Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
@telemetr_io_bot
Telegram analytics bot

The bot can:

  • analyze channel audience
  • channels intersections
Category
Channel location and language
እኔ የያሲኔ ወዳጅ ለኢስላም ማድረግ ከሚገባኝ የገዘፈ ግዴታ ቅንጣት በመፍጨርጨር ላይ ነኝ ዓላማችን ያውቀነውን ማሳወቅ ነው 🍀 Comment ☞  @Nemira_1  ለአስተያየት መስጫ  @Nemira_1  በሀሳብ ለመደገፍ 👉  @Nemira_1  ወይም☞  @NemiraBot  
Show more
29 692-27
~12 385
~0
41.68%
Telegram general rating
Globally
61 117place
of 3 824 617
86place
of 899
In category
158place
of 1 040

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

8 524
18
8 295
10
7 587
14
የነብዩ ሰ. ዐ ወ ክብር ለማጉደፍ በውሻ ምስል የሳላቸው ቆሻሻው ግለሰብ በመኪና አደጋ ሞተ || አልሃምዱሊላህ https://youtu.be/mHKHn8iFsko
የነብዩ ሰ. ዐ ወ ክብር ለማጉደፍ በውሻ ምስል የሳላቸው ቆሻሻው ግለሰብ በመኪና አደጋ ሞተ || አልሃምዱሊላህ
#ethiopia #malcolmxethio
8 509
16
የውድ ነብያችን(ሰዓወ) ጠላት በሞት ተወገደ ከሞት ለማምለጥ በፖሊስ ሲጠበቅ የቆየው ከነጠባቂ ፖሊሶቹ ሞተ የውዱን ነብይ ክብር ለማጉደፍ በማሰብ በ2007 በውሻ ምስል ላይ የሳቸው ምስል ነው በሚል የካርቶን ምስል ሰርቶ የአለምን ሙስሊም አስቆጥቶ የነበረው ስዊዲናዊው ግለሰብ በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል:: ላርስ ቪልክስ የተባለው ይህ ግለሰብ ይህን የካርቶን ምስል ሰርቶ ካሰራጨ ቡኃላ በደረሰበት ውግዘት ለደህንነቱ ሲባል በፖሊስ ጥበቃ ስር ህይወቱን ሲመራ የቆየ ሲሆን በሲቭል ፖሊሶች መኪና በሁለት ሲቭል ፖሊሶች ታጅቦ በመኪና እየየጓዘ በነበረበት ወቅት ከትልቅ መኪና ጋር ተጋጭቶ በ 75አመቱ ህይወቱ አልፏል:: በሰራው ወንጀል ስጋት ከሞት ለማምለጥ በፖሊስ ሲጠበቅ ቢቆይም ከነጠባቂ ፖሊሶቹ ሞት በመኪና አደጋ ጠልፎ ወስዶታል:: ይህን ሙጅሪም ግለሰብ የእጁን አላህ ይሰጠው ዘንድ ዱዓችን ነው! Abu Dawd Osman
Show more ...
10 030
56
ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆየቱ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም። በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። የፌስቡክ መተግበሪያዎች መቋረጥን ተከትሎ በትዊተር ፕላትፎርሙ ላይ ከፍተኛ የሆነ የተጠቃሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።
8 558
7
እጅግ በጣም የሚያሳዝኑት የወሎ ተፈናቃዎች ያሉበት አሳዝኝ ሁኔታ ከቦታው ከ Kila ጋር የተደረገ ቆይታ https://youtu.be/Mzx3xPqy7MY
እጅግ በጣም የሚያሳዝኑት የወሎ ተፈናቃዎች ያሉበት አሳዝኝ ሁኔታ ከቦታው ከ Kila ጋር የተደረገ ቆይታ
#ethiopia #malcolmxethio #amhara ##wello
8 407
2
ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል። በፌስቡክ ስር የሚገኙት መተግበሪያዎቹ በተለያዩ የዓለም ሀገራት መስራት አቁመዋል። ኢትዮጵያ ውስጥም አገልግሎቶቹ ተቋርጠዋል። መተግበሪያዎቹ በበርካታ አገራት መቋረጣቸውን ዓለም ዐቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቆጣጣሪ ተቋም ኔትብሎክስ አሳውቋል። ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ፌስቡክ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
7 873
28
8 940
4
ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ። ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሊ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
8 138
3
የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ በገዛ ፍቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸውን አሳወቁ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሳን ዐብዱላሂ መሐመድ በገዛ ፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን አሳውቀዋል። ወይዘሮ ፊልሳን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፉት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ፣ ሥራውን ከተቀበሉበት ወቅት ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ አንስተዋል። ሆኖም ሚኒስትሯ ሥነ ምግባርን የሚጥሱ ሁኔታዎች መተማመንን እንደሚጥሱ ከመጥቀስ ውጭ ሥራቸውን ለምን እንደለቀቁ በይፋ አልገለጹም። ወይዘሮ ፊልሳን ዐብዱላሂ መሐመድ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ከመጋቢት 3፣ 2012 ጀምሮ ነው። 🔴 መረጃው ያደረሰን Amba Digital - አምባ Amba Digital - አምባ ዲጂታል
