cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ELOHIM LIFE CHANNEL(ELC)

ይሄ የክርስቲያን ቻናል የተከፈተበት አላማ ክርስቲያኖችን ላቅ ወዳለና ተጽዕኖ ወደሚፈጥር ሕይወት ለማምጣት ነው።በዚህ ቻናል ውስጥ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። ከእነዚህም ውስጥ ፦የአዕማድ ሰዎች ንግግሮች ፦ከታማኝ ምንጭ የተገኙ ዜናዎች ፦የድሮም የአሁንም አዳዲስ ዝማሬዎች ፦ህይወት ለዋጭ፣የሚያንጽ ስብከቶችና ትምህርቶች ስነጽሁፎች፣ታሪክና ምሳሌዎች። https://youtu.be/-bmaoih

Show more
Advertising posts
409Subscribers
No data24 hours
-27 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"150 አመት እኖራለው" ማይክል ጃክሰን በንድ ወቅት ይህን ተናግሮ ነበር። 75አመታትን የአለም ህዝብን በተሰጥኦው የማዝናናት እና ቀሪው ግማሹን 75 አመታት ደግሞ ፈጣሪውን በማገልገል ለመኖር አስቦ ነበር። ይህንንም ለማሳካት ሲል የሚመገባቸውን ምግቦች ጤናማ ማድረግ  እና በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ንፁህ አየር እንዲኖር በማሰብ Oxygen Bag በተባለ ድንኳን መሰል አልጋ ውስጥ ይተኛ ነበር።ለዚህም እጅግ በጣም በርካታ ዶላሮችን አፍስሶ ነበር። ነገር ግን ምን ይደረጋል በፈጣሪ እቅድ ነው እምንኖረው እና እ.ኤ.አ. በ2009 ከሚወደው ስራው እና 150 አመታትን እኖርባታለው ብሎ ያሰባትን አለም 50አመታትን ኖሮ ላይመለስ ተሰናበታት። ---------------------------------------//----------------------------------- ለየትኛው እድሜ ነው ምናቅደው? ስለነገ እናቅዳለን እንጂ ነገ ምን እንደምንሆን አናውቅም።ስለዚህ ባለን ነገርና በተሰጠን ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር እንኑር።አንደፈለግን ኖረን በመጨረሻ ጌታን ማሰብ ሳይሆን በጉብዝና ወራት፣ወቅት ሁሉን ነገር ማድረግ በምንችልበት ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠንን ስራ ለነገ ብለን ሳይሆን ቀን ሳለ ማድረግ ሚገባንን እናድርግ። ነፍሴ ወደአምላኳ ስጋም ወደአፈሩ ሣይመለስ ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
3
🔴🔴🔴SECURITY ALERT⚠️⚠️⚠️⚠️ ቴሌግራማቹን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ!!! 🔺ቴሌግራም ላይ ከማንኛውም ሰው በ cutt.ly ወይም bit.ly የሚጀምር ማንኛውም ሊንክ ተልኮላችሁ ስታገኙ እንዳትከፍቱት ምክንያቱም ሰሞኑን የመጣ ቫይረስ አለ ሙሉ ለሙሉ የተፃፃፋችሁትን እና Join ያደረጋችሁትን ቻናሎች ሁሉ ያጠፋውና እንደ አዲስ ነው አካውንት ክፈቱ የሚላቹ ይሔ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው ። 🔺እንደዚህ ዓይነት ሊንኮች በምታውቋቸው ሰዎች ስም ጭምር ሊላክላችሁ ይችላል ነገር ግን በጭራሽ እንዳትከፍቱ። 🔺በተጨማሪም ከሀከሮች አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት Password Two-Step Verification On አድርጉ! #TIKVAH @ELOHIMLIFECHANNEL
