en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

ዮሳብ

ዮሳብ

Open in Telegram

Channel Description: Welcome to our channel, where we dive into the fascinating world of psychology! Here, you'll find insightful tips and practical advice to enhance your mental well-being and understand human behavior.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
220
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-330 days
Posts Archive
Book recommendations 1. "Ilaalcha" (Mataa Duree: Attitude/Mindset) ​Barreessaa: Dr. Firoomsaa Alamaayyoo ​Waa'ee Kitaabichaa: Kitaabni kun guutumaan guutuutti saayikoloojii ilaalcha namaa irratti xiyyeeffata. Saayikoloojii keessatti ilaalchi keenya akkamitti akka amala keenya fi carraa milkaa'ina keenya to'atu ballinaan ibsa. Nama saayikoloojii barateef ilaalcha namaa sakatta'uuf baay'ee gaariidha. ​2. "Milkaa'ina Jireenyaa" ​Barreessaa: Gadaa Gammachuu ​Waa'ee Kitaabichaa: Kitaabni kun saayikoloojii of-fooyyessuu (Practical/Self-Help Psychology) irratti xiyyeeffata. Akkamitti sammuu keenya sodaa fi dhiphina jireenyaa keessaa baasnee gara yaada gaariitti (Positive Thinking) fiduu akka dandannu karaa saayinsawaa ta'een barsiisa. ​3. "Dandettii Waliigaltee fi Amala Namaa" ​Waa'ee Kitaabichaa: Kitaabonni dandeettii namoota biroo waliin haasa'uu fi amala isaanii hubachuu (Social Psychology) irratti xiyyeeffatan gara Afaan Oromootti hiikaman jiru. Kunis namoota akkamitti akka amansiisan fi amala isaanii akkamitti akka dubbisan si gargaara.

Repost from ጲንኤል
ዝምታ.... ወደኛ ሳይደርሱ ረጅም ጊዜ እንዲያልፍ ወደማይፈቅዱ ነገሮች ለመሄድ ነጻ የሚያደርግ መንገድ ነው። በዕለት ተዕለት ህይወታችን ብዙ ነገሮች ሀሳቦች ድምፆች እና ግፊቶች ያለማቋረጥ ይወተውቱናል። እነዚህ ነገሮች ብዙ ጊዜ እውነተኛ ማንነታችንን የሚሸፍኑ ጉልበታችንን የሚበሉ እና ወደ ውስጣዊ ሰላማችን እንዳንደርስ የሚያግዱን ናቸው። ዝምታ  ከዚህ ውጫዊና ረብ የለሽ ግርግር የምንወጣበት መሸሸጊያ ነው። ዝምታን ስንመርጥ እኛን ወደ እውነተኛው መዳረሻችን ሊያቀርቡን የሚችሉትን የህይወት እሴቶች ከመረባረብ እና ጊዜ ከመሻማት እናድናቸዋለን። ብዙ ጊዜ በጊዜያዊ ነገሮች ስንጠመድ ለአእምሮአችን ለነፍሳችን እና ለህይወት አላማችን አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች ለምሳሌ፦ ጸሎት ራስን መመርመር አልያም እውነትን መፈለግ ሊሆን ይችላል ... ወደ እኛ እንዳይደርሱ እንቅፋት እንፈጥራለን። ዝምታ ይህንን ጊዜያዊ ግርግር በማቆም አስፈላጊ የሆኑትና የዘገዩብን ነገሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ህይወታችን እንዲመጡ በር ይከፍታል። በዝምታ ውስጥ ስንሆን አስፈላጊው ነገር ወደ እኛ ለመምጣት መንገድ ያገኛል ምክንያቱም እኛ የምናስቀድመው ድምፅ በሌለበት የህይወት ጥሪ በቀጥታ ልባችን ላይ ይደርሳልና በዝምታ ውስጥ ስትሆን ማንም አይፈርድብህም ምንም ነገር አትጠብቅም ለማንም ነገር ማብራሪያ አትሰጥም። ይህ ሙሉ ነጻነት ነው። በዚህ የነጻነት ሁኔታ ውስጥ ነው እንግዲህ እውነተኛው ማንነትህ ከፈጣሪህ ጋር የሚገናኘው። https://t.me/Oct13wed

በሰዎች መካከል ባለው መስተጋብር ውስጥ አንድ ያልተጻፈ ትልቅ እውነታ አለ፤ እሱም የመለያየት ጥበብ ነው። ብዙ ጊዜ የምናስበው መለያየት በጭቅጭቅና በለቅሶ ብቻ የሚሆን ይመስለናል። ነገር ግን ይህም አለ ፦ አክሩፎ የሄደ ሰው ተመልሶ ሊመጣ ይችላል፤ ፈገግ ብሎ የሄደ ግን ዳግም አይመለስም! ተከፍቶ የሄደ ሰው፣ ውስጡ ገና ተስፋና የመልስ ጥያቄ አለ። ፈገግ ብሎ የሄደ ግን ሁሉንም ነገር በውስጡ ጨርሶ፣ ምርጫውን አክብሮ፣ ትዝታውን ብቻ ይዞ የተጓዘ የልብ ጀግና ነው። ስለዚህም ነው አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ህይወት ውስጥ ስንወጣ "ፈገግ ብለን" መውጣት የሚኖርብን። እንዴት ነው ወገን አይመስላችሁም ? ✍yosab (Andualem )

የሰው ልጅ ህይወት ልክ እንደ ወንዝ ፍሰት ናት፤ የት ጋ መፍሰስ እንደጀመረችና የት ጋ መድረሷን ሳናስተውል ዘመናት ይነጉዳሉ። በትናንትና በዛሬ መካከል ያለውን ሽግግር ቆመን አናየውም። ለካስ መለወጥ
የሰው ልጅ ህይወት ልክ እንደ ወንዝ ፍሰት ናት፤ የት ጋ መፍሰስ እንደጀመረችና የት ጋ መድረሷን ሳናስተውል ዘመናት ይነጉዳሉ። በትናንትና በዛሬ መካከል ያለውን ሽግግር ቆመን አናየውም። ለካስ መለወጥን በዓይናችን ሳንመለከት፣ በአኗኗራችን ድንገት እናየዋለን!

