en
Feedback
ጥልቅ እይታዎች

ጥልቅ እይታዎች

Open in Telegram

💜 የማራኪ እና አስደማሚ ጥበቦች ስብስብ‥⚘

Show more
3 389
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-830 days
Posts Archive
photo content

💜 ፈጅር ሰላትን አላህ የወደዳት እና ከሷ ጋር መገናኘትን የወደደላት ልብ እንጂ ማንም አያገኛትም ። አላህ ይወፍቀን 😢

💜 ሰሃቦች ሱናን ሱና ስለሆነ ይተገብሩት ነበር… እኛ ግን ሱናን ሱና ስለሆነ እንተወዋለን!!

💜 ከመግሪብ አዛን በኋላ ሐራም ነገር ያው ሐራም ነው አዛኑ ሐላል አያደርገውም ።

💜 የረመዳንን ብርሃን እየተጠባበቁ ያሉ በፅልመት የተሞሉ ነፍሶች … አላህ ደርሰው ፣ ጾመው ፣ ታዝኖላቸው ፣ ይቅር ተብለውና ከጀሀነም እሳት ነፃ ከሚወጡት ያድርገን ።

💜 በሐራም መንገድ ያገኘሽ ለሐላሉ አይፈልግሽም ።

💜 ህመም ሲመጣ ከወንጀል ትቶብታለህ መዳን ሲመጣ ደግሞ ወደ ወንጀሉ ትመለሳለህ‥

💜 ዘፈን የሚከፈትበትና ሰላት ወደ ኋላ ሚዘገይበት ቤት ባለቤቶቹ ሩቅያ ሳይሆን ወደ አላህ መመለስ (ተውባ) ነው የሚያስፈልጋቸው ።

💜 ከቸርነት ሁሉ መጥፎው ማለት የመልካም ስራዎችህን ምንዳ ለሌሎች በሐሜት ፣ በቅጥፈት ፣ ነገር በማዋሰድና በመስደብ መለገስህ ነው ። ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ)

💜 ስለ እከሌ ወንጀል ሲነግሩህ " አላህ ለኛም ለርሱም ይቅር ይበለን " በልና ዝም በል ።

💜 ለምንድነው ያዘንከው? ብለው ሲጠይቁህ ๏ ኢስቲግፋሬ ትንሽ ነው ቁርአንንም እርቄዋለሁ ብለህ በእውነት መልስላቸው ።

💜 ወንድ ልጅ አይኑን ባለመስበሩ ከባድ ሒሳብ ይጠብቀዋል‥ ๏ ሴት ልጅም መሸፈን የነበረባትን በመግለጧ ከባድ ሒሳብ አለላት ።

💜 ወንጀል ሲታወቅ ይበተናል ሲተውና ሲረስ–ሳ ደግሞ እየበዛ ይሄዳልና ተውባህ ከማድረግ እንዳንዘናጋ ።

💜 መረጋጋትና ስክነት የሚመጣው ያለን ነገር በቂ መሆኑን ስንገነዘብና ስናመሰግን ነው ። አልሀምዱ ሊላህ

💜 የእርጅና ጊዜ ላይኖረን ይችላልና ወጣትነታችንን በደጋግ ነገራቶች እንሙላው ።

💜 ጀነት ውስጥ ንፋስ የማይሰብረውና ፀሐይ የማያጠወልገውን ተክል ትከሉ ። ሱብሃነላህ ፣ ወልሀምዱ ሊላህ ፣ ወላኢላሀ ኢለላህ ፣ ወላሁ አክበር

💜 ከሰለፎች አንዱ ሰደቃ ከማብዛቱ የተነሳ ሰዎች ሲወቅሱት አንድ ሰው ከአንድ ቤት ወደ ሌላ ቤት መቀየር ሲፈልግ ለቆ ከሚሄደው ቤት ውስጥ አንድን ነገር ያስቀር ነበር ወይ? አላቸው ። #ዱንያን እንደተረዷት በተረዳናት ዛሬ ጁሙዓህ እንደመሆኑ ቀድመውን ወደዛኛው ቤት ለተሻገሩ ቤተሰቦቻችን ሰደቃ ማውጣት አንዘንጋ መልካም ጁሙዓህ

💜 በጣም ከሚያስጠላ የሪያእ አይነት የሆነን ሰው ውዴታ ለማግኘት ብለህ እራስህን ሙጠዋእ እና ዒባዳ ላይ ጎበዝ እንደሆንክ ማሳየት ነው ።

💜 ሰዎችን እንደፈለግክ ብታገለግላቸውና የቱንም ያህል መስዋእት ብትከፍልላቸው ይህን ማድረግ ስታቆም የተጠላህ ትሆናለህ ።

💔 ለገዳዩ ፣ ለአጋዡ ፣ ድርጊቱ ላስደሰተው ፣ ለተሳዳቢውና ዝም ላለው ሁሉ ወየሁለት ። ๏ አላህ ይህን ሁሉ ያለ ቅጣት በከንቱ አያልፈውም ።
💔 ለገዳዩ ፣ ለአጋዡ ፣ ድርጊቱ ላስደሰተው ፣ ለተሳዳቢውና ዝም ላለው ሁሉ ወየሁለት ። ๏ አላህ ይህን ሁሉ ያለ ቅጣት በከንቱ አያልፈውም ።