cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo

መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ እንደፈለግን መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየሀገሩን ወግና ልማድ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው። ለጥያቄዎና አስተያየትዎ @bsratbot ለተጨማሪ ት/ት @atronss_bot https://telegram.me/atronss

Show more
Advertising posts
3 517
Subscribers
No data24 hours
-177 days
-8430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"እኔም ፋኖ ነኝ!!!" ኢንተርኔት በመዝጋት የህዝብን ድምጽ በማፈን የሚካሄድን እና የህዝብ ጭፍጨፋን በጽኑ እቃወማለሁ! የተከበርከው የአማራ ልጅ! ይህን መልዕክት ቢያንስ ለ15 ሰው አድርስ።
Show all...
Show all...
"እርሷ ብቻናት" ተሰምቶ የማይጠገብ ዝማሬ በዘማሪ ግዛቸው ሹካ Subscrbers🤏🔔 Like👍 sher⤵️ በማድረግ ናታኒም ቲዩብ ቤተሰብ ይሁኑ!!

Show all...
የአርቲስቶችንና የታዋቂ ሰወች የኢሊሙናቲ አባሎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሼር ትውልድ ያድን ወጣቱ ይደራጅ ዋጋቸውን ያግኙ ሰላም ለኢትዮጵያ

