en
Feedback
አብርሆት

አብርሆት

Open in Telegram

ሀሳቦች ዛሬ ካለንበት የዳፍንት (የጨለማ) አለም ወደ ነገ ወደ ተሻለው ብርሀን የሚመሩን መርተውም የሚያገናኙን ድልድዬች ናቸው። ፡ ለአስተያየቶ፡ @bellalsina @ThomB23

Show more
3 738
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#የቀጠለ... እነሱ ግን ድሮም ሲንገዳገድ አላማራቸውም ነበርና ጭራሽ የማይመስል ነገር እየዘባረቀ ሊፈታቸው ሲሞክር "አብዶ ሊያሳብደን ነው" ብለው እየመቱና እየገፈተሩ ሙከራውን ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ አረጉበት።" ፡ እንደ ፕሌቶ አስተምህሮ ይህ አሁን እኛ የምንኖርበት አለም በሰማይ ያለው 'ፍፁማዊ አለም' ጥላ እንጂ እውነተኛ አይደለም። አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እስኪ ስለ ፍፁም ክብ (perfect circle) እናውቃለን። ነገር ግን ኮንፓስም ሆነ ማንኛውም መሣሪያ ተጠቅማችሁ የምትስሉት ክብ 'ፍፁም ክብ' አይደለም ትንሽ imperfection አለው። ምን አለፋችሁ ማንም ሰው ፍፁም ክብ ተመልክቶ አያውቅም። ታድያ ይሄ ሃሳብ ከየት መጣ? ሌላ ይቺ ልጅ ውብ ናት ወይም ፍርዱ ፍትሀዊ አይደለም እንላለን። ነገር ግን ውበት ወይም ፍትህ ምንድነው የሚለውን በትክክል ዲፋይን ማድረግ አንችልም ፤ ታዲያ ስለነዚህ ነገሮች እንዴት ማሰብ ቻልን? ፡ በፕሌቶ አስተምህሮ መሠረት ፈጣሪ ምድር ላይ ላለ እያንዳንዱ ነገር አንድ አንድ ፍፁማዊ ቅርፅ (perfect Form) ወይም ሞዴል በመስራት በዛኛው አለም ውስጥ አስቀምጧል ( ይህ ሞዴል 'ቅርፅ' እንጂ አካል (matter) የለውም )፡፡ ፡ ታዲያ ይህንን ቅርፅ ዘላለማዊ በሆነችው ነፍሳችን / አዕምሯችን ላይ በሀሳብ መልክ አትሞና ስጋ አልብሶ ወደምድር ይልከናል። እኛ ግን ወደዚህ ዝብርቅርቅ አለም ስንመጣ ያኛውን አለም እንረሳዋለን። ፡ ስለዚህ ይህን አለም በማየት ብቻ ሊኖረን የሚችለው ሃሳብ እንደአተያያችን የሚለያይ አንፃራዊ opinion እንጂ ፍፁም የሆነ እውቀት (knowledge) አይደለም። ይቀጥላል @abrhott

