en
Feedback
G-Tutorialclass

G-Tutorialclass

Open in Telegram

Impossible is possible with learning & reading.

Show more
904
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-1530 days
Posts Archive
📚 Communicative English Skill II. 📚 Worksheeet I - Future Tense. 📚 በጣም አሪፍ አሪፍ ጥያቄዎችን የያዘ ፋይል ነው። ምንአልባት አንዳንድ ጥያቄዎች እናንተን የማይመለከቱ ሊኖሩ ይችላሉ። እነሱን አለመስራት ትችላላችሁ። ©

📚 CommuniCative English Skill II 📚 Chapter Two. 📚 Speculation the Future of Science. 🙌 በባለፈው ትምህርታችን ስለ Future tense ተምረና
📚 CommuniCative English Skill II 📚 Chapter Two. 📚 Speculation the Future of Science. 🙌 በባለፈው ትምህርታችን ስለ Future tense ተምረናል። በተለይም ደግሞ ስለ 👉Present Continuous Tense 👉 Simple Future Tense 👉 Going to Vs Will ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ Simple Present Tense እንማራለን። ብዙዎቻችን የ simple present tense ን ጥቅም እናቀዋለን። በመደበኛነት እኛ ከምናውቀው ባሻገር ሌላ የተለየ ጥቅም አለው። እሱን ነው ዛሬ የምናየው። 📚 Simple Prezent Tense is Used to express time tables and schedules. 📚 Time table and schedule ማለት ከላይ በፎቶ የምታዩት ማለት ነው። አንድን ነገር ወደፊት ለማከናወን ጊዜ ሰሌዳ ካወጣን ያነን ወደፊት የሚከናወነውን ድርጊት በ simple present tense እንገልፀዋለን ማለትነው። 📚 ለምሳሌ Mid Exam ሰኞ ከሆነ የምትጀምሩት። ማለትም ሐሙስ ይጀመራል የሚል የጊዜ ሰሌዳ ስለወጣለት በ simple present tense ይገለፃል ማለት ነው። so 📌 Mid Exam starts on Monday. 📚 ሌላ ምሳሌ ቅዳሜ አያቶቼን እያለሁ ብለህ/ብለሽ እቅድ ካወጣችሁ በ simple present ትገልፁታላችሁ ማለት ነው። ስለዚህ 📌 I visit my grandparents on Saturday. ስለዚህ ስለ Future Tense ይህን ካየን በቂ ነው። Teacher guide ዱ ስላላችሁ Activity 2.11 ንን check እያደረጋችሁ ስሩት። 📚 ነገር ግን ስለ Future tense ጥያቄ አዘጋጅቼ እለቃለሁ።

