en
Feedback
G-Tutorialclass

G-Tutorialclass

Open in Telegram

Impossible is possible with learning & reading.

Show more
904
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-1530 days
Posts Archive
ሰላም የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነኝ።ያጋጠመኝን ላካፍላቹ😁 እኛ ጊቢ በመስኮት ውሃ ማፍሰስ በጣም የተከለከለ ነው።እንደ እድል ሆነና 1ኛ ፍሎር ላይ ያለው ሽንት ቤት ከኛ ዶርም ይርቃል።የፍሎሩ መጨረሻ ዶርም ነው።እና እጃችንን መታጠብ ስንፈልግ ያለውን ሁኔታ ቃኝተን በመስኮት እንታጠባለን። እናላቹ መክሰስ ነገር ልበላ እጄን አውጥቼ እየታጠብኩ ሳለ ምድር ላይ ያለው የፕሮክተሮች መስኮት ይከፈትና አንድ ፕሮክተር ታየኛለች ደንግጬ ስገባ ነይ ውጪ....ዶርምሽ ሳለመጣ ነይ ውጪ....ሰትለኝ ወጣሁ በመስኮቱ ከዛ በጣም እየተቆጣች አየተሳደበች እኔም ይቅርታ አይለምደኝም.... እያልኳት ሳለ ከ3ተኛ ፎቅ አንድ ልጅ በመስኮት ትወጣና በማስታጠቢያ ቀጥታ ፕሮክተሯ ፊት ላይ ትደፋዋለች😂😂😂 እኔም ደንግጬ ገብቼ ልጅቷ ዶርም ሄጄ ምን እንደደፋችባት ሰጠይቃት እግሯን ታጥባ እንደደፋችው ትነግረኛለች😂😂😂።ወዲያው ዶርም ቆልፈን ወጣን።ፕሮክተሮቹም ካንዴም ሁለቴ መጠው አጡኝ(እድሌ😜)።በዛው ረሱት መሰል እኔንም ተውኝ።እና ኢቺን ገጠመኝ መቼም አረሳትም።😂😂😂 ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

ሰላም ቤተሰብ የግቢ ትውስታ ሲባል ሁሌ የማረሳውን ትውስታየን ላካፍላችሁ ነገሩ እንዲህ ነው ከዛሬ አራት አመት በፊት በወሎ ዩኒቨርስቲ ደሴ ካምፓስ አዲስ እንደገባን ከእለታት አንድ ቀን ከምሽቱ 1፡30 ገደማ ከሁለት የዶርም ልጆች ጋር ሆነን ከ አንዷ ጓደኛየ እህት ዘንድ እቃ ለመመለስ እየሄን ሳለ ማብራት ጠፋ እኛም አጋጣሚ ብሎኩ የተራራቀ ስለነበር አንመለስም ብለን በሞባይላችን እያበራን ሄድን። ዶርሙ መጨረሻ ፍሎር ነበር ደረጃውን እንደጨረስን ወደ ዶርም ልሄድ ስንል ጬኸት ሰማን ቀልድ መስሎን ነበር ከዛ እሪታው አቀለጠችው ጬኽት ወደሰማንበት አቅጣጫ ባትሪያችንን ዞር ስናደርግ የሆነ ሰው ፊቱንበጥቁር ብርድ ልብስ ተሸፍኖ በር ላይ ቁሟል🦹‍♂️።ስናበራበት ወደኛ መጣ ደነገጥን ከዛ መሮጥ ጀመርን🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️። በጣም ደነገጥን የፍሬሽ ነገር እኛ የምናውቀው ሴት ብሎክ ወንድ እንደማይገባ ነው ። ከዛ ደረጃውን እየዘለልን በድንጋጤ በዛላይ ማብራት የለ። አንዱን ደረጃ ወርደን ስንጨርስ ሂደን ከግርግዳ ጋር እንላተማለን። እውነት የምላችሁ ከመጨረሻ ፎሎር ግራውንድ ድረስ ደረጃ ብዙ ጊዜ ልወድቅ ነበር። እማይደረስ የለም ከብሎኩ ወጣን አረፍን ብለን አንዷ ጓደኛችን ከኃላ ነበረች እየጠበቅናት እያለ ሁለት ሴቶች ከ ውጭ ገቡ ሰውየውን ሲያዪ እንዲሁም ጬኸቱን ሲሰሙ እየሮጡ ሲወጡ በዛ ሰአት ያለሁበን አለቅም አብራኝ የቆመችው ሮጠች 🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️ ፍትልክ ጥላኝ መሮጥ ጀመርኩ ብርድ ስለነበር ካልስ ለብሸ ነበር ጫማው ለስላሳ ስለነበር እያዳለጠኝ እንዴት ልሩጥ እንደምን ተፍጨርጭሬ ዶርም ደረስኩ ትንሽ ከተረጋጋሁ በኃላ አንድ እግሬ ጫማ አጣሁት ቢፈለግ ጠፋ እኔ ማጥለቅ አለማጥለቄን አላቅም መሮጤን ብቻ እንጂ። ከዛ መጨረሻ ከዶርም ውጭ ተገኘ።። አይ ፍሬሽ መሆን ለካ ነገሩ የጮኸችው ልጅ ሰይጣን ይዟት ነበር👹👹👹 ሰውየው ደግሞ የጊቢ ዘበኛ ነበር ጩኸቱን ሲሰማ ለማጣራት ሄዶ እየተመለሰ ነበር። እኛ ግን እኛን የተከተለ መስሎን ነው። ይሄን ገጠመኝ መቼም አልረሳውም። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

