cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የያሲኔ ወዳጅ 🇪🇹PAGE🇪🇹

እኔ የያሲኔ ወዳጅ ለኢስላም ማድረግ ከሚገባኝ የገዘፈ ግዴታ ቅንጣት በመፍጨርጨር ላይ ነኝ ዓላማችን ያውቀነውን ማሳወቅ ነው 🍀 Comment ☞ @Nemira_1 ለአስተያየት መስጫ @Nemira_1 በሀሳብ ለመደገፍ 👉 @Nemira_1 ወይም☞ @NemiraBot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
15 214
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ዛሬ ዓለምን እያነጋገረ ከዋሉትው ዜናዎች መካከል አንዱ ትልቅ ዜና ስድስት የዕድሜ ልክ የተበየነባቸው ፍልስጤማዉያን የኢስላሚክ ጂሃድ ከፍተኛ አባላት በጉድጓድ ዉስጥ ለዉስጥ አልፈው ዛሬ ማለዳ በከፍተኛ ደረጃ ጥበቃ ከሚደረግለት የኢስራኢል እስር ቤት ማምለጥ ነው፡፡ ከእስር ቤት ዉስጥ ወደ ዉጭው አጥር የተቆፈረው ጉድጓድ አሥራ ምናምን ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡ ከስድስቱ አራቱ ዕድሜልክ የተፈረደባቸው ነበሩ። ሰዎቹ በሄሌኮፍተር እገዛ ጭምር እየተፈለጉ ነው፡፡ “በርተህ ቆፍር የጉድጓዱ የመጨረሻው ጫፍ ላይ የምታገኘው ብርሃንን ነው” ይላሉ ፍልስጤማውያን በመፈክራቸው ስለ ነፃነት ዋጋ ሲናገሩ፡፡ 'ሰው ነፃነቴን ካለ ድንጋይ ይሰረስራል።' Muhammed Seid Abx
Show all...
የቀጥታ ስርጭት #ሂጅራ ኢስላማዊ ባንክ የምረቃ ደማቅ ፕሮግራም https://youtu.be/bxjyFw2lJR8
Show all...
በአማርኛ ተፅፎ ወደ ዐረብኛ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢስላማዊ የታሪክ መፅሃፍ። «ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ» የተሰኘውና የዛሬ አስር ዓመት ለሕትመት የበቃው የኡስታዝ አህመዲን ጀበል የታሪክ መጽሐፍ ወሂብ አብዱልዋሲ እና ሙክታር ከዋጃ በተሰኙ ግለሰቦች አማካኝነት ከአማርኛ ወደ አረብኛ ተተርጉሞ ለዐረብኛ አንባቢያን በኳታር ሀገር ዶሃ ለህትመት በቅቷል። መጽሐፉ ለጊዜው በኳታር ሀገር በሚገኘው በግዙፉ «ጀሪር የመጽሐፍት መደብር» ሦስቱ ቅርንጫፎች ዉስጥ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
Show all...
«ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!» ✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳ የእስር ባልደረባዬ ወንድም ሙሐመድ አባተ ጠያቂያችን የነበሩት እናቱ አርፈዋል። አላህ በምህረቱ ይመልከታቸው። በትዕግስታችሁ አላህ ላንተና ለመላው ቤተሰባችሁ ታላቅ ምንዳን ይመንዳችሁ። ለሞቱት እናታችንም አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይለግሳቸው። መከራችሁንም አላህ በመልካም ሁኔታ ይለውጥላችሁ። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1028367904668415&id=100024856459321
Show all...
አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። ✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳ የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ። በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000427892232 ይማም አህመድ ኢስማዒል ይስማው ሙሐመድ ተስፋዬ
Show all...
የኡስታዝ መሀመድ አወል ሳላህ የቀብር ስነስርአት ተፈፀመ አላህ የጀነት ያድረገው ሁላችንም በዱአ አንርሳው
Show all...
የመሀመድ አወል ሳላህ የቀብር ስነ ሰርአት በቀጥታ ከኮልፌ አላህ ይዘንለት https://youtu.be/sK73rHtH2go
Show all...
አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። Share በማድረግ ያሰራጩ የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ ልጆች ልጆቻችን ናቸው። ቤተሰቦቹ ቤተሰቦቻችን ናቸው። እርሱን ማጣት ሃዘኑ ከባድ ነው። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ። በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000427892232 ይማም አህመድ ኢስማዒል ይስማው ሙሐመድ ተስፋዬ
Show all...
