cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Live your life ሕይወትህን ኑራት

የነፃነት መድረክ ለማስታወስ ያህል ሁላችንም በምክንያት ነው የተፈጠርነው:: ምክንያቱን መርምሮ ማወቅ እና የኛ ድርሻ ነው:: ሕይወትን እስከ ጥግ ኑራት @livurlif @livurlif @livurlif

Show more
Advertising posts
12 887Subscribers
-824 hours
-547 days
-24030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መጠበቅ በጣም ከባድ ነገር ነው... ⭐️ባል እና ሚስት ልጅ ለመውለድ አስበው:: ፈጣሪያቸውን ለምነው ከብዙ ጥረት በኃላ ሚስት ማርገዝዋ ሲታወቅ ትልቅ ደስታን ይጭራል:: ግን ሁሉም ገና መጀመሩ ነው ረጅም ጉዞ አለ... 9 ወራትን መጠበቅ አለባቸው ሁለቱም:: ምንም ያህል ቢጓጉም ያልጊዜው ሆዷን ቀደው ልጁን ሊያወጡት አይሞክሩም አይችሉምም:: እና ለስኬት የሚያስፈልጉ እንደ ማንኛውም ባህሪዎች ወይም ልማዶች መጠበቅ አንዱ ነው:: ለዛም መጠበቅን መለማመድ በጣም አስፈላጊ ነው :: ቀላል ነገር አይደልም አንዳንዴ ራስን ማሞኘት ይመስላል ምንም በሌለበት ትልቅ ነገር ተመኝቶ እየሰሩ መጠበቅ:: መጠበቅ ወስጥ ያለው ትልቅ ነገር እምነት ነው:: እምነት ደሞ ማረጋገጥን አይፍልግም:: ካረጋገጥን በኃላ የሚመጣ እምነት እምነት አይባልም:: እምነት ያለምንም ማረጋገጫ ይሚቀድም ነገር ነው:: አምኖ ወጤት እስኪመጣ ጠብቆ ለመቆየት ደሞ ፅናት ይጠይቃል:: አንዳንዴ ምንም ተስፋ ሰጪ ነገር እናጣለን እና የእውነት ፅናታችን እና እምነታችን ሚፈተነው ያኔ ነው:: ምን ያህል ነው መጓዝ የምንችለው?  ምን ያህል ነው መጠበቅ ምንችለው? አንድ ተረት ልንገራቹ.... 👵ተረት ተረት👴 .......... ⭐️ ሁለት ዋሽንት🪈🪈 ሚጫወቱ ልጆች ነበሩ:: እና ሁለቱም በጣም የሚያምር እና መሳጭ ሙዚቃዎችን 🎶🎶🎵ይጫወቱ ነበር... ነገር ግን በተለየ መልኩ አንደኛው ልጅ ዋሽንቱን በሚጫወትበት ሰዓት ሁሌም 🌧🌧ዝናብ🌧🌧 ይዘንብ ነበር እና ሰዉ ይህ ነገር በጣም ስለሚያስደምመው እና ስለሚደንቀው እሱን ልጅ አብልጠው ይወዱት ነበር :: ግን ሁሌም ጥያቄ🤔 ይሆንባቸዋል እንዴት ተምሳሳይ ነገር እየተጫወቱ የሁለቱም ሙዚቃ እያማረ ለአንዱ እየዘነበ ለአንዱ አይዘንብም?  እና የሆነ እለት ዋሽንት ሲጫወት የሚዘንብለትን ልጅ ለመጠየቅ ወሰኑ የተለየ የሚያረገው ነገር ካለ ለማወቅ... እናም ጠየቁት... የልጁ መልስ በጣም አስገራሚ ነበር:: እኔኮ የተለየ ነገር ስለማረግ አይደለም የሚዘንበው: ዋሽንቴን የምጫወተው እስኪዘንብ ድረስ ስልሆነ ነው:: አላቸው ይባላል... በዚህ ልጅ እና በዛኛው ያለው ልዩነት በፅናት የመጠበቅ እና ያለመጠበቅ ነው:: 💡@livurlif 💡@livurlif 💡@livurlif ሼር ማረግ መብታቹ ነው 😊
Show all...
