ዮሳብ
Open in Telegram
Channel Description: Welcome to our channel, where we dive into the fascinating world of psychology! Here, you'll find insightful tips and practical advice to enhance your mental well-being and understand human behavior.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
220
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-330 days
Posts Archive
220
Repost from ጲንኤል
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣ የፍልስፍናና የእግዚአብሔር ምስጋና ታላቅ መንፈሳዊ ሀብት ነው።
ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምስጋናና ስለ መንፈሳዊ ዜማ ሲናገር፣ የምስጋና ድምፅ የሰውን ልብ ከምድር ከንቱነት ወደ ሰማያዊው ምስጢር እንደሚያሸጋግርና ነፍስን ከአምላኳ ጋር እንደሚያገናኝ ያስተምራል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ «በገናን አንሱ፤ በበገናም ለእግዚአብሔር ዘምሩ» እያለ እንደተናገረው፣ በገና የንጉሡ የዳዊት እጆች ያረፉበት፣ የነቢያት መንፈስ የፈሰሰበት፣ የቅዱሳን ማኅሌትና የእግዚአብሔር ምሕረት መጠየቂያ ታላቅ የዜማ ዕቃ ነው።
እኛም የዚህን ታላቅ መንፈሳዊ ሀብትና ጥበብ መሠረት በመጣስ ሳይሆን በመጠበቅ፣ ትውልድ ከመንፈሳዊ ሥሩ እንዳይደናቀፍና የቅዱስ ዳዊትን በገና ድርደራ በጥበብና በፍልስፍናው መንገድ እንማር ዘንድ ይህን ታላቅ የትምህርት መንገድ ያሻናል። የበገና ድርደራ ድምፅን ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ነፍስን የማንጻት፣ ምስጢርን የማስተዋልና ከአምላክ ጋር የጠበቀ ቅርበት የመፍጠር ጥበብ ነው።
በኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት የ1ኛ ዙር የበገና ሥልጠና ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ይህ ታላቅ ጥበብ ከተራ የዓለም ድምፅ ተለይቶ ወደ እግዚአብሔር ቅድስና የሚመራበትን ምስጢር ለመቅሰም፣ በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ እንድትሳተፉና የዚህ ታላቅ ጥበብ አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
https://t.me/Oct13wed
220
ቃላት ዝምታን ሰብረው ሲወጡ ትልቅ ኃይል ይሆናሉ፤
አስተውለን ካልተጠቀምንባቸው ግን ሰይፍ ይሆናሉ።
እና ወግን መልካም ቃልን እናጋራ !
መልካም ምሽት !
220
አዲሱ ዓመት ከተለመደው ቀናት አንዱ ሳይሆን አዳዲስ ተስፋዎችን፣ ስኬቶችንና ታላላቅ እድሎችን ይዞልን የሚመጣ ይሁንልን። ።እንኳን ለ አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የደስታና የሁላችንም ህልሞች የሚሳኩበት ብሩህ ዘመን ይሁንልን። መልካም አዲስ ዓመት!
220
+1
ያች በቀጫጭን መስመሮች ተከትባ የተላከች ደብዳቤ በእጅህ ስትገባ፣ የሕይወትህ አዲስ ምዕራፍ በይፋ መከፈቱን አበሰረች—የወረዳ ዐቃቤ-ሕግ ደረጃ-1!
ስማኝ ወንድሜ... ይህ የሹመት ወረቀት የሥራ መደብ መታወቂያ ብቻ አይደለም፤ የሺዎች አምባሳደርነት፣ የደካሞች ተስፋና የእውነት ጋሻ የመሆን ትልቅ አደራ እንጂ!