..........እውነታው ግን ይሄ ነው፤ በምድር ላይ ዋጋ የተከፈለበት ነገር ሁሉ የራሱ የሆነ አንዳች መዘዝ አለው። እኛ ግን ገንዘብ ስንቆጥር ለምርጫችን ብቻ ዋጋ የከፈልን ይመስለናል። አይደለም! የከፈልነው ዋጋ ለገዛነው ነገር "እሱነት" (ድብቅ ማንነት) ጭምር ነው። ያ የገዛነው ነገር "እሱነት" ደግሞ ሁለት ገፅታ አለው፤ መርዝም ነው፣ መድኃኒትም ነው! ባዶነታችንን የምናክምበት፣ ዓለምን የምንጨብጥበት መስሎን በውድ የምንገዛው ቴክኖሎጂ፣ አጠቃቀማችንን ካላወቅንበት ራሱ መልሶ ህይወታችንን የሚመርዝ ክፉ ‘ጥበብ’ ሆኖ ያርፈዋል። ✍yosab

ዮሳብ: ፍቅር የስሜት ልጓም ነው! ፍቅር በብዙ ዜማ ይዘፈናል፤ በብዙ መንገድም ይተረጎማል። ነገር ግን የእውነተኛነቱ ትልቁ መመዘኛ፣ የሚነደውን የስሜት እሳት የመግራትና አቅጣጫ የማስያዝ አቅሙ ላይ ነው። "ፍቅር የስሜት ልጓም ነው" ስንል፣ ስሜትን ጨፍልቆ የሚያጠፋ ሳይሆን፣ ለክብርና ለዘላቂነት ሲል በትዕግሥት የሚገራ የጥበብ እጅ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ፈረስ ያለ ልጓም አቅጣጫ አጥቶ ጋላቢውን ለውድቀት እንደሚዳርግ ሁሉ፣ የሰው ልጅ ስሜትም ያለ ፍቅር ልጓምነት ሲለቀቅ መጨረሻው ስብራት ይሆናል። እውነተኛ ፍቅር ባለበት ስፍራ ሁሉ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሥጋዊ እርካታ ብቻ ሳይሆን ለነፍስ መፅደቅም ነው። "ማፍቀር ማለት መቸኮል ማለት አይደለም።" ከጋብቻ በፊት ራስን መግዛት መቻል በፍቅረኛሞች መካከል የማይናወጥ የታማኝነት ዐለት ይተክላል። ባጭሩ... ፍቅር ስሜትን መግደል ሳይሆን፣ ለቅዶስ ጋብቻ ዓላማ አቆይቶ መጋለብ ነው። እና ወግን መሻታችንን ለማግኘት ክብራችንን እንጠብቅ ። ፍቅር የስሜታችን ልጓም ነው ✍Andualem (yosab)