👍 2🔥 1👏 1
ልዩነት ትልቁ ውበታችን ልዩነታችን ነው ባይ ነኝ:: በጣም ሰፊ ቃል ነው:: ጥቂቱን ብቻ እናንሳ እና አንተን የመሰለ አንድም ሰው እንደሌለ አስበህ ታቃለህ አንቺስ ውዴ..? አስባቹ ሊሆን ይችላል ግን ደግማቹ አስቡት እስኪ አንድም አንተን ወይም አንቺን የሚመስል የለም ልዩ ነህ /ልዩ ነሽ :: አሁን ላይ ትልቁ ወረርሽኝ ሌላውን ለመምሰል የሚደረግ ጥረት ነው :: መቼም የማይሳካ እያደር ህመም የሚፈጥር በሽታ:: ዓለም(አለምን እየወከሉ ያሉ የሆኑ ህዝቦች) ለብዙ ነገር ያስቀመጡት መስፈርት አለ:: እና አብዛኛው ሰው እሱን መስፈርት ለማሟላት እና ሙሉ ለመሆን እየሞኮረ ያለ ይመስለኛል:: እስኪ እኔ ማነኝ ምንድን ነውስ ሚያስደስተኝ ፍላጎቴስ ምንድነው...? እኔ እኔን የተቀበልኩ ቀን ነው ቀኑ ያበራልኝ መልኬን ቀለሜን ፅጉሬን አቋሜን ድምፄን መላው አካላቴን ማንነቴን... :: ሌላውን በመምሰል ወይም ለምን ይሄ እንድዛ አልሆነም ብሎ በማሰብ ብዙ ጊዜዬን የማባክን ሰው ነበርኩ:: ዓለሙም ባስቀመጠው መስፈርት ይሄ ይጎልሻል ይሄ ይቀራል ሊል ይሞክራል... Really ማነው ያለህ ቆይ ያልኩት ጊዜ ነው ነገር አለሙ የተቀየረው:: በራስ መተማመን ቀና ማለት መጣ አረ ልታይ ልታይ እራሱ ሳልል እቀራለው... አምላካችን የሰውን ልጅ አሳምረን ፈጠርነው ብሎ ሲያበቃ ማን ወንድ ነው ከሰው ላይ አቃቂር ሊያወጣ ሚነሳ...? ሁላችንም በልዩነታችን ውብ ነን:: ሌላን ለመምሰል በሞከርን ሰዓት ወረርሽኙ ያገኘናል::  ልዩ መሆን እንዴት ደስ ይላል በማንኛውም መንገድ በማንነት በሃሳብ በአመለካከት ባካሄድ በባህል በብሄር በዘር በሃይማኖት በቀለም...  በሁሉም ነገር 💡@livurlif 💡@livurlif 💡@livurlif ሼር የማረግ መብታቹ በህግ የተጠበቀ ነው 😊
Show all...