🟢👉ድራማ_ለመስራት_አንመጣም🟢🟢👉_ምክረ_አበው_ለተጠየቁት_ጥያቄዎች_መልስ_ሙሉ_ክፍል128k.m4a123.30 MB
የጵጵስና ሢመት የሚጠይቀው ቅድመ ሁኔታ ክፍል ፩ በዲ/ን አሻግሬ አምጤ ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ጵጵስና መንፈሳዊ አባትነት በመሆኑ ለዚህ ሢመት የሚታጩ መነኰሳት የሚመረጡት በጥንቃቄ ነው። በጥንቃቄ መመረጥ የሚያስፈልገውም ኃላፊነቱ ሰማያዊ፣ ሹመቱ አምላካዊ በመሆኑ ነው። መነኰሳትን ለመንፈሳዊው ሾመት የሚያጩዋቸው አባቶች ቢሆኑም ሢመቱ አምላካዊ በመሆኑ የሚመረጡት ሰዎች አምላክን የሚያስደስቱ፣ ሰዎችን ወደ አምላክ ለማቅረብ የማይታክቱ መሆን አለመሆናቸው ከግንዛቤ ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ጥንቃቄ የሚጠይቀውም ኃላፊነቱ የሰውን ሕይወት ለመጠበቅ የሚሰጥ ሹመት በመሆኑ ነው። በኒቂያ የተሰበሰቡ ቅዱሳን አባቶቻችን የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በሕይወት እያለ እና መንበሩን ምንም አይነት ችግር ሳይገጥመው መላጥያኖስ የተባለው ግለሰብ በራሱ ፍላጎት ተነሣሥቶ ጳጳሳትን በመሾሙ በአገር አቀፍ ጉባኤ ተወግዞ የነበረ ቢሆንም ውግዘቱን በመተላለፍ በማን አለብኝነት የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት እየጣሰ በአፈንጋጭነቱ ቀጥሎ ስለነበር የኒቅያ ጎባኤ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ውሳኔ አስተላልፏል። ጉባኤው ያስተላለፈው ውሳኔ “መላጥያኖስና በእርሱ የተሾሙ ጳጳሳትና ካህናት ቤተ ክርስቲያንን የማወክና ሥርዓትን የመጣስ ተግባራቸው ምሕረት የማይገባው ቢሆንም ጉባኤው ቅጣቱን በማቅለል መላጥዮስ የጵጵስና ስምና ክብር ብቻ እንዲኖረው፣ በሀገረ ስብከቱ ከተማ ብቻ ተወስኖ እንዲኖር እንጂ በሌሎች ሰበካዎች እንዳይገኝ፣ ጳጳሳትንም መርጦ እንዳይሾም ወስኗል። በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት በየሀገረ ስብከታቸው እያሉ በመላጥዮስ ተሹመናል የሚሉት ተደርበው ማወካቸው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠ ነው። በመላጥዮስ የተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ደግሞ ትሕትናቸውና ግብረ ገብነታቸው ታይቶ በሕጋዊ ሢመት አንዲሾሙ አገልግሎታቸውም በቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሥር እንዲሆን” (NPNF,second serious, vol. 3, 2012, P,46)። አስቀድሜ በጠቀስኩት የኒቅያ ውሳኔ ብዙ ቁም ነገሮች የተካተቱበት መሆኑን አንባብያን የሚረዱት ነው። የመጀመሪያው ጉዳይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትዕግሥትና ሆደ ሰፊነት በጉልህ የሚያሳይ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑ ነው። የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሆደ ሰፊነት የሚገልጠውም “መላጥዮስ ምሕረት የማይገባው ቢሆንም ቅጣቱን በማቅለል የጵጵስና ስምና ክብር ብቻ እንዲኖረው” መፍቀዱኑ ነው። አንባብያን ልብ ልንለው የሚገባው መላጥዮስ ምሕረት የማይገባው ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአንድ ሰው ነፍስ ስለሚገዳትና በውግዘት ቆርጦ ከመጣል ይልቅ ምሕረት በማድረግ ዕድል መስጠት ተገቢ መሆኑን ስለምትገንዘብ አባቶች ያሳዩት ርኅራኄ የሚያስገርም ነው። ምድራዊ ነገሥታትም እንዲህ ያለውን ሆደ ሰፊነት የሚያሳዩ ቢሆኑ ኖሮ ጦርነትና መገዳደል ተወግዶ በዓለም ላይ ሰላም በሰፈነ ነበር። አባቶች ብዙ ነገሮችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለመላጥዮስ ምሕረት ቢያደርጉለትም መላጥዮስ ወደ ጥፋት ተመልሶ ቤተ ክርስቲያንን እንዳያውክ እግድ አስቀምጠውበታል። ለጥፋት ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባት አትሰማ እንደተባለው እርሱ ግን በጥፋቱ ቀጥሎ ከአርዮሳውያን ጋር የጥፋት