cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Minber TV

#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ! #ሚንበር_ቲቪን ለማግኘት 📡 በኢትዮሳት ይከታተሉ:– 👇 ፍሪኩዌንሲ:- 11545 ሲምቦልሬት:- 30000 ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል ★★★★★

Show more
Advertising posts
39 716
Subscribers
-324 hours
+1207 days
+12730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ልዩ “ኸበር” - 76 ዓመታት ያስቆጠረው መቅሰፍት ጣሪቅ አቡ አዙም ከሚገኝበት ጋዛ ለዓለም ይድረስ ብሎ ዛሬ ማለዳ ባሠራጨው ዘገባ፣ እስራኤል በፍልስጤም ንጹሐን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት በአየር እና በመሬት መቀጠሏን ይገልጻል፡፡ ጋዜጠኛው የአልጀዚራ ባልደረባ ነው፡፡ ጣሪቅ በተለይ ባለፉት ሰባት ወራት እስራኤል በንጹሐን ላይ ቦምብ ስታዘንብ እግር በእግር እየተከተለ ሲዘግብ ቆይቷል፡፡ ሕፃናት እና እናቶችን ጨምሮ ንጹሐን ሲረግፉ ዐይቷል፡፡ ውሎ አዳራቸውን፣ ሕልማቸውንም ጭምር የሚያጋሩት ወዳጆቹም በሞት ሲወሰዱ በአቅመ ቢስነት ሸኝቷል፡፡ የእስራኤል ቦምብ የሞያ ባልንጀሮቹንም ነጥቆታል፡፡ ጣሪቅ አቡ አዙም የዕለት ተዕለት ውሏቸውን የሚዘግብላቸው ፍልስጤማዊያን ሰቆቃ የጀመረው እ.አ.አ ከ76 ዓመት በፊት በዛሬው ቀን ሜይ 15/1948 ነበር፡፡ በእስራኤል መሬታቸው በወረራ ተይዞ ጥቃት የሚፈራረቅባቸው ፍልስጤማዊያን፣ ይህን ቀን መቅሰፍት (“ነክበህ”) ብለው ይጠሩታል፡፡ በየዓመቱም ይታሰባል፡፡ በዚህ ወቅት አይሁዳዊያን በፍልስጤማዊያን ላይ ጦርነት ከፍተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቀያቸውን ጥለው እንዲሸሹ አድርገዋል፡፡ የቀጠለው ጥቃት የፍልስጤማዊያንን የሰባት ዐስርት ዓመታት ኑሮ ተቆጣጥሮት ሕይወታቸውን በሰቆቃ ሞልቶታል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ፍልስጤማዊያን በመሬታቸው ላይ ለመንቀሳቀስ ጭምር ፍቃድ ሰጪው ሌላ ሆኗል፡፡ እስራኤል በተለይ ከ1995 ወዲህ በወረራ የያዘችውን ዌስት ባንክን በሦስት ሸንሽና በ700 ሺሕ ሠፋሪዎች ሞልታ ፍልስጤማዊያን በአንድ አካባቢ እንዲወሰኑ አድርጋለች፡፡ በዌስት ባንክ እስራኤል የራሷን ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ስታሠፍር ከዐስር ሺሕ በላይ የፍልስጤማዊያን ግንባታዎችን አውድማ ነው፡፡ መሬታቸው ባዕድ የተወረረባቸው ፍልስጤማዊያን፣ ወደ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ የይለፍ ፍቃድ ለማግኘት በማለዳ መሰለፋቸውም የዕለት ውሏቸው አካል ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ እስራኤል የፍልስጤማዊያኑ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥላ ሥማቸው በሥራ ፈትነት ከዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ሆኗል፡፡ እስራኤል የፍልስጤማዊያኑን ሰቆቃ የምታበረታው የንግድ እንቅስቃሴንም በማፈን ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፍልስጤም ከአጎራባች ዐረብ ሀገራት ጋር የንግድ ግንኙነቷ ተቆርጧል፡፡ የወጪ እና ገቢ ንግዷም በእስራኤል በኩል እንዲያልፍ ጉልበተኛ ተሹሞበታል፡፡ እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ የጣለችው ገደብ ወደ ቴክኖሎጂም የሚሻገር ነው፡፡ እስራኤል ለራሷ 5ጂ ኔትወርክ ስትጠቀም፣ ፍልስጤማዊኑ በ3ጂ ኔትወርክ እንዲወሰኑ ተደርገዋል፡፡ እስራኤል በገደብ የምትለቀውን ኔትወርክ ፍልስጤማዊያኑን ለመሰለል ጥቅም ላይ የምታውለው ነው፡፡ ፍልስጤማዊን የኔትወርክ ብቻ ሳይሆን የውሃ እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ላይ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡ ለ76 ዓመታት በወረራ በያዘችው መሬት ላይ የተሾመችው እስራኤል፣ ከጥቅምት 2024 ወዲህ በንጹሐን ላይ የምትሰነዝረውን ሰብዓዊነት የጎደለው ጥቃት በመጠን አስፋፍታ ቢያንስ 35 ሺሕ ሰዎችን ገድላለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺሕ የሚሆኑት ሕፃናት ናቸው፡፡ ፍልስጤማዊያኑ መቅሰፍት ሲሉ የሚጠሩትን የዛሬውን ቀን ሲያስቡ፣ በዓመታት ሰቆቃ ውስጥ ከአጠገባቸው የተለዩዋቸውን እያስታወሱ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ) (ይህ ጥንቅር በዋነኝነት የተወሰደው ከአልጀዚራ ነው፡፡)
Show all...