12 989
23
#መሞትማ ሁሉም ነፍስ ይሞታል! ይህ ሰው የሞተው ግን ለአራት ወር የአላህን ቃል ለማሰማት ከሞቀው ቤቱ በራቀበት አላህ ቀርቦት ነው! 'ኹሩጅ' ላይ እያለ ድካም በቃህ እረፍ ተብሎ ነው! ኢላሂ! እንደዚህ ዓይነት ሞት! © tofiq bahru
12 018
25
#መሞትማ ሁሉም ነፍስ ይሞታል! ይህ ሰው የሞተው ግን ለአራት ወር የአላህን ቃል ለማሰማት ከሞቀው ቤቱ በራቀበት አላህ ቀርቦት ነው! 'ኹሩጅ' ላይ እያለ ድካም በቃህ እረፍ ተብሎ ነው! ኢላሂ! እንደዚህ ዓይነት ሞት! © tofiq bahru

IMG_20210925_231627_460.webp

1
0
#መሞትማ ሁሉም ነፍስ ይሞታል! ይህ ሰው የሞተው ግን ለአራት ወር የአላህን ቃል ለማሰማት ከሞቀው ቤቱ በራቀበት አላህ ቀርቦት ነው! 'ኹሩጅ' ላይ እያለ ድካም በቃህ እረፍ ተብሎ ነው! ኢላሂ! እንደዚህ ዓይነት ሞት! © tofiq bahru

IMG_20210925_231627_460.webp

1
0
አንደሉስ የቁርኣን ሂፍዝ ማዕከል ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎችን በዛሬው እለት በድምቀት አስመረቀ። በቄራ ሰላም መስጂድ ውስጥ የሚገኘው አንደሉስ መድረሳ ማዕከል በመጀመሪያ ዙር የአዳር የቁርአን ሂፍዝ ትምህርት ለ2 ተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች እንዲሁም በክረምት ኮርስ ለ1ወር የተማሩትን ተማሪዎች ታላላቅ አሊሞች፣ዳኢዎች፣ኡስታዞች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።
11 656
12
ታላቅ የሂፍዝ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም እሁድ መስከረም 09 /2014 ከጠዋቱ 3: 00 ጀምሮ በቄራ ሰላም መስጂድ ውስጥ የሚገኘው አንደሉስ መድረሳ ማዕከል በመጀመሪያ ዙር የአዳር የቁርአን ሂፍዝ ትምህርት ለ2 ተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች እንዲሁም በክረምት ኮርስ ለ1ወር የተማሩትን ተማሪዎች ታላላቅ አሊሞች፣ዳኢዎች፣ኡስታዞች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በድምቀት ያስመርቃል። በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
10 549
17
10 607
37
የቀጥታ ስርጭት #ሂጅራ ኢስላማዊ ባንክ የምረቃ ደማቅ ፕሮግራም https://youtu.be/bxjyFw2lJR8
የቀጥታ ስርጭት #ሂጅራ ኢስላማዊ ባንክ የምረቃ ደማቅ ፕሮግራም
9 451
11
በአማርኛ ተፅፎ ወደ ዐረብኛ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢስላማዊ የታሪክ መፅሃፍ። «ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ» የተሰኘውና የዛሬ አስር ዓመት ለሕትመት የበቃው የኡስታዝ አህመዲን ጀበል የታሪክ መጽሐፍ ወሂብ አብዱልዋሲ እና ሙክታር ከዋጃ በተሰኙ ግለሰቦች አማካኝነት ከአማርኛ ወደ አረብኛ ተተርጉሞ ለዐረብኛ አንባቢያን በኳታር ሀገር ዶሃ ለህትመት በቅቷል። መጽሐፉ ለጊዜው በኳታር ሀገር በሚገኘው በግዙፉ «ጀሪር የመጽሐፍት መደብር» ሦስቱ ቅርንጫፎች ዉስጥ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
14 869
24
«ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!» ✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳✴✳ የእስር ባልደረባዬ ወንድም ሙሐመድ አባተ ጠያቂያችን የነበሩት እናቱ አርፈዋል። አላህ በምህረቱ ይመልከታቸው። በትዕግስታችሁ አላህ ላንተና ለመላው ቤተሰባችሁ ታላቅ ምንዳን ይመንዳችሁ። ለሞቱት እናታችንም አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይለግሳቸው። መከራችሁንም አላህ በመልካም ሁኔታ ይለውጥላችሁ። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1028367904668415&id=100024856459321
11 290
8
አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። ✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳ የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ። በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000427892232 ይማም አህመድ ኢስማዒል ይስማው ሙሐመድ ተስፋዬ
11 796
15
11 972
19
የመሀመድ አወል ሳላህ የቀብር ስነ ሰርአት በቀጥታ ከኮልፌ አላህ ይዘንለት https://youtu.be/sK73rHtH2go
የመሀመድ ሰላህ የቀብር ስነሰርአት በቀጥታ ከኮልፌ አላህ ይዘንለት
10 412
21
አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። Share በማድረግ ያሰራጩ የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ ልጆች ልጆቻችን ናቸው። ቤተሰቦቹ ቤተሰቦቻችን ናቸው። እርሱን ማጣት ሃዘኑ ከባድ ነው። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ። በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000427892232 ይማም አህመድ ኢስማዒል ይስማው ሙሐመድ ተስፋዬ
13 445
73
ኢና ሊላሂ ወ ኢነ ኢለይሂ ራጅዑን ተወዳጁ መሀመድ አወል ሳላህ ወደ አኼራ ሄደ አላህ ለሱ ጀነተል ፍርዶስን ለቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን ሁላችንም ዱአ እናድርግለት ዙህር ላይ በኮልፌ መካነ መቃብር ሁላችንም እንገኝ አላህ ይዘንለት ያረቢቢ
11 786
93
አስደሳች ዜና ታሊባን እነ አሜሪካን በጦርነት በማሸነፍ አፍጋኒስታንን ኢስላማዊ መንግስት ስር ተቆጣጠረች አላሁ አክበር https://youtu.be/JHcqttMTgkE
አስደሳች ዜና ታሊባን እነ አሜሪካን በጦርነት በማሸነፍ አፍጋኒስታንን ኢስላማዊ መንግስት ስር ተቆጣጠረች አላሁ አክበር
#Ethiopia #Malcolmxethio
14 129
19
ሰበር ዜና መጅሊስ የመጅሊሱን ህንፃና መሬቶች የነጃሺ የመስጂድና የምርምር ተቋም እነረዲሁም አዲስ የተሰራውን የመጅሊስ ህንፃ ከታለመለት አላማ ውጪ ሸንሽኖ በሕገ ወጥ መልኩ ለማከራየት እየተሰራ መሆኑ ታወቀ ለመጅሊሱ ለውጥ ክሽፈት ሲታትሩ የነበሩት ግለሰቦች እውነተኛ አላማ መጋለጥ ጀምሯል! የመጅሊሱ ፀረ ለውጥ ሀይሎች አላማ አልፋና ኦሜጋ የሙስሊሙን ተቋም መዝረፍ እና ትኩረታቸው ሁሉ የጥቂት ግልሰቦችን ጥቅም ማስጠበቅ እንደነበረ የሥራ አመራር ቦርዱ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል። በተለይም በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ ለወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ሙሉ ትኩረቱን ሰጥቶ ባለበት ወቅት ለህገወጥ ሥራዎቻቸው ህዝቡ ስለሚዘናጋ ያመቸናል በሚል የመጅሊሱን ህንፃና መሬቶች ከታለመለት አላማ ውጭ ለመጠቀም በይፋ ማስታወቂያ አውጥተው ተከራዮችን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኙ የሥራ አመራር ቦርዱ ደርሶበታል። እነዚህ ህገ ወጥ ግለሰቦች የዋና ግቢ አዲሱን ህንፃ ከታለመለት የመጅሊሱ ህዝባዊ አገልግሎት በተቃራኒ በረጅም ጊዜ ኪራይ ገንዘብ ለተለያዩ የግል ጥቅማጥቅሞች ክፍያ ለማዋል በእንቅሰቃሴ ላይ ይገኛሉ። ይባስ ብሎም የነጃሺ አለም አቀፍ የመስጊድና የምርምር ተቋም ቦታ ለታለመው ግንባታ የቀረበውን የ60 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አንቀበልም በማለት ከመለሱ በኋላ አሁን ግቢውን በጥቃቅን ሱቆች ሸንሽኖ ለረጅም አመታት ለማከራየት እየተሞከረ ይገኛል። በዚህ ቦታ ላይ የይገባኛል ክርክር ካስነሱት ኃይሎች ግፊት በተጨማሪ ቦታው በመንግስት የተሰጠው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ግንባታ እንዲገነባበት ካልሆነ መልሶ ለመቀማት ከማስጠንቀቂያ ጭምር ጋር እንደነበር ይታወሳል። በመሆኑም አሁን የተያዘው የኪራይ ሰብሳቢነት ሂደት ከተሳካ ከቦታው ቅንጥብጣቢ ለመሰብሰብ በረጅም ጊዜ ውል የግንባታውን ሂደት እንዳይሳካ በማድረግ የሙስሊሙን ህልም ማጨለም ይሆናል። በዚህ ሂደት እንደ ከዚህ ቀደሙ የመጅሊስ አመራር የመጅሊሱን ንብረቶች በመሸጥ እና በማከራየት የግል ጥቅሞችን በማጋበስ ህዝቡ ገፍቶ "ተቋሜን" ብሎ ሲጠይቅ ያለምንም ተጠያቂነት ዞር ለማለት እንደታሰበ ያሳያል። ስለሆነም ከላይ የተገለፀው የህንፃ እና ቦታ ኪራይ ውሳኔ በህገ ወጥ አካላት የተላለፈ የህዝቡን ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ ተግባር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። በተጨማሪም ይህን የቀረበውን ህገወጥ የኪራይ ማስታወቂያ ተከትሎ ነገ በህግ ሊያስጠይቅ ስለሚችል ማንም ወገን የገዛ ገንዘቡን እንዳያባክን እና የህዝበ ሙስሊሙ ሀብት ምዝበራ ላይ እንዳይሳተፍ የሥራ አመራር ቦርዱ በጥብቅ ያሳስባል። ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን በተከታታይ የምናጋራ ይሆናል።
Show more ...