ኅብረት እየፈጠረ ቤተ ክርስቲያንን ሲወጋ ቅዱስ አትናቴዎስንም ሲያሳድድ ኖሯል። አባቶቻችን ያስቀመጡት እግድም መላጥዮስ በሀገረ ስብከቱ ከተማ ብቻ ተወስኖ እንዲኖርና በሌሎች ሰበካዎች እንዳይገኝ፣ ኤጲስ ቆጶሳትንም እንዳይመርጥ እና እንዳይሾም ማድረጋቸው ነው። ከዚህ ውሳኔ መረዳት የሚቻለው መላጥዮስ ይዞ የቀረው የጵጵስናውን ስም ብቻ መሆኑን ነው። እንዲህ ያለው ውሳኔ ልብ ላለውና ራሱ የፈጸመውን ስሕተት ለመመርመር ለሚጣጣር ክርስቲያን የንስሓ ጊዜ የሚሰጥ፣ ወደ አሳዘነው አምላኩ የመመለሻ ዕድል የሚያጎናጽፍ፣ የበደላትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የመታረቂያ ጊዜ ማግኛ ነው። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት የሚታወቀው አባቶች በሌላቸው ሥልጣን በአባቶች መንበር ጣልቃ በመግባት መነኰሳትን መርጠው ኤጲስ ቆጶስነት መሾም ሳይሆን ኃላፊነት መቀበል ይቻላቸዋል ተብለው ሲመለሡ እንኳ አይቻለንም ሲሉ ነው። ንጽሕናቸው ታይቶ መንጋውን ለመምራት ይችላሉ ተብሎ ለጵጵስና መዓርግ ሲታጩ በትሕትና የማይቻላቸው መሆናቸውን በመናገር እንዲተዋቸው ይማጸናሉ። አባቶች ከሹመት የሚሸሹት አንድም በትሕትና፣ ሁለትም ኃላፊነቱ በሌሎች ኃጢአት የሚያስጠይቅ በመሆኑ በራሳችን ኃጢአት ብቻ እንጠየቅ እንጂ ለምን በጥፋት ላይ ጥፋት በመፈጸም አምላካችንን እናሳዝናለን በማለት ነው። ሌላው ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ነጥብ በመላጥዮስ የተሾሙትን ጳጳሳት በተመለከተ ትሕትናቸውና ግብረ ገብነታቸው ታይቶ በሕጋዊው ሊቀ ጳጳስ ኤጲስ ቆጶስነት ይሾሙ ዘንድ፣ አገልግሎታቸውም በእለ እስክንድሮስ ሥር ይከናወን ዘንድ መወሰኑ ነው። እንዲህ ያለውን ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠውን መልካም ዕድል አጣመው በመተርጎም ሥጋዊ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ደም ለመፍሰስ ምክንያት የሆኑት አካላት መካተት እንደማይገባቸው የሚያሳውቀው ትሕትናቸውና ግብረ ገብነታቸው ታይቶ የሚለው ቅድመ ሁኔታ ነው። አንድ ሊቀ ጳጳስ በሚመደብበት ሀገረ ስብከት ለሚገኘው ለጠቅላላው ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባት በመሆኑ (፳፻፱ ዓ.ም የተሻሻለው ቃለ ዐዋዲ፣፹፪ ) ለአባትነት ሲታጭ በመልካም አርአያነቱ የሚታወቅ እንጂ እጁ በደም የተነከረ፣ መጣልን የሚባል እንጂ መጣብን የማይባል ሊሆን ስለሚገባው ነው። ነቀፋ ያለበት ግለሰብ አባት ተብሎ በአንድ ሀገረ ስብከት ቢመደብ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን እንደ አባት ሊቀበሉት ቀርቶ በዓይናቸው ማየትና እርሱ በሚገኝበት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው መንፈሳዊ አገልግሎት ማግኘት እንደማፈልጉ መረዳት ይገባል። ሰው ለማስደሰት ወይም ቍጥር ለመሙላት መንፈሳዊነት የሌላቸውንና የሰው ልጅ ድኅነት ግድ የማይሰጣቸውን ግለሰቦች መርጦ መመደብ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መታወቅ ይኖርበታል። አባቶች እንዲህ ያለውን ቅድመ ሁኔታ ያካተቱት ምንም እንኳ ኢቀኖናዊ በሆነ ሢመት ተካትተው የነበረ ቢሆን ከሰው ልጅ ስሕተት አይጠፋምና ምግባር ትሩፋታቸው ለሌሎች የሚተርፍ፣ መንጋውን ለመበተን ሳይሆን ለመጠበቅ ትጋት ያላቸው አባቶች ካሉ ዕድሉ እንዳያልፋቸው የተከሠተውን ችግር ምክንያት አድርጎ በሕጋዊው ሢመት ቢታለፉ ምእመናን ሊያገኙት ከሚገባው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳይቀርባቸው ነው። ልብ ሊባል የሚገባው የኒቅያ ጉባኤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ ያስተላለፈው ቤተ ክርስቲያንን እና ምእመኖቿን የሚጠቅሙ ሰዎች ቀርተው መንጋውን ለማገልገል ዳተኛ የሆኑት ግለሰቦች ተሾመው ቤተ ክርስቲያን እንዳትታወክ እንጂ ተሿሚዎችን ለማስደሰት አይደለም። ይቆየን ምንጭ:ማህበረ ቅዱሳን

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.