ክፍል 3 የቀጠለ ፡ ፕሌቶ vs አርስቶትል.. ፡ በ ሶስት መቶ ዓመተ ዓለም አካባቢ የጥበብ መፍለቂያ የነበረችው ጥንታዊቷ ግሪክ ሁለቱን የምንግዜም የምድራችን ታላላቅ ፈላስፎች ለአለም አበረከተች። ይ
ክፍል 3 የቀጠለ ፡ ፕሌቶ vs አርስቶትል.. ፡ በ ሶስት መቶ ዓመተ ዓለም አካባቢ የጥበብ መፍለቂያ የነበረችው ጥንታዊቷ ግሪክ ሁለቱን የምንግዜም የምድራችን ታላላቅ ፈላስፎች ለአለም አበረከተች። ይኸው ሁለት ሺ አመታት ቢያልፉም ፤ ብዙ ሺዎች ቢፈላሰፉም የሁለቱ ተፅእኖ ግን ፈፅሞ አልደበዘዘም። ፡ ፕሌቶ ፡ ኒቼን ጨምሮ ብዙዎች ክርስትና እንደ 'ገነት' እና 'ዘላለማዊ ነፍስ' የመሳሰሉ ሀሳቦችን የወረሰው ከፕሌቶ ነው ይላሉ። የፕሌቶን ፍልስፍና በቀላሉ ለመረዳት 'ሪፐብሊክ' ላይ ያሰፈራትን ታዋቂ 'የዋሻ ምሳሌ' (allegory of the cave) እንመልከት። ፡ "ሙሉ ዕድሜ ዘመናቸውን በዋሻ ውስጥ የኖሩ እስረኞችን አስቡ። እስረኞቹ ከጀርባቸው ጭል ጭል በምትል እሳት አማካኝነት - በዋሻው ግድግዳ ላይ - የውጪውን አለም ጥላ መመለከት ይችላሉ። ከተወለዱ ጀምሮ ሌላ ነገር ስላልተመልከቱ ከዋሻው ውጪ ስላለ አለም አስበውም ሆነ አልመው አያውቁም። ታድያ አንድ ቀን ከመሀላቸው አንዱ ከታሰረበት አምልጦ ከዋሻው የመውጣት ዕድል ያገኛል። ፀሃይን ለመጀመሪያ ግዜ ሲመለከት በጨለማ ውስጥ የኖረ አይኑ ከመታዋር ለጥቂት ይተርፋል። ከቆይታ በዃላ ብርሃኑን ተላምዶ ዙሪያውን ቢመለከት ተሂዶ የማያልቅ ሰፊ አለም ፤ ታይቶ የማይጠገብ ውብ ህብረ ቀለም ከቦታል። ብዙ ነገር ከተመለከተ በኋላ ዋሻ ውስጥ የታሰሩትን ጓደኞቹን ያስታውስና ያየውን ሊያሳያቸው ፤ ግርምቱን ሊያካፍላቸው እየሮጠ ወደዋሻው ይመለሳል። ነገር ግን ብርሃን የለመደ አይኑ በዋሻው ውስጥ እንደድሮው ሊያለት አልቻለም። እንደምንም እየተንገዳገደ ወደጓደኞቹ ደርሶ ስለተመለከተው ነገር በታላቅ ተመስጦ እየተረከ ከታሰሩበት ሊፈታቸው ይሞክራል። እነሱ ግን .... ይቀጥላል... @abrhott

⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉༄༄༄⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉ Never stop trying Never stop believing Never give up Your day will come.

ክፍል 2 የቀጠለ... 1) Metaphysics :- 'የመጀመሪያው ሳይንስ' ይለዋል አርስቶትል። የት ነው ያለነው? ከየትስ መጣን? ይህ የምናየው አለም እውነተኛው አለም ነው? የሚመራው ቋሚ በሆነ የተ
ክፍል 2 የቀጠለ... 1) Metaphysics :- 'የመጀመሪያው ሳይንስ' ይለዋል አርስቶትል። የት ነው ያለነው? ከየትስ መጣን? ይህ የምናየው አለም እውነተኛው አለም ነው? የሚመራው ቋሚ በሆነ የተፈጥሮ ህግ ወይስ ከኋላ ባለ የማይታይ ሀይል? : 2) Epistemology :- ደግሞ የሚያጠናው ምን ያህል ማወቅ እንችላለን የሚለውን ነው። የስሜት ህዋሳት የሚነግሩን መረጃ ትክክል ነው? እንዴት እናረጋግጥ? ከማየት እና መስማት ውጪስ ሌላ እውቀት ማግኛ መንገድ አለ? : 3) Ethics :- Ok! ከላይ ያሉት ሁለቱ ሊያዝጉን ይችላሉ። ይኼኛው ግን ወሳኝ ነው። እንዴት እንኑር? ጥሩ እና መጥፎ የሚባል ህይወት አለ? ፡ ፓለቲክስ እና ኤስቴቲክስ የተቀሩት የፍልስፍና ዘርፎች ሲሆኑ Logic /ምክንያታዊ አስተሳስብ/ ደግሞ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ የምንጠቀምበት መሳሪያ ነው። ይቀጥላል... ለወዳጆ ያጋሩልን @abrhott

ክፍል 1 : መግቢያ : አያን ራንድ በአንድ መድረክ ላይ ስለፍልስፍና መሠረታዊነት ለማሳየት አንድ ምሳሌ ተጠቅማ ነበር : "አስትሮኖመር ነህ እንበል። ብቻህን በጠፈር ውስጥ እየተጓዝክ ሳለ መንኮራኩር
ክፍል 1 : መግቢያ : አያን ራንድ በአንድ መድረክ ላይ ስለፍልስፍና መሠረታዊነት ለማሳየት አንድ ምሳሌ ተጠቅማ ነበር : "አስትሮኖመር ነህ እንበል። ብቻህን በጠፈር ውስጥ እየተጓዝክ ሳለ መንኮራኩርህ የሆነ ችግር ያጋጥማትና ትከሰከሳለች። ከቆይታ በኋላ ወደ ቀልብህ ተመልሰህ ስታይ.....መንኮራኩራ ከጥቅም ውጪ ሆናለች ፤ ወደምድር ለመመለስ የነበረህ ተስፋም አክትሞለታል። ዙርያህን ስትቃኝ ሁሉም ነገር እንግዳ ነው። ልክ በዚያች ቅፅበት ሶስት ጥያቄዎች ወደጭንቅላትህ ይመጣሉ። : 1) የት ነኝ? 2) ይህን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? 3) እሺ ምን ላርግ? : በርግጥ ይሄ ዝም ብሎ የአንዲት ሴት የፈጠራ ታሪክ ነው ልንል እንችላለን። ግን ደግመን ደጋግመን ካሰብነው ይህ ታሪክ የሁላችንም እውነታ ነው። : ~ ሁላችንም በድንገት እንግዳ ወደሆነ አለም የተጣልን ምስኪን ፍጡራን ነን። እነዚህን ሶስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በራሳህ መንገድ መልስ ሳትሰጥ እንቅልፍ የሚባል ነገር የለም። በርግጥ ባህል እና ሀይማኖት የሰጡህን መልስ (worldview & manual) እንዳለ በመቀበል ወደ እንቅልፍህ መመለስ ትችላለህ። ነገር ግን አባብለው ያስተኙህን ሀይማኖት እና ባህል አስኮርፈህም ቢሆን እውነቱን በራስህ መንገድ ለመፈለግ ከተነሳህ well......Well come to philosophy! : ስለዚህ ከላይ ባሉት ጥያቄዎች ላይ ተመስርተን ፍልስፍናን በሶስት እንክፈለው። : ይቀጥላል @abrhott

#የቀጠለ... ይህንንም በምሳሌ እንየው : ፈሪ ነኝ ብለህ ታስብ ይሆናል። ትልቅ ውሻ ሊነክስህ ወዳንተ እየመጣ ነው። ድንጋይ አንስተህ ስታባርረው ከሸሸ ፈሪ ፤ ካልሸሸ ደግሞ ደፋር ውሻ ነው። አንተ
#የቀጠለ... ይህንንም በምሳሌ እንየው : ፈሪ ነኝ ብለህ ታስብ ይሆናል። ትልቅ ውሻ ሊነክስህ ወዳንተ እየመጣ ነው። ድንጋይ አንስተህ ስታባርረው ከሸሸ ፈሪ ፤ ካልሸሸ ደግሞ ደፋር ውሻ ነው። አንተ ግን ከውሻው ትለያለህ። ውሻው ወዳንተ ሲመጣ ትሮጣለህ እየሮጥክ እያለ ግን 'እየሮጥክ እንደሆነ የሚነግርህና በየትኛውም ቅፅበት ቆመህ ውሻውን የመጋፈጥ እድል የሚሰጥህ ንቃተ ህሊና (CONSCIOUSNESS) ባለቤት ነህ። ኮንሽየስነስህን አዳምጠህ ዞረህ ስትጋፈጥ ጀግና ሆንክ ማለት ነው። : ስለዚህ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ቢያንስ የመሞከር ነፃነት አለህ። : ይህ ነፃነት ግን ብቻውን አይመጣም። ሙሉ ነፃነት አለህ ማለት ሙሉ ሃላፊነት አለብህ ማለት ነው። ለሆንከውም ሆነ ለምትሆነው ነገር ሁሉ ተጠያቂው አንተ ነህ።(No excuse) : አማኝ ብትሆንም ከዚህ ነፃነት አትድንም።ምክንያቱም አንደኛ የምትከተለውን ሃይማኖት የምትመርጠው አንተው ነህ። ሲቀጥል ''ለማደርገው ነገር እዛው ስሄድ ይቅጣኝ እንጂ ምድር ላይ ባለው ነፃነቴ ግን ፈጣሪም ቢሆን ጣልቃ መግባት አይችልም'' ይላል ሳርት። : ይህንን ሙሉና አስፈሪ ነፃነት ለመግለፅ 'MAN IS CONDEMNED TO BE FREE' / ሰው ነፃ እንዲሆን ተረግሟል ይለናል። ይጥላል @abrhott