17 724
24
12 452
2
በደሴ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ ================ የደሴ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋ ሕዝብ “ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባለ” የሰዓት እላፊ አዋጅ መጣሉን አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ፍቃድ ከተሰጣቸው የጸጥታ አካላት ውጪ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ማድረግ ተከልክሏል ብሏል። የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ደግሞ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን የከተማዋ አስተዳደርን በመጥቀስ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል። ከሰሞኑ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን ግጭት በመሸሽ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ወደ ደሴ ተፈናቅሎ እየገባ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል። የከተማ አስተዳደሩም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሐይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሠራት ላይ እገኛለሁ ብሏል።
Show more ...
15 566
28
የሳውዲ መንግስት ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በሚስኪን ስደተኛ ኢትዮጲኖች ላይ ለምን ይፍፅማል ? ረሱል እንኳን ዱአ ያረገላት ሀገር እኮ ናት ሀበሻ https://youtu.be/0prvHWw9ZFA
የሳውዲ መንግስት ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በሚስኪን ስደተኛ ኢትዮጲኖች ላይ ለምን ይፍፅማል ? ረሱል እንኳን ዱአ ያረገላት ሀገር እኮ ናት ሀበሻ
#Ethiopia #Malcolmxethio #Saudiethio
12 327
16
ሀገር አጣብቅኝ ውስጥ ባለችበት ሙፍቲ ዛሬም ህዝበ ሙስሊሙን ወደ አመፅ ሚያሰገባ ተግባር እየፈፀሙ ነው ሰበር ዜና *** ከለዉጡ በኋላ የተባረሩት በአዲስ አበባ 10ሩም ክፍለ ከተሞች የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራሮች ዳግም ወደቦታቸው እንዲመለሱ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር በደብዳቤ ጠየቁ! ------- RN05 . ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የቀድሞ ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ጋሻ-ጃግሬዎች የነበሩ እና በሙስሊሙ ላይ ተጭነው ለዛ ሁሉ ግፍ እና መከራ ተባባሪ የነበሩ ለዉጡ ሲመጣ ምንም ሳይጠየቁ ከስልጣናቸው ብቻ እንዲወርዱ ከተደረጉት መሃል ከነበሩት ዉስጥ የአዲስ አበባ መጅሊስ የአስሩም ክፍለከተሞች የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ቀድሞ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ መጻፋቸውን የሚገልጽ መረጃ ደርሶናል ። . በአንድ በኩል "ህዝባዊ መጅሊስ ለማቁቋም ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር አብሬ እየሰራሁ ነው" የሚሉት ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዘዳንት የሸህ ሱልጣን አማንን ደብዳቤ በመሻር የቀድሞው አህባሽ መራሽና ህዝበ ሙስሊሙን ለበርካታ ስቃዮችና እንግልቶች ያበቃው መጅሊስ ወደ ስልጣን እንዲመለስ መወሰናቸውን እና ለዚሁም እየሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
Show more ...