Show all...
#short teachings#1 አብርሃም ልጅ ፈለገና እግዚአብሔር ሕዝብ ሰጠው።ዛሬ የእግዚአብሔር በረከት ለአንተ አን ከጠበቅከውና ከፈለግከው በላይ ነውና ከሚሰጥህ ነገር በላይ እርሱን እያየህ እርሱን ጠብቅ። እግዚአብሔርን ስትታገስና ስትጠብቅ ከምታስበውና ከምትጠብቀው በላይ ይሰጥሃል።እግዚአብሔር ሊመልስልህ ያለውን ነገር ያዘገየው እርሱን እንድታይና እንድትጠብቅ ነው።እርሱን ስትፈልግ የምትፈልገው ነገር ይከተልሃል።እግዚአብሔርን መጠበቅ ዋጋ ቢያስከፍልም ለጠበቅከው መጠበቅና መታገስ ግን ብድራት/ዋጋ/ አለው። አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው ለታገሰ ሰው ጸጋ ላስቻለው አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም #share @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
የአዕማድ ሰዎች ንግግር "በሉቃስ ወንጌል ላይ ሳታቋርጡ ስበኩ ሳይሆን ሳታቋርጡ ጸልዩ ነው የሚለው።ለመስበክ ብዙ አስቸጋሪ አይደለም፣በምትጸልዩበት ጊዜ ግን በገለልተኛ ስፍራ ላይ ከጨለማ ኃይላት ጋር የውጊያን ጸሎት እየተፋለማችሁ ነው።ያን ጊዜ ድል የማድረግ ምስጢር በሚገባ ምን እንደሆነ ትረዳላችሁ።" -ኢቫን ሮበርትስ #share @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
"አንተ ጣት ነህ" አንድ ጊዜ አንድ ወጣት ላልተለወጠና ንስሀ ገብቶ ስለማይመለስ ጎረቤቱ እንዲህ እያለ ይጸልያል "ጌታ ሆይ እባክህ በጣትህ ንካው !" እያለ ይጸልያል።ጌታ እስከሚናገረው ድረስ ይሄንን ጸሎት ይደጋግማል። በመጨረሻም ጌታ ተናገረው "አንተ የእግዚአብሔር ጣት ነህ።ባልንጀራህን ጠርተኸው ስለ መዳን አንዲት ቃል ነግረኸው ታውቃለህ? አሁን ሂድና ጎረቤትህን ጥራውና ንገረው እናም ጸሎትህ ምላሽ ያገኛል።"አለው።ይሄም የእግዚአብሔር አገልጋይ ራሱን ኰነነ ከተንበረከከበት ተነሣ። "እንግዲህ እድል ባገኘን መጠን ለሰው ሁሉ መልካም እናድርግ።" አያችሁ ወገኖቼ አንዳንድ ጊዜ ምንጸልየውን አናውቅም።እግዚአብሔር የሆነ ሰው የጸሎት መልስ አድርጎ አስቀምጦን እኛ ግን ሌላ አካል መልስ እንደሆንን እንዲነግረን እንጠብቃለን።አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ድሆችን እንዲባርክ እንጠብቃለን ነገር ግን እግዚአብሔር ድሆችን ሚባርከው በእኛ ነው።የማይታየው እግዚአብሔር በምንታየው በእኛ ውስጥ በረከትን፣ወንጌልን፣የሚበዛን ነገር አስቀምጧል።ከዛሬ ጀምሮ ጌታን አንድ ነገር እንጠይቅ እኔ ለማን አስፈልጋለው?እግዚአብሔር ከሚመልስልን መልስ ጋር ደግሞ እንቁም እንነሳና አድርጉ ያለንን እናድርግ።እኛ የእግዚአብሔር ጣት ነን፣እርሱ በእኛ ሚሰራው ስራ አለ።እንወቅ፣እንነሳ፣እንስራ ! #share @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
👍 1
Show all...
Jesus Saves the little Children | Addis Ababa, Ethiopia Evangelism w/ Apostle David Lynn