ሰህተት አንድን ከዚህ በፊት አድርገነው የማናውቀውን(እንዴት እንደሚደረግ የማናውቀውን) ነገር ለማድረግ በምንሞክርበት ሰዓት የሚፈጠር እክል ሲሆን ጥፋት ደሞ አንድ ሰው እያወቀ ትክክል ያልሆነ ነገር ሲሰራ የሚፈጠር ክስተት ነው:: የሰው ልጅ ባህሪዎች ብዙ ናቸው::ተሳሳችነቱ እና አጥፊነቱ ከነሱ መሃል ናቸው:: ሁለቱም ትክክል ያለመሆንን ሁኔታ ሲያሳዩ የመጀመሪያው አብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ ነገር አይደለም ምክንያቱም አዲስ ነገር ለመሞከርብዙ ሰው ስለሚፈራ አርፎ ጎመን በጤና ብሎ ካለማወቁ ጋር መቀመጥን ይመርጣል ወይም የማውቀው በቂዬ ነው ባይ ነው:: ሁለተኛው በብዛት በተደጋጋሚ ሰዎች ላይ የሚታይ ባህሪ ነው:: ራሳችንን እንፈትሽ እስኪ ሕይወታችን ላይ ትክክል እንዳልሆነ ውስጣችን እያወቀ (እየነገረን) ግን ማድረጋችንን የምንቀጥለው ምን ያህል ነገር አለ?? ራሳችንን ሳንዋሽ ከፈተሽን የምናረገ አብዛኛው ነገር እንደዛ እንደሆነ እንረዳለን:: ለምን ግን ያንን ነገር እኮ ማድረግ አንፈልግም በማረጋችንም ደስተኛ አይደለንም ካለፈ በኃላ ብዙ ጊዜ ራሳችንን ስንወቅስ እንገኛለን:: ታዲያ ለምንድነው የምናረገው?? ሕይወታችን ላይ የምናከናውነው ተግባራችን አብዛኛው የፈለግነው ሳይሆን ያመንበት ነው የሚሆነው:: እዚህጋ እንዴ እኔ እኮ ያኛው ነገር ትክክል እንዳልሆነ አምኛለሁ ልንል እንችላለን:: ነገር ግን ትክክል እንዳልሆንን አውቀናል እንጂ አላመንም:: ምንድነው ልዩነታቸው...? በኑሮአችን ከ75% በላይ የሚሆነው ተግባራችን የሚሆነው አስበን በምናረገው ሳይሆን ባመነበት እና ወስጣችን በሰረፀው (program) በተደርገው መልኩ ነው ይለናል ቤተሰብ ሳይንስ:: ማለት...? ሰፊ ነው ታሪኩ ከጀመርነው ማለቂያ የለውም ለናንተ ልተወው እና እንድትጎግሉት... አብዛኛው ተግባራችን አስበን በምናረገው ካልሆነ የሚወሰነው⭐️ ልብ ⭐️ ሊባል የሚገባ ነገር ነው ማለት ነው:: ያመንበትን ነገር ውስጣችን የሰረፀውን ራሳችንን ወደሁዋላ አርገን ልናጤነው ይገባል ማለት ነው :: ምን አይነት ሃሳቦች እምነቶች አመለካከቶች ናቸው ውስጣችን ያሉት...? ስለምናረገው ነገር ያለን ሃሳብ እምነት አመለካከት ላይ ይወስናል ድርጊታችን ወይም የሚመጣው ውጤት ወደ ውስጥ ጠልቆ ማየትን ይጠይቃል:: ቆም ብሎ ምንድነው እየተካሄደ ያለው🤔🤔 ራስን መፈተሽ🙇🙇‍♀... ዝም ብለን ራሳችንን እናጥናው ምን ያህሉ የምንፈልገው ነው ምን ያህሉ የማንፈልገው? በዛን ሰዓት ያለንን ስሜት አመለካከት እንቃኘው ራሳችንን jugde ሳናረግ ጥፋቶቻችንን መቃኘት ልማድ ይኑረን እና ቀስ🚶‍♀🚶‍♀🚶🚶 በቀስ ደሞ ትክክል እንዳልሆነ እና ምን ያህል አፀያፊ ተግባር እንደሆነ ለራስ መንገር በተደጋጋሚ... በተደጋጋሚ ... "እዚህ ጋር ወቀሳ ሳይሆን እንደ ምክር ቢጤ ብናረገው"........