሉ። ታድያ ምን ላደርግ ነው እሺ?" አላት። ፊቱ ላይ የሀዘን ዳመና አጥሎበታል። አንገቱን ወደታች አቀርቅሮ በሀሳብ ተውጧል። "በቃ ደውልላቸውና ምንም እንዳልተዘጋጀ አሳውቀህ ይቅርታ በላቸው። እነርሱ እንግዶችኮ አይደሉም ቤተሰቦችህ ናቸው።" አለች። ባል ልቡ በሀዘን ተሰብሮ ከቤት ወጣ። ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ የቤቱ በር መንኳኳት ጀመረ። ሚስት ተነሳችና በሩን ከፈተችው። አይን ለአይን ይተያዩ ጀመር። ድንጋጤ ውስጧን ገፈፈው። እንደድንገት በሩን የከፈተቻቸው ሰዎች የርሱ ቤተሰቦች ሳይሆኑ የርሷ ቤተሰብ፣ ወንድም እህቶቿና ልጆቻቸው ነበሩ። "ባለቤትሽ የት ነው?" ሲል ጠየቃት አባቷ። እሷም "እ… አሁን ቅርብ ሰዓት ወጥቶ ነው" አለች። "ትናንትኮ ለዛሬ የምሳ ግብዣ ጥሪ እንዳለ ነግሮን ነበር። እንዴት ጋብዞን እሱ ይጠፋል?" አላት። ሚስት የምትሆነው ጠፋት። አንዳች ይሆናል ብላ የማታስበው ከባድ ዱብዳ የወረደባት መሰላት። ነገሩ ግር አሰኝቷት እጆቿን ቆላለፈች። ይገርማል! ቤት ያፈራው ምግብ ለሷ ቤተሰቦች የማይመጥን ለርሱ ቤተሰቦች ደግሞ ተገቢ መሆኑ ነው። ሞባይሏን አንስታ ደወለች። ስልኩ ተነሳ። "ሄሎ… ቤተሰቦቼ የምግቡ ግብዣ ላይ እንደሚመጡ ለምን አላሳወቅከኝም?" አለች ጭንቀት በተሞላበት ቀጭን ድምፅ። "ያው ያንቺ ቤተሰቦች ማለት የኔ ቤተሰቦች ናቸው። ልዩነት አለው እንዴ?" አላት ባል። "እባክህን ከሆቴል የተዘጋጀ ምግብ ይዘህ ና! ቤት ውስጥ ምግብ የለም።" አለች። ሳይታወቃት የመርበትበት ነፋስ ስሜት ውስጥ የሰጠመች ይመስላል። "እኔ አሁን ሩቅ ቦታ ነው ያለሁት። እነዚህኮ እንግዶች አይደሉም ቤተሰቦችሽ ናቸው። ለኔ ቤተሰቦች ልትመግቢ የነበረውን ቤት ያፈራውን ምግብ አቅርቢላቸው። እሱን ይመገቡ። ይህም ቤተሰቦቼን ለማክበር ትምህርት ይሁንሽ" ስልኩ ተዘጋ! 💡"ሰዎች እንዲያደርጉልህ በምትፈልገው ነገር ሰዎችን አስተናግድ!"💡 https://t.me/keeweketadmas
Show all...
ከብዙዎች በጥቂቱ

ዕውቀትን የሚያስጨብጡ ኢስላማዊ፣ሳይኮሎጂን እና ሌሎችንም ማህበራዊ ታሪኮችን ያዘሉ ፅሁፎችን(pdf መፅሀፍት) የሚዳሰሱበት እና በልዩ እና ማራኪ ሁኔታ ተሰናድተው የሚቀርቡበት ልዩ Channel join For any comment and suggestion @bumrika

የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎች ------------------------- አንድ ሠው ወደ ሶቅራጠስ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡ ‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሠማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስ ግን ዝም አለ፡፡ ሠውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለ፡፡ ሶቅራጦስም ይህ ሰው እንደማይለቀው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡ ‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም፡- ‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡ ሶቅራጦስም፡- ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡ ሶቅራጦስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው ይባላል፡፡ ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው? ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው? አሁን እኮ ሰው ዝም ብሎ የተነገረውን ስለሚሰማ በቀላሉ እንደ እንስሳ የሚነዳ ሆኗል፡፡ በየሶሻል ሚዲያው ላይ ፖስት የሚደረጉት ብዙዎቹ መረጃዎች እውነት ያልሆኑ፣ መልካምነት የሌላቸው እና ለእኛ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ናቸው፡፡ በተቃራኒው የውሸት መረጃዎች ሆነው ስንቱን ያጭበረበሩ፣ ሰይጣናዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚገፋፉ ሆነው ሳለ ያለማቅማማት እንሰማቸዋለን፡፡ አሁን አሁን እውነት ከሚናገሩት ሰዎች በላይ በመርዝ የተለወሰ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች የተሻለ ብዙ ተከታይ አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን ከሚሰብኩ ሰዎች ይልቅ የጥፋት ሰባኪዎች ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ ፍለጠው/ቁረጠው ባዮች ናቸው የጀገኑት፡፡ እነሱን ማስቆም አይቻል ይሆናል፤ ነገር ግን እነሱን አለመስማት/አለመከተል ቀላል ነው፡፡ እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡ @keewketadmas
Show all...
ጀርመን ውስጥ ነፃ ለመሆን መሞከር የሰዎች ተፈጥሮአዊ መብት ስለሆነ ከእስር ቤት ለማምለጥ ለሚሞክር እስረኛ ቅጣት አያስቀጣም። 😂 @keewketadmas
Show all...
🌸🌸ይህን ያውቁ ኖሯል??? 🌸🌸 የመካከለኛው ዘመን( medieval time) በአብዛኛው ቆሻሻ ጨለማና በመጥፎ ሽታ የተሞላ እንደ ነበር ይገመታል በወቅቱ የነበረው አብዛኛው የአውሮፖ ማህበረሰብ annual bath ተብሎ በሚጠራው የእጥበት ስርአት በአመት አንድ ግዜ ብቻ ይታጠብ እንደነበር ይነገራል። _ የሙስሊሙ አለም በአንፃሩ የንፅህና ይዞታው አሁን በሰለጠነው አለም ካለው ሁኔታ ጋር የሚወዳደር ነበር የአላህ መልዕክተኛ ( ሰ.ዐ.ወ) ንፅህና የአንድ ሰው የእምነቱ ክፍል እንደሆነ አስተምረዋል ለዚህም ነው፦ የምዕራቡ አለም ሰዎች በመጥፎ ሽታ በተሞሉበት ወቅት ሙስሊሞች ግን ለንፅህና የሚያገለግል ሮቦት እስከመስራት ደርሰው ነበር ሱብሀነከ ረቢ @keewketadmas
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.