👍 7😢 4💔 3 1
ልዩ “ኸበር” - 76 ዓመታት ያስቆጠረው መቅሰፍት
Show all...
በጎዳናዎች ላይ ወደ እስልምና በመጣራት የሚታወቀው ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ በ50 ዓመት ዕድሜው ወደ አኺራ ተሻገረ ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 7 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 7 – 1445 | ሚንበር ቲቪ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ጎዳናዎች ላይ ወደ እስልምና በመጣራት የሚታወቀው ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ ወደ አኺራ መሻገሩ የተሰማው ትናንት ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ነው፡፡ ወንድም ፈቂህ ሕይወቱ ያለፈው በሻሸመኔ ከተማ ሲሆን ሕልፈቱ ድንገተኛ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡ ወንድም ፈቂህ ላለፉት 23 ዓመታት አዲስ አበባን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ አማራ እና ሲዳማ ክልል የተለያዩ ከተሞች በአደባባይ ወደ እስልምና በመጣራት በሥፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ወንድም ፈቂህ በሰኔ/2014 ከሚንበር ቲቪ “የኔ መንገድ” ፕሮግራም ጋር በነበረው ቆይታ የአደባባይ የዳዕዋ ሥራው ትዳሩን እንዳሳጣው ተናግሮ ነበር፡፡ ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ፣ በአዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች በሚያደርገው የዳዕዋ ሥራ እስር እና ድብደባ ሲያስተናግድ እንደቆየም ተናግሯል፡፡ ወንድም ፈቂህ ወደ እስልምና መጣራቱ ለእስር በሚዳርገው ጊዚ ጭምር ሥራውን በመቀጠል የተለያዩ ግለሰቦች ወደ እስልምና እንዲመለሱ ሰበብ መሆኑን ገልጧል፡፡ የቀድሞው ወታደር ፈቂህ ገለቶ፣ ወደ አኺራ የተሻገረው በ50 ዓመት ዕድሜው ነው፡፡ ሚንበር ቲቪ በወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል። ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን! (ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ ጋር በሰኔ/2014 ከሚንበር ቲቪ ጋር ያደረገውን ቆይታ ከአስተያየት መስጫ ስር ያገኙታል) ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
😢 29💔 6👍 1
አቶ ነስሩ የትናንት ሐይወታቸውን ሳይቀባቡ ራሳቸውን ሳያንቆለጳጵሱ እቅጯን ባለፈው ሳምንት ነግረውን ነበር። ዛሬም ካቆሙበት እንቀጥላለን። ብዙዎቻችሁ በአቶ ነስሩ ታሪክ የተሰማችሁን ገልጻችሁልናል። እናመሠግናለን። አቶ ነስሩን ተከትሎ በርካቶች እኔም ታሪክ አለኝ ብለው ቢሯችን መጥተዋል። ሁሉንም መዝነን በሂደት የምናቀርበው ይሆናል። ዛሬ ምሽት 3:00 የአሊ ደነቦ ዘሮችን አስደናቂ ታሪክ በአራተኛው ትውልድ በአቶ ናስር ሐሰን ዳሞ ይቀርብልናል በሰአቱ ጠብቁን። #የሕይወት_ገፅ #ከቦዠ_እምነት_ወደ_እስልምና ክፍል 2 #አሊ_ደነቦ ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 7 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 7 – 1445 | ሚንበር ቲቪ ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
👍 6
በጛዛ ንጹሃን ላይ የሚደርሰው የሚበቃ ኣይመስልም። ወደ ራፋህ የዘለቀው የሞት ሰራዊት የግፍ ዘመቻው ራፋህ ላይ የሚያበቃ ኣይመስልም። ዛሬ ምሽት ከ1:45 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን! #እነሆ_ኸበር #የሚበቃ_አይመስልም! ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 6 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 6 – 1445 | ሚንበር ቲቪ ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
💔 31👍 13😢 8 3🥰 3