ኢና ሊላሂ ወ ኢነ ኢለይሂ ራጅዑን ተወዳጁ መሀመድ አወል ሳላህ ወደ አኼራ ሄደ አላህ ለሱ ጀነተል ፍርዶስን ለቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን ሁላችንም ዱአ እናድርግለት ዙህር ላይ በኮልፌ መካነ መቃብር ሁላችንም እንገኝ አላህ ይዘንለት ያረቢቢ
Show all...
አስደሳች ዜና ታሊባን እነ አሜሪካን በጦርነት በማሸነፍ አፍጋኒስታንን ኢስላማዊ መንግስት ስር ተቆጣጠረች አላሁ አክበር https://youtu.be/JHcqttMTgkE
Show all...
ሰበር ዜና መጅሊስ የመጅሊሱን ህንፃና መሬቶች የነጃሺ የመስጂድና የምርምር ተቋም እነረዲሁም አዲስ የተሰራውን የመጅሊስ ህንፃ ከታለመለት አላማ ውጪ ሸንሽኖ በሕገ ወጥ መልኩ ለማከራየት እየተሰራ መሆኑ ታወቀ ለመጅሊሱ ለውጥ ክሽፈት ሲታትሩ የነበሩት ግለሰቦች እውነተኛ አላማ መጋለጥ ጀምሯል! የመጅሊሱ ፀረ ለውጥ ሀይሎች አላማ አልፋና ኦሜጋ የሙስሊሙን ተቋም መዝረፍ እና ትኩረታቸው ሁሉ የጥቂት ግልሰቦችን ጥቅም ማስጠበቅ እንደነበረ የሥራ አመራር ቦርዱ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል። በተለይም በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ ለወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ሙሉ ትኩረቱን ሰጥቶ ባለበት ወቅት ለህገወጥ ሥራዎቻቸው ህዝቡ ስለሚዘናጋ ያመቸናል በሚል የመጅሊሱን ህንፃና መሬቶች ከታለመለት አላማ ውጭ ለመጠቀም በይፋ ማስታወቂያ አውጥተው ተከራዮችን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኙ የሥራ አመራር ቦርዱ ደርሶበታል። እነዚህ ህገ ወጥ ግለሰቦች የዋና ግቢ አዲሱን ህንፃ ከታለመለት የመጅሊሱ ህዝባዊ አገልግሎት በተቃራኒ በረጅም ጊዜ ኪራይ ገንዘብ ለተለያዩ የግል ጥቅማጥቅሞች ክፍያ ለማዋል በእንቅሰቃሴ ላይ ይገኛሉ። ይባስ ብሎም የነጃሺ አለም አቀፍ የመስጊድና የምርምር ተቋም ቦታ ለታለመው ግንባታ የቀረበውን የ60 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አንቀበልም በማለት ከመለሱ በኋላ አሁን ግቢውን በጥቃቅን ሱቆች ሸንሽኖ ለረጅም አመታት ለማከራየት እየተሞከረ ይገኛል። በዚህ ቦታ ላይ የይገባኛል ክርክር ካስነሱት ኃይሎች ግፊት በተጨማሪ ቦታው በመንግስት የተሰጠው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ግንባታ እንዲገነባበት ካልሆነ መልሶ ለመቀማት ከማስጠንቀቂያ ጭምር ጋር እንደነበር ይታወሳል። በመሆኑም አሁን የተያዘው የኪራይ ሰብሳቢነት ሂደት ከተሳካ ከቦታው ቅንጥብጣቢ ለመሰብሰብ በረጅም ጊዜ ውል የግንባታውን ሂደት እንዳይሳካ በማድረግ የሙስሊሙን ህልም ማጨለም ይሆናል። በዚህ ሂደት እንደ ከዚህ ቀደሙ የመጅሊስ አመራር የመጅሊሱን ንብረቶች በመሸጥ እና በማከራየት የግል ጥቅሞችን በማጋበስ ህዝቡ ገፍቶ "ተቋሜን" ብሎ ሲጠይቅ ያለምንም ተጠያቂነት ዞር ለማለት እንደታሰበ ያሳያል። ስለሆነም ከላይ የተገለፀው የህንፃ እና ቦታ ኪራይ ውሳኔ በህገ ወጥ አካላት የተላለፈ የህዝቡን ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ ተግባር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። በተጨማሪም ይህን የቀረበውን ህገወጥ የኪራይ ማስታወቂያ ተከትሎ ነገ በህግ ሊያስጠይቅ ስለሚችል ማንም ወገን የገዛ ገንዘቡን እንዳያባክን እና የህዝበ ሙስሊሙ ሀብት ምዝበራ ላይ እንዳይሳተፍ የሥራ አመራር ቦርዱ በጥብቅ ያሳስባል። ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን በተከታታይ የምናጋራ ይሆናል።
Show all...
