cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Show more
Advertising posts
13 486
Subscribers
-224 hours
+1187 days
+61430 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
⛔️⛔️ሰበር ዜና! የዘንድሮ የኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የመጀመሪያው በረራ በሰላም መዲና ደርሰዋል።
1 52316Loading...
02
ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል፦ ‹‹ ለሰዎች ብሎ መስራት ሽርክ  ነው፡፡ ለሰዎች ብሎ ስራን መተው ይዩልኝ (ሪያእ) ነው፡፡ ኢኽላስ ማለት ደግሞ ከሁለቱ አላህ ሲያድንህ ነው፡፡›› አል አዝካር ሊነወዊይ (1/33)
1 89728Loading...
03
Media files
1 7286Loading...
04
Media files
1 9861Loading...
05
Media files
3 0337Loading...
06
Media files
3 0639Loading...
07
Media files
3 6469Loading...
08
11 ምላሾች «ሙታንን መጣራት ሰበብ ስለሆነ እንጂ አደራጊው አላህ መሆኑን ስለምናምን ሺርክ አይሆንም!» በሸይኽ ኢልያስ አህመድ NesihaTv https://youtu.be/QEm-jU4lytY ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!! Telegram፡ https://t.me/nesihatv YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCX2E30J71sKpnLQuGr7kt6w Facebook፡ facebook.com/nesihatv WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaaWvl5CXC3Ic7glOv3U @nesihatv
3 5169Loading...
09
Media files
3 33710Loading...
10
Media files
3 81713Loading...
11
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «የጁምዓ እለት አንዲት ሰአት አለች፣ አንድ የአላህ ባርያ ዱዓ አድርጎ ያቺን ሰዓት አይገጠምም፤ አላህ ዱዓውን ቢቀበለው እንጂ።»
3 49311Loading...
12
📌 በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!!  ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በተከበሩት መልእክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። በመቀጠል፤ ያለንበትን የረጀብ ወር በማስመልከት የሚፈፀሙ የቢድዓ ተግባራት ተበራክተዋል። የረጀብን የመጀመሪያ እለት፣ የመጀመሪያ ጁምዓ፣ አስራ አምስተኛውን እለት እንዲሁም ሀያ ሰባተኛውን ቀን ማክበር ቢድዓ መሆኑን፤ በሌሎች ወሮች  እንደሚፈፀሙት የሰኞና ሀሙስ ወይም አያመልቢድ ፃሞች ካልሆነ ወሩን አስመልክቶ የተደነገገ ልዩ ፆምም ይሁን ሰላት እንደሌለ ገልጫለሁ።   ይህ ማለት ግን ረጀብን ከሌሎች ወራቶች የሚለየው ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም።  የረጀብ ወር፤ በሱረቱል ተዉባህ ቁጥር 36  ከተጠቆሙት የተከበሩ አራት ወራት (አሽሁሩል ሁሩም) አንዱ  ነው። አላህ እንዲህ ይላል፤  [إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِنْدَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْراً فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ فَلا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنْفُسَكُمْ] التوبة/36  « አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር፤  በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ (በጥብቁ ሰሌዳ ለውሀልማህፉዝ) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን (የሰየመው) ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤» አልተውባህ 36 عَنْ أَبِي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ , ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ , وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ) رواه البخاري ومسلم. ከአቢ በክራህ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «አመት አስራ ሁለት ወራት ነው፤ ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ”ረጀብ” ወር ነው።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ዙልሂጃ የታወቀው የሀጅ ወር ነው፤  ዙልቂዕዳ ደግሞ ሁጃጆች ወደ መካ የሚያቀኑበት ወር ሲሆን፤  ሙሀረምም ከሀጅ ስነስርአት በኋላ ሰዎች ወደቀያቸው የሚመለሱበት ወር ነው።  አላህ ረጀብንም ከእነዚህ  የረከበሩ ወራት  አድርጎታል።  እነዚህ ወራት (የተከበሩ) ናቸው ስንል፤ 1- እነዚህ ወረሰቶች ጦርነት የተከለከለባቸው ወራት ናቸው።   ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈፀመባቸው እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ ካልሆነ በስተቀር ውጊያ አይፈቀድም። 2- በነዚህ ወራት አላህ ክልክል ያደረጋቸውን ነገሮች መፈፀም በሌላ ወራት ወንጀልን እንደመፈፀም አይደለም። ስለዚህም አላህ እነዚህን ወራቶች ለይቶ ነብሳችንን እንዳንበድል አሳስቦናል፤ «በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ» ።  እራስን መበደል አስከፊ መሀይምነት ነው። በአንድ ሰውና በጌታው መካከል የሚፈፀም እራስን መበደል ለአላህ መፈፀም የሚገባን ሀላፊነት አለመወጣት ነው። በራስ ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ትልቁ  በአምልኮ ፍጥረታትን ከአላህ ጋር ማጋራት “ሽርክ" ነው። ሰዎች ላይ የሚፈፀም በደልም ቢሆን የሚጎዳው ሰሪዉን ነውና እራስን መበደል ነው። ለራሱ ያወቀ በማንኛውም ጊዜ ከበደል ይርቃል።  ኢባደላህ! አላህ እነዚህን ወራቶች አክብሯቸዋልና እኛም ከፍተኛ ክብር መስጠት ይገባናል።  እነዚህ ወራቶች ሲገቡ፤ አላህ ክብርን እንደለገሳቸው ልናስታውስና ከወንጀል ለመራቅ ያለንን ቁርጠኝነት ልናድስ ይገባል። ይህ ልባዊ ኢባዳ ነው።  ወንጀልን በማንኛውም መፈፀም የተከለከለ ቢሆንም በነዚህ ወራት ግን ክልክልነቱ የበረታ ነው። ስለዚህም ከምንም አይነት ወንጀሎች መጠንቀቅ እና ወደ አላህ መመለስ ያስፈልገናል።   ከትናንሽም ይሁን ከትላልቅ ወንጀሎች በአላህ እንጠበቅ።  ሸይጣንን እናሸንፍ! አላህ ከጥፋት ይጠብቀን.. አሚን!!
3 64714Loading...
13
Media files
3 67413Loading...
14
Media files
3 49715Loading...
15
ማንንም ለመስደመም ብለህ አታነብ፣ ለራስህ አንብብ፣ ያኔ በራስህ፣ በዝምታህ፣ በቸልተኝነትህ፣ በምርጫህ ትገረማለህ። ብዙ ነገሮችን በማለፍ ብቻ ተጠቃሚ እንደምትሆን ይሰማሃል ፣ አጉል ክርክር ብዙውን ጊዜ አለመግባባት ወይም የቅድመ ዝግጅት ውጤት መሆኑ ይገባሃል።
4 27833Loading...
16
Media files
3 4588Loading...
17
Media files
3 6129Loading...