Repost from N/a
                             ጎዶሎህን  ፈልግ እኩለ ሌሊት ሊሆን 10 ጉዳይ ይላል ። ከጓደኞቼ  ጋር ከ labirari  አንድ ላይ መተን ዶርም ከገባን በኃላ  ወደየ  ትራሳችን  ተጣደፍን ። እኔ ግን አጋዬ ጫፍ ላይ ተቀምጬ  "የሕይወት ማጣፈጫ ቅመም  ምን ይሁን..? "ብዬ  ውሎዬ ላይ  ስላገኘዋትን ልጅ  ማስብ ጀመርኩ.... ማለዳው ከደመናው ስር  አምልጣ በወጣች  በሚያምር የግርዶች ፀሃይ የተጀመረው ሲሆን በኃላ ኃላ ደመናው ውበቷን የጠዋት ጠዛ አደረጋት እንጂ ...... ዝናባማ ሆኖ በዋለው  ቀን ለሁለተኛው መንፈቀ ዓመት የመጨርሻ ፍተና (final) ቀኑን ሙሉ እናነባለን ብለን   ከዶርማችን እና ከካፌችን እራቅ ወዳለው ባዶ የመማሪያ  ክፍል (Speace)  እኔ፣ በእድሜ የበሰለው ሁሌም እርጋታ የማይለየው  አስተዋዪ እና የትም  ከማንም ጋር መኖር የሚችለው በግቢያችን ከ Remedial እስከ GC ተማሪዎች  የሚያውቁት የሚያውቁት ብቻ አይደለም የሚወዱት    የሐረሩ ሰው እኔ" ወጣቱ"ብዬ ምጠራው   ሆነን  ሄድን ።በመንግዳችን ላይ በወጣቱ ባህሪ ምክንያት Stack እያደረግን ( መንገደኛውን ሰው ሰላም እያልን)   ሞተን ሞተን speace ደረስን ። ቁጭ ብለን ማንበብ  እንደጀመርን መንበዛበዝ(Busy  መሆን)  የማይሰለቸው የሃረሩ ወጣት  የስንኩን ጥሪ አስከትሎ  ጥሎን ወጣ ። "ቆይ ግን ይሄ ልጅ መች ነው ለራሱ የሚሆነው" አለኝ አስተዋዩ ሰው  ቁጣ፣ግርምት፣ፍቅር አንድ ላይ ሆነው በሚነበቡበት ገፅታው  እኔም ፈገግ ብዬ  "ምን  ታውቀው የለ እንዴ ይህ  አዲስ ነገር ነው...?" አልኩት ፍገግታዬን እየጨመርኩ። ወጣቱ ከሄደ  ከትንሽ  ደቂቃ በኃላ  ሰማዩ እንደ ነሃሴ  ወር  ዝናብ  ለ2ሰዓት   አለቃቀሰ  ።እኔ ና አስተውዩም ወጣቱ እንደማይመጣ አውቀን  ደብሮን በድብርቱ ላይ ደሞ ዝናቡ ተጨምሮበት እዛው ወንብራችንን አስተካክለን  "ለጥ በጋይገርን ፍርናሽ" እንዳለው  እከ  እኛም "ለጥ....... የዝናብን እንቅልፍ  አስቡት እንደነገሩ እድርጌ የተኛውበት ነገርም ትንሽ ምቾት ስላልሰጠኝ ተነስቼ  Video edit ማድረግ ጀመርኩ።ግን የተሰማኝ ረሃብ እንድቀጥል  አልፈቀደልኝም።  "ረሃብ ክፉ ነው"  ይባል የለ ። ዝናቡ  ከእንቅልፋችን ጋር ተዳምረው  የCafeው ሰዓት አስመልጦን  ስለነበር  አስተዋዩን ከተኛበት በቀስታ  "ተነስ ርቦኛል Launch ምሳ እንብላ" አልኩት   እሱም  ሞርምሮት (እርቦት) ቆይቷል ለካ በፍጥንነ ተነስቶ ፊቱን ከሞንጮሮሩ (አሸንዳው) ባልተፈቀደላት መንገድ በምትወርደው ውሃ  ታጠበ ።   አንድ በአይነት እና ፓስታ በአትክልትታችንን እየበላን  በመሃል የ አስተዋዩ ስልክ ጮኽ ።   ወጣቱ ነው።   "launch  ነን"  ና ብለነው  እኛ ወደ ስራችን(ምግባችን)...... ብዙም ሳይቆይ ወጣቱ ከተፍ አለ።  ለጥናት ይሆነናል ብሎ አስተዋዩ አልጠጣም ስላለ  ለእኔ እና ለሱ 2 ብና አዘዘ ። እየጠጣን  ስለ ትላንቱ Ucl final የአርሰናል  አቻ መውጣቱን እና በመለያ ምት መሸነፉን እያወራን..... በመሃል  "ተነሱ እንሂድ"  አለን አስተዋዩ ። ትዛዝ ተቀብለን እየሄድን ሳለ ከሌላ ፕላኔት የመጣች ምትመስል....አቤት አይን! አቤት አፍንጫ! አቤት ፈገግታ!  አቤት አንገት! ከሁሉም ነገር በላይ የገዛኝ ግን የቁመታ ነገር ነው። "ተቃራንኒ ዋልታዎች  ይሳሳባሉ "አይደል ሚባለው? በቃ ሳበችኝ ነው ምላቹ..... "ወጣቱ የዝች ልጅ አድናቂ እኮ ነኝ እያት አታምርም ?" አልኩት። እሱም  ፊቱ ላይ በማይጠፋው ፈገግታ  እያለኝ "ና ጣጣ የለውም " ብሎኝ  እጄን እየጎተተ  የልጅቷን  ስም በቁልምጫ እየጠራኝ  ወሰደኝ።   ስሟን ጠርቶ   "አድናኪሽ ነው " ብሏት ወደ 2ቱ ለጓደኞች አመራ። እኔዮዬ በቁመቷ ተማርኬ  ፊቷን ለማየት  እያንጋጠጥኩ  እሷም  እኔን ለማየት አይኖቿን  እያዘመመች ሳለ  አይኖቼ ከ አይኖቿ  ጋር  ተጋጩ! እንኳን  ተፈነካከቱ! "ስንት ሜትር ነሽ?" አልኳት እሷም እየፈገገችከ "86" አለችኝ ።  ልክ እንደዛ ስትለኝ  ለኔ እራሱ ሳይገባኝ የቁመቴ ሜትር  ጠፋኝ።  አረ እንኳንም  ተፋኝ  በሳ ተሸፍኜ  በሳ ቁመት እጠራለው  እኛ ከተስማማን ሰዉ ምን አገባው...ክ/ሽ/ቹ.? ለካ የሕይወት  ማጣፈጫ  ልዩነት፣ ጉድለትን መሞላላት ነው።  አስቡት እስቲ የወላጆቻቸውንን  አንድነት።    እንዱ የሌለው አንዱ አለው ፣አንዱ ያለው  አንዱ የለውም ያቺን ልዩነት  በታላቅ   ሃሴት  እየተሞላሉ   ይኖራሉ። ሌላው ቀርቶ እራሱ...  የኛ የራሳችን  ፍላጎት  እኛ ጋር ያለውን  እኛ ብቻ የምናውክቅውን  ክፍተት(ጎዶሎአችንን) የሚሞላልንን  አይደል  የምንፈልገው......?   ጎዶሎህን ፈልግ opposites attracted ነኝ