የተለየ ገጠመኝ ባይኖረኝም ትኩስ ወጥ ለማስጨለፍ ከጓደኛዬ ጋር ከአንዱ ድስት ወደአንዱ ድስት ምንንከራተተው እና ግማሽ ድስት ወጥ አልቆ አዲስ እስኪመጣ ቆመን ምንጠብቀው ነገር ናፍቆኛል😔😔 መደወላቡ ይግደለኝ😘 ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

ገጠመኝ ታድያስ ቤተሰብ ....ሰላሌ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዓመት የገጠመኝን ገጠመኝ ላጫውታችሁ አንድ ቀን ምሽት ነው ወደ ዶርም ልገባ ስል 2 ፖሊሶች በር ላይ ነበሩ ያው ተግባቢ ስለሆንኩ ሰላም አልኳቸው ሰላም አሉኝና አንዱ ይሄን ማብሪያ ማጥፊያ(switch) ማነው የሰበረው አለኝ አላቅም አልኩት ለምንድነው ምትሰብሩት ሲለኝ ጥጋበኛ ይሆናል የሰበረው ከቤተሰቦቻችን በተለቀመ ብር ተሰርቶ የሀገረ ሀብት ምናምን ስለው አሪፍ ነው አስተሳሰብህ አለኝ ከዛ ደና ደሩ ብያቸው ገባሁ። ስገባ ጫት እየቃሙ ነበረ የዶርም ልጆች እኔ ዝምብዬ handout ማንበብ ጀመርኩ ትንሽ ቆይቶ ዶርምተሪ መጣ በሩ አልተቆለፈም ነበር በርግዶ ሲገባ ጫቱን አየ ምንም ሳይል ቀጥ ብሎ ሄዶ ፖሊስ ጠራ። እስኪመጣ ግን ጫቱን በመስኮት ወረወሩ። የመጡት ፖሊሶች አጋጣሚ ቅድም ያዋራዋቸው ነበሩ። ብቻ ባጭሩ ወደ ውጪ አስወጥተው ደበደቡን በመሀል አንዱ ፖሊስ አየኝና አንተ ጥሩ ልጅ አልነበርክ እንዴ? አለኝ ከዛ ዶርምተሪው አይ እሱ ና ያ የሉበትም ብሎ ገባን። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

📢 የግቢ ገጠመኞች!😂

📚 Adis Ababa university : general Physics worksheet 💬 It contain 12 questions ፦ ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

💬 Gonder university : general physics worksheet : ✅ It contain three chapters፦ 📚 chapter one (6 questions) 📚 chapter two (7 questions) 📚 chapter three ( 6 questions) ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

📢   በሶ ❗️ በሶ ሳትይዝ ካንፓስ እንዳትሄድ.....! 📚 በሶ ሲባል ምን ትዝ አለኝ መሰላቹህ ፍሬሽ እያለሁ ጥቂት በሶና ስኳር ይዜ ነበር እናም የሆነ ቀን ውግ ይድረሰኝ ብዬ በሶ መጣት አማረኝ ፤ አምሮኝም አልቀረ ውሃ ቀድቼ በሶና ስኳሬን ማሚ በነገረችኝ መሰረት mix አረኩና በበሶው ላይ ውሃ ጨምሬ shake ማድረግ ጀመርኩ ፤  ትንሽ ወዝ ወዝ እንዳረኩት ግን ድምፅ አልባ ቅጥቀጣ ብቻ ተረፈኝ ምንሼ ብዬ በርገድ ሳደርገው ገራሚ ሁኖልኛል እንዴዴዴ ይቺም የሴት ስራ መሆኗ ነው ❓ እረ አልሰማሽም ብዬ ውሃ ብጨምርም በሶዋ ገንፎነቴ ይሻለኛል ብላ ግግም አለች  ፥ እንገግም ካልንማ ካንቺ አናንስም ብዬ በማንኪያ ጥርግ አድርጌ እንክት.( እና የላቤን ውጤት ልደፋ ሲያምራችሁ...!) 📚 ሁለተኛ በሶ አልበጠብጥም ብዬ ልገዘት ስል አንዱ የዶርም ልጅ ጠኔው ሞርሙሮት መሰለኝ በኔው ውሃ በጥበጥ አርጎ የበሶ ነፍስ አድንነትን አስረዳኝ ። እኔም በዛው የበሶ አበጣበጥን ተማርኩ ማለት ነው ። በሶ እንዴት ይበጥበጥ .... ❓ Apparatus of በሶ 🍼 የበሶ ዱቄት (beso flavour) 🍼 ውሃ በሃይላንድ 🍼 መበጥበጫ ዕቃ 🍼 ስኳር (ከበሶው ጋር ካልተፈጨ) 🍼 ማንኪያ or piece of paper 🍼 በርሃብ የተመታ አፍ፣ሆድ እና ከርስ 💡 Procedure of shaking በሶ( ለኔ ቢጤ ወንዶች...! ) 1⃣ በመጀመሪያ የምንችለውን ያህል ውሃ በመበጥበጫው መጨመር 2⃣ በውሃችን ልክ ስኳር መጨመር ( ለ500ml water 3 የስኳር ማንኪያ sugar ) 3⃣ ስኳሩንና ውሃውን ማዋሃድ( Either ማማሰል or መበጥበጥ ) 4⃣ ሶስት ማንኪያ የበሶ ዱቄት  መጨመርና በመበጥበጥ ማዋሃድ 5⃣ የበሶ ውህዱ ርሃብ የሚጨምር ድምፅ እስኪሰጥ ድረስ የበሶ ዱቄት መጨመር 6⃣ በርሃብ የተመታውን አፍ በግሩም በሶ ነፍስ መዝራት ...አለቀ ..!       አዘጋጅና አቅራቢ ሼፍ ሙጃ ረዳት ዞግ  Ok ሼፉ ለሴሚስተር ምን ያክል በሶ ይበቃናል ❓ ለnon ካፌ ተማሪዎች ሶስት ኪሎ በሶ በቂ ነው ከተቻለ ስኳሩንም አንድ ላይ ብታስፈጩት ለመያዝና ለመበጥበጥም ምቹ ነው።  ለስፖርተኛ ተማሪዎች አስር ኪሎም ብትይዙ ሸክሙ አይጎዳችሁም ( በጠፋ ስኳር አስር ኪሎ ተሸክመህ በኋላ....)  እንደኔ በሶ የማይደላቹህ ከሆነ ደግሞ ዳቦ ቆሎ ኩኪስ ምናምን ግድ ነው ። 📚 በሶ ማለት ግቢ ውስጥ ነፍስ አድን ነገር ናት so እንዳትንቋት ቁርስ ባትበሉም የርሃብ ስሜት እንደፈጠርኩባቹህ ይገባኛል በጣም ይቅርታ ...! ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

📚ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል Medicine እየተማሩ ያሉ ልጆች ስለ መግቢያ ፍተናውን ሙሉ መረጃ የሰጡበት ፋይል 💡ይሄ አላችሁ ማለት በቃ የሚቀርብላችሁን Entrance Exam እንድለፋችሁ ቁጠሩት 🔍ሁሉም መረጃ በዚህ አለ። 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

📊 የ ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ _ በ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ የ Entrance ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ በነፃ Medicine የሚያስተምር ግቢ ነው። 🎩 ትመርቃችሁ ስታበቁ እዛው ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ተቀጥራችሁ እንድታገለግሉ ይደረጋል። 📚 እነኚን ልትጠየቁ ስለምትችሉ ከወዲሁ ተዘጋጁባቸው ❓Basic public health Medical questions 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

+6
📚Modules ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

+9
📚Modules ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

📢 አንዲት እህታችን "Fresh ተማሪ ሆኜ የገጠመኝ ነገር ነበርና ላጋራችሁ" ብላናለች አንብቡት። ❗️ለሴቶች ብቻ ነው ወንዶችን አይመለከትም ይሀውላቹ ሴቶችዬ ልክ ግቢ ገብቼ ሳምንት ምናምን ከቆየው በኋላ ነበር ብዙ ወንዶች ስልክ ቁጥሬን ከየት እንደሚያገኙ ባላውቅም ይደውሉልኛል ስተገቡ ታዩታላቹ በተለይ ቆንጆ ከሆንሽ አያድርስ ነው ያም ይሄም በፍቅርሽ የወደቀ ነው የሚያስመስለው እኔ ብዙም ቶሎ ሰውን የምቀርብ አይነት ሰው አይደለሁም ተናዳጅ ነኝ እናም ለሚደውሉልኝ ብዙም ጥሩ መልስ ስለማልሰጣቸው ይሰደቡኛል ደሞ የሚገርመው ከሚደውሉልኝ ወንዶች አብዛኞቹ GC ተማሪዎች ናቸዉ Gcwoch ብዙም እንደሌላው ተመሪ አይጨናነቁም እና አብዛኛው የእነሱ ስራ ሴቶችን ማሳደድ ነው በተለይ freshochን እነሱንም ተጠንቀቁ እና አንድ በጣም የሚያስቸግረኝ GC ተማሪ ነበር በጣም ብዙ ጊዜ እንገናኝ ሲለኝ እምቢ አልኩት ከዛ አንድ ቀን ከጓደኞቼ መሀል ጎትቶኝ ሰደበኝ በጣም በሚደብሩ ቃላቶች እውነት ምን እንደነካኝ አላውቅም በጥፊ ብዬው ስመለስ ነው እራሴን ያወኩት ደነገጥኩኝ ግን በጣም ተናድጄ ነበር ከየት እንደመጡ እንኳን ያላወቋቸው ተማሪዎች ከሁዋላ ሲጮኹ እና ሲያሾፉብኝ ሰምቼ ምንም አላልኩም ዝም ብዬ መንገዴን ቀጠልኩ ከዛ ቀን በኋላ ብዙ ወንዶች እየተጠቋቀሙ ያቺ እንትናን የመታችው እያሉ ያሾፉብኛል ነገ አንዱ ጠብ ሲያረግሽ እና ዬለ ይሉኛል ምንም ቢሉ ግድ አይሰጠኝም ነበር ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ እና ፍቅር ምናምን ነገር ብዙም አይደለዉም ግን First Semester ሊያልቅ አከባቢ የሆነ ልጅ ተዋወኩ ከልጁ ጋ በጣም ተቀራረብን በጓደኛዬ አማካኝነት ነበር የተዋወቅነው በቃ ምን ልበላቹ በየቀኑ እንደዋወላለን ወደድኩት ሁሉ ነገሩ ደስ ይላል በማጠናበት ሰአት space እየመጣ ትመለሺያለሽ እያለ ይዞኝ ይወጣ ነበር በቃ ማጥናት አልቻልኩም ከዛ አንድ ቀን እወድሻለሁ አበረን እንሁን ምናምን አለኝ። አቤት ያኔ የነበረው ደስታዬ ምንም ማሰብ አልፈለኩም አብረን ሆነን ትምህርትም ተረሳ ማንበብ ሙሉ በሙሉ ባልተውም እንደ ድሮ አልነበረም ገና ፍቅር ከመጀመራችን break ደረሰ በየቀኑ ነበረ ምንደዋወለው ........ውጤት ተለቆ ሳየው በጣም ነበር የደነገጥኩት 3.07 ነበር ያመጣሁት አልጠበኩም ነበር እራሴን ማስተካከል አለብኝ ብዬ ባስብም ጊቢ ስሄድ ግን አልቻልኩም በቃ ሲጠራኝ እሄዳለሁ በቃ የሆነ ጊዜ አብረን ማጥናት ጀመርን ግን አልሆነም እሱ GC ነበርና ብዙም አያነብም ግን እንደ ድሮ አይደውልልኝም እኔ ነበረኩ ምደውልለት በቃ በጣም ጨንቆኝ ማለቀስ ነበር ስራዬ ወይ ከትምህርቴ አለሆንኩ ይባስ ብሎ አንድ ቀን "በቃ ላንቺ ያለኝ ስሜት ቀንሶዋል" አለኝ ያኔ ይሄን ቃል ከአፉ ስሰማ መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ ደስታዬ ነበር። በጣም የሚያስጠላ ጊዜ ነበር ምንም እራሴን መሆን አልቻልኩም አስከ ዛሬ ድረስ እንደምንም ጓደኛዬ አየተቆጣችኝ አያፅናናችኝ ማንበብ ጀመርኩ ግን በቃ ብቻ ከባድ ነው final ተፈትነን ወደየቤታችን ገባን እስከ ዛሬም አንድ ቀን ተሳስቶ እንኳን ደውሎልኝ አያውቅም ፈጠሪ ይመስገን ye second semester ወጤታ ምንም አይልም ነበረ 3.42 ነበረ ያመጣሁት ግን እሄ ሁሉ ነገር ባይኖር አሪፍ ወጤት ይኖረኝ ነበር። ❗️ እባካችሁ ሴቶች ግቢ ስትሄዱ የሄዳቹበትን ዓላማ አትርሱ ሁሉም በጊዜው ይደርሳል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

#WachemoUniversity በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 15 እና 16/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለሬ
#WachemoUniversity በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 15 እና 16/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለሬመዲያል ፕሮግራም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 21 እና 22/2015 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ • የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው • ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው • የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት • 3×4 ፎቶግራፍ (8) • የሌሊት አልባሳት • የስፖርት ትጥቅ በ Re-admission እና Withdrawal የወጣችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ዳግም ቅበላ የካቲት 17 እና 18/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

#ድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት አምጥተው በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን የካቲት 20 እና 21 /2015 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋ
#ድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት አምጥተው በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን የካቲት 20 እና 21 /2015 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ተማሪዎች በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት አድርጉ። ተማሪዎች ስትሄዱ ፦ - የ8ኛ፣ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰዳችሁበትን ማስረጃ - የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ዋናውን እና ኮፒ - 3×4 ስድስት ጉርድ ፎቶፍራፍ - የመኝታ አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መሄድ አለባችሁ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013                       @Keleme_2013

ማስታወቂያ‼️ አድማ ላይ ለምትገኙት ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ አመት ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት...!! ✅በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት 🙏🙏 ⭕️TOP STUDENT
ማስታወቂያ‼️ አድማ ላይ ለምትገኙት ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ አመት ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት...!! ✅በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት 🙏🙏 ⭕️TOP STUDENTS " TOPPERS HOME" #ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 #share #share 🙏🙏🙏🙏🙏 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝 ▶️🌟💧@ethio_schools ▶️🌟💧@ethio_schools ▶️🌟💧@ethio_schools 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝

📌Wollo University Emerging Technology Final Exam ለማነኛውም ጥቆማ @topstudads #share #share 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝 ▶️🌟💧@ethio_school
📌Wollo University Emerging Technology Final Exam ለማነኛውም ጥቆማ @topstudads #share #share 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝 ▶️🌟💧@ethio_schools ▶️🌟💧@ethio_schools ▶️🌟💧@ethio_schools 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝

📌Wollo University Emerging Technology Final Exam ለማነኛውም ጥቆማ @topstudads #share #share 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝 ▶️🌟💧@ethio_school
📌Wollo University Emerging Technology Final Exam ለማነኛውም ጥቆማ @topstudads #share #share 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝 ▶️🌟💧@ethio_schools ▶️🌟💧@ethio_schools ▶️🌟💧@ethio_schools 🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝

Mizan teppi university economics final exam 2013/14 #share #share @ethio_schools @ethio_schools @ethio_schools
Mizan teppi university economics final exam 2013/14 #share #share @ethio_schools @ethio_schools @ethio_schools

Mizan teppi university economics final exam 2013/14 #share #share @ethio_schools @ethio_schools @ethio_schools
Mizan teppi university economics final exam 2013/14 #share #share @ethio_schools @ethio_schools @ethio_schools