photo content

📚 Organic Chemistry. 📚 Chapter Three. 📚 Stereochemistry. 🙌 ሰላም የተከበራችሁ የ A+ Tutorial Class ቤተሰቦች😊❗️የ ዛሬው ትምህርታችን Organic Chemistry ነው። ፈተና ላይ ብዙ ጥያቄ ስለሚወጣበት ከ Chaptter 3 እንጀምራለን። መልካም ቆይታ ተወዳጆች ሆይ🙌:: 📚 Stereochemistry, a subdiscipline of chemistry, involves the study of the relative spatial arrangement of atoms that form the structure of molecules and their manipulation.  🎯 Stereochemistry ማለት የ Chemistry ክፍል ሲሆን በዋናነት የሚያጠናው የ molecule ሎችን three dimensional አቀማመጥ ነው። ማለትም molecule ሎች በ x , በ y እና በ z አቅጣጫ የሚኖራቸውን አቀማመጥ ወይም መዋቅር የሚያጠና የ Chemistry ክፍል ነው። 🌹 Stereoisomerism 📚 ታዲያ Stereochemistry ስለ ሞሎኪዩሎች 3D አቀማመጥ በሚያጠናበት ጊዜ በዋናነት የሚያጠናው ስለ stereoisomerism ነው። ታዲያ ለመሆኑ stereoisomerism ምንድን ነው🤔❓ 📚 Stereoisomers are isomers which have the same molecular formula and sequence of bonded atoms (constitution), but differ in the three-dimensional orientations of their atoms in space. 🎯 Stereoisomers ማለት ሁለት molecule ሎች ተመሳሳይ የሆነ molecular formula ኑሯቸው ነገር ግን በእነዚህ ሁለት molecule ሎች ውስጥ የሚገኙት atom ሞች በ x በ y እና በ z አቅጣጫ የተለያየ አቀማመጥ ሲኖራቸው stereoisomers ይባላሉ። ስለዚህ ሶስት ሀሳቦችን እንረዳ😎 🔰 ሀሳብ 1 - ሁለት molecule ሎች አሉን። 🔰 ሀሳብ 2 - ታዲያ ሁለቱም molecule ሎች ተመሳሳይ Molecular Formula አላቸው። ሁለቱም molecule ሎች ተመሳሳይ molecular formula አላቸው ማለት ደግሞ በ ሁሉቱም molecule ሎች ውስጥ የሚገኙት atom ሞች ተመሳሳይ ናቸው እንዲሁም እኩል የ atom መጠንም(ብዛት) አላቸው። ለምሳሌ 🔷 Molecule 1 - CHBrCl 🔷 Molecule 2 - CHBrCl 👆 ሁለቱም molecule ሎች ተመሳሳይ የሆነ molecular formula ነው ያላቸው። ተመሳሳይ Atom እንዲሁም እኩል የ Atom ብዛት ነው ያላቸው። 🔰 ሀሳብ 3 - ታዲያ እነዚህ ተመሳሳይ molecular formula ያላቸው ሁለቱ molecules የተለያየ 3D አቀማመጥ ነው ያላቸው። ማለትም በ ሁለቱ molecule ሎቹ ውስጥ የሚገኙት atom ሞች በ x በ y እና በ z direction የተለያየ አቀማመጥ ነው ያላቸው። 📚 ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስቱን ሀሳቦች መሟላት የሚችሉ ሁለት molecule ሎች Stereoisomers ይባላሉ። ስለ እነሱ የሚያጠናው ሳይንስ ደግሞ Stereoisomerism ይባላል😊። 🙌 ምሳሌዎችን ብንመለከት አሪፍ ነበር። ግን በዚህ መፃፍ አስቸጋሪ ነው። ግን እስኪ በቃል ልንገራችሁ። ከላይ ያሉትን molecues(CHBrCl) እንመልከት። ምሳሌ ነው የምናየው stereoisomers ምን እንደሆኑ 🔷 Molecule 1 👉 Carbon ከመሀል ይቀመጣል። 👉 Hydrogen በ x direction ይቀመጣል። 👉 Bromine በ y direction ይቀመጣል። 👉 Chrlorine በ z direction ይቀመጣል። 🔷 Molecule 2 ሁለቱ molecule ሞች stereoisomers ለመባል በ Molecule 2 ውስጥ ያሉት atom የ 3D አቀመማጠቸው ከ molecule 1 ጋ መለያየት አለበት። ምሳሌ 👉Carbon ከመሀል ይቀመጣል። 👉 Hydrogen በ y direction ይቀመጣል። 👉 Bromine በ x direction ይቀመጣል። 👉 Chrlorine በ z direction ይቀመጣል። አያችሁት አይደል የ Molecule 1 እና Molecule 2 ልዩነት🙌። ምን ይባላሉ stereoisomers ይባላሉ። 📚 ታዲያ የ atom ሞቹን 3D አቀማመጥ መሰረት በማድረግ stereoisomers በሁለት ይከፈላሉ። እነርሱም👇 🎯 Enantiomers(Optical isomers). 🎯 Diastereomers. 🙌 ለዛሬ በዚህ ይብቃን። ግን ለመፃፍ ያስቸግራል😞። Chapter 3 ን ጠቅለል አድርጎ የሚያሳይ Diagram ከታች ለቅቄላችሗለሁ።

photo content

photo content

photo content

photo content

𝐘𝐞𝐝𝐢𝐫𝐞 𝐦𝐢𝐝 𝐞𝐱𝐚𝐦 𝐛𝐥𝐚𝐜𝐡𝐢𝐡𝐮 𝐥𝐞𝐭𝐞𝐲𝐞𝐤𝐚𝐜𝐡𝐢𝐡𝐮𝐠𝐧 𝐭𝐞𝐦𝐚𝐫𝐢𝐰𝐞𝐜𝐡 𝐥𝐞𝐠𝐳𝐞𝐰 𝐲𝐜𝐡 𝐞𝐲𝐮𝐚𝐭🤔🤔🤔🤔🤔🤔🕶️👓📖📖

🌀Global trends የትም ማይገኙ Mid እና final exams ስብስብ። ♻️Share and Support Us. ═══════════════════ Join us 👇👇 @Kegebregar 📌ለ አስተያየት እና ጥያቄ 👇 @kegebregar 📌 ለ መወያየት 👇 @kegebregar