18 406
46
14 919
9
12 342
8
አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ አክበር ላኢላሀኢልለላህ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ 🙏 አላሁ አክበር ከቢራ ወልሐምዱሊላሂ ከሲራ ወሱብሐነላሂ ቡክረተን ወአሲላ ላኢላሀኢልለላሁ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ ☝️ ዱዓችንን አላህ ይቀበለን!🤲 ዒዱኩም ሙባረክ 🕋🎈🎊 ያማረ
13 163
68
ነገ ሰኞ ሀምሌ 12/2013 የዐረፋ ቀን ነው። ★★★★★★★★★★★★★★ ★ T.me/ahmedin99 🔴 የአላህ መልክተኛ [ﷺ] «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢአት ያስምራል።» ብለዋል። ሙስሊም ዘግበውታል። ኢማም አል—ሙናዊ [ረሒ] እንዲህ ብለዋል: ‐ ገና ያልተከሰተውን «የመጪውን ዓመት ኃጢኣት» ያስምራል ሲባል ምን ማለት ነው?: — ❶ በመጪው ዓመት ከኃጢኣት ይጠብቀዋል ማለት ነው። ❷ ለመጪው ዓመት ኃጢኣቱ ማሰረዣ የሚሆን ምንዳ ይሰጠዋል ማለት ነው። ወይም ❸ ሰውየው በህይወት ቆይቶ ኃጢኣት ቢሰራ እንኳን ይሰረዝለታል ማለት ነው።» ፈይዱል ቀዲር ቅፅ 4፣ ገፅ 230 መልዕክቱን ለሌሎች በማጋራት ሌሎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምክንያት እንሁን።
18 000
157
🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ - ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣ - ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡ 1- ልብሴን ያወልቃሉ፣ 2- ያጥቡኛል፣ 3- ይከፍኑኛል፣ 4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣ 5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣ 6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣ 7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡ ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡ 8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል - ቁልፎቼ 🔑🗝 - መጽሐፎቼ 📚 - ጫማዎቼ 👟 - ልብሦቼ 👖👔….. በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ - በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣ - የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣ - የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣ - በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣ - ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣ - ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤ - ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል - ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤ ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! … በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ 1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ 2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣ 3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣ የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!! 1- መልክህ፣ 2- ሀብትህ፣ 4- ጤናህ፣ 5- ልጅህ፣ 6- ቪላህ፣ 7- ዝናህ፣ 8- ሚስትህ/ባልሽ ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡ እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ 1- በግዴታዎች፣ 2- በሱንና ነገሮች፣ 3- በድብቅ መፅውት፣ 4- መልካም ሥራ አብዛ፣ 5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣ ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡ መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡ ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ሼር ሼር .....✔️
Show more ...
26 285
559
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን የደሴ ከተማ እውቅ አሊም የነበሩት ሼይኽ ሙሀመድ አብዱል ከሪም ወደ አኼራ ሄዱ ሼይኽ መሐመድ ከልጅነታችን ጀምሮ ስናውቃቸው ቤታቸው በኪታቦች የተሞላ ነበር:: በደሴ ከተማ እንደሳቸው በርካታ ኪታቦች የነበረው አሊም የነበረ አይመስለኝም:: ህይወታቸውን ከሀዲስ እና ኪታብ ጋር አሳልፈው ነው ያለፉት:: ህዝባቸውን በኢማምነት እንዲሁም ኪታብ ሲያቀሩ እና ሲያስተምሩ ለብዙ አመት ካገለገሉ ቡኃላ በሳኡዲ አረቢያ ኑሯቸውን አድርገው እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ እዛው ቆይታ አድርገዋል:: በተመሳሳይም የእድሜ ባለፀጋ የነበሩት የመናዊው ታላቅ አሊም ሼይኽ መሐመድ እስማኤል አል አምራኒ ወደ አኼራ ሄደዋል:: እኚህ አሊም የየመን ሙፍቲ፣ቃዲዕ እና ታላቅ ሙሐዲስ ነበሩ:: አልጀዚራ ስለሳቸው ህልፈት የሚከተለውን ጥንቅር አዘጋጅቶ አቅርቧል https://www.facebook.com/aljazeerachannel/videos/177253057768676/ ከቂያማ ምልክቶች መካከል የኢልም መነሳት አንዱ ነው:: ኢልም የሚነሳውም በአሊሞች ሞት ነው:: እነዚህን የመሳሰሉ አሊሞቻችንን በሞት ማጣት ለኡማው ትልቅ ኪሳራ ነው:: ለሞቱብን አሊሞች አላህ ይማራቸዉ። ቤተሰቦቻቸዉን ሶብር ይስጥልን። ለኡማውም ምትክ አሊሞችን አላህ ያውጣልን
Show more ...