18
ለ1445 የአሏህ እንግዶች የአሠልጣኞች  ሥልጠና  ተሰጠ። ሚያዚያ 27፣ 2016 (አዲስ አ በባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት "የዘመነ መስተንግዶ ለአርረሕማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል ለ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የሐጅ ተጓዦች በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ የአሠልጣኞች ሥልጠና መስጠት ጀመረ። ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ  ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ   አብዱልፈታህ መሐመድ ናስር በዘንድሮ የሐጅ ጉዞ የሑጃጁን ክብር የጠበቀና ከወትሮ የተለየ ለማድረግ ምክር ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል። የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደሚጀምር የተናገሩት ኃላፊው የአላህ እንግዶች በጉዞ ወቅት በሐገር ዉስጥና በሳዑዲ እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ እና እንዲደጋገፉ አሳስበዋል። ሑጃጁ የበረራ ጊዜውን እንዲያውቅ ምክር ቤቱ የመረጃ መስጪያ ቁጥር 9933 የከፈተ ሲኾን፣ ከምክር ቤቱ ለሑጃጁ ወቅታዊ መረጃ  በEtho Hajj አጭር መልዕክት ማስተላለፊያ  እየላከ በመኾኑ ሑጃጁ እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል። የሐጅ ጉዞ ቀጥታ ወደ መዲና መኾኑን የተናገሩት ኃላፊዉ ሑጃጁ የሚጓዝበትን የበረራ ቀን እና በመዲና የሚያርፍበትን ሆቴል ከወዲሁ እንዲያውቅ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለያዩ የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል። አብዛኛው የሐገራችን ሑጃጅ ከገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ በመሆኑ ለሐጅ ሲመዘገቡ በሰጡት የስልክ ቁጥር ሳዑዲ ሆነው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት  እንዲችሉ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን ኃላፊው ተናግረዋል። በዛሬው የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ የተሳተፉት ከመቀሌ፣ ከወራቤ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ እና ከፉሪ የምዝገባ ጣቢያዎች  የተመረጡ ሠልጣኞች ናቸው። **** ሸዋል 26፣ 1445 ዓ.ሂ. *​** የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት። ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1
4 0651Loading...
19
🕋 ⁩ሐጅ ድኅነት እና ወንጀሎችን ለማስወገድ  አይነተኛ ፈውስ ነው! የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ 🔶" በሐጅ እና በዑምራ መካከል ምንም ክፍተት ሳታደርጉ በማከታተል ሐጅና ዑምራን ፈፅሙ። እሳት የብረት ጉድፎችን  ሙልጭ አድርጎ እንዲሚያሰወግደው ሁሉ እነሱም ድህነትና  ወንጀሎችን ያስወግዳሉ።" 📚【አልባኒ ሰሒህ ብለውታል (1200)】 ✿ ✿ ✿ ✿ ✿ ✿
4 40314Loading...
20
✨🍃 ሐጅ ከእስልምና ምሰሶዎች አንዱ ነው። ይህን እውነታ አምኖ፣አቅም ኖሮት ሐጅ ያላደረገ ሰው ታላቅ አደጋ ውስጥ ነው።
4 44311Loading...
21
«በጠዋፍ ጊዜ ውዱኣውን ያፈረሰ ሰው፤ ጠዋፉ ተበላሽቷል። በመሆኑም ውዱእ አድርጎ ጦዋፉን እንደገና መቀጠል አለበት እንጂ በመጀመሪያዎቹ የጠዋፍ ዙሮች ላይ ማስቀጠል አይፈቀድለትም።» የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ 📕ፈትዋ ቁጥር (17809)
4 26910Loading...
22
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ 🕋«ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣ የአሏህን ትእዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከኃጢእቶቹ ሙሉ ጠርቶ ይመለሳል» 📚【ቡኻሪ ና ሙስሊም】 💎عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سَمِعْتُ النبي ﷺ يقول: من حجَّ لله فلم يرفث ولم يفسق رجع كيوم ولدته أمه . 📚متفق عليه
5 05916Loading...