“ #Social_Justice_in_Islam " በሚል ርዕስ በታዋቂው ሙፈኪር (አሰላሳይ) ሰይድ ቁጥብ የተዘጋጀው መጽሐፍ፤ የኃይማኖት ምንጮችን ከማንሳት እና ከመመርመር ጀምሮ ሙስሊሞች እንዴት በምዕራቡ ዓለም ተፅዕኖ እንደወደቁ ያነሳል። በዋናነት ማኅበራዊ ፍትህ በኢስላም የተሰጠውን ሥፍራ ከተለያዩ ማዕዘናት አንጻር በመቃኘት ምልከታውን የሚያኖረው ይህ መጽሐፍ፤ በተረኛ የመጽሐፍ ዳሰሳ አቅራቢው ወንድም ቢንመሊክ አብዱ ዕለተ እሁድ ግንቦት 4/2016 በዋሊያ መፅሐፍት አዳራሽ በርካቶች በታደሙበት ግሩም በሆነ መንገድ ቅኝት ተሠርቶበታል።  "በንባብ ወደ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በኢ ኤም ኤስ ሊግ አዘጋጅነት የተከወነውን የመፅሐፍ ቅኝት ዝግጅት ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁ!! #ቅኝተ_መጻሕፍት ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 6 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 6 – 1445 | ሚንበር ቲቪ ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
👍 7 3👌 1
የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 6 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 6 – 1445 | ሚንበር ቲቪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባ አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ። ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያፀደቀው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ነው። ረቂቅ አዋጁ የአርሶ አደር፣  አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ አገሪቱ ከደረሰችበት ዘርፈ ብዙ እድገት ጋር እኩል ለማራመድ ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማደራጀትና ለተጠቃሚው በአግባቡ ለማሠራጨት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ በመፍጠር መንግስት እና የመሬት ተጠቃሚዎች አስተማማኝ የሆነ መረጃ የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ የወጣ መሆኑን በዛሬው የምክር ቤት ውሎ ተገልጿል። ረቂቅ አዋጁ የተፈጥሮ ሐብቶችን በዘላቂነት በመጠበቅና በማልማት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ማረጋገጥና አካታች ሥርዓት መደንገግ አስፈላጊ መሆኑን የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ አብራርተዋል። ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አድርጎ አፅድቆታል፡፡ ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
👍 15
አሜሪካዊው የጦር መኮንን ሀገሩ ለእስራኤል የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ በመቃመም ሥራውን ለቀቀ ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 6 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 6 – 1445 | ሚንበር ቲቪ በአሜሪካ ጦር ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ የስለላ መሥሪያ ቤት የሚሠራው ሐሪሰን ማን፣ ሀገሩ በጋዛ ንጹሐን ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመች ለምትገኘው እስራኤል የምትሰጠውን ድጋፍ በመቃወም ሥራውን ለቀቀ፡፡ የጦር መኮንኑ ሐሪሰን ማን በሊንክድን ባሠራጨው መልቀቂያ ላይ፣ ሥራው ለንጹሐን ፍልስጤማዊያን ግድያ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው በሚል ጭንቀት ውስጥ እንደከተተው ገልጧል፡፡ የአሜሪካ መከላከያ የስለላ መሥሪያ ቤት ሥራ በቃኝ ያለው የጦር መኮንን፣ መልቀቂያ እስካስገባበት ጊዜ ድረስ በመካከለኛው ምሥራቅ እና አፍሪካ ክፍል ውስጥ ተንታኝ ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ዋሽንግተን