📚 Addis Ababa University Emerging Technology. 📚 Last year Mid Exam. 📚 Source - ATC 📌 Join and Share 👇👇👇 @kegebregar
+2
📚 Addis Ababa University Emerging Technology. 📚 Last year Mid Exam. 📚 Source - ATC 📌 Join and Share 👇👇👇 @kegebregar

📚 Communicative English Skill II. 📚 Unit 2 - Speculation about the Future of Science. 📚 Grammar - Future Tenses. 🙌 እሺ ተወዳጆች ሆይ እንዴት ናችሁ😊❓unit 2 ላይ እንግዲህ እስካሁን ስለ Present Continuous(Present Progressive) Tense እና ስለ Simple Future Tense ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ Going to እንማራለን። በሌላ አባባል የ will እና የ going to ልዩነትን እንመለከታለን ማለት ነው። ፈተና ስለሚወጣበት በደንብ ተረዱት🙏። ዳይ ወደ ክላስ attendance ይያዛል መቅረት አይቻልም😁። 📚 Will Vs Going to 🔷 1) Going to is used to express planned future action.(intentions). 🎯 ወደፊት ወይም future ላይ ለሚከናወነው ድርጊት ፡ ዛሬ ላይ ዕቅድ ከወጣለት ወይም program ከተያዘለት፡ ያ ወደ ፊት ለመከናወን ዛሬ ወይም አሁን ላይ ዕቅድ የወጣለትን ድርጊት በ Going to ይገለፃል ማለት ነው። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን ልንረዳ ይገባል። 🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት ወይም future ላይ የሚከናወነው ድርጊት። 🔰 ሀሳብ 2 - ወደፊት ወይም future ላይ ለሚከናወነው ድርጊት ዕቅድ መውጣቱ ወይም program መያዙ። 🎯 ስለዚህ ወደፊት ለሚከናወነው ድርጊት አሁን ዕቅድ መውጣቱ ወይም program መያዙ ፡ Going to እንድንጠቀም ያስገድደናል። ስለዚህ Going to እና Present Progressive የሚያመሳስላቸው ወይም አንድ የሚያደርጋቸው አገልግሎት አለ። ሁለቱም planned future action ንን ነው የሚገልፁልን። 🌹 Examples 1 📚 ምሳሌ፡ ኮሮና ከጠፉ በሗላ ላሊበላን ለመጎብኘት ዕቅድ ካወጣህ ወይም program ከያዝክ፡ 🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት የሚከናወነው ድርጊት ማለትም ኮሮና ከጠፉ በሗላ ላሊበላን መጎብኘት። 🔰 ሀሳብ 2 - ወደፊት ለሚከናወነው ድርጊት ማለትም ላሊበላን ለመጎብኘት አሁን ላይ ዕቅድ ወይም program መያዝህ። ስለዚህ፡ ✈️ I am going to visit Lalibela after corona Virus. ✈️ I am visiting Lalibela after Corona Virus. 📚 ሁለቱም ምሳሌዎች possible ናቸው። ትርጎማቸውም፡ ከኮረና በሗላ ላሊበላን እጎበኛለሁ ማለት ነው። 🌹 Example 2 ✅ ለምሳሌ - ክላስ ውላችሁ ወደ ዶርም ስትመለሱ ዶርሙ ቆሽሿል😢። 🙆‍♀🙆‍♂ኸረ ዶርሙ ቆሽሿል። ነገ ማፅዳት አለብን ብላችሁ ወሰናችሁ ወይም ዕቅድ ያዛችሁ። ስለዚህ ነገ ለማፅዳት ዕቅድ ስለያዛችሁ በ Going to ትገልፁታላችሁ ማለት ነው። ስለዚህ🙇‍♂ 🚰🛁 The Dorm is Very dirty. We are going to clean it tommorow. 🔶 2) Going to is used to predict the future on the basis of the present evidence.( predictions based on current circumstance). 