23
በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት ይፈቀዳልን? በበአላት ሰሞን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል ከሚለን ፖስቶች መካከል ከፊሎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ናቸው። ለጌታ መወለድ፣ ለጌታ መሰቀል፣ ለጌታ ሞቶ መነሳት (ትንሳኤና) መሰል ክስተቶች እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። አንዳንዴ በስህተት ሌላ ግዜም ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እጅግ ከባድና በአኼራ ዋጋ የሚያስከፍል መዘናጋት ነው!! በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ ክልክል ነው። መከባበር እና አብሮነትን ለማሳየት ከእምነታችን መንሸራተት አይጠበቅብንም። ዲን ከምንም በላይ ነውና ሸሪዓን መተላለፍ ፍፁም ጥፋት ነው!! ፈጣሪ ወለደ ተወለደ የሚለው አስተምህሮ የጥፋትነቱ ክብደት ሰማያትንና ምድርን ሊሰነጥቅ እንደሚቀርብ ቁርአን ይነግረናል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር በመፈፀማቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት ከሙስሊም አይጠበቅም!! (وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰا * لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَیۡـًٔا إِدࣰّا *  تَكَادُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ یَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا *  أَن دَعَوۡا۟ لِلرَّحۡمَـٰنِ وَلَدࣰا *  وَمَا یَنۢبَغِی لِلرَّحۡمَـٰنِ أَن یَتَّخِذَ وَلَدًا *  إِن كُلُّ مَن فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّاۤ ءَاتِی ٱلرَّحۡمَـٰنِ عَبۡدࣰا *  لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدࣰّا *  وَكُلُّهُمۡ ءَاتِیهِ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ فَرۡدًا) [«አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ በእርሱ (በንግግራቸው ምክንያት) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅ አለው ስለአሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም!! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም] Surah Maryam 88 - 95 ለመሆኑ አንድን ካፊር ለሀይማኖታዊ በአል እንኳን አደረሰህ ስትለው፤ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለምን? እንኳን አደረሰህ... ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለማወጅ፣ ለመስቀል ለመስገድና  የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር እንኳን በቃህ! እንኳን አደረሰህ... ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር እንኳን በቃህ! የኩፍር ተግባርን ለመከወን ከሆነ የደረሰው ለምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን እንላለን? እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤ «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው። ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው! ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ።  ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል»  አህካም አህሉዚማህ የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።» መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44  በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርዶችን መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም በአሉን መካፈል ስለሆነ የተከለከለ ነው!! በዚህ ፅሁፍ መጠቆም የፈለኩት ምንም አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ሀራም ነው የሚል መልእክት አይደለም። በተለይም ከክርስቲያን እና አይሁዶች ጋር ባለን ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የተፈቀዱ ብዙ በመልካም የመኗኗር እሴቶች አሉን።  ሆኖም ሀይማኖታዊ ወሰኖች የሉም ማለት አይደለም። የተፈቀደውን ስንተገብር እንደ ያልተፈቀደ ጋብቻ፣ በአላት ላይ መሳተፍ፣ ለሞቱት የአላህን ማርታ መለመንና ባጠቃላይ በዲን መመሳሰልን ግን በፍፁም አንፈፅምም። ይህንን የእምነትና የሀይማኖት ወሰን መናድ አይቻልም። ማንነታችንን ማክበር፣ ግንኙነታችንን በዲናዊ ገደቦች ማጠር ብሎም አለመሟሟት ለሌሎች ሞራል ዲንና ማንነት ከመጨነቅ ይቀድማል። ዲን ከምንም በላይ ነውና ከመሸማቀቅ እንውጣ። ይህ  የዲናችን መገለጫ እንጂ እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት የሚታይ አይደለም። በነገራችን ላይ የአንድ እምነት ተከታይ ከሌሎች ለመቀራረብ ብሎ ከራሱ እምነት ጋር የሚጣላበት ሁኔታ ድሮ ቀርቷል። ሌሎቹም ቢሆኑ ይህ በኛ ሀይማኖት አልፈቀድም እና ይቅርታ ይሉሀል። (فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ) አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡ [Surah Al-Qalam 8 - 10] ወላሁ አዕለም አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን! ____ አቡጁነይድ ረጀብ 24/1437 ዓ.ሒ / ሜይ 1/ 2016 ከጥቂት ማሻሻያዎች ጋር
3 80736Loading...
