en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

Prime Media

Prime Media

Open in Telegram

Prime Media is an East-African media organization founded to stand for the truth. Follow us here for high quality news updates and entertainment.

Show more
1 903
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
Jewar-Sept-18

photo content
+3

መሀመድ አደም ቡሴ እንደፃፈው ፕራይም ሚድያ መስከረም 2/2019 (አዲስ አበባ) ተመሳሳይ ዓላማ ከሌላቸው ኃይሎች ጋር ትብብር በመፍጠር የሚመጣ የህዝብ ነፃነት እንደማይኖር የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ገለፁ። አሁን በ”ፅምዶ” ስም እየተሰባሰብን ነው የሚሉ ሃይሎች የጋራ ጠላት ያሉት እንጂ የጋራ አላማ እንደሌላቸው ተናግረዋል። የጋራ አለማ በሌለበት የጠላቴ ጠላት በሚል የሚደረግ ትብብር ለውጥ ብያመጣ እንኳ ሀገሪቷን ከትርምስ ወደ ትርምስ የሚያሻግር አይነት እንደሆነ አስረድተዋል። ኦሮሚያን የትርምሱ እና ቀውስ ማእከል ለማድረግ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ በፍፁም ተቀባይነት እንደማይኖረውም የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ በፅምዶ ስር ተሰባስበናል የሚሉ ቡድኖች ፀረ ኦሮሞ አቋሞች በተደጋጋሚ ማንፀባረቃቸው እና አንዳንዶቹ ደግሞ በተለይ እንደ ፋኖ አይነቱ አሁን ራሱ አቋማቸውን በተግባር የኦሮሞ ህዝብ እየጨፈጨፉ እና እያፈናቀሉ እንዲሁም ሁል ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም የሚፃረር አቋም እያራመዱ በአንድ ጥላ ስር እንጣመድ ማለት የማይመስል ነው ብለዋል። የከፋ ነገር ለኦሮሞ እየደገሱ እንተባበር ማለት ፌዝ እንደሆነ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ገልፀዋል። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር ግርማ ጉተማ(ፒኤችዲ) የሰሜኖች ጥምረት በሚል አሁን እየተቀነቀነ ያለው ኦሮሚያን ጨምሮ ለደቡቡ የሀገሪቱ ህዝቦች ስጋት እንደሆነ ተናግረዋል። እየተካሄደ ያለው ነገር የኤርትራ መንግስት፣ የትግራይ ሃይሎች እና የፋኖ ሃይሎች የመጣመር አይነት መሆኑን ጠቅሰው፣ ጥምረቱ ታክቲካል እንጂ ስትራቴጂካዊ አይደለም ብለዋል። ሁሉም ተጣማሪዎች የየራሳቸውን አላማ ለየግላቸው ይዘው፣ መንግስት መጣልን ብቻ የጋራ አድርገው እንደምንቀሳቀሱ ገልፀዋል። ይሄ ደግሞ አደጋ እንዳለው ገልፀው፣ የጋራ አላማ ከሌላ መንግስት እንኳ ቢወርድ ሀገሪቷን ለከፍተኛ ትርምስ የሚዳርግ መሆኑን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር ግርማ ጉተማ(ፒኤችዲ) ገልፀዋል። የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ጥምረት የሚያተርፈው ነገር የለም፣ እንደውም የሀገሪቷን ትርምስ ወደ ኦሮሚያ የሚያመጣ መሆኑን አስረድተዋል። በካናዳ ዩንቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪ እና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ፕሮፌሰር አባስ ሀጂ ኘሞ በበኩላቸው ፅምዶ በሚል ጥላ ስር የተሰባሰቡ ሃይሎች የኦሮሞ እና ሌሎች የኢትዮጵያ በስተደቡብ ህዝቦች ጠላት መሆናቸውን አስረድተዋል። ፕሮፌሰር አባስ ሀጂ ኘሞ የፅምዶ ፅንሰሀሳብ እኩልነት ሳይሆን የሰሜኖችን የበላይነት መመለስ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አይነቱ ስብስብ ጋር የሚጣመር የኦሮሞ ሃይል ከቶውኑ አይኖርም ያሉት ፕሮፌሰር አባስ ሀጂ ኘሞ፣ ልጣመር የሚል ካለ ከህዝቡ የመነጠል አደጋ ይጠብቀዋል ነው ያሉት። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር እና የህግ ምሁሩ አቶ ደጀኔ ጣፋ በበኩላቸው፣ ከሰሜን ለኦሮሞ ህዝብ የሚመጣ ስልጣን እና ነፃነት የለም ብለዋል። ፅምዶ የኤርትራ መንግስት፣ የትግራይ ሃይሎች እና የፋኖ ጥምረት ነው፣ የኦሮሞ ሃይሎች በዚህ ውስጥ የሚጣመዱበት አግባቢ እና የአላማ አንድነት የለም ነው ያሉት። በፅምዶ የሚፈታ የኦሮሞ ፖሊቲካ ችግር እንደሌለ ነው ያስረዱት አቶ ደጀኔ። የህግ ምሁሩ እና የፖሊቲካ ተንታኙ ፀገዬ ረጋሳ(ፒኤችዲ) በበኩላቸው፣ የኦሮሞን ህዝብ ለማጥፋት ከሚሰራ፣ መሬቱን የሚወር እና ህዝቡን ከሚያፈናቅል ሃይል ጋር ጥምረት ብሎ ነገር የለም፣ ወደፊትም አይኖርም ብለዋል። አላማችን አቢይን አውርደን ከአቢይ የከፋ ማምጣት እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል። “ፅንፈኛ ቡድን ፋኖ አቢይን የሚጠላው ኦሮሞን አላጠፈልኝም፣ የኦሮሞ ብሄርተኝነትን አላስወገደልኝም፣ ኦሮሚያን አላፈረሰልኝም በማለት ነው” የሚሉት ፀጋዬ ረጋሳ(ፒኤችዲ)፣ ከእንደዚህ አይነቱ ጋር መጣመድ ለኦሮሞ ህዝብ ምን ለማምጣት ነው በማለት ይጠይቃሉ። የኦሮሞ ህዝብ ኦሮሞ መጥፋት አለበት ከሚል ቡድን ጋር መቼም ትብብር እንደማይፈጥር አስረድተዋል። ፅምዶን በተመለከተ ደግሞ አስተያየት የሰጡት ፀጋዬ ረጋሰ(ፒኤችዲ)፣ የፅምዶ አፈቀላጤ የሆኑን አካላት በተደጋጋሚ ፀረ ኦሮሞ ንግርት ስያስተጋቡ መስማታቸውን ገልፀዋል። “የትግራይ ሃይሎች አፈቀላጤ ሚዲያዎች ጭምር ኢትዮጵያን ከኦሮሞ ለማዳን ወደ ፊንፊኔ መምጣት ተልእኮ ላይ እንዳሉ ስናገሩ ተስተውለዋል፣ ፀረ አቢይ ዘመቻቸው እንዲሳካላቸው የኦሮሞ ህዝብ ላይ መጨፈር የለባቸውም” ብለዋል። አንዳንድ የትግራይ ሰዎች የኦሮሞን ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለመደፍጠጥ ከወዲሁ ስዳዳቸው መስተዋላቸውን ጠቅሰው፣ ይሄ ፍፁም ተቀባይነት እንደማይኖረው ተናግረዋል። የትግል አጋርነት የፈምትፈልጉ ከሆነ የኦሮሞን ህዝብ ትግል አጀንዳ የግድ ማክበር አለባችሁ ሲሉ ፀጋዬ ረጋሰ(ፒኤችዲ) አሳስበዋል። የኦሮሞን ህዝብ የትግል አጀንዳ ለመጋፋት የሚሞክርን ማንኛውም አካል የኦሮሞ ህዝብ እንደሚታገለው ገልፀዋል።

Prime Media - Statistics & analytics of Telegram channel @primemediapm