4_5791774471081697399.mp33.71 KB

አምቢ ክብር ነው! (feven) ከልጅነቴ ጀምሮ በአንድ ነገር ነው የምታወቀው—በ“እሺ ባይነቴ”። ለእኔ “እሺ” ማለት ተራ ቃል ሳይሆን የማንነቴ መገለጫ፣ የደግነቴ መታወቂያ ነበር። ሰው እንዳይቀየመኝ፣ ፍቅሬ እንዳይቀንስ፣ በነገሮች ሁሉ ሰላም እንዲሆን ሁልጊዜም አንደበቴ እሺ ነበር። እኔ ጋር “እምቢ” የሚባል ቃል ጨርሶ አልነበረም። ታዲያ እድሜዬ አድጎ፣ የቤተሰብ እቅፍ አልፎ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገባሁ። ዩኒቨርሲቲ ደግሞ እንደምታውቁት የባህርይ አውደ-ርዕይ ነው። ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ፣ የተለያየ ፍላጎትና ስብዕና ያላቸውን በርካታ ጓደኞችን አገናኘኝ። እዚያም ቢሆን ግን ያ የልጅነት መታወቂያዬ አልተቀየረም። ሁሉም የሚያውቀኝ በዚሁ ባህሪዬ ነው። አንዱ ሲጠራኝ “እሺ”... ሌላው ጉዳይ ሲያዘኝ “እሺ”... ሌላኛዋ እንሂድ ስትለኝ “እሺ”...። ለእኔ “እምቢ” ማለት ሰማይና ምድርን እንደማላተም ያህል ይከብደኝ ነበር። የራሴ ፕሮግራም ይኑረኝ አይኑረኝ፣ ስሜቴ ይፍቀድ አይፍቀድ ሳላስብ፣ የሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት ስል ብቻ በ“እሺ” ጎርፍ እምሰጥ ነበር። ነገር ግን... ይህ ሁሉንም ደስ የማሰኘት አባዜዬ አንድ ቀን ዋጋ ሊያስከፍለኝ መጣ። ሁሉንም “እሺ” እያልኩ የራሴን ሰላም፣ የራሴን ጥናት፣ የራሴን ምርጫና በመጨረሻም ራሴን ማጣት ጀመርኩ። በሰዎች ፍላጎት መሀል የምትናውዝ፣ የራሷ መሪ የሌላት ጀልባ መሆን ምን እንደሆነ የተረዳሁት ያኔ ነው። ውስጤ እየዛለ፣ ማንነቴ እየደበዘዘ መጣ። በአንድ ወቅት ከጓደኞቼ መካከል ፌቨን የምትባል ልጅ ነበረች። አስተዋይና የሰዎችን ስነ-ልቦና የምታነብ ሴት ናት። ይሄንን የእሺታ ማዕበል ውስጥ መስጠሜንና ራሴን እያጣሁ መምጣቴን ቅድማ ተረዳችው። አንድ ቀን በጣም ደክሞኝ፣ የራሴ ጉዳይ ተደራርቦብኝ እያለ፣ አሁንም ሌላ ሰው ላለማስቀየም ስል “እሺ” ስል ሰማችኝ። ፊቴ ላይ ያለውን መጫጫንና የውስጤን ጭንቀት አይታ ወደ እኔ ጠጋ አለች። በትዝብትና በአዘኔታ እያየችኝ እንዲህ አለችኝ፦ “ለመሆኑ ምን ሆነሃል? 'እምቢ' እኮ ክብር ነው!” ይህች ቃል በጆሮዬ ስትገባ እንደ መብረቅ ነበር የረገጠችኝ። “እምቢ... ክብር ነው?” ብዬ በውስጤ ደገምኩት። እስከዚያች ሰዓት ድረስ “እምቢ” ማለት ክፉ መሆን፣ ሰውን መጥላት፣ ወይ ጨካኝነት ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን ፌቨን በአንድ አረፍተ-ነገር ሙሉ የህይወት ፍልስፍናዬን ገለበጠችው። “እምቢ” ማለት ሰውን መጥላት ሳይሆን፣ ለራስህ ምርጫ፣ ለራስህ ጊዜና ለራስህ ማንነት እውቅናና ክብር መስጠት መሆኑን ገባኝ። ራሱን የማያከብር ሰው ደግሞ ለሌሎች የሚተርፍ እውነተኛ ደግነት ሊኖረው አይችልም። ከዚያች ቀን ጀምሮ “እምቢ” ማለትን መለማመድ ጀመርኩ። መጀመሪያ ላይ እምቢ ምላሴ ላይ ይጎረብጥ ነበር። ነገር ግን በአግባቡ እና በስነስርዓት “አልችልም” ወይም “እምቢ” ማለት ስጀምር፣ የጠፋው ማንነቴና ክብሬ ወደ እኔ መመለስ ጀመረ። የሚገርመው፣ እምቢ ስላልኳቸው የራቁኝ ሰዎች ሳይሆኑ፣ ይበልጥ ለውሳኔዬ ክብር የሰጡኝ ሰዎች በዙ። አዎ... “እሺ” ማለት ደግነት ቢሆንም፣ ልክ እንደ ጨው መጠኑ ሲበዛ ግን ማንነትን ያሳንሳል። ለሰዎች ሁሉ “እሺ” እያልን ራሳችንን “እምቢ” ከምንል፣ አንዳንዴ ለራሳችን “እሺ” ለማለት ለሰዎች “እምቢ” ማለትን መልመድ አለብን። ምክንያቱም ፌቨን እንዳለችው... “እምቢ” መቻል የራስ አክብሮት መገለጫ ትልቅ ክብር ነው! ✍️Andualem (yosab ) 24/09/2018ዓ.ም