24
•|🌸 ጋብቻ ምን ይፈልጋል?! ትዳር በባህሪ፣ በሃላፊነት እና በፅኑ አእምሮ በትእግስት የሰለጠነች የጎለመሰ ሴትን ይፈልጋል... ሀሳቧና ጭንቀቷ በትዳር መ ብቻ የሆነች ጎረምሳ ልጅ አይደለም። ትዳር ወንድን በቃሉ ፍች እንጂ ወንድ አይደለም...የጋብቻን ትርጉም የሚያውቅ እና ሚስትን የማክበርና የማድነቅን ትርጉም የሚያውቅ፣ኃላፊነት ያለው፣ሰፊ አእምሮ ያለው እና ረጅም እይታ ያለው ሰው ነው። የህይወት እና የአላህ መልእክተኛ ትእዛዝ በትዳር ውስጥ መተግበር ... እና ኃላፊነትን እና የሃይማኖቱን አስፈላጊነት በትክክል የማያውቅ ወጣት አይደለም ። ጋብቻ ለሴት ውበት ወይም ለወንድ ውበት አይደለም...በፍቅር፣በእዝነት እና በመረጋጋት ላይ የተመሰረተ ቤትን ለአላህና ለመልእክተኛው በመታዘዝ አጥር የተከበበ ነው። በትዳር ጓደኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በጣም አስፈላጊው እና ትልቁ መንገድ ደግሞ ለአላህ መታዘዛቸው እና ከድብቅ ሆነ በአደባባይ ወንጀሎች ከኃጢአት መራቅ ነው።
4 25278Loading...
25
📹 የመሲሕ ባሮች ሆይ 1 ጥያቄ አለን?                              የ ኢብኑል ቀይም መካሪ ግጥም
3 21011Loading...
26
ወንድምህ ማለት … ካለህ ላይ ትሰጠዋለህ እሱም ይሰጥሀል ለችግርህ ጊዜ ከጎንህ ይቆማል፣ አንተ ከሱ ኪስ ትወስዳለህ እሱም ካንተ ኪስ ይወስዳል ፣ ሁሌ መስማማት ላይኖር ይችላል፣ አዎ በአንዳንድ ጉዳዮች ላትስማማ ትችላለህ በአንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ ትስማማለህ አንተ ትወቅሰዋለህ እሱም ይወቅስሀል መጨረሻ ላይ ግን እርስ በርሳችሁ ትታረቃላችሁ ልባችሁ ላይ ቂምን አትቋጥሩም የቀኑ መጨረሻም ሌሊት ላይ አብራችሁ በሳቅ በጨዋታ ታሳልፋላችሁ።ይህ ነው ትክክለኛ ወንድማማችነት።አንተ ስትደሰት ይደሰታል፣ አንተ ተከፍተህ ማየት አይወድም አንተ ስትከፋ እሱም ይከፋዋል ፣ አንተ በሌለህበት ስትታማ ካንተ ይከላከልልሀል ፣ ነውርህን ይሸፍንልሃል ፣ ወደ መልካም ነገር እጅህን ስትዘረጋ እሱም ይዘረጋል፣ ክፍተትም ካለብህ ይሸፍንልሃል፣ እንጂ እንደሌላው ዳር ይዞ አንተን አያማም ፣ የሆነ ችግር ወይም አደጋ ቢደርስብህ ቀድሞ የሚደርስልህ ወንድምህ ነው! የሆነን ነገር ከጠየቅከው ይሰጥሀል ፣ አኩርፈኸው ዝም ብትለው እሱ በሰላምታ ይጀምርሃል ያናግርሃል ፣ መልካም በሆኑ ነገራቶች ከራሱ አንተን ያስቀድማል ፣ ለችግርህ ቀድሞ ይደርሳል ፣ ከአይኑ ስትሰወር ይናፍቅሀል ይፈልግሀል፣ ስትዘነጋም ያነቃሃል።ጌታውን ሲለምን ዱዓዕ ሲያረግ አይረሳህም ፣ በዱዓው ያስታውስሃል። ወንድም ማለት ራስ ላይ የሚደፋ አክሊል ፣ አንገት ላይ የሚደረግ ጌጥ ነው ፣ እርሱ ማለት ላንተ ውበት ነው። ወንድም በሆነ ችግር ወድቆ ብታገኘው ልታነሳው ይገባል ፣ ችግር ላይ ቢወድቅ እርዳው ደግፈው ፣ ቢደክም ቢልፈሰፈስ አንሳው አበርታው ። ወንድም ማለት በችግር ጊዜ ደራሽ ነው ፣ አጋዥ ነው ፣ በችግር ጊዜ እንደ ጥላ ያገለግልሀል ፣ ልትወድቅ ስትል እንደ ምርኩዝ ያገለግልሃል። 👉 ስለ ወንድምነት ካደረገው የጁምዓ ኹጥባ የተወሰደ https://t.me/sultan_54
3 69450Loading...