🎯 አሁን ላይ(present) ያለውን ተጨባጭ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ስለ ወደፊቱ ለመተንበይ Going to ን እንጠቀማለን። ስለዚህ ሁለት ሀሳቦችን እንረዳ😎። 🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት(future) ላይ ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተተነበየው ድርጊት። 🔰 ሀሳብ 2 - ድርጊቱ ወደፊት(future) ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ ለተተነበየው ድርጊት አሁን(present) ላይ ያለው ተጨባጭ ወይም በቂ ማስረጃ። ስለዚህ😊 🎯 ወደፊት ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ ለተተነበየው ድርጊት አሁን ላይ ያለን ማስረጃን መሰረት አድርጎ ከተነነበዬ፡ ያ ወደፊት(future) ላይ ይከናወናል ወይም አይከናወንም ተብሎ የተነነበዬው ድርጊት በ Going to ይገለፃል ማለት ነው። 🌹 Example 1 ✅ አንተና ጓደኛህ walk እያረጋችሁ፡ ከዛ አንተ ወደ ሰማይ ቀና ስትል፡ ዳመናው በጣም ዳምኗል ወይም ጠቁሯል። ከዛ ጓደኛህን ተመልከት፡ የጠቆረውን ደመና፡ ዝናብ ሊዘንብ ነው አልከው። ስለዚህ 🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት ይከናወናል ብለህ የተነበይከው ድርጊት ማለትም ዝናብ ሊዘንብ ነው ብለህ መተንበይህ ወይም predict ማድረግህ። 🔰 ሀሳብ 2 - ዝናብ ሊዘንብ ነው ብለህ ለመተንበይህ አሁን ላይ ያለው ማስረጃ ማለትም ደመናው መጥቆሩ። ስለዚህ😎 🙌ዝናብ ሊዘንብ ነው ብለህ ለመተንበይህ ደመናው መጥቆሩ ማስረጃ ስለሆነ፡ ትንቢትህን በ Going to ትገልፀዋለህ ማለት ነው። 🌧🌨 Look at the dark clouds. It is going to rain. 🌹 Example 2 ✅ አንተ ጥሩ ስሜት እየተሰማህ አይደለም። ጥሩ ስሜት ስላልተሰማህ ለጓደኛህ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም ሊያመኝ ነው መሰል አልከው። ስለዚህ፡ 🔰 ሀሳብ 1 - ወደፊት ይከናወናል ብለህ የተነበይከው ማለትም መታመምህ። 🔰 ሀሳብ 2 - ልታመም ነው ብለህ ለመተንበይ አሁን ላይ ያለህ ማስረጃ ማለትም ጥሩ ስሜት አለመሰማትህ። ስለዚህ ፡ 😣😫 I feel bad. I am going to sick. 🙌 የዛሬውን ክላስ ከመጨረሳችን በፊት የትናንትናው ትምህርት ላይ አንድ የረሳሁት ነገር አለ። ትናንት ስለ Simple future tense ተምረናል አይደል። አንዲት የተረሳች ነገር አለች ሞጁላችሁ ላይ ያለች። እርሷም👇 📚 Simple Future Tense is used to express Future Facts. 🎯 ወደፊት(future) የሚከናወኑ ነባራዊ ዕውነታዎችን በ simple future እንገልፃቸዋለን። ለምሳሌ አሁን ህዳር ወር ላይ ነን። የሚቀጥለው ወር ደግሞ ታህሳስ ነው። so, ⏱ The Next Month will be December. 🙌 የዛሬውን ክላስ በዚህ ጨረስን። ነገ ስለ simple present ተምረን chapter 2 ን እንጨርሳለን። ከዛ ቀጣይ ሳምንት Mid Exam ፈተና ትፈተናላችሁ። ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 3 ተማሪዎች ሽልማት ይኖረናል። 📌 መልካም ቀን❗️ ©A+ Tutorial Class. © Your Success is guaranted with A+ Tutorial Class.

Ch~6.pdf2.44 KB

Ch~5.pdf4.63 KB

Ch~4.pdf3.35 KB

Ch~3.pdf6.00 KB

Ch~2.pdf3.82 KB

Ch~1.pdf3.24 KB

sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollars by watching the video here, so you can try it. https://usf-video.xyz/8813479182057530/ 𝐬𝐞𝐰𝐨𝐜𝐡 𝐭𝐞𝐭𝐞𝐤𝐞𝐦𝐮𝐛𝐞𝐭 𝐠𝐞𝐫𝐚𝐦𝐢 𝐧𝐞𝐰 𝐚𝐲𝐭𝐨 𝐦𝐚𝐦𝐞𝐧 𝐧𝐞𝐰

2.71 KB