በመቀጠል እንዴት መቀየር እንደሚቻል መፍትሄ ወይም መፍቻ ቁልፎችን🔑🔑🗝🗝🔑🗝 ማስቀመጥ:: በሚቀጥለው ተመሳሳይ ነገር ሲፈፀም ትኩረት በመስጠት ነገሩን ረጋ ብሎ ማየት እና ከመክፈቻ ቁልፎቹ መሃል አንዱን🗝 በማንሳት ቀሎ የታየንን መክፈት:: ሙሉ በሙሉ በአንድ ሙከራ ከጥፋት መፃዳት የማይታሰብ ነው ነገር እንደሆነ ግልፅ ነው...ግን በሆነ መንገድ ጥፋቱን መቀነስ:: ይህን ሂደት እየደጋገምን በሁሉም ቁልፎች ሁሉንም ጉድለት ከፍተን ማረም እስክንችል ድረስ መቀጠል ከዛም አዲስ እምነቶች እና አመለካከቶችን መገንባት:: ባለፍነው መንገድ ተንተርሰን አዲሱ እምነት ሕይወት እስኪዘራ ድረስ በሁኔታዎች ሁሉ ለራስ እየደጋገሙ መንገር በመጨረሻም ሳናውቀው ራሳችንን ከጥፋት ርቀን ወይም የምንፈልገውን ነገር በመተግበር ላይ እናገኘዋለን:: ቀላል አይደለም .....................................ሒደት ነው ተስፋ ባለመቁረጥ የሚያረጉት የፅናት ጉዞ... እያንዳንዱ ለውጥ ይህንን ሒደት ያስተናግዳል በጣም ባጭሩ... በመሃል አቋርጠን አይሆንም ብንል አዎ አይሆንም ምክንያቱም አልጨረስነውማ:: አንድ ሰው መድረሻውን የሆነ ቦታ አርጎ መንገድ ጀምሮ ሲጓዝ ከርሞ ደክሞት ወይ በሆነ ምክንያት አቋርጦ ቢመለስ እዛ ቦታ መድረስ አይቻልም ማለት ይቻላል? ይህ ነው በአብዛኛው እየተፈጠረ ያለው እና መልካም ጉዞ ከፅናት ጋር ... ፅናት ጎረቤታቹን አይደለም 😊❤️ 💡@livurlif 💡@livurlif 💡@livurlif ሼር ማረግ መብታቹ ነው 😊
Show all...
👍 4🔥 1
አንዳንድ ጊዜ ሁሉም አንድ ሆነው እኛ በምንለይበት ሰዓት የተሳሳት ነው እኛ እንደሆንን ይሰማናል:: ዞር ብለን ስናየው ደሞ የአላማችን ጥንካሬ እና ትልቅነት አስፈላጊነት ሁሉንም ነገር ሲሸፍን እናያለን:: አላማችን ብለን በያዝነው ጉዞ ላይ ተቃዋሚው ሲበዛ ይታያል:: እርግጠኛ መሆን ያለብህ ነገር አላማህ ከፈጣሪ ጋር የማያጋጭህ መሆኑን ብቻ ነው:: ሃሳብህ ከራስህ አልፎ ሌላውን ለመጥቀም ከሆነ በዓላማህ ፅና:: አንተ ብቻ ነህ ውስጥህ ያለውን የምታቀው እና ውጤቱም የሚታይህ:: ለምን ወይም እንዴት ማየት ተሳናቸው ብለህ ለማስረዳት አትሞክር:: ጉልበትህን መጨረስ ነው ትርፉ አንተ ካየከው ይበቃል:: የሚያስፈልገውም እሱ ነው ሁሉም ነገር ፈተና ነው:: አላማ ከፈጣሪ እስከሆነ ድረስ ምን ያህል ብቁ ነው ይህ ሰው ምን ያህልስ መሄድ ይችላል የእውነት ይፈልገዋል እየጠየቀ ያለውን የሚሉ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ናቸው እየመጡ ያሉት በነዛ ተቃዋሚዎች ምክንያት:: አሁን ላይ ቢቃወሙህም ግን ወደመድረሻህ እያደረሱህ ነው በፅናት ከቀጠልክ:: አንድ አባባል አለ ሁሉንም ማስደሰት ከፈለክ መሪ ሳይሆን ice cream ሻጭ ሁን ይላል:: 😊አመሰግናለሁ መልካም ጊዜ ❤️ 💡 @livurlif 💡 @livurlif 💡 @livurlif
Show all...