ምናለፋችሁ… አንዳንድ ጊዜ ሰይጣን ራሱ ፍርድ ቤት ቆሞ "እኔ እዚህ ውስጥ የለሁበትም፤ የሰው ልጅ በራሱ ላይ የሚያደርሰውን በደል አይቼ እኔው ራሴ እያዘንኩ ነው!" እያለ በቁጭት የሚከራከር ይመስለኛል 😲 "ሰው ራሱን ካልጎዳ በቀር ማንም የሚጎዳው የለም። የሰው ልጅ ራሱን የሚጎዳውን ያህል ጠላቱ ሰይጣን እንኳን አይጎዳውም!" ለካስ የሰው ልጅ የራሱን ስም ማጥፋት፣ የራሱን ስኬት ማሰናከልና የራሱን ሰላም ማደፍረስ ላይ ተወዳዳሪ የለውም ሰይጣን እንኳን በሃሳብ መጥቶ ሊገፋፋን እንጂ፣ አስገድዶ ሊያጠፋን አይችልም 👿 እኛ ግን በገዛ ፈቃዳችን ራሳችንን የምናቆስልባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው ⚠️🕳️ ✍Andualem (Yosab) 23/09/2018ዓ.ም https://t.me/andupsychology 📲🧠

Repost from N/a
Let’s Take Our Vision to the National Stage! 🚀 Dear Empathetic Bloom Family, The values we share—empathy, growth, and empowe
Let’s Take Our Vision to the National Stage! 🚀 Dear Empathetic Bloom Family, The values we share—empathy, growth, and empowerment—are meant to reach beyond our campus. Today, I am asking for your support as I run for President of the Ethiopian Psychology Students Association (EPSA). I have spent my time here building a platform that puts students first, and I am ready to scale that impact nationwide. My goal is to ensure that every psychology student in Ethiopia has the support, resources, and voice they deserve. I need your vote to make this vision a reality. 👉 Cast your vote here: http://epsahub.com/ Our journey together has only just begun. Let’s lead with empathy and grow together on a national level! #EmpatheticBloom #LeadWithEmpathy #EPSAElections #VoteForChange

የእግር ዲፕሎማሲ(Andualem ) በባለፈው ዕለት እኔና የክለባችን 'ዜሮ ፕላን' አባላት ስልጠና ልንወስድ በሙሉ ተነሳሽነት ወደ ሴቶች ዞሮ ፕላን ዶርም አመራን። ነገር ግን፣ ልክ የዶርሙ ደጃፍ ላይ
የእግር ዲፕሎማሲ(Andualem ) በባለፈው ዕለት እኔና የክለባችን 'ዜሮ ፕላን' አባላት ስልጠና ልንወስድ በሙሉ ተነሳሽነት ወደ ሴቶች ዞሮ ፕላን ዶርም አመራን። ነገር ግን፣ ልክ የዶርሙ ደጃፍ ላይ ስንደርስ ያ የነበረን የጀግንነት ስሜት በድንገት ቆመ! ሁላችንም እርስ በእርስ ተያየን። በአይናችን ውስጥ አንድ ዓይነት ፍርሃት ይነበባል—የካልሲ ሽታ ፍርሃት! ቀኑን ሙሉ ስንንቀሳቀስበት የዋለው ካልሲያችን ክፉኛ ቆሽሾ ስለነበር፣ ጫማችንን ማውለቅ ከበደን። ወደ ውስጥ ገብተን የዶርሙን ሰላም እንዳናውከው ሰጋን። በመጨረሻም ሌላ አማራጭ ስላልነበረን፣ እጅግ በጣም ቀስ ብለን፣ ልክ ፈንጂ እንደሚረግጥ ሰው ዘንበል በማለት ጫማችንን በስስት አወለቅነው። በር ተከፍቶ ወደ ውስጥ ገባን። ገና ፍራሹ ላይ መቀመጫችን ሳይነካ፣ ያ የፈራነው "የመዓዛ ማዕበል" ቀድሞ አፍንጫችን ላይ ድቅን አለ። እኔም ሆንኩ ሌሎቹ ጓደኞቼ እርስ በእርስ እየተጠቃቀስን በስሱ መሳሳቅ ጀመርን። እንግዲህ እዚህ ጋ ነው ሚስጥራዊው ስልት የተጀመረው! ሰው እንዳያውቅብንና ነገሩን ለመሸፋፈን ስንል፣ ዝም ብለን እግራችንን አንዴ እናጥበዋለን፣ አንዴ ደግሞ በሱሪያችን ሰብሰብ አድርገን እንደረጎዋለን። ልክ "አልሸሹም ዞር አሉ" አይነት የእግር ዲፕሎማሲ ጨዋታ! ይሁን እንጂ እንዲህ እያደረግን ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ቀስ በቀስ የምንወስደው ስልጠና ወሬው እየሞቀና እየደመቀ መጣ። ሳቁ፣ ጨዋታውና ውይይቱ የዶርሙን ድባብ ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠረው፣ ያ መጀመሪያ ያስጨነቀን የካልሲ ሽታ ቀስ በቀስ እየጠፋ ሄደ። (ወይስ አፍንጫችን ለመደው? ያ እንግዲህ የኛ ሚስጥር ነው!) ለማንኛውም፣ ስልጠናችንን በታላቅ ሳቅና በማይረሳ ትዝታ አጠናቀቅን። https://t.me/andupsychology https://t.me/andupsychology

