cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Central Ethiopia Regional Health Bureau

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ 🔵 https://m.facebook.com/centralethiopiarhb 📞 📩

Show more
Advertising posts
3 601
Subscribers
-124 hours
+257 days
+12230 days
Posts Archive
በኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ወቅት ነባራዊ ሁኔታዎች እና የተሰጡ ምላሾች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉ ተገለጸ። ኳሊቲ ሄልዝ ኬር አክቲቪቲ ፕሮጀክት ከሚደግፋቸው የሀዲያ ዞን 3 ወረዳዎች እንዲሁም ከጉራጌ ዞን 1 ወረዳ ላይ የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተከናወኑ ተግባራት አንዲሁም የተሰሩ የምላሽ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው እለት በሆሳዕና ከተማ መደረጉን የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ገልጿል። የክትባት አገ/ት ጥራትና ደህንነትን የማሰ ጠበቅ ፋይዳና አገ/ት አሰጣጥ ላይ ያሉ የአፈጻጸም ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችል መግባባት ላይ ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑም ተገልጿል። የማ/ኢት/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና-ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የጤና አገ/ት ተደራሽ ለማድረግ የክትባ ጥራትን ማስጠበቅ ተገቢ ነው ብለዋል። በጤና ተቋማት የሚሰጡ የክትባት አገልግሎቶች ጥራትና ደህንነታቸው ተጠብቆ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የጤና ኤክ/ን ባለሙያዎች የጤና ባለሙያዎች የሚያበረክቱት አሰተዋጽኦ ጉልህ ፋይዳ ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ልዩ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አቶ ወልደሰንበት አክለው ገልጸዋል። በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች፣ ሕጻናትና ሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጂሶ የክትባትን ጥራት ለማስጠበቅ በየወቅቱ የተሰጡ ሥልጠናዎች ያመጡት ውጤት ላይ ተገቢው ክትትል ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ ስለክትባት አገ/ት ለተለያዩ ባለድሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት የማህረሰቡ ንቃተ ጤና ከፍ እያለ መምጣቱን የጠቆሙት አቶ ተስፈዬ መሠረታዊ የሆነ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የተለያዩ አደረጃጀቶችንና ተጽእኖ ፈጣሪ አካላትን እንዲሁም ምቹ አጋጠማቸዎችን በመጠቀም አጠናከሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በ22 ወረዳዎች መከሰቱን ከቀረበው ሰነድ መረዳት የተቻለ ሲሆን ከክልል ጤና ቢሮ እስከታችኛው መዋቅር በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ባደረጉት ርብርብ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስከትል የነበረውን የጤና ጉዳት እና ሞት መቀነስ መቻሉም ተገልጿል። የክትባት ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ በክትባት ተደራሽ የሚደረጉ ታላሚዎች ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ ክትባት እንዲያገኙ በማድረግ ፍትሀዊ የሆነ የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ጠይቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመላክተው የፖሊዮ በሽታ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን መነሻ በማድረግ የክትባት አሰጣጥ ሥርዓቱን ማጠናከር ይገባልም ተብሏል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም በጋምቤላ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች አዲስ በፖሊዮ በሽታ ወረርሽኝ የተያዙ ሰባት ሰዎች መገኘታቸውን መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን ሥርጭቱን ለመግታትና ለመቆጣጠር መረባረብ እንደሚገባ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መልዕክት የሚጠቁም በመሆኑ የቅድመ መከላከል ስራዎችን ማጠናከር አንደሚገባ ተገልጿል ፡፡ ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ የክልላችን አካባቢዎች የተከሰቱ ወረርሽኞች ካስከፈሉት ዋጋ ትምህርት በመውሰድ የቅድመ መከላከል ስራዎችን አጠናክሮ ለወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት መገንባት ይገባልም ተብሏል። የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...
👍 1
የግልና የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ ተላላፊ በሽታዎችን ከመከላከላ አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ገለፁ። ተላላፊ በሽታዎችን በ85% በመከላከል ረገድ የግልና የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው የጠቆሙት አቶ ማሙሽ በሀገር ደረጃ የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጲያ ንቅናቄ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት በመግለጽ እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክረምቱን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን የግልና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ፣ መጸዳጃ ቤቶችን በአግባቡ በመያዝ እና በመጠቀም በተላላፊ በሽታዎች ምክንያት የሚከሰተውን ህመምና ሞት ለመቀነስ ርብርብ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጲያ በ3 ወረዳዎች የጽዱ ኢት/ያ ፓይለት ፕሮግራም ተጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ የዚህ ፕሮግራም ዓላማም በማህበረሰብ እና በግለሰብ ደረጃ መጸዳጃ ቤት እንዲኖር በማድረግ እንዲሁም የምግብ አዘገጃጀት እና አያያዝ፣ የውሃ አያያዝ ጥሩ እንዲሆን የማስተማር ስራ መጀመሩን እንዲሁም የንጹህ ውሃ አቅርቦት የግብዓትና የፋይናንስ ተግባራትን በማሳለጥ የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በየደረጃው ርብርብ ሊደረግ ይገባል ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል። የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...