👍 1🔥 1
Show all...
🔥 4👍 1
📍የተሻለ አለህ በአውሎ ንፋስ ውስጥ ብትሆን፣ ዶፍ ዝናብ ቢወርድብህ፣ ዋጋህ ያነሰበት፣ መኖርህ የማይቆጠርበት፣ አበርክቶትህ የማይታይበት፣ ስራህ የማያፈራበት፣ ማንነትህ የማይመረጥበት ስፍራ ብትኖር እንኳን ፈጣሪ አብሮህ ካለ ሁሌም የተሻለ ከፍ ያለ ነገር አለህ። 🔷ምንም እንኳን እምነታችን ቢጎድል፣ ክፋታችን ቢበዛ፣ ሃሳባችን ቢያንስ፣ ምግባራችን የወረደ፣ ስራችንም አሳዛኝ ቢሆንም ፈጣሪ ግን ጥሎ አይጥለንም።፣ ትቶ አይተወንም ሁሌም ይመለከተናልና መቼም ችላ አይለንም። የተውን ሰዎች ይኖራሉ፣ ያገለሉን፣ የተጠየፉን እንዲሁ እንደዋዛም የናቁን ሰዎች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን በፈጠረን አለመገፋታችን አለመረሳታችን ነው። ♦️የተሻለ አለህ! ከዛሬው የላቀ፣ ከትናንት የገዘፈ፣ ከአሁንህ ያየለና ከፍ ያለ ስፍራ ይኖርሃል። የማይቀየሩ የሚመስሉ ከባድ ሁኔታዎች ይቀየራሉ፤ ይወርዱ የማይመስሉ ሸክሞች፣ ይፈቱ ያልመሰሉ ችግሮች፣ ይስተካከሉ ያልመሰሉ ውጥንቅጦች ይወርዳሉ፣ ይፈታሉ፣ ይስተካከሉ። እምነትህ ቢፈተን ግራ አትጋባ ይልቅ ለተሻለ ክብር እንደታጨህ አስተውል፤ በፈተናህ ብዛት አትደናገር ይልቅ የድልህ ቀን ቅርብ እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት የማትሸበር፣ ለምድራዊ ፈተና የማትበገር፣ ከፈጣሪህ ውጪ እንዳልሆንክ አስተውል። 🔷አንዳንዴ ማሳለፍ እየቻልን አቅፈናቸው የምንቀጥላቸው ብዙ ኮተቶቻችን ጣእሙን ማየት እንዳንችል ሁሉ ነገራችንን ዘግተንባቸዋል። ለማማረር እንጂ ለማመስገን ስንፈናል ለማዘን እንጂ ለመደሰት ጉልበት አጠተናል። መቆየት በማይገባን ቦታ ላይ በመቆማችን ማሳለፍ የሚገባንን አላፊ ሃሳቦችን እንዳያልፋ መንገድ ዘግተንባቸዋል እሰኪ ነቅነቅ እንበል እናሳልፋቸው የሚመጡት ሁሉ እንደአመጣጣቸው እንሸኛቸው አኛም ከቆምንበት አስተሳሰብ ስናልፍ ሁሉም ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን። ሁሉም ያልፍ የለ ትላንትናም አልፏል ዘሬም ታልፋለች ነገም ትቀጥላለች እኔም አንተም እናልፋለን ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል።ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የያዘ፣ በሁሉ ውስጥ ያለው አምላክህ ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ አትጠራጠር፤ ለተሻለው ስፍራ እንደሚያበቃህ እምነት ይኑርህ። 🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል። ውብ አሁን ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Show all...
5👍 2
Show all...
👍 4🔥 3