27
Media files
3 2701Loading...
28
Media files
3 6689Loading...
29
Media files
3 7124Loading...
30
በነፃነት እና በማንበብ መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለ፣ ብዙ ባነበብክ ቁጥር በዙሪያህ ካሉ ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶች የበለጠ ነፃ ትወጣለህ። 🖤
4 62722Loading...
31
📢 አዲስ የደርስ ማስታወቂያ 📚 አዲስ የሚጀመረው ኪታብ: - الأصول الثلاثة ኡሱሉ አስ– ሰላሣህ 🎙ትምህርቱን የሚሰጠው :- ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር 🕌 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ:- ቃሊቲ ቸራሊያ ሀምዛ ትሮፒካል መስጂድ 🕐 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቀንና ሰዐት :- ዘውትር ማክሰኞ እና እሮብ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ 🗓 ትምህርቱ ሚጀመረው :- ዛቴ ረቡዕ ሸዋል 22–1445 ሂጅሪ (ሚያዚያ 23–2016) ይሆናል። 📍 ትምህርቱን በቲክቶክ ለመከታተል  ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 👇👇👇 https://www.tiktok.com/@sultan.khedir?_t=8lzFBaC7FEU&_r=1
3 7137Loading...
32
Media files
3 3225Loading...
33
Media files
3 52011Loading...
34
من أجمل التلاوة…
3 4896Loading...
35
Media files
3 55719Loading...
36
اللهم إني أتبرأ من حولي وقوتي، وألتجئ إلى حولك وقوّتك، اللهم أعنِّي ولا تُعِن عليَّ، وانصرني ولا تنصر عليَّ، واهدني ويسِّر الهُدى لي
3 7906Loading...
37
Media files
3 98911Loading...
38
Media files
4 4509Loading...
39
Media files
3 9823Loading...
40
Media files
3 8886Loading...
00:38
Video unavailableShow in Telegram
⛔️⛔️ሰበር ዜና! የዘንድሮ የኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የመጀመሪያው በረራ በሰላም መዲና ደርሰዋል።
Show all...
👍 52👌 1
ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል፦ ‹‹ ለሰዎች ብሎ መስራት ሽርክ  ነው፡፡ ለሰዎች ብሎ ስራን መተው ይዩልኝ (ሪያእ) ነው፡፡ ኢኽላስ ማለት ደግሞ ከሁለቱ አላህ ሲያድንህ ነው፡፡›› አል አዝካር ሊነወዊይ (1/33)
Show all...
👍 8🥰 2
11 ምላሾች «ሙታንን መጣራት ሰበብ ስለሆነ እንጂ አደራጊው አላህ መሆኑን ስለምናምን ሺርክ አይሆንም!» በሸይኽ ኢልያስ አህመድ NesihaTv https://youtu.be/QEm-jU4lytY ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!! Telegram፡ https://t.me/nesihatv YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCX2E30J71sKpnLQuGr7kt6w Facebook፡ facebook.com/nesihatv WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaaWvl5CXC3Ic7glOv3U @nesihatv
Show all...
11 ምላሾች በሸይኽ ኢልያስ አህመድ || NesihaTv

Copyright @NesihaTv 📨 ነሲሓ ቲቪ "ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!"📡 Satellite: Nilesat Frequency: 11555 or 11554 ...

👌 7👍 2 2