በደሴ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ ================ የደሴ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋ ሕዝብ “ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባለ” የሰዓት እላፊ አዋጅ መጣሉን አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ፍቃድ ከተሰጣቸው የጸጥታ አካላት ውጪ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ማድረግ ተከልክሏል ብሏል። የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ደግሞ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን የከተማዋ አስተዳደርን በመጥቀስ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል። ከሰሞኑ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን ግጭት በመሸሽ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ወደ ደሴ ተፈናቅሎ እየገባ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል። የከተማ አስተዳደሩም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሐይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሠራት ላይ እገኛለሁ ብሏል።
Show all...
የሳውዲ መንግስት ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በሚስኪን ስደተኛ ኢትዮጲኖች ላይ ለምን ይፍፅማል ? ረሱል እንኳን ዱአ ያረገላት ሀገር እኮ ናት ሀበሻ https://youtu.be/0prvHWw9ZFA
Show all...
ሀገር አጣብቅኝ ውስጥ ባለችበት ሙፍቲ ዛሬም ህዝበ ሙስሊሙን ወደ አመፅ ሚያሰገባ ተግባር እየፈፀሙ ነው ሰበር ዜና *** ከለዉጡ በኋላ የተባረሩት በአዲስ አበባ 10ሩም ክፍለ ከተሞች የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራሮች ዳግም ወደቦታቸው እንዲመለሱ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር በደብዳቤ ጠየቁ! ------- RN05 . ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የቀድሞ ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ጋሻ-ጃግሬዎች የነበሩ እና በሙስሊሙ ላይ ተጭነው ለዛ ሁሉ ግፍ እና መከራ ተባባሪ የነበሩ ለዉጡ ሲመጣ ምንም ሳይጠየቁ ከስልጣናቸው ብቻ እንዲወርዱ ከተደረጉት መሃል ከነበሩት ዉስጥ የአዲስ አበባ መጅሊስ የአስሩም ክፍለከተሞች የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ቀድሞ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ መጻፋቸውን የሚገልጽ መረጃ ደርሶናል ። . በአንድ በኩል "ህዝባዊ መጅሊስ ለማቁቋም ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር አብሬ እየሰራሁ ነው" የሚሉት ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዘዳንት የሸህ ሱልጣን አማንን ደብዳቤ በመሻር የቀድሞው አህባሽ መራሽና ህዝበ ሙስሊሙን ለበርካታ ስቃዮችና እንግልቶች ያበቃው መጅሊስ ወደ ስልጣን እንዲመለስ መወሰናቸውን እና ለዚሁም እየሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
Show all...
የኢድ ድባብ በሀወሳ #ኢድሙባረክ #Eidmubark
Show all...
የኢድ ድባብ በደሴ #ኢድሙባረክ #Eidmubark
Show all...
አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ አክበር ላኢላሀኢልለላህ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ 🙏 አላሁ አክበር ከቢራ ወልሐምዱሊላሂ ከሲራ ወሱብሐነላሂ ቡክረተን ወአሲላ ላኢላሀኢልለላሁ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ ☝️ ዱዓችንን አላህ ይቀበለን!🤲 ዒዱኩም ሙባረክ 🕋🎈🎊 ያማረ
Show all...
ነገ ሰኞ ሀምሌ 12/2013 የዐረፋ ቀን ነው። ★★★★★★★★★★★★★★ ★ T.me/ahmedin99 🔴 የአላህ መልክተኛ [ﷺ] «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢአት ያስምራል።» ብለዋል። ሙስሊም ዘግበውታል። ኢማም አል—ሙናዊ [ረሒ] እንዲህ ብለዋል: ‐ ገና ያልተከሰተውን «የመጪውን ዓመት ኃጢኣት» ያስምራል ሲባል ምን ማለት ነው?: — ❶ በመጪው ዓመት ከኃጢኣት ይጠብቀዋል ማለት ነው። ❷ ለመጪው ዓመት ኃጢኣቱ ማሰረዣ የሚሆን ምንዳ ይሰጠዋል ማለት ነው። ወይም ❸ ሰውየው በህይወት ቆይቶ ኃጢኣት ቢሰራ እንኳን ይሰረዝለታል ማለት ነው።» ፈይዱል ቀዲር ቅፅ 4፣ ገፅ 230 መልዕክቱን ለሌሎች በማጋራት ሌሎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምክንያት እንሁን።
Show all...
🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ - ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣ - ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡ 1- ልብሴን ያወልቃሉ፣ 2- ያጥቡኛል፣ 3- ይከፍኑኛል፣ 4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣ 5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣ 6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣ 7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡ ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡ 8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል - ቁልፎቼ 🔑🗝 - መጽሐፎቼ 📚 - ጫማዎቼ 👟 - ልብሦቼ 👖👔….. በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ - በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣ - የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣ - የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣ - በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣ - ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣ - ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤ - ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል - ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤ ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! … በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ 1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ 2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣ 3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣ የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!! 1- መልክህ፣ 2- ሀብትህ፣ 4- ጤናህ፣ 5- ልጅህ፣ 6- ቪላህ፣ 7- ዝናህ፣ 8- ሚስትህ/ባልሽ ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡ እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ 1- በግዴታዎች፣ 2- በሱንና ነገሮች፣ 3- በድብቅ መፅውት፣ 4- መልካም ሥራ አብዛ፣ 5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣ ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡ መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡ ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ሼር ሼር .....✔️
Show all...
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን የደሴ ከተማ እውቅ አሊም የነበሩት ሼይኽ ሙሀመድ አብዱል ከሪም ወደ አኼራ ሄዱ ሼይኽ መሐመድ ከልጅነታችን ጀምሮ ስናውቃቸው ቤታቸው በኪታቦች የተሞላ ነበር:: በደሴ ከተማ እንደሳቸው በርካታ ኪታቦች የነበረው አሊም የነበረ አይመስለኝም:: ህይወታቸውን ከሀዲስ እና ኪታብ ጋር አሳልፈው ነው ያለፉት:: ህዝባቸውን በኢማምነት እንዲሁም ኪታብ ሲያቀሩ እና ሲያስተምሩ ለብዙ አመት ካገለገሉ ቡኃላ በሳኡዲ አረቢያ ኑሯቸውን አድርገው እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ እዛው ቆይታ አድርገዋል:: በተመሳሳይም የእድሜ ባለፀጋ የነበሩት የመናዊው ታላቅ አሊም ሼይኽ መሐመድ እስማኤል አል አምራኒ ወደ አኼራ ሄደዋል:: እኚህ አሊም የየመን ሙፍቲ፣ቃዲዕ እና ታላቅ ሙሐዲስ ነበሩ:: አልጀዚራ ስለሳቸው ህልፈት የሚከተለውን ጥንቅር አዘጋጅቶ አቅርቧል https://www.facebook.com/aljazeerachannel/videos/177253057768676/ ከቂያማ ምልክቶች መካከል የኢልም መነሳት አንዱ ነው:: ኢልም የሚነሳውም በአሊሞች ሞት ነው:: እነዚህን የመሳሰሉ አሊሞቻችንን በሞት ማጣት ለኡማው ትልቅ ኪሳራ ነው:: ለሞቱብን አሊሞች አላህ ይማራቸዉ። ቤተሰቦቻቸዉን ሶብር ይስጥልን። ለኡማውም ምትክ አሊሞችን አላህ ያውጣልን
Show all...
ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ አስሩ የዙል ሒጃህ ውድ ቀናት እሁድ እንደሚጀምር ታወቀ አላህ ይቀበለን ከሚጶሙት ያድርገን
Show all...
#ኢናሊላሂ_ወኢናኢለይሂ_ራጂዑን #ያስደነግጣል😭 #አላህ_ይርሃምህ 😭 "ወንድሜ በዱአ አትርሱኝ" እንዳለ አሸለበ😭😭😭 "የመጨረሻ ደረጃላይ ደርሻለው መሰለኝ ፀጉሬእየተነቀለ ነው! ቤተሰብ እንዳይጨነቅ እያለ አንዋሬ ከነሳቁ ማታ ከምሽቱ 2:30 ህንድ ህክምና ላይ እያለ አረፈ😭 ወንድማችን ድነህ እንደምትመጣ ተስፋ ብናደርግም አላህ የወደደው ሆነ! #አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቅህ ለተጨነቃቹና ለደካማቹ ሁሉ መፅናናቱን ይስጣችሁ🙏 #ህይወት እንዲህ ናት!ሁሉም ነገር ቢሞላልህ ያለ አላህ ፍቃድ አንዲት ሰከንድ አታልፍም😭 ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፡፡ (ከጊዜያቱ) አይቀደሙምም፡፡
Show all...
አስደሳች ሰበር ዜና •በትግራይ የሚደረገው ጦርነት ለጊዜው መቆሞ ተነገረ መከላከያ መቀሌን ለቆ ወጣቷል አልሃምዱሊላህ https://youtu.be/qT-MArZsnRE
Show all...
ሰበር አስቸኳይ ሼር || በሳውዲ እስር ቤት ለሚሰቃዩ ወገኖች አፋጣኝ እርዳታ እናድርግ ኢምባሲ በመሄድ እናድርግላቸው አሰራ ኢጋማ ያላቹ ብቻ ሂዱ https://youtu.be/pEmTc8Fydlg
Show all...