#ስለ_ነፃነት ክፍል አንድ ለህላዌ ፈላስፎች እና ሀሳብያን (Existentialists) አንዱ የራስ ምታት የግለሰብ ነፃነት ነው። ሀሳብያኑ እንደሌላው ሁሉ በዚህም አይስማሙም። እኛም በየቀኑ የአንድ
#ስለ_ነፃነት ክፍል አንድ ለህላዌ ፈላስፎች እና ሀሳብያን (Existentialists) አንዱ የራስ ምታት የግለሰብ ነፃነት ነው። ሀሳብያኑ እንደሌላው ሁሉ በዚህም አይስማሙም። እኛም በየቀኑ የአንድ ፈላስፋን ምልከታ እያየን ሀሳብ እንለዋወጣለን። : ዣን ፖል ሳርት : ለሳርት የሰው ልጅ መሰረታዊ ተፈጥሮ ነፃነት ነው። ይሄንንም ለማስረዳት የሚጠቀምባት አንድ ታዋቂ አባባል አለችው። <EXISTENCE PRECEDES ESSENCE > በፈጣሪ ህልውና ለማያምነው ሳርት ከመሆን መኖር ይቀድማል። ይህን አባባል በምሳሌ እንየው : ተዋናይ ነሽ -- ቲያትር ለመተወን ወደመድረክ ከመውጣትሽ በፊት ያንቺ ገፀ-ባህሪ ድርጊት ፣ ንግግር ባጠቃላይ በፊልሙ ውስጥ የሚያጋጥሙሽ ነገሮች ሁሉ ባንቺ እንዲሁም በቲያትሩ ደራሲ እና ዳይሪክተር ጭንቅላት ውስጥ አለ (ይታወቃል)። ይህም ማለት ገፀ-ባህሪሽ ወደ ህልውና ከመምጣቷ (ከመኖሯ) በፊት ማን/ምን መሆኗ ቀድሟል ማለት ነው። : ሰው ግን ምን እንደሚናገርም ሆነ እንደሚያደርግ ሳይወሰንለት ወደ መድረክ የተጣለ ተዋናይ ነው። (MAN IS AN ACTOR WITHOUT A LINE.) ሰው ወደምድር ከመጣሉ በፊት 'ምንም' የነበርና በ'ለት ተ'ለት ንግግሩና ተግባሩ ማንነቱን እየሰራ የሚኖር ፍጡር ነው።(MAN IS WHAT HE MAKES OF HIMSELF AND Nothing else.) : ሳርት ይህን ሲል የሰውን ልጅ ማንነት የሚወስኑ ውስጣዊ (ተፈጥሯዊ ባህሪ እና ስሜት)እና ውጫዊ (አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች)እንዳሉ ሳያስተውል ቀርቶ አይደለም። ይህንንም በምሳሌ እንየው : ይቀጥላል @abrhott

#የመፅሐፍ_ጥቆማ ሐሰተኛው የአንዱ መኖር ለላውን ማወክ ሆኖ ተሰማኝ::ከመኖር ፍላጎት የመነጨ ጠላትነት እንደ ውሃ ከመሬት ፈልቋል፡፡ሳይደራረሱ ሳይነባበሩ አንዱ ለላውን ተጭኖታል፡፡የሚያወዳድራቸው ነገር ሳይኖር በንፅፅር ልባቸው ጠፍቷል....ከሆነብን ይልቅ ሊሆንብን የተዘጋጀው እጅግ ከብዶ አጎበጠኝ (አለማየሁ ገላጋይ)

photo content

I have the coolest dance moves in my head, the problem is moving my body😒

I need a relationship as strong as Nokia 3...I'm tired of all these Android & iPhone love...Just a little fall then there you are with a broken screen. 🚶🚶

