cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ

አላህን በደስታህ ጊዜ ተዋወቅ በችግር ጊዜ ያውቅሀልና!!!

Show more
Advertising posts
397
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
በመላው አለም የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ከሀገራቸው የተፈናቀሉበትን "አል-ናቕባ" 76ኛ ዓመት ዘክረዋል! ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 7/ 2016) ... በዌስት ባንክ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ዛሬ ግንቦት 15 2024 እለት "የአል-ናቕባ" ማለትም ታላቅ መቅሰፍት የወረደበት እለት የአደጋ ግዜ ሳይረን ለሰባ ስድስት ሰከንድ በማሰማት ዘክረዋል። ... እ.ኤ.አ ግንቦት 15 ቀን 1948 የእስራኤል ወታደሮች ፣ ሚኒሻዎችና ታጣቂዎች 750,000 ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው በማፈናቀል እንዲሰደዱ ያደረጓቸው ሲሆን ላለፉት ሰባ ስድስት አመታት ወደ ሀገራቸው እና መሬታቸው እንዳይመለሱ በማገድ በጎረቤት ሀገራት የስደተኛ ጣቢያዎች ለመኖር የተገደዱበት ክስተት የተከሰተበት በመሆኑ ፍልስጤማውያን ዕለቱን አል-ናቕባ ማለትም ታላቁ የመከራ ቀን በሚል በየአመቱ ይዘክሩታል። ... በዚህ አመት እስራኤል ባለፉት ሰባት ወራት በጋዛ በመፈፀም ላይ ያለችው ጥቃት ከ34,000 በላይ ንፁሀን ፍልስጤማውያንን በተገደሉበት ሁኔታ እና ጥቃቱ በቀጠለበት ሁኔታ የሚዘከር መሆኑ ፍልስጤማውያን እለቱን ከሰባ ስድስት አመታት በፊት ቅድመ አያቶቻቸው፣ አያቶቻቸው ከተሰማቸው ሀዘን ተመሳሳይ በሆነ ወይም በላቀ ከባድ ሀዘን ተውጠው የሚዘክሩት እንደሚሆን የአልጀዚራው ከፍተኛ ፖለቲካ ተንታኝ " ማርዋን በሻራ" አስተያየቱን ይገልፃል። ... እስራኤላዊው የታሪክ ምሁር "ፕ.ሮ ኤላንን ባፔ"የእስራኤል መንግስት ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ማፈናቀል ከ1948 ቀደም ሲል የጀመረ ሲሆን በእኔ ሃሣብ አል-ናቕባ 1948 የተከሰተ ቢሆንም ላለፉት ሰባ ስድስት አመታት የቀጠለና ያልተቋረጠ አሳዛኝ ክስተት ነው። በማለት እለቱን ገልፆታል። ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
የሲርለና የበጎ አድራጎት ድርጅት በስልጤ ዞን 4 የውሀ ጉርጓዶችን በአንድ ቀን አስመርቆ አገልግሎት መስጠት አስጀመረ! ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 07/2016) ... በ4 አመት ውስጥ ብቻ የውሀ ችግር ላለባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች 271 የውሀ ጉርጓዶችን አስቆፍሮ የአካባቢያቸውን የውሀ ችግር መቅረፍ የቻለው የሲርለና የበጎ አድራጎት ድርጅት በዛሬው እለትም በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ውሀ ለተቸገሩ ወገኖች በተለያዩ ቀበሌዎች 4 ጉርጓዶችን አስመርቆ ስራ አስጀምሯል። .. የተለያዩ አህለል ኸይሮች በሚያደርጉት እገዛ የውሀ ጉርጓዶችን የሚያስቆፍረው የሲርለና ዛሬም በህይወት ለሌሉት  እናታቸው እና አባታቸው ሰደቀቱል ጃሪያ እንዲሆንላቸው ወጪውን በሸፈኑ ቤተሰቦቿ እና ኸይር ስራን ለመስራት እጃቸውን ከመዘርጋት ወደኋላ በማይሉ ሌሎች አህለል ኸይሮች በተደረገ ድጋፍ 4 የውሀ ጉርጓዶችን በማስመረቅ ስራ አስጀምሯል። .. ረጅም መንገድ በእግር በመሄድ ንፁህ ውሀ የማያገኙ የነበሩት የስልጢ ወረዳ አራቱ ቀበሌ ነዋሪዎች ለየሲርለና ስራ አስኪያጅ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ እና ለኸይር ስራው መሳካት ትልቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ደማቅ አቀባበል በማድረግ እና ስጦታዎችን በመስጠት ደስታቸውን ገልፀዋል። .. ይህ ኸይር ስራ ነገ እና ከነገ ወዲያም የሚቀጥል ሲሆን 9 የውሀ ጉርጓዶችን በማስመረቅ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ... (እርሶም በዚህ የኸይር ስራ የመሳተፍ ፍላጎት ካሎት +251911221582 Ustaz Nuru Turki 0947636323 , 0968747475 በነዚህ አድራሻዎች የሲርለናዎችን ማግኘት ይችላሉ።) ... ¤ሀሩን ሚዲያ በቦታው ተገኝቶ ያጠናቀረውን ዝግጅት በቅርቡ ወደናንተ ያደርሳል! ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ?!! ቢስሚላህ ! ከ 25 አመት በሗላ የጠፋኝን ሰዉ ወንድሜ የህያ ኢብኑ ኑህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፎት ባይ ገረመኝ !! የዛን ዘመን አፍላ የቁርአንና የዳዕዋ ንቅናቄን ከየት እንደመጣ ሳናዉቅ ነበር የተቀላቀለን ። ፂሙ ያደገ የፓኪስታን ልብስ የለበሰ በቀኝ እጁ ሲዋክ በግራ እጁ ሙስበሃ ይዞ የፈጅርን ሰላት ለመስገድ የሂፍዝ ተማሪዎች ዉዱእ ማድረጊያ ላይ በዛ ብርድ ወቅት እንጣደፋለን ። ከመሀላችን ሞቅ ባለ ከፍ ባለ ድምፅ “ እናንተ ወጣቶች በናንተ ጊዜ ዲን ሲደፈር ነብያችን ሰ.ዐ.ወ ክብራቸዉ ሲነካ እናንተ እያላችሁ እንዴት ይሆን ለጅሀድ ተነስ እኔ አሰለጥንሀለሁ !” የሚል የወጣቱን ስሜት በሚቀሰቅስ መልኩ በቁጣ ንግግር አደረገ ። ብዙዎቻችን ሙሀመድ ሱሩር በሚል የቀረበንን ሰዉ ያኔ ተዋወቅነዉ ከፈጅር ሰላት በሓላ የቁርአን ሀለቃ ላይ አብሮን ተቀመጠ ። መስጅድ ላይ በተበላሸ ምላስ የቁርአን አያቶችን እየሰባበረ ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ የዋሁ ማህበረሰባችን እና ወጣቱ ተከተለዉ ። በጣም የሚገርሙ ሊታመኑ የማይችሉ ለሀገር ሲል ከኤርትራ ጋር በተደረገ ጦርነት መሳተፉንና ለኢስላም ሲል አፍጋኒስታን ድረስ ዘልቆ የተዋጋበትን ባዶ ታሪክ ለወጣቱ ይግተዉ ጀመር አንዳንዱ በየት ብለን ጅሀድ በወጣን እስኪል ድረስ የማልረሳዉ ሁሌ ግን ጥያቄ የሚሆንብኝ የነበረዉ ጠዋት ከሀለቃ በሗላ ከቁርስ በፊት ወደ ዉጭ እንዳንወጣ እንከለከል ነበር ። ለምን አትሉም ? ሙሀመድ ሱሩር ካራቴ እየሰራ ጩሀቱን እንጅ ስራዉን ማየት እንዳንችል ምክኒያቱም በጩሀቱ ብቻ ካራቲስት እንደሆነ እንድንመሰክር ። ማህበረሰባችን በዚህ ብቻ አልቆመም በዲኗ ጠንካራ የሆነች ልጅ ተፈልጋ ተዳረ ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የሙሀመድ ሱሩር ማንነት ይጋለጥ ጀመረ ። ይቀጥላል !! Abdurahman Sultan
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ከ ሐጅ ቪዛ ውጪ ሐጅ ማድረግ እንደማይፈ ቀድ የሳውዲ የሐጅ ሚኒቴር አስጠነቀቀ። የሳውዲ አረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ፣ ከሐጅ ቪዛ ዉጪ በማንኛውም የቪዛ አይነቶች ሐጅ ማድረግ እንደ ማይፈቀድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለፀ። የጉብኝት ፣ የቱሪስት ፣ የትራንዚት : የስራና መሰል በሳውዲ አረቢያ የሚሰጡ ቪዛዎችን በመጠቀም ሐጅ ለማድረግ የሚሞክሩ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል። ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል። ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል። ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል። "ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል። የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
Show all...
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በክፍለ-ከተማው ውስጥ ከሚገኙ ዳኢዎች ጋር የትውውቅ መርሃ-ግብር ማድረጉን ገለፀ! ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 07/2016) ... የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በክፍለ-ከተማው ውስጥ ከሚገኙ ዳኢዎች ጋር ባደረገው የትውውቅ መርሃ-ግብር ላይ ወደፊት አብሮና ተባብሮ ለምስራት ከስምምነት መድረሳቸውንና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ለሀሩን ሚዲያ በላከው መረጃ ገልጿል። ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ? (ክፍል 2 ) ቢስሚላህ ! በቁጥር አንድ እንደ ጀመርኩላችሁ የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ቤተሰቦቹ የጁ ዉስጥ እንደ ሆኑ ያወራል ( በርግጥ አንዳቸዉም ቤተሰቡ ነኝ ብሎ የመጣ አላዉቅም ) ሰዉየዉ በአንድ ወቅት መርሳ ከተማ ላይ ለትልቅ እስላማዊ ዝግጅት ስንጓዝ ከፊት ወንበር ጋቢና ላይ ተቀምጧል ታላላቅ ዓሊሞችና ጎደኞቼ ከሓላ ተቀምጠን ከካራቲስትነት ከፍ ብሎ በሆነ ጦርነት ( ስሙን ረሳሁት ሀገር ዉስጥ በተደረገ ) ላይ ከሄሊኮብተር ሲወርድ እንደተጎዳ አገግሞ እንደ ዳነ ያወራል ። ይህ ሰዉ በማበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ የቁርአን ሂፍዝ ማእከሉ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ ሚስትም አገባ ትንሽ ቆይቶ ሀኪም ነኝ የህክምና ት/ት መማር አለባችሁ ብሎ ከመርከዝ ልጆች አምስት ሰዉ መርጦ በጊዜዉ እኔ አብዱራህማን ሱልጧን ዶ/ር አህመድ ኑርየ ኢንጂነር ሙሀመድ ጀዉሀር ( አሏህ ይማረዉ ሁላችሁም ዱዓ አድርጉለት ) ሌሎች ሁለት ወንድሞቼ ረሳሃቸዉ ሁነን ለአንድ ሳምንት መርፌ እንዴት እንሚሰጥ አስተማረን እኔም በሳምንት የመርከዙ ሀኪም ሆኜ እርፍ !። በጊዜዉ ለህክምና ብዙ ትልልቅ ሰዎች ይመጡ ነበር ቪ B2 ወግቶ በጊዜዉ የማይታመን ብር ነበር የሚጠይቀዉ ለምን የሚለዉም አልነበረም ። ሚስት የሓላ ሓላ ስቃዪ በዛ ከአንድ የዲን መምህር ነኝ ከሚል ሰዉ የማይጠበቁ ነገሮችን ስታይ ለማን ትናገር ማንስ ያምናታል ። የመርከዝ ልጆችም ለሁለት መከፈል ጀመሩ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ያዮትንና የጠረጠሩትን ልጆች የኢማን ድክመት አለባቸዉ ፡ ጅሀድ ይጠላሉ የተለያዮ ስም እየለጠፈ የመርከዙ ልጆችን ከፋፈላቸዉ በመሀባ እንባ ይራጩ የነበሩ ወንድማማቾች ተኮራረፉ ። ባጭሩ የወልዲያ ሰዉ ዳዒ አለመሆኑን እየተረዳ ይመስላል ስለዚህ ክትትል ጀምሯል ። የሚገርሙ ታሪኮች ይቀጥላሉ ወልዲያ የጀመዓዉና የሚስቱ ታሪክ ከቆቦ እስከ ኮምቦልቻ …..። © Abdurahman Sultan