Welcome to Christ's Forgiveness Ministries. To learn more about the ministry, get involved, or to donate, visit our ministry website:

https://christsforgiveness.com

To support or donate to the ministry:

https://bit.ly/3gaGMUZ

FOLLOW US: Facebook:

https://www.facebook.com/ChristsForgivenessMinistries/

Instagram:

https://instagram.com/davidlynnofficial

Email us at: [email protected] Subscribe For More:

https://bit.ly/christsforgiveness

#christsforgiveness #evangelism #davidlynn

ክርስትናና እስልምና አንድ ጊዜ ጳጳስ ፍሮድሻም ሚባሉ ሰው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ:- “በብዙ የዓለም ክፍሎች ለክርስትና ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ሰር ዊልያም ማክግሪጎር ጋር በአንድ ወቅት በምዕራብ አፍሪካ ስላለው የእስልምና እምነት ፈጣን እድገት ተወያየን። ክርስትና፡ ‘ይህ ብቻ ነው፡ እያንዳንዱ ሙስሊም ራሱን እንደ ሚሲዮናዊ አድርጎ ይቆጥራል፡ አብዛኛው ክርስቲያኖች ግን የሌላ ሰው ስራ ነው ብለው ያስባሉ።"ብለው አሉ። እውነት ነው በዚህ ዘመን ክርስቲያኑም አለማዊ አለማዊውም ክርስትያን መስሎ የሚታይበት ድብልቅልቆሹ የበዛበት ዘመን ነው።እስልምና ውስጥ ከአለባበስ ጀምሮ እስላም መሆናቸውን የሚገለጹ ብዙ ነገሮች ያደርጋሉ።ያም ብቻ አይደለም ዊልያም ማክግሪጎር እንዳሉት እስላሞች እራሳቸውን እንደሚሲዮናዊ ወይም እስልምናን ለማስፋፋት እንደተላኩ ያምናሉ።ስለዚህ በመዋለድም ሆነ ከሰው ጋር ባላቸው ግንኙነት ሁሉ ኃይማኖታቸውን ሚሰብኩበት መንገድ ብዙ ነው።ክርስቲያኖች ግን ወንጌል መስበክን ወንጌልን ለሚሰብኩ አገልጋዮች ብቻ የተሰጠ አድርገን ስለምናይ የምስራቹን ለማውራት ያቅተናል።ሁላችንም በያለንበት ሚስዮናዊ የተላኩ ነን።ወንጌል የሁላችንም ስራ ነው።አንድ ለአንድም ሰበክን በጀማም ሰበክን ዋናው የጠፋውን የሰው ልጅ ወደቤቱ ማስገባትና ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው።ለዚህ ምን ያህል እንተጋለን?መልሱን ለየራሳችን እንመልሰው። #የጌታ ጸጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ። #ሼር @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
"GOSPEL"= G-For GOD so loved the world, that he gave his O-Only S-Begotten SON that whosoever believes in him should not P-Perish E-But have EVERLASTING L-Life በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። For God so loved the world, that he gave his only begotten Son, that whosoever believeth in him should not perish, but have everlasting life. ዮሐ 3፡16 @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
👍 1
የእግዚአብሔር ቃል ጠላትን የምትቃወምበት ትልቁ መሣሪያ ነው። @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
ከሚጠቀለለው ነገር በላይ የሚጠቀለልበት ሚያሳስበው አምላክ አለን ========================================================= እዚህ ምድር ላይ ማንም ምንም ልትሆን ትችላለህ።ደግ ሰው፣ሀብታም ሰው፣ደሀ ሰው፣ባለጠጋ፣ታዋቂ፣ወታደር፣ማናጀር የትኛውም ነገር ልትሆን ትችላለህ።እግዚአብሔር ይሄም ያም የትኛውም ነገር ትኩረቱን አይስበውም።እግዚአብሔር ጉዳዩ ከእኛ የሆነ ነገር ጋር አይደለም።እግዚአብሔር እኛ ከሆንነው በላይ ልጁ በእኛ ውስጥ እኛም በእርሱ ውስጥ መኖራችን ግን ለእርሱ ዋና ነገር ነው።ብዙ ጊዜ ለስጦታ፣ለሽልማት፣ለልደት፣ለሰርግ ይዘን የምንሄደውን ዕቃ በስጦታ መጠቅለያ ጠቅልለን ይዘን እንሄዳለን፤ምክንያቱም ይዘን የምንሄደውን ዕቃ ስጦታ ወይም ሽልማት ተቀባዩ ከፍቶ እንዲያየው ስለምንፈልግ።እግዚአብሔርም እንዲህ ነው ምንም ልትሆን ምንም ልታደርግ ትችላለህ ነገር ግን ያንን መልካም ስራህን፣የሆንከውን ነገር አለማትን በፈጠረበት በልጁ ደግሞ አለምን የሚጠቀልለው በክርስቶስ በአንድያ ልጁ ስለሆነ ፍጥረት ሁሉ በልጁ እንዲጠቀለል ይፈልጋል። እግዚአብሔር ያንን መጠቅለያ ፈቶ ማየት ይፈልጋል።ልጅነት፣ጽድቅ፣ቅድስና፣መልካም ስራ ሁሉ በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ነው።ካልተጠቀለልክ እግዚአብሔር ጋር መልካም ስራህ፣ጽድቅህ፣ቅድስናህ መንገድ ላይ ይቀራል እግዚአብሔር ጋር አይደርስም።እግዚአብሔር ከምንጠቀለለው በላይ የምንጠቀለልበት አንድያ ልጁ በእኛ ህይወት ውስጥ እርሱም በእኛ መሆኑ ያሳስበዋል። ======================================================== በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡10 ======================================================== ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። የዮሐንስ ወንጌል 3፡17 ======================================================== ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን። ዕብራውያን 1፡2 ======================================================== #share @ELOHIMLIFECHANNEL @ELOHIMLIFEBOT @Heliccv
Show all...
1