👍 3
ግንቦት 20/2016 ዓ/ም የዜጎችን የጤና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና ጥራት ያለው  የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በመረጃ እና  በእዉቀት ላይ የተመሠረተ የዳሰሳ ጥናት  መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ  ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብኣትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከተለያዩ ዞኖችና ከጤና ተቋሟት ለተዉጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የጤና ተቋማት አገልግሎት ጥራት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት አተገባበር ላይ  ዉይይት አካሂዷል። በክልሉ በሚገኙት በተመረጡ ዞኖችና  ጤና ተቋማት ላይ  መሠረታዊ ከተቀመጠው ዝቅተኛ መስፈርት አሟልቶ ከመስራት አንጻር ችግሮችን በመለየት እና ሊሻሻሉ የሚችሉ ነገሮችን ግብአት ሊሆን በሚችል መልኩ በመጠቀም ደረጃዉን የጠበቀ  የዳሰሳ ጥናት መጀመሩ ታዉቋል። የቢሮው ምክትልና የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር  አቶ ፋሲካ አለሙ  የዳሰሳ ጥናቱን አስመልክቶ የማጠቃለያ ሀሳብ ሲያሰቀምጡ የዜጎችን የጤና  ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና ጥራት ያለው  የጤና አገልግሎት ተደራሻ ለማድረግ የሚያስችል በመረጃ እና  በእዉቀት ላይ የተመሠረተ የጤና ተቋማት ስታንዳርድ ትግበራ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት በቅንጅት እና በትኩረት መስራት እንደሚገባ  ገልፀዋል ። አቶ ፋሲካ አክለዉም ይህ ጥናት ዉጤታማ ሆኖ መሬት እስከሚወርድ ድረስ በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮች እና ባለ ድርሻ አካላት በቂ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ። አቶ ጎሳ ደርቤ ከጤና ሚኒስቴር ጤናና ጤና ነክ ተቋማት  ቁጥጥር ዳይሮክቶሬት ባለሙያ የዳሰሳ ጥናቱን አጀማመር አስመልክቶ እንደተናገሩት ወገኖቻችን የተሻለ የጤና  አገልግሎት እንዲያገኙ ትክክለኛ  እና እዉነተኛ  መረጃ በማሰባሰብ የጤና ተቋማት ያሉበትን  ስታንዳርድ በመለየት እና በመገምገም ዉጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። አቶ ተፈራ አሰፋ የዳሰሳ ጥናቱን መረጃ ከሚሰበስቡት ዉስጥ አንዱ ሲሆን ይህ መድረክ መረጃዉን ለማሰባሰብ  በቂ ክህሎት ያገኘበት መሆኑን ገልፆ ሥራዉ በትኩረትና  በቅንጅት የሚሰራ ስለሆነ ሁላችንም በመደጋገፍ በተጠያቂነት መንፈስ መስራት አለብን በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል ።     የማዕከላዊ  ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ
Show all...
👍 2
👍 4
የባህል ህክምና አዋቂዎች አገልግሎት መስጠት ያለባቸው ተመዝግበውና በተፈቀደላቸው የሙያ ደረጃ ብቻ መሆን እንዳለበት ተገለፀ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብኣቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በዘርፉ ሃገር በቀል እውቀቶች እንዲጎለብቱ እየሰራ መሆኑንም ጠቁሟል። ባለስልጣኑ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ምግብና መድሃኒቶችን ደህንነትና ህገወጥ ዝውውር ከመቆጣጠር ባሻገር የባህል ህክምናን የመከታተልና የመደገፍ ሃላፊነት እንዳለበትም ተጠቁሟል። ከዚህ መነሻም በቅርቡ በሆሳዕናና ወልቂጤ ማዕከላት 300 ለሚሆኑ የጤና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ሰጥቶ የህብረተሰቡን ጤና ለማስጠበቅ በልዩ ትኩረት ወደ ተግባር መግባቱም ተነግሯል ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ እንዳሉት ተቋሙ በባህል ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችን የመመዝገብ፣ ፈቃድ የመስጠትና ዘርፉ በህጋዊ መንገድ አስተዋጽኦው እንዲጎለብት የማድረግ ሃላፊነት ተጥሎበታል። ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው ህጋዊ አካል ፈቃድ ሳያገኝና ከተፈቀደለት ደረጃ ውጭ የባህል እና ተደጋጋፊ ወይም አማራጭ ህክምና አገልግሎት መስጠት አይችልም ያሉት አቶ ፋሲካ ያም ሆኖ ፈቃድ ሳያወጡ መስራትና የተጋነኑ ማስታወቂያዎችን ማስነገር በአሁኑ ወቅት እየተለመደ መምጣቱን ተናግረዋል ። ስለሆነም በክልሉ ያሉ የባህል ህክምና አዋቂዎች ተመዝግበው ብቃት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡና እውቀቱ የትውልድ ቅብብሎሽ እንዲኖረው ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ከተፈቀደላቸው ደረጃ በላይ መስራት በህግ እንደሚያስጠይቅ አስታውቀዋል ። ዘርፉ በጤናው ሴክተር ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ሀገር በቀል እውቀቶችን ማዳበርና ለባህል ህክምና አዋቂዎች የበለጠ የስራ ነፃነትና የህግ ከለላ ሰጥቶ ከዘመናዊ ህክምና ጎን ለጎን እንዲበለፅግ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል ። ህብረተሰቡ በተለይ የምግብና መድሃኒት ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ህገወጥ ንግድና ዝውውርን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ፣ ጥቆማዎችን በመስጠትና ከጤና ተቆጣጣሪዎች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ጤናውን እንዲያስጠብቅ አቶ ፋሲካ ጥሪ አቅርበዋል። ለማ/ኢት/ክ/መ/ኮ/ጉ /ዘገባ የማ/ኢት/ክ/መ/ ጤና ቢሮ
Show all...
1
👍 3 2