ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
Open in Telegram
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Show more1 678
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1730 days
Posts Archive
በዲበኩሉ ጌታ 'ራስ'ነት በምድር ዘላለም ቀዳሚነት ደምቆ እና ጥሞ ተጣጥሞ ያለፈው ግጥም ሲጥም 3 በጨረፍታ ይህን ይመስል ነበር። ከመደበኛ አጣሚዎቻችን በተጨማሪ በታዳሚነትም በአቅራቢነትም በድንገቴ ተገኝተው መሰናዶውን ካጣሙሉን ውስጥ ዮሐንስ ሃብተማርያም ()፣ Kal'sT (The Wordsmith) እና ማሕሌት ማይረጉን እንዲሁም የተገኛችሁትን ሁሉ ምስጋና ልናቀብላችሁ እንወዳለን።
ለተሻለ ከፍታ እየተጋን ነውና አሁንም ብርቱ እገዛችሁ አይለየን!
እስቲ ደሞ ቀጣዩን 'ራስ' ገምቱ. . . ማን ሊሆን ወይም ልትሆን ትችላለች?
do you wanna know
how it feels to let go
Hold a rose
smell the fragrance
Embrace it
Just cuddle the beauty
dance with the scent
laugh with life
fell in love
Hold it day and night
and day and night
till day passes
And become amonth
did you see her dying
Okay
I think
Now you'e got it
The pain of letting go!
© Mekdes Moges
አምላክ ሰውን ሳያውቅ
ሰው አምላክ ሳያመልክ
የነበረው ዓለም
ዳር ይዘት'ና መልክ፣
ጥበብ ጽንስ ነበር
ይዞ አይደርሱት ተምኔት።
©ዲበኩሉ ጌታ
ትኬቶች የሚገኙባቸው ቦታዎች
1 ፒያሳ ሱማሌ ተራ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ዛውያ ቲቪ ቢሮ
2 ቤተል አልመሻን ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ኡሚ የየቲም የልማት መረዳጃ ተቋም
3 ቤተል ፋሚሊ ታወር 4ኛ ፎቅ ሚስተር ኮፊ
ለበለጠ መረጃ +251929501670
ለኑረት ዋስትናው :ለትንሹ ኩራት
ምን እንኳ ቢመረጥ……ትልቁ ቢቀጠር
ለትልቅ እውነት : ለጋን እሱነቱ
ደጋፊ ማንነት………ይፈልጋል ጠጠር !!
……………………………………**
[ #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት]
በቅርብ ቀን #ከሔራን
@heranawi
ከመልካም በዓል ምኞት ጋር የወርኃ ታህሳስ የግጥም መጽሔትን ዘግየት ብለንም ቢሆን እንሆ አቅርበናል።
በቀጣይ መጽሔታችን የእናንተኑ ስራ እንጠብቃለን።
በ https://drive.google.com/file/d/1HushONVS9C8XU_xzalz55cis8Ol2KMK5/view?usp=drivesdk ገብታችሁ እዩልን፣ አውርዳችሁም የራሳችሁ ልታደርጉት ትችላላችሁ፣ አንብባችሁ ስታበቁ ግን አስተያየት አቀብሉን።
ግጥማቸውንና ምስሎቻቸውን እያቀበሉ ወሩን ላደመቁልን ሁሉ ምስጋና ይድረስ!!!
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥበብበአደባባይ #የግጥምመጽሔት
#gietmsitem #poeticsaturdays #artinaddis #poetrybooklet
Cover Sketch Credit: Moon'it
ለጊዜው በሰጠነው በርካታ ስሙ ነጠቃ፣ after poetry፣ የእሳት ዳር ጨዋታ በተለይም ደግሞ ከ'እሁድ ሰዎች' በተወሰደ ቃል 'ንሸጣ' ካልነው ውስጥ ጨረፍታ ዜማ በ መንቢ. . .
ይህ የዝግጅታችን ክፍል በሚገባው መጠን ተሰንዶ ያልተገኙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ የበለጠ እንሰራለን ዋናውን ዝግጅትም 'እራሶቻችንን' በሚመጥን ከፍታ ለመዘገብ ይበልጥ እንተጋለን።
እስከአሁን የተገኛችሁ ከልባችሁ ለሰጣችሁን ሃሳብ ሁሉ ተመስገኑልን!!!
መሰናዶዋ በሚገባ ከመነሻቸው የሚዘከሩ ገጣሚዎችን እያወደሰች ወይም በ'ዚህ ዘመን' ቋንቋ እንድናሽቃብጥላቸው የሚያስገድዱንን፣ የዘመናችንን የስነ ግጥም መልክ በራሳቸው ቀለም የሚጽፉትን 'Headline Poets' ስራዎቻቸውን እያጋራች ለበርካቶችም የትውውቅ መንገድ እየሆነች ትቀጥላለች!
ኑ ተነጠቁ! ኑ ንጠቁ! ኑ ተነሸጡ!
...ንሸጣ ለተነሻጭ ብቻ እንጂ ለሁላችሁም ነው!
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ለተገኛችሁ ተገኝታችሁም ላጣማችሁ ሁሉ ምስግና ይሁን! #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
''ስለ ስልጣን አቀራረቡ በተመለከተ:- ገጣሚው ግጥምን የመወረብ፣ የመደነስ ችሎታዎቹ ድንቅ ያሰኙታል። ዝማሜውን ተከትሎ ቃል እያነሳ ሲያሻው እየደፋ ከፍ ሲል ቸብቸቦውን እያስቸበቸበ መረግዱን እያስመረገደ የግጥሙን ቆሌ ይካድማል ...''
ይህን ያለው የመጀመሪያው ኩነታችን 'ራስ' የዘንባባ መጽሐፍ ደራሲና ገጣሚ ምግባር ሲራጅ ነው። ይህ የተባለለት ደሞ የአሁኑን 'ራስ' ዲበኩሉ ጌታን አጅቦ እንደ አጋፋሪ የሚያጋፍርልን ተስፋ የተሰኘች የስነ ግጥም ስብስብ መጽሐፍ አሳትሞ ያስነበበን አስቱ ነው።
#አስቱ #አስታወሰኝ_ረጋሳ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ሻሎም እና ልዩን ተዋወቋቸው። ጋዜጠኛው በዲበ ኩሉ 'የምድር ዘላለም' ላይ ዳሰሳም ያቀርባል። ታዳጊዋ ደሞ በየወሩ የምንሰጠውን እድል በሚገባ ልትጠቀምበት የተሰናዳች አጣሚ (ጣዕም) ዘሪ ነች!
ሕይወት እና ሚዛን
አለመመጠን ሁለት ነወ
አንዱ ማነስ ሲሆን
ሌላው መብለጡ ነው።
...
ደማቁ ቀለም ምንግዜም ደማቅ ነው
ኮከቦች አገዙት ጨለማ ጋረደው፤
ነቃፊን ደጋፊን፣
ሁለቱን ወገን
ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መጠን
ይቻላል ማሳመን።
...
ያልታየ መልክህን፣ ጥረት ትጋትህን
ከኋላ ተነስቶ፣ ከፊት መውጣትህን
አይተናል፣ ለይተናል፤
ጀንበር ድል ፋናህን፤
አንተ ያልመጠንከው - ልቀህ በመሄድ ነው !!!
©ዲበኩሉ ጌታ
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