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን በሀገሯ ለማሰራት የሰራተኛ ምልመላ ልትጀምር መሆኑ ተገለፀ! .. ኢትዮጵያ እና ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በኩዌት ሀገር የስራ አድል አንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነቱን ለማጠናቀቅ የመጨረሻው ሂደት ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ .. የመግባቢያ ስምምነቱ በዚህ ወር መጨረሻ ይፈረማል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ የሰራተኞችን መብት፤ አሰሪዎች የስራ ውል በሚያቋርጡበት ጊዜ  ሰራተኞች ስለሚያገኙት ክፍያ፤ የሰራተኞች የሳምንት፣ የአመት እረፍት እና ተያያዥ ስምምነቶችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ .. የሰራተኛ ምልመላው ስምምነቱ እንደተፈረመ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ ኩዌት ያጋጠማትን የሰራተኞች እጥረት ይቀርፋልም ነው የተባለው፡፡ ...
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር ታሪክ አለን ከዚህ ሰው ጋር፡፡ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ በጎዳና ላይ ደዕዋ ሲያደርግ ታውቁታላታችሁ፡፡ ምንም ማንንም የማይፈራ ሙጃሂድ ነው። ስፒከሩ በተዳጋጋሚ ታስሮበት በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተትም አጋጥሞኛል፡፡ ከልጅነት እስከ ወጣትነትና ጎልማሳነት ምናልባት እስካዛሬዋ እስከመጨረሻዋ የዱንያ ላይ ቀን ድረስ ሐያቱን በሙሉ በደዕዋ አሳልፏል፡፡ አላረፈም። ኢስላምን ለማድረስ ሁሌ እንደተጓዘ ስለማየው ቤት ይገባ ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ ብዙ ጊዜ፡፡ ዛሬ ሻሻመኔ ላይ ድንገት ማረፉን ሰማሁ፡፡ ፈቂ ገለቶ አላህ ይዘንልህ፡፡ ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፤ በሞተበት ነገር ላይም ይቀሰቀሳል፡፡ ደጋግ ባሮችህ ወዳንተ እየመጡ ነው። አላህ ሆይ! ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ እንላለን ።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ ዩዝድ መደገፊያ ትራሶች መግዛት ለምትፈልጉ ብዛት 8 ፍሬ 4ፍሬ ትንንሽ ትራሶች ዋጋ 9600 P.N 0988159585
Show all...
በኳታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው የአለም ሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ተፋ ከአለም አቀፍ ሙስሊም ምሁራን ኘሬዝዳንት ዶ/ር አሊ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋየው ተገልጿል። ... የታላቁ አል-ነጃሺ 00 ማዕከል ማስጀመሪያ ኘሮግራም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጋር በመተባበር የአል-ነጃሺ 00 መልሶ ግንባታና ልማት ኢኒሼቴቨ (ARDI)ጋር በመሆን የኘሮጀክት ማስጀመር የማብራሪያ ኘሮግራም መካሄዱ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት የጠ/ም/ቤቱ ኘሬዝዳንት በኳታር ዶሃ እያደረጉ በሚገኙት የስራ ጉብኝት ከአለም አቀፍ ሙስሊም ምሁራን ኘሬዝዳንት ዶ/ር አሊ ቀራህ ዳጊ ጋር ኘሮጀክቱ ለሃገር እና በቀጠናዉ ባለዉ ጠቀሜታ ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል ተብሏል። ...
Show all...