11 406
11
ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ አስሩ የዙል ሒጃህ ውድ ቀናት እሁድ እንደሚጀምር ታወቀ አላህ ይቀበለን ከሚጶሙት ያድርገን
17 991
53
20 348
26
አስደሳች ሰበር ዜና •በትግራይ የሚደረገው ጦርነት ለጊዜው መቆሞ ተነገረ መከላከያ መቀሌን ለቆ ወጣቷል አልሃምዱሊላህ https://youtu.be/qT-MArZsnRE
አስደሳች ሰበር ዜና •በትግራይ የሚደረገው ጦርነት ለጊዜው መቆሞ ተነገረ መከላከያ መቀሌን ለቆ ወጣቷል አልሃምዱሊላህ
#Ethiopia #Mekele #Tigray #Malcolmxethio
20 746
27
ሰበር አስቸኳይ ሼር || በሳውዲ እስር ቤት ለሚሰቃዩ ወገኖች አፋጣኝ እርዳታ እናድርግ ኢምባሲ በመሄድ እናድርግላቸው አሰራ ኢጋማ ያላቹ ብቻ ሂዱ https://youtu.be/pEmTc8Fydlg
ሰበር አስቸኳይ ሼር || በሳውዲ እስር ቤት ለሚሰቃዩ ወገኖች አፋጣኝ እርዳታ እናድርግ ኢምባሲ በመሄድ እናድርግላቸው አሰራ ኢጋማ ያላቹ ብቻ ሂዱ
#Ethiopia #Malcolmxethio #SaudiArebia
14 688
20
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በርካታ የጅማ ህዝብ እንደመረጠው ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ጀበሉ አልሳተፍም ቢልም ስሙ አልተሰረዘም ነበር https://youtu.be/dO1VO_A6ZJg
ሰበር ዜና •ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በርካታ የጅማ ህዝብ እንደመረጠው ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ጀበሉ አልሳተፍም ቢልም ስሙ አልተሰረዘም ነበር
#Ethiopia #Malcolmxethio #AhmdinJebel
15 167
10
የአለማችን ከዋክብት ተጫዋቾች የቅንጦት ሽርሽር በሚያደርጉበት በዚህ ሰዓት ፣ ሳዲዮ ማኔ በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ በሴኔጋል የደሀ መንደሮች ከጓደኞቹ ጋር ማንጎ እየበላ ነው ፡፡ ቀላልነት በተሻለ ምርጥ ያደርግሀል ፣ ማኔ፣
13 122
27
ጀግናው ቦታውን አግኝቷል ገና ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል አሰደሳች ዜና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩነት የግል ተወዳዳሪ በሆነበት፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በኢሉ አባቦራ ዞን፣ በመቱ ወረዳ ለፓርላማ አሸናፊ ሆኗል።
12 443
28
በሳዑዲ ዓረቢያ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የሚወያይ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ወደ ሀገሪቱ አቀና በሳዑዲ ዓረቢያ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የሚወያይ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ወደ ሀገሪቱ ማቅናቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ጋር ለመነጋገር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተወጣጣ የልዑካን ቡድን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሄዷል። የልዑካን ቡድኑ ሰነድ አልባ የሆኑ እና ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚፈልጉ ዜጎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። በልዑካን ቡድኑ እና ከሳዑዲ ዓረቢያ ባለሥልጣናት መካከል በሚደረገው ውይይት መነሻነት በርከት ያሉ ተመላሾች የኮሮና በሽታን ፕሮቶኮል በጠበቀ መልኩ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ይጠበቃል ተብሏል። በሁለቱም ወገን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ዘንድ ጉዳዩ በቅርበት ክትትል የሚደረግበት ይሆናል። በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለማቃለል እና በክብር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ትብብር በጣም አስፈላጊ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት አስታውቋል። ከውይይቱ የሚገኘው ውጤት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር አንዱ ማሳያ እንደሚሆን ነው የተገለጸው። ETV
Show more ...
15 032
26
ስለ ሳውዲ ወገኖች ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ያጣራውት ያለው እውነተኛ መረጃ || ዝምታውን ሰብሯል || https://youtu.be/zR6ZsW_7Vao
ሰበር መረጃ • ስለ ሳውዲ ወገኖች ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ያጣራውት ያለው እውነተኛ መረጃ || ዝምታውን ሰብሯል ||
#Ethiopia #Malcolmxethio
12 166
7
አስደሳች ዜና• ሼኽ አላሙዲን የአፋሩን መስጂድ እስከ 200 ሚሊዮን የሚፈጀውን እንደሚያሰሩ ተናገሩ || ስለ ሳውዲው መረጃ ይዘናል || ይከታተሉ https://youtu.be/_NbZcUP5FEU
አስደሳች ዜና• ሼኽ አላሙዲን የአፋሩን መስጂድ እስከ 200 ሚሊዮን የሚፈጀውን እንደሚያሰሩ ተናገሩ || ስለ ሳውዲው መረጃ ይዘናል ||
#Ethiopia #Malcolmxethio #ሼኽአላሙዲን #Alamudin
12 159
7
ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ የአሳይታውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ቃል ገቡ ………………… በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ አማካኝነት ለአፋር ህዝብ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ታላቁን የሱልጣን አሊ ሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል እና ሌሎች የልማት ስራዎች አስገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ ተገብቶ የነበረ ቢሆንም እውቁ የሃገራችን ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ብዙ ገንዘባቸውን ውጪ ካደረጉ ቡኃላ በፖለቲካ አሻጥር ምክንያት በክልሉ እያካሄዱ ከነበሩት በርካታ የልማት ስራዎች ተገፍተው እንዲወጡ በማድረግ እና የዚህን ፕሮጀክት ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆሙ በመግፋት ግንባታው እና የልማት ስራዎች እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል:: ሼይኽ መሐመድ በክልሉ በርካታ ኢንቨስትመንት እና የልማት ስራዎች በመስራት ህዝባቸውን እና መላው ሃገራቸውን ለመጥቀም ብዙ ቢንቀሳቀሱም በቀድሞ ስርኣት ከክልሉ ከሁሉም የልማት እንቅስቃሴያቸው ሙሉ ለሙሉ ተገፍተው እንዲወጡ ተደርገዋል:: ለሁለት አስርት አመታት ግንባታው የቆመው እና እሳቸው ያስጀመሩት ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ዳግም ተጠናቆ ህዝቡን እና ሃገርን እንዲጠቅም ለማስቻል እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ሲሆን ከቀናት በፊትም ተቋሙ በሚገኝበት አሳይታ ከተማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል እርሱን ጨምሮ የተለያዩ ታላላቅ ኡለሞች፣ዱዓቶች እና የክልል መጅሊስ አመራሮች የተካፈሉበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሂዷል:: በዚህ ፕሮግራም ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ ፕሮጀክቱን ላስጀመሩት እና ከክልሉ በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ለተደረጉት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ በይፋ ወደ ክልሉ ተመልሰው ለህዝባቸው ማድረግ የሚፈልጉትን የልማት ስራዎች ሁሉ ይሰሩ ዘንድ ሁኔታዎችን በሙሉ እንደሚያስተካክሉ ቃል በመግባት ጥሪ አድርገውላቸዋል:: ይህን ለአፋር ህዝብ እና ለሃገር የሚጠቅም ግዙፍ ተቋም የተፈጠሩ ችግሮችን በማስተካከል ዳግም ግንባታው ይጠናቀቅ ዘንድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ የቀረበላቸው ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ምንም እንኳን ከበርካታ የልማት ስራዎቻቸው በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ቢደረጉም ለህዝባቸው እና ለሃገራቸው ካላቸው ፍቅር እና መልካም እሳቤ የተነሳ የቀረበላቸው ጥሪ በመቀበል ፕሮጀክቱን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ ቃል መግባታቸውን በተወካያቸው አማካኝነት አሳውቀውኛል:: አልሐምዱሊሏህ እኚህ ታላቅ ሃገር ወዳድ ባለሃብት ሃገራቸውም እና ህዝባቸውን ለመጥቀም ለልማት ሥራዎች ብዙ ገንዘባቸውን አፍስሰው በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ቢደረጉም ከህዝባቸው እና ሃገራቸው የሚበልጥባቸው ምንም እንደሌለ በማስመስከር ይህን ታላቅ ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ቃል በመግባታቸው በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ የህዝቡን ጥሪ ለሳቸው በማድረስ እና ሁኔታዎች እንዲመቻቹ በማድረግ ትልቁን ሚና ለተጫወተው ለሳቸው ተወካይ ወንድም ጀማል አህመድም ምስጋናዬ የላቀ ነው:: ወንድም ጀማል ሃገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችንም ሆነ ሌሎች ኸይር ስራዎችን እሳቸው እንዲሳተፉበት በማድረግም ሆነ በግሉም በርካታ የኸይር ስራዎችን በመስራት ለማህበረሰቡም ለሃገርም ትልቅ አስተዋፅኦ እና ድጋፍ እያበረከተ ያለ ሃገር ወዳድ ወንድማችን ነው:: ሼይኽ መሐመድ አል አሙዲ ወደሚወዱት ሃገራቸው አላህ በሰላም እንዲመልሳቸው፣ መልካም ስራቸውን ሁሉ አላህ እንዲቀበላቸው፣ ለሃገራቸው እና ለህዝባቸውም ብዙ ማድረግ የሚፈልጉትን መልካም ስራ ሁሉ ለመስራት ይችሉ ዘንድ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይወፍቃቸው ዘንድ ዱዓዬ ነው:: በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ላገዘን እና በርካታ የኸይር ስራዎች ላይ እየተሳተፈ ለሚገኘው የሳቸው ተወካይ ለሆነው ወንድም ጀማል አህመድም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው! ©ኡስታዝ አቡበክር አህመድ
Show more ...
11 683
18
9 073
3
በተጨማሪም የዶች ቨሌ ዘገባ እንዲህ ይላል በሳዑዲ ዓረቢያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ መንግሥት የፀጥታ ኃይላት ከፍተኛ ወከባ፣ እስር እና ዝርፊያ እየደረሰባቸው ነው። የሳዑዲ ዓረቢያ የጸጥታ ኃይላት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ቤቶች እየዘረፉ ለእስር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን የችግሩ ሰለባ ኢትዮጵያውያን ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። ቃላቸውን ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል ለ8 ዓመት በጅዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ካልድ ሲራጅ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳላቸው እየተናገሩ ከባለቤታቸው እና ሁለት ልጆቻቸው ጋር ለ3 ቀን ታስረው መፈታታቸውን ገልጸዋል። አቶ ካሊድ፥"ቀጥታ መጡ፤ ልክ ከዝሁር በኋላ ከምሳ ሰአት በኋላ መጡ፤ ሰበሩ። ኢቃማ [ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ] አለን እያልናቸው እንኳን ሊሰሙን አልቻሉም፤...ተንጋግተው መጥተው ነው ቤቱን ሰብረው የገቡት" ብለዋል። ከትናንትና ወዲያ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ የጸጥታ ኃይላቱ "ሀበሻ" የሚሏቸውን ኢትዮጵያውያን ማሰርና ቤቶቻቸውን መስበር መቀጠላቸውን ነዋሪዎች አመልክተዋል። አቶ አሕመድ ሁሴን የተባሉ ነዋሪ ደግሞ ወከባ፣እስርና ዝርፊያው መቀጠሉን ተናግረዋል። «ተደበደበ፤ኅብረተሰቡ ንብረቱን ተወረሰ። ምነው ሂዱ ከተባልን ንብረታችንን እንኳን ይዘን ብንሄድ ? እንኳን የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የመኖሪያ ፈቃድ ያለንም ብንሆን ወደ ሀገራችሁ ግቡ ብንባል በሰላም ብንገባ ምንአለበት እና ኅብረተሰቡ ተዘረፈ እያልን አሁንም ኤምባሲ እየደወልን እየተናገርን ነው" ብለዋል። አክለውም፥ "ሰሞኑን በሐበሻ ላይ የሚሠራው ሥራ ያለአግባብ ነው፤ ይመጣሉ ፤ ቤት ይሰብራሉ፤ሰብረው ሰዉን ይወስዳሉ ፤ ከዚያ ተከትሎ ወጣቱ ተከትሎ እየገባ ኅብረተሰቡ ተዘርፏል" ሲሉ ገልፀዋል።
Show more ...
