en
Feedback
ዝክረ ቅዱሳን

ዝክረ ቅዱሳን

Open in Telegram

ይህ የቴሌግራም ቻናል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር እና ካከበራቸው ቅዱሳኑ ከቃል-ኪዳናቸው የምንካፈልበትና ዝክራቸውን የምናስብበት አገልግሎት ነው። "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Show more
1 539
Subscribers
-124 hours
-67 days
-1830 days
Posts Archive
https://www.youtube.com/live/ezAOtDd5bjw?si=DCXucEb0Mgm6Wu0e 🔴 ሥርዓተ ማኅሌት ከርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም | ቀጥታ ስርጭት | ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ | Aba Gebrekidan

ይህንን ዓላማ ለመፈጸም ለምንገነባው ሆስፒታል በቂ ቦታ ለማግኘት የረዳንን እግዘብሔርን እርሱም ያከበራቸው ቅዱሳንን እያመሰገንን በእውነተኛው መድኃኒታችን በመድኃኔዓለም ቀን የሆስፒታላችን የመሠረት ድንጋይ ልናስቀምጥ መሆናችን ደግሞ ደስታችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል። ከዚህም የደረስነው ነገም የምንደርሰው በማይናወጸው መሠረት በእርሱ ላይ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቁመን ነውና። ከመስቀሉ ሥር እናቱን “እናት ትሁናችሁ” ብሎ ባይሰጠንስ ቋጠሮ ሲጸናብን ማን ለእርሱ ነግሮ ያስፈታልን ነበር? ልጅ እያለን ወደ ወላጅ እናታችን እናለቅስ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ከመድኃኔዓለም እናት እያለቀስን የወደድነውን የምንቀበልባት እናት ድንግል ማርያምን ስለሰጠንም እናመሰግነዋለን ። ውድ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን መሬት እንድናገኝ የረዱንን ሁሉ የጉባኤ አምላክ ይስጥልን በሰማይ ቦታ ይስጣችሁ እያላችሁ እንድትመርቁልን እየጠየቅን፤ ቀዳሚት ፳፯-፲-፳፲፰ ዓም ከጧቱ 3:00 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በባሕርዳር የመሠረት ድንጋዩን ስለምናስቀምጥ እንኳን አደረሳችሁ፣እንኳን ደስ አላችሁ፣ አብራችሁን ለቆማችሁ ሁለ መድኃኔዓለም ከእናንተ ጋር ይሁን። እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ ሁሉን የጀመርህ ሁለን የምትፈጽም ሁሉን የያዝህ ሁሉን የወሰንህ መድኃኔዓለም ሆይ ከአንተው ተጠግተን የጀመርነውን እንደምትፈጽምልን ፈጽመን እናምናለን ። ለአንተ ለባሕርይ አባትህ ለአብ ለማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን ! አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር