en
Feedback
ለ አሻዒራና አህባሽ ጥናታዊ ምላሽ Refutation Of The Asharis & Ahbash

ለ አሻዒራና አህባሽ ጥናታዊ ምላሽ Refutation Of The Asharis & Ahbash

Open in Telegram

የቻናሉ ትኩረት! ✔ የአህባሽን ግድፈቶች በመረጃ ማጋለጥ እና ጥናታዊ ምላሾችን ማሰራጨት! ✔ ተዉሒድ እና ሽርክን በማብራራት የነብያትን ተልዕኮ ማስገንዘብ 👍 የአህባሽ ብዥታ በዒልም ሲረታ! قناة خاصة بنشر الردود العلمية على فرقة الأحباش الضالة باللغة الأمهرية الإثيوبية

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
1 008
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ስለ አህመድ አር’ሪፋዒ ከራማ በአህባሾች የተነገረ ቅጥፈት! የአህባሹ መሪ አብዱላሂ አልሀረሪ ስለ ሪፋዒያ ከራማ ሲናገር እንደኖረ ሁሉ የሱ ተማሪ የአህባሹ ሸኽ ጀሚል ሀሊም ስለ አህመድ አር ሪፋዒ ከራማ ቅጥፈት ያወራል። አህመድ አሪፋዒ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም) ቀብር ዘንድ ሄዶ (አሰላሙአለይኩም) ብሎ ሰላምታ በማቅረብ በግጥም እጃቸውን እንዲዘረጉለት ሲጠይቃቸው። ነብዩ ከቀብሩ (ውአለይኩሙሰላም ልጄ ሆይ! በማለት ከመለሱለት በኃላ ቀብራቸው ተሰንጥቆ እጃቸውን አወጡና ሪፋኢይ በተሰበሰቡት ሰዎች ፊት እጃቸውን ሳመ) ይለናል። ይህ አይን ያወጣ ውሸት መሆኑ አያጠያይቅም። በቅድሚያ ታሪኩ ለመከሰቱ የሸይኹ አድናቂዎች ከሚቀባበሉት ወሬ ባለፈ የሚቀርብ ምንም አይነት መረጃ የላቸውም። ይህ ደግሞ ታላቅ ክስተት እንደመሆኑ እውነት ቢሆን ኡለማዎችና የታሪክ ሰዎች ባላለፉት ነበር። ሌላው አላህ ሰዎች ከሞቱ በኀላ እስከ ትንሳኤ ድረስ በነሱና በዱንያ ሰዎች መካከል ግርዶሽ አድርጓል። አላህ እንዲህ ይላል፦ { حَتَّىٰۤ إِذَا جَاۤءَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ رَبِّ ٱرۡجِعُونِ * لَعَلِّیۤ أَعۡمَلُ صَـٰلِحࣰا فِیمَا تَرَكۡتُۚ كَلَّاۤۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَاۤىِٕلُهَاۖ وَمِن وَرَاۤىِٕهِم بَرۡزَخٌ إِلَىٰ یَوۡمِ یُبۡعَثُونَ } አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡ «በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶሽ አልለ፡፡ [አልሙእሚኑን: 99-100] ይህ ባይሆን ኖሮ በሰሐቦች ዘመን መልእክተኛው ተነስተው ቢያናግሯቸው የሚያስመኝ ብዙ ፈተናዎች ሲከሰቱ ባስነሳቸው ነበር። አህመድ አሪፋዒ የኖረው በሂጅራ አቆጣጠር (512–578) ነበር። ይህ ቢከሰት ኖሮ ከሱ በፊት በድንቁ የሰለፎች ዘመን የኖሩት ሰሀቦች፣ ታቢኢዮችና ሷሊሆች ለዚህ የተገቡ ነበሩ። ከዚህም አልፎ በሞቱ ግዜ ሰሀቦች ዱንያ ስትጨልምባቸው ያፅናኗቸው ነበር። ግን ይህ አልሆነም! ታላቁ አሊም ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ስለዚህ ቅጥፈት ተጠይቀው የመለሱትን ብንመለከት፦ ይህ ምንም እውነትነት የሌለው ባጢል። አላህ እንደነገረን መልእክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህ በፃፈባቸውን ሞት አልፈዋል። { إِنَّكَ مَیِّتࣱ وَإِنَّهُم مَّیِّتُونَ } (አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው) አዝ’ዙመር: 30 በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ መላእክት የኡመቶቻቸውን ሰላምታ እንደሚያደርሷቸው፣ ሰዎች ሰለዋት በሳቸው ላይ ሲያደርጉም እንደሚያደርሷቸውና እንደሚመልሱም ተናግረዋል። በዚህ ዙርያ ብዙ ሀዲሶች ተዘግበዋል ሆኖም እጅ ዘርግተው ሰዎችን ይጨብጣሉ የሚል መረጃ ግን የለም። ይህ ክስተት ሀሰት ለመሆኑ ይህ በቂ መረጃ ነው። ሆኖም ተከስቷል ቢባል እንኳ ሸይጧን ተመሳስሎበት እሱንና ተከታዮቹን እያጭበረበራቸው ነውና አላህን እንድንፈራና ዲናችንን ምንጩ በመረጃ እንድንከተል አደራ ብለዋል። ምንጭ፦ አል መጅሙዕ 9/310 አህባሾች የሚሰብኩትን የጥመት ጦሪቃ #ሪፋዒያ ሰባኪዎች እንደ አንዳንድ የሂንዱ እና የኢቫንጀሊዝም ሰባኪዎች በድግምትና ከጅኖች ጋር በመመሳጠር ተአምር ፈፀምን ይላሉ። እራስን በስለት የመውጋትና እሳት የመንካት ከራማ አለን በማለት ይመፃደቀሉ። ይህ ፍፁም የሷሊሆች መንገድ አይደለም!! አላህ ከጥመት ይጠብቀን አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ ሰኔ 28/2014 @abujunaidposts ___ * ሸይኽ ኡሰይሚን ስለ ሪፋዒያ ጦሪቃ https://youtu.be/68EhI_vDE-I * The Rifaa’is who stab themselves with knives but are not affected by it https://islamqa.info/en/answers/9338/the-rifaais-who-stab-themselves-with-knives-but-are-not-affected-by-it * بطلان تقبيل الرفاعي يدى النبي صلى الله عليه وسلم https://youtu.be/hSEoUm_FgG0 #ከራማት #ዱስቱር #ሱፊያ #ሪፋዒያ #አህባሽ #አሻዒራ _ @abujunaidposts

(የመጨረሻ ክፍል) አሕባሽ ሲጨመቅ

አሕባሾች ደዕዋ ላይ ያስከተሉት መዘዝ

አሕባሾች የዑለማዎች ቅርስ ላይ ያስከተሏቸው መዘዞች

ከሴቶችና ከአለባበሳቸው ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ የአሕባሾች ፈታዋ

የተሳሳቱ ገንዘብና ኸምርን የሚመለከቱ የአሕባሾች ፈታዋ

የተሳሳቱና ችግሮችን ያስከተሉ የአሕባሾች ፈትዋና የፊቅህ ነጥቦች

የአሕባሾች ረብሻ በዓለም ዙሪያ

አሕባሾችና ኡማውን መከፋፈል

አሕባሾች ያመጡት የእምነት/ የዐቂዳ መዘዝ

ዑለማዎችን ማጣጣል በማን ተጀመረ? ጉዳቱስ ምን ይመስላል?

አሕባሾች ለዘመናችን ታላላቅ ዑለማዎች ያላቸው አመለካከት

አሕባሾች ለቀደምት የዲን ዑለማዎች ያላቸው አመለካከት

አሕባሾችን በተመለከተ የፈትዋና ኢስላማዊ ጥናቶች ቋሚ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫና ማብራሪያው

የሽይኹል- ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ እምነት (ዐቂዳ) ምን ይመስላል?

ሽይኹል- ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ ማን ናቸው?

አሕባሾች ወሃቢያ የሚሏቸው ሰዎች ላይ የሚዋሹበት ምክንያት ምንድነው?

ስለ ሸይኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ በዘመኑ የነበሩ ሊቃውንት ምን አሉ?