የውስጥ ማዕበል ✍Andualem (yosab) ወገን... አሁን አሁን ላይ እራሴን እየፈራሁት ነው። እኔን ሁልጊዜ በሳቄና በደመቀ ሰላምታዬ የሚያውቁኝ የካምፓስ ልጆች ሁሉ፣ ፊቴ ላይ የሆነ ነገር አንብበው “አንዱ ምን ሆነሃል?” ይሉኛል። የሁሉም ጥያቄ አንድ አይነት መሆኑ ራሱ ግርም ይለኛል። ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ከጓደኛዬ ፌቨን ጋር አቡ ምግብ ቤት ውስጥ ምሳ እየበላን፣ ሳይታሰብ ትኩር ብላ አየችኝና “አንዱ... ምን ሆነሃል ግን?” አለችኝ። ጥያቄዋ ልክ እንደ መርፌ ወጋኝ። ፣ እሷ ስትጠይቀኝ ከወትሮው በተለየ መንገድ እራሴን እንድመለከት ስላስገደደኝ፣ እሷን ሸኝቼ ፈጥኜ ወደ ዶርም ጉዞዬን አቀናሁ። ጭልምልም ባለው የዶርማችን ክፍል ውስጥ፣ ከአልጋዬ ጫፍ ላይ ተቀምጫለሁ። የሌሎቹ የዶርም ልጆች ወይ ላይብረሪ ሄደዋል ወይም ካፌ፤ ክፍሉ ውስጥ ያለው ብቸኝነት ግን አየሩን ራሱ የከበደ አስመስሎታል። አዝኛለሁ። ልቤ ልክ እንደ ስስ ሸክላ ተሰባብሯል። አይኖቼ ዝም ብለው፣ ያለ ምንም ምክንያት ቢፈሱና የውስጤን ጭጋግ በንጹህ እንባ ቢያጥቡት ደስ ባለኝ ነበር። በሳይኮሎጂ ክፍለ-ጊዜ ስለ ‘Mental Health’ እና ስለ ስሜቶች መዘበራረቅ የተማርኳቸው ንድፈ-ሀሳቦች ሁሉ አሁን ከውስጤ ጠፍተዋል። የሆነ ጥልቅ ስብራት እና መጎዳት ይሰማኛል... ግን ለምን? መልስ የለኝም። በትክክል በዚህ ስሜት ውስጥ እያለሁ ግን፣ ከራሱ ከህመሙ በላይ የሚከብደው መቅሰፍት መጣ። የዶርሙ በር በሀይል ተከፍቶ የዶርሜ ልጅ ገባ። መጽሃፎቹን ጠረጴዛው ላይ እያኖረ ወደ እኔ ዞረ። “ምንድነው የሆንከው አንዱ?” ይህችን ጥያቄ ይዞ በሩን ከፍቶ የሚመጣ ሰው... ከራሱ ከስሜቱ በላይ ሰውን ያደክማል፣ ይበልጥም ግራ ያጋባል። ፦ የሚጠይቁኝ ሰዎች በጥሩ ስሜትና ተቆርቁረው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ሰዓት ጥያቄያቸው ልክ እንደ መርማሪ ፖሊስ ያጨናንቃል። እኔ ራሴ ያሳዘነኝን ነገር መነሻ ፈልጌ ባላገኘሁበት ሁኔታ፣ “ምን ሆንክ?” ተብሎ ለሰዎች ሪፖርት ማቅረብ ይቻላል ? ይህ ከባድ ስቃይ ነው። “አላውቀውም” ስትል፣ “እንዴት አታውቅም? የሳይኮሎጂ ተማሪ ሆነህ ደግሞ?” የሚል ሌላ ሰንሰለታማ ጥያቄ ይከተላል። ትልቁ እውነት፦ እኔ ራሴ መፍታት ያልቻልኩትን የውስጤን እንቆቅልሽ፣ ለሌላ ሰው ለማስረዳት የምሞክርበት ምንም አይነት አቅም አሁን የለኝም። አንዳንድ ጊዜ ስሜቶች ሰዋሰውና ቃላት የላቸውም። ዝም ብለው በጭጋግ መልክ ይመጣሉ፣ ዝም ብለው ያደማሉ። በዚህ ሰዓት የሚያስፈልገኝ መፍትሄ አፈላላጊ ሰው፣ ወይም "አይዞህ" የሚል ምክር ሳይሆን... ፍጹም ጸጥታ ብቻ ነው። ፊቴን ወደ ግድግዳው አዙሬ ብርድ ልብሴን ሳስብ፣ በውስጤ የመጨረሻውን የልመና ቃል ......ይቀጥላል አንዱ ነኝ እባካችሁ ማብራሪያ አትጠይቁኝ። ተዉኝ በቃ! https://t.me/andupsychology https://t.me/andupsychology https://t.me/andupsychology

4_5815273272245226141.mp31.32 KB

Andualem (yosab)

Check out "Google Calendar" https://play.google.com/store/apps/details?id=com.google.android.calendar ወገን የማትጠቀሙ ልጆች ተጠቀሙ☺️