አሁን አእምሮዬ ወደፊት ተራምዶ በየችሎቱ የምታደርገውን ያን ሞቅ ያለ፣ የጽናትና የሕግ አንቀጾች ፍልሚያ በዓይነ ኅሊናዬ ያየዋል። አንተ የሕጉን አንቀጽ እያጎላህ፣ በእውነት ሰይፍ የሐሰትን ምሽግ ስትንዳ... በዚያች ትንሽ ችሎት ውስጥ ፍትሕ እንደ ጸደይ አበባ እያበበችና እያሸበረቀች ስትሄድ ለማየት አሁኑኑ ጓጉቻለሁ!
ወንጀለኞች ፍርሃት ሲያድራቸው፣ በግፍ የተገፉ ደካሞች ደግሞ በአንተ መኖር ተስፋ ያደርጋሉ፤ ምክንያቱም አንተ በሚዛኑ ላይ ቅንነትን የምትጭን፣ የሕግና የእውነት ዘበኛ ልትሆን ተዘጋጅተሃል።
አምላክ ማስተዋሉን፣ የቆራጥነት የማይወላወል ጥበቡን አብዝቶ ይስጥህ።
እንኳን አበቃህ፣ እንኳን ደስ አለህ ወንድሜ!
220
☦️🕯️ A tree is known by its fruit; a man by his deeds. A good deed is never lost; he who sows courtesy reaps friendship, and he who plants kindness gathers love.🕯️☦️
♰ Saint Basil The Great ♰
220
አንዳንዴ ህይወት የፈለግነውን ያህል አልጋ በአልጋ ባትሆንልንም፣ ያቀድነውን ያህል ስኬት በእጃችን ባናስገባም፣ ትልቅ የውስጥ እረፍት የሚሰጥ አንድ ነገር አለ—እሱም ንጹህ ህሊና ነው።
በሰዎች መካከል ገብቶ አለመያያዝ፣ የሰውን ውድቀት አይቶ አለመደሰት፣ ወይም የሰውን ስኬት አይቶ አለመቅናት በትልቅነቱ ቀላል ይመስላል፤ ነገር ግን በዚች ውስብስብ ዓለም ውስጥ ልብን እንደወረደ ንጹህ አድርጎ ማቆየት ትልቅ ጀግንነት ነው። ሰው ነንና እንሳሳታለን፣ እንሰናከላለን፤ ዋናው ነገር ግን ሆን ብሎ የሰውን ስም አለማጥፋት፣ ለሰው እንባ ምክንያት አለመሆን እና ስህተትን አምኖ ይቅርታን መጠየቅ መቻል ነው።
አለም በብዙ ነገር ልትፈርደብን ትችላለች። ባለን ነገር ወይም በሌለን ነገር ልትመዝነን ትችላለች። በመጨረሻው ግን ከአልጋችን ስንተኛ ከራሳችን ጋር የሚቀረው፣ ከፈጣሪያችን ጋር የሚያነጋግረን የልባችን ጥራት ብቻ ነው።
"ልቤ ንጹህ ነው" ብሎ በሙሉ እምነት መናገር መቻል፣ ከማንኛውም ቁሳዊ ስኬት በላይ ትልቅ የነፍስ ሀብት ነው።
220
አንድ ሰው በሕፃንነቱ ያጋጠመውን እጅግ አስከፊ ገጠመኝ ሳያውቀው ከንቃተ-ሕሊናው (Consciousness) አውጥቶ ወደ ህሊና-ቦዝ (Unconscious) ክፍል ገፍትሮ የመሸሸግ ሂደት በሲግመንድ ፍሮይድ የስነ-ልቦና ቲዎሪ ምን ይባላል?
220
እንዴት አመሻችሁ!
ይህ ቻናል የእናንተም ጭምር ነው! ስለዚህ ለእናንተ የበለጠ ጠቃሚና አሳታፊ የሆኑ ነገሮችን ለማቅረብ እፈልጋለሁ። በዋናነት ምን ዓይነት መረጃዎችና ጽሑፎች እንዲበዙላችሁ ትፈልጋላችሁ? ከስር ባለው ፖል ይምረጡ! 👇