10 173
16
በ11ኛ ሰአት ለምን ከምርጫህ እራስህን አገለልክ? ከአህመዲን ጀበል ጋር የተደረገ ቆይታ https://youtu.be/G22z5D_r5s8 https://youtu.be/G22z5D_r5s8
ሰበር ዜና ጀግናው አህመዲን ጀበሉ በምርጫው እንደማይሳተፍ ተናገረ ከአህመዲን ጋር የተደረገ ልዩ ቆይታ ይከታተሉ
#Ethiopia #Malcolmxethio #AhmedinJebel
12 608
26
አስደሳች ዜና በአፋር ታሪክ ተሰራ አላሁ አክበር ለአሊ ሚራህ መስጂድ ግንባታ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ https://youtu.be/Oknvva9f_pA
አስደሳች ዜና በአፋር ታሪክ ተሰራ አላሁ አክበር ለአሊ ሚራህ መስጂድ ግንባታ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ
#Ethiopia #Malcolmxethio #Afar #AfarMuslim
14 057
6
የአፉር ክልል ፕሬዝዳንት ስለ ዛሬ በአሳይታ ካሉት **** «እዚህ ፊት ለፊቴ(በድምፃችን ይሰማ ጊዜ) የተፈተኑ ሰዎች ይታዮኛል። ፈተና ደግሞ ሰነፉንና ጎነዙን ይለይልናል ......ፈተና ባይኖር ሁሉም ጀግና ነኝ እያለ ይፎክር ነበር። (ሙስሊም ውስጥም)» አቶ አወል አርባ የ/አ/ክ/መ ፕሬዝዳንት
13 490
9
ሼህ ሰዒድ ያሲን በካሽ 1,000,000 ሚሊዮን ብር ኡስታዝ አቡበከር አህመድና ባለቤቱ ሀናን በድምሩ 200,000 ብር ሱልጣን አሊሚራህ መድረሳ ግንባታ የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር #አሳይታ
11 159
7
አስደሳች ዜና ለረዥም አመታት ሲጠበቅ የነበረው የመጀመሪያው ኢስላማዊ ዘምዘም ባንክ ዛሬ የመክፈቻ ስነ ስርዐቱን በይፋ ያደርጋል!! __________________________ ለዘመናት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዘምዘም ባንክ ለሐገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን አገልግሎት መጀመሩን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ባንኩ የሸሪአን መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አገልግሎቱንም የሚሰጡት በባንክ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላቸው ስመጥር ባለሞያዎች ናቸው፡፡ የኮር ባንኪነግ ሲስተማችን አጅግ ዘመናዊ ሲሆን በሲስተም አቅራቢዎችና በሸሪአ ባለሞያዎች በኩል ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው ነው፡፡ እንኳን ደስ አላቹህ #ዘምዘምባንክ #ZemzemBank #ባንክ #ኢትዮጲያ #Ethiopia
17 089
52
አስደሳች ዜና • እንኳን ደስ አላቹህ ለበርካታ አመታት ሲጠበቅ የነበረው ዘምዘም ኢስላማዊ ባንክ ከነገ ጀምሮ ስራ እንደሚጀምር ታወቀ አልሃምዱሊላህhttps://youtu.be/nRjwpb1dt28
አስደሳች ዜና • እንኳን ደስ አላቹህ ለበርካታ አመታት ሲጠበቅ የነበረው ዘምዘም ኢስላማዊ ባንክ ከነገ ጀምሮ ስራ እንደሚጀምር ታወቀ አልሃምዱሊላህ
#Ethiopia #Malcolmxethio #ZemZemBank
15 497
10
Last updated: 27.11.21
Privacy Policy