Him: Babe, send me your picture Her: Aww, I’m ugly oo. Him: I know, I want to scare someone😂 .... Good night Fam❤️

Do you know you can actually jump from an aeroplane without using parachute. But it's once in a lifetime!😏

Why Is It Important To Have A Life Philosophy? If you feel extremely overburdened by your daily share of activities, this que
Why Is It Important To Have A Life Philosophy? If you feel extremely overburdened by your daily share of activities, this question might feel like it makes no sense. You might say: “Well, I have a lot of things I’m pursuing right now. A series of goals. A long sequence of unfinished projects. A lot of commitments and deadlines. What’s the fun in adding philosophy in this long list? Once I have everything sorted out, I can always have the luxury of delineating the broader contours of life philosophy.” But, my friend, there are others who have absolutely no problem answering this with conviction — This is what I want. Everything becomes a bit clearer when you bring that level of clarity in your goal. It’s not what you want to get done today, tomorrow or even this year. It’s what you’re trying to get out of life. What you are doing now, is it helpful in making it a reality? “A clear, well-defined philosophy gives you the guidelines and boundaries that keep you on track,” 

#ሁሉም የሰው ልጅ እስረኛ ነው፤ ሰፊ እስር ቤት በመሆኑ መታሰሩን ይዘነጋዋል እንጂ!"

እዚህ ሀገር ያሉ ሰዎች. ከእግዚአብሄር ቀጥሎ የሚያምኑትና የሚያመልኩት አሉባልታ ነው። ያለነቢያት ሜዳ ለሜዳ የሚንከራተቱት፣ ነቢያቶቻቸውን በየምድጃው ዳር በአሉባልታ ስለበተኑ ነው. . . . (የምድጃ ፕሮፓጋንዳ ከቲቪ ፕሮፓጋንዳ ይበልጣል) ጌሾ መስቀል ላይ ስለቸነከሩት ነው . . .(በወፍራም ጠላ እየተወራረደ የታማ፤ በቃ'ው!) ለጥርስ እንደተገራ መላላጫ ፍትፍታቸው ስር ወርውረውት ነው . . .(በቁንጣን ይሉኝታ የተገዛ ርዕዮተ-ዓለም ኃይለኛ ነው) ቢመረመር ከእግዚአብሔር እንኳን የሚያጣላቸው አሉባልታ ሳይሆን አይቀርም። በአደባባይ ቢነገርም ባይነገርም . . . ዜጎቿ ቢማሩም ባይማሩም . . . የሚገባቸውና የሚስባቸው፤ በመረጃ የታጠረ እውነትና እውቀት ሳይሆን በማሞ፣ በማሚትና በደንገሎች የሚለደስባቸው ሜሮን እንደሆነ ያምናሉ። ተጠቅመንበታልና ድምፃችንን ዝቅ አድርገን እንዲህ እንላለን ይላሉ፤ 👇 #ሺህ ጦረኛ የማይበግራቸውን ተራሮች በወሬ ትንፋሽ እንጥላለን' 😂 *** የስንብት ቀለማት 📚 #በአዳም_ረታ

መልካም ገና! BAGA AYYAANA QILLEETIN ISIN GAYE! ርሑስ በኣል ልደት! Merry Christmas عيد ميلاد سعيد ciid wanaagsan
መልካም ገና! BAGA AYYAANA QILLEETIN ISIN GAYE! ርሑስ በኣል ልደት! Merry Christmas عيد ميلاد سعيد ciid wanaagsan

*sitting infront of a hot chick in taxi* me: *staring at her* In my mind: plans our whole life together In her mind: ምን አባቱ ያፈጣል

ነገ መልካም ይሆናል !!

Ladies are so extra dramatic when they get mad. Everything is "bye, delete my number, you won't hear from me no more, I hate you, I'm done, have a blessed life, leave me alone. And they will sit there waiting for a reply 😹🙊