አቦ እንፀፀት (yosab) በመውደቅ እና ወርቆ በመቅረት መካከል ሰፊ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለ። ሰው ሆኖ የማይሳሳት፣የለም። ሁላችንም በጊዜያት መጋረጃ ውስጥ የየራሳችን የጥቁር ነጠብጣብ ታሪክ አለን፤ ሀጢአት ሰርተናል፣ ተሰናክለናል። ነገር ግን የሰው ልጅ ትልቁ ውድቀት ስህተት መስራቱ ላይ አይደለም። በሳይኮሎጂው አለም "Cognitive Dissonance" (የአእምሮ መታወክ) የሚባል እውነታ አለ። አንድ ሰው ስህተት ሲሰራ ውስጣዊ ማንነቱና የሞራል እሴቱ ይጋጫሉ። ይህንን ጭንቀት ለማስታገስ መፍትሄው ሁለት ብቻ ነው፦ ወይ ስህተትን አምኖ በፀፀት መታደስ፣ ወይም ደግሞ ስህተቱን ለማስተባበል የውሸት ትረካዎችን መፍጠር። እውነተኛው ውድቀት የሚጀምረው፣ ከሰራነው ስህተት ይልቅ "ለምን ሰራሁት?" ብሎ ራሱን የሚጠይቅ፣ ድርጊቱን በፀፀት የሚመረምር የተሰበረ ልብ ሲጠፋና አእምሯችን ወደ ሁለተኛው አማራጭ — ወደ መካድ ሲያደላ ነው። አንድ ሰው በስህተት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ቢወድቅና "ወድቄያለሁና አንሱኝ" ብሎ ቢጮኽ፣ አካሉ ቢቆስልም መውጫው ቅርብ ነው። ነገር ግን ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ፣ ፍርሃቱንና የጥፋተኝነት ስሜቱን ለመሸፈን ሲል፦ "ይህ እኮ ጉድጓድ አይደለም፣ ቤቴ ነው! ጨለማውም ይመቸኛል" ብሎ ራሱን ሲያታልልና መውደቁን ሲክድ ያኔ ጨለማው ሙሉ በሙሉ ይውጠዋል። አለመፀፀት ማለት ልክ እንደዚሁ ነው። ህሊናን በራስ-መከላከያ ቅጥር (Defense Mechanism) እና በትዕቢት ማደንዘዣ አደንዝዞ፣ የሰራነውን በደል እንደ ትክክለኛ ድርጊት መቁጠር ነው። ስነ-ልቦና እንደሚነግረን፣ ጥፋትን ደጋግሞ ማስተባበል ውሎ አድሮ የሰውን ልጅ የመራራትና የማሰብ ህሊናዊ ባህሪውን ያጠፋዋል ። https://t.me/andupsychology https://t.me/andupsychology https://t.me/andupsychology ✍Andualem (yosab ) 18/09/2018ዓ.ም

ዶክተር ምትኩ ከሰዓት በኋላ ያለው የክፍል ድባብ በፀጥታ ተሞልቷል። የተማሪዎቹ ትኩረት ሁሉ በክፍሉ መሃል ወደሚገኙት ሰው ላይ አርፏል። ዶክተር ምትኩ—በዘመናት የማስተማር ልምድ የለሰለሰና ጥልቅ መረጋጋት የሚሰማበት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ የነጭ ጠመኔውን አቧራ ከእጃቸው ላይ እያረገፉ ወደ ተማሪዎቻቸው ዞሩ። መነፅራቸውን በጣታቸው ቀና አደረጉና ሁላችንንም በተራ በዓይናቸው ቃኙን። ያች የሁልጊዜዋ፣ የዕውቀት መጋረጃ የምትከፍት ፈገግታቸው ፊታቸው ላይ በራች። "ስማችሁኛል አይደል?" አሉ። ድምፃቸው የክፍሉን ፀጥታ ሰብሮ ወደ ውስጥ ሲዘልቅ። "ብዙ ጊዜ እኛ ትልልቅ ሰዎች፣ መምህራንና ወላጆች ህፃናትን እንደ ሸክላ ጭቃ እንጭናቸዋለን። እንደፈለግን አድርገን ልንቀርፃቸው እንሞክራለን። ግን ትልቁ ስህተታችን የሚጀምረው እዚህ ጋ ነው።" ጠመኔውን በእርጋታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጡና እጆቻቸውን አጣመሩ። የንግግራቸው ክብደት ክፍሉን አየር በአንዴ ቀየረው። "ህፃን ልጅ ማለት ገና ያልተጻፈበት ነጭ ወረቀት ነው የሚሉትን የድሮ ሰዎች ታውቋቸዋላችሁ። እኔ ግን ዛሬ የምላችሁ ሌላ ነው። ህፃናት እንዲሁ ባዶ ነጭ ወረቀት ብቻ አይደሉም፤ እነሱ ገና ከጅምሩ የራሳቸው የተፈጥሮ ቀለምና ስውር ስዕል ይዘው የመጡ ድንቅ መጽሐፍት ናቸው! የእኛ ስራ በእነሱ ላይ የፈለግነውን የራሳችንን ታሪክ መፃፍ ሳይሆን፣ በውስጣቸው ተደብቆ ያለውን ያንን መልካም ማንነት ፈልፍሎ ማውጣትና ማለምለም ብቻ ነው።" ዶክተር ምትኩ በጥያቄ አስተያየት ወደ እኔ ጠጋ አሉ። "ለመሆኑ... አንድ ህፃን ልጅ ወለል ላይ ተቀምጦ ሲጫወት ምን ይታይሃል?" እኔም ደንገጥ ብዬ ፣ "ጨዋታና... መረበሽ?" ሲል መለስኩኝ። ዶክተር ምትኩ እራሳቸውን እየነቀነቁ ሳቁ። በክፍሉ ውስጥ የነበረው ውጥረት በሳቃቸው ቀነሱት ። "አይደለም! ጨዋታ ለህፃን ልጅ ተራ መረበሽ ሳይሆን ትልቁ ሳይንሳዊ ላቦራቶሪው ነው። አሻንጉሊት ሲሰብር ጥፊና ጩኸት ሳይሆን የሚያስፈልገው፣ 'ለመሆኑ ይህ ነገር ለምን ተሰበረ? ውስጥስ ምን አለው?' ብሎ ለመመርመር ያለውን የሳይንቲስትነት ስሜት ማድነቅ ነው።" ወደ ጥቁር ሰሌዳው ተመልሰው ዞሩና በትልቁ አንድ ቃል ጻፉ። "አንድ ህፃን በመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት የሚያገኘው ፍቅር፣ ትኩረትና ደህንነት፣ ለዘላለም የሚኖርበትን የስነ-ልቦና ህንፃ መሰረት ይጥላል። መሰረቱ ካልጠነከረ፣ ወደፊት የምንገነባው ፎቅ ምንም ያህል ቢዋብና ቢረዝም... መውደቁ መቼም ቢሆን አይቀሬ ነው።" በመጨረሻም ዶክተር ምትኩ መነፅራቸውን አውርደው ጠረጴዛው ላይ አስቀመጡት። ንግግራቸውን ሁላችንም ልብ ውስጥ በሚቀርጽ ከባድ መደምደሚያ እንዲህ ሲሉ ቋጩት፡ "ስለዚህ፣ ነገ ወላጅ ወይም በዚህ ሙያ ላይ የምትሰማሩ ባለሙያ ስትሆኑ ህፃናትን ዝም ብላችሁ አትገስጿቸው፤ በደንብ ስሟቸው። እነሱ የሚናገሩት በቃላት ብቻ አይደለም። በለቅሶአቸው፣ በሳቃቸው... እንዲያውም አንዳንዴ በዝምታቸው ጭምር ትልቅ መልእክት ያስተላልፋሉ። የልጅነት ስነ-ልቦናን ማወቅ ማለት፣ የሰውን ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በበጎ መንገድ መቅረፅ ማለት ነው። እኔም ታዳያ የሳችውን ንግግር ና ትምህርት ከማርና ከወተት በላይ አጣጥሜው ክረምቱን ............ይቀጥላል Andualem (yosab) https://t.me/andupsychology https://t.me/andupsychology