ፖስት የሐሪሰን ማንን መልቀቂያ በተመለከተ ለአሜሪካ ጦር ቃል አቀባይ ጥያቄ አቅርቤ፣ የመልቀቂያውን ትክክለኛነት አረጋግጠውልኛል ብሏል፡፡ እንደ ቃል አቀባዩ ከሆነ፣ የጦር መኮንኑ የመልቀቂያ ጥያቄ የቀረበው ከ5 ወር በፊት በኅዳር ወር ነው፡፡ ሐሪሰን ማን በመለቀቂያው ላይ እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ከጀመረች አንስቶ ከበርካታ ዘግናኝ ምስሎች ጋር ፊት ለፊት መጋፈጡን በመጥቀስ፣ “ሥራዬን እና ምሥሎቹን ማስታረቅ ከበደኝ” ብሏል፡፡ ሐሪሰን በማስታወሻው ይህ ሁኔታ “የሐፍረት እና ጥፋተኝት” ስሜት ውስጥ እንደጣለውም አብራርቷል፡፡ የሐሪሰን ማን ሀገር አሜሪካ፣ እስራኤል በጋዛ ንጹሐን ላይ ለምትፈጽመው መጠነ ሠፊ ጥቃት፣ የጦር መሣሪያ እና የስለላ ድጋፍ ትሰጣለች፡፡ ሀገሪቱ ለእስራኤል በምትሰጠው ድጋፍ ሳቢያ እንደ ጦር መኮንኑ ሁሉ፣ ሥራቸውን የለቀቁ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን የአሜሪካ ጋዜጦች ጽፈዋል፡፡ ጋዜጦቹ ከእነዚህ ውስጥ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ ከአስር ዓመት በላይ የሠራውን ጆሽ ፖል የተባለ ግለሰብ፣ በስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ የሰብዓዊ መብት ክፍል ውስጥ ባልደረባ የነበረችውን አኔል ሼኒል፣ በዚያው ስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ የዐረቢኛ ቃል አቀባይ የነበረችውን ሐላ ራህሪትን ዘርዝረዋል፡፡ አሜሪካ የምትደግፋት እስራኤል ከመስከረም 2016 ጀምሮ በጋዛ በምትፈጽመው ጥቃት ቢያንስ 35 ሺሕ ንጹሐን ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 14 ሺሕ ሕፃናት ይገኙበታል፡፡ ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
👍 25👏 3
አሜሪካዊው የጦር መኮንን ሀገሩ ለእስራኤል የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ በመቃመም ሥራውን ለቀቀ
Show all...
35👍 1
በወቅታዊ የሙስሊሙ ዓለም ጉዳዮች ላይ የሚመክር የሊቃውንት ጉባዔ በዛሬው እለት ተጀመረ ዕለተ ሰኞ ግንቦት 5 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 5 – 1445 | ሚንበር ቲቪ በወቅታዊ የሙስሊሙ ዓለም ጉዳዮች ላይ የሚመክረው የዓለም ሙስሊም ሊቃውንት ጉባዔ ዛሬ ግንቦት 5/2016 እለት በቱርክ ኢስታንቡል ተጀመረ፡፡ በዚህ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባዔ በሙስሊሙ ዓለም ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች እና ቀውሶችን ለመፍታት እንዲሁም የሙስሊሙን ዓለም አንድነት የሚሸረሽሩ የአካሄድ ችግሮችን ለመቅረፍ የመፍትሔ ሐሳቦችን ያቀርባል ተብሏል፡፡ ጉባዔው በዛሬው እለት ከመጀመሩ አስቀድሞ ትናንት ምሽት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ለታዳሚዎች የራት ግብዣ አድርገውላቸዋል፡፡ በዚህ የራት ምሽት ላይ ንግግር ያደረጉት ኤርዶጋን፣ እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ የምትፈጽውን ጥቃት በማንሳት ኮንነውታል፡፡ ፕሬዝዳንቱ እስራኤል በንጹሐን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ማስቆም ሀገራቸው ብር ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡ በጉባዔው ላይ የዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊቃውንት ኅብረት ሊቀመንበር ሸይኽ ዓሊ አልቀራዳጊ እና ሌሎችም ዕውቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንት ንግግር እና ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መረጃ ከሆነ ከጥናት አቅራቢዎቹ መካከል ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይገኙበታል፡፡ ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
Show all...
👍 25 6😁 1😱 1😍 1