የምንወደው ወጥመድ ነገሩ እንዲህ ነው። ሰው መቼም ሲፈጠር ባዶነቱን የሚሞላለት፣ ልቡን የሚያሞቅለት ነገር ይፈልጋል። እናም ይወዳል—ሰውን፣ ንብረትን፣ ምቾትን፣ አልፎ ተርፎም የራሱን አስተሳሰብ። መው
የምንወደው ወጥመድ ነገሩ እንዲህ ነው። ሰው መቼም ሲፈጠር ባዶነቱን የሚሞላለት፣ ልቡን የሚያሞቅለት ነገር ይፈልጋል። እናም ይወዳል—ሰውን፣ ንብረትን፣ ምቾትን፣ አልፎ ተርፎም የራሱን አስተሳሰብ። መውደድማ መታደል ነው፤ አለምን የምናይበት መነፅራችን፣ የህይወታችን ጨው ነው። ነገር ግን ይሄው መውደድ ድንበር ሲያጣ፣ "ያለ እሱማ ህይወት የለችም" ወደሚል የልብ ስደት ሲቀየር ነገሩ መልክ ይቀይራል። ገርም እኮ ነው! ነፃነቱን ለማግኘት የአለምን ጦርነት ሁሉ ሊጋፈጥ የሚችለው ያ ጀግና ሰው፣ የሚወደው ነገር ሲመጣ ግን በገዛ እጁ ማርኮኛነቱን ያውጃል። "የወደዱት አይጥፋ" በሚል ሰበብ፣ የልቡን ቁልፍ አሳልፎ ይሰጣል። ነፃነቱን አቅልጦ፣ ህይወቱን አስይዞ ለዚያ ለሚወደው ነገር ይገብራል። በገዛ ፈቃዱ የወርቅ ቀፎ ሰርቶ፣ "እባክህን ዝጋብኝ" ብሎ ቁልፉን ለሌላ አካል ይሰጣል። ታዲያ ያኔ ነው ፈተናው የሚጀምረው። የያዝነው መስሎን ተይዘን እንቀራለን። መውደዱ ወጥመድ ሲሆን፣ እንደ ማር ወለላ የጣፈጠን ነገር እንደ እሬት መራራ መሆን ይጀምራል። "ላለመተው" ስንል ስንት የማንፈልገውን እንቀበላለን? ስንትስ የህሊና ዋጋ እንከፍላለን? ሰው የሚወደውን ላለማጣት ሲል ራሱን ሲያጣ ማየት ያኔ የተለመደ ይሆናል። ለካስ እውነተኛ መውደድ ማሰር ሳይሆን መልቀቅ፣ መሰዋት ሳይሆን ማኖር ነው! ለዚህ እኮ ነው አሁንም ጸሎታችን መሆን ያለበት፦ "ፈጣሪ በምንወደው ነገር አይፈትነን፤ የልባችን መውደድ የህይወታችን ወጥመድ ሳይሆን፣ የበረከታችን መንገድ ይሁን። ✍Andualem (ዮሳብ)