en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

ዮሳብ

ዮሳብ

Open in Telegram

Channel Description: Welcome to our channel, where we dive into the fascinating world of psychology! Here, you'll find insightful tips and practical advice to enhance your mental well-being and understand human behavior.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
220
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-330 days
Posts Archive
በመተያየት መጽናናት መተያየት ያፀናል ያጽናናል፡፡ ጳውሎስ የቁም እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም ሲወሰድ በመንገድ ላይ ክርስቲያኖችን አየ፡- “ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና” ይላል (የሐዋ.ሥ. 28 15)፡፡ ጳውሎስን የሚያህል ሐዋርያ በማየት ከተጽናና እኛማ እንዴት!? ክርስቲያን ሲገናኝ ምንም ባያደርግም በመተያየቱ ብቻ የሚያገኘው መጽናናት አለ፡፡ መጽናናት ከችግሩ በላይ በሆነ ምክንያት መደሰት ነው፡፡ ወይም መከራው እያለ ከመከራው በላይ በሆነ ምክንያት ማረፍ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም መጽናናት በእሳት ውስጥ ያለ ገነት ነው፡፡ ጳውሎስ ሰንሰለቱ በእጁ አለ፣ ነገር ግን ተጽናና፣ ክሱ አልተለወጠም፣ ነገር ግን ተጽናና፡፡ እግዚአብሔር የሚያጽናናን ችግሩን በማስወገድ ብቻ ሳይሆን ችግሩ እያለም ደስታን በመስጠት ያጽናናል፡፡ ችግሩን ስናይ እግዚአብሔር ይሰወርብናል፣ እግዚአብሔርን ስናይ ደሞ ችግራችን አንሶ እንበረታን፡፡  አንዳችን ለአንዳችን መጽናኛ አድርጎናልና እባካችሁ እንተያይ፣ ኅብረት እናድርግ፡፡ "ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤" ሮሜ  1:11

✝የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ። ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ። "ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር !  እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።     አቡነ ሺኖዳ  ሳልሳዊ

አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ? እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት” ትለዋለህ? ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ? ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር'' ትለዋለህ? ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ” እንዴት ትለዋለህ? ሥጋዊና መንፈሳዊወን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን” ለምን ትላለህ? ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራበት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ? በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅርእንደምንል" እንዴት ትላለህ? የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን” እንዴት ትላለህ? ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን” እንዴት ትላለህ? ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

photo content
+8

ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው። ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን እትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል። ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፣ ተጠማ፣ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔርየምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታደናት ዘንድ

ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፣ ድኽነትህም አይደለም። ሰው የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ከፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ ዕንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው። እንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹAF ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች)

Story adrg asderg
Story adrg asderg

አማኑኤል

photo content

photo content

ጽኑ በሽተኛ ስለሆንኩ ወደ ጽኑ መድኃኒት ተጠጋሁ። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

===Golden principles on the path to salvation=== A certain monk asked St. Anthony the Great, "What must I do to be saved?" Th
===Golden principles on the path to salvation=== A certain monk asked St. Anthony the Great, "What must I do to be saved?" The elder answered him, "Don't trust in your own righteousness, don't worry about what's past, and constrain your tongue and your stomach." (Ancient Patericon, 1.2) Another brother asked Abba Macarius, "How can I be saved?" The elder answered him, "Be like one dead: do not think about insults from people, nor of glory, and you will be saved." (Ancient Patericon, 10.45)

የልዩ ፍላጎት ልጅዎ ለትምህርት ቤት ዝግጁ ነው? ልጅዎ ፊደላትንና ቁጥሮችን ያውቃል፤ ግን ለትምህርት ቤት በቂ ዝግጅት አለው? ለትምህርት ቤት ዝግጁ መሆን ፊደልና ቁጥር ማወቅ ብቻ አይደለም። ልጅዎ፦ መመሪያን መረዳትና መከተል ይችላል? ✔️ ፍላጎቱንና ስሜቱን መግለጽ ይችላል? ✔️ ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወትና መግባባት ይችላል? ✔️ ተራውን መጠበቅ ይችላል? ✔️ ስሜቱን በተገቢው መንገድ መቆጣጠር ይችላል? ✔️ ከቤት ውጭ በራሱ መንገድ መላመድ ይችላል? ቀደም ብሎ የሚጀምር ድጋፍ የልጅዎን መማር፣ መግባባት፣ ራስን መቻል እና ማህበራዊ ክህሎቶች በጊዜው እንዲጎለብቱ ትልቅ እድል ይፈጥራል። በብሉም የሳይኮሎጂ አገልግሎት ልጅዎ ለትምህርት ቤት፣ ለቤት እና ለዕለት ተዕለት ሕይወት የሚያስፈልጉትን መሰረታዊ ክህሎቶች እንዲያዳብር ከልጅዎና ከቤተሰብዎ ጋር እንሰራለን። የልጅዎን እድገት ለነገ አታስቀምጡ፤ ዛሬ ይጀምሩ! +251-986-777-555 #ብሉም_የሳይኮሎጂ_አገልግሎት #ልዩፍላጎት #የልጆችእድገት #ትምህርትቤትዝግጅት #የወላጆችምክር

Welcome Program for 2nd to 4th year students In the name of the Father, the Son, and the Holy Spirit, one God, Amen 🙏🙏🙏 Christian in Christ In the Son, the Son of God How are you, the family of the Most High God, the children of the Holy Virgin Mary, the friends of the saints, who are called by the Holy Spirit? Amen!!!! May the name of our God be praised 🙏🙏🙏 Tomorrow, Saturday, 23/01/2019 As the Welcome Program and the special program we look forward to every week on Saturdays begin, we urge everyone to attend, and in the name of God Almighty, we send our message 🙏🙏🙏 Reminder 👉 Respect the time. 👉 Move well. 👉 It is impossible to miss ⛪️ Location: Semera Course Location ⏰⏰ It starts at 11:00. May God be with us all 🙏🙏🙏

የዌልካም መረሃ ግብር ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት   ተማሪዎች በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን🙏🙏🙏 በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ወልደ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳውያን የተሰኛችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመስቀል ስር የአደራ ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንዴት ቆያችሁ ? አሜን!!!! የአምላካችን የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን 🙏🙏🙏     ነገ ማለትም ቅዳሜ በቀን 23/01/2019   የዌልካም መርሃግብር እና እንድሁም በየሳምንቱ በጉጉት የምንጠብቅው ቅዳሜ  ልዩ መረሃ ግብር ስለሚጀምር በመቀሳቀስ  ሁላችንም እንድንገኝ ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም መልዕክታችንን እናስተላልፋለን 🙏🙏🙏                 ማሳሰቢያ 👉 ሰዓት ይከበር 👉 በደንብ እንቀሳቀስ 👉 መቅረት አይቻልም ⛪️ ቦታ : ሰመራ ኮርስ ቦታ         ⏰⏰  11:00 የሚጀመርበት ነው። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን🙏🙏🙏

photo content
+2

Why we cannot pray together with heretics? Why it would not be "just an act of friendship and peace"? Let's at first remember
Why we cannot pray together with heretics? Why it would not be "just an act of friendship and peace"? Let's at first remember that forbidden fruit in the Eden looked sweet and safe too but this turned out to be a great delusion with awful circumstances. The same happens with prayer with non Orthodox. 1) We are not prohibited from having any casual communication with non-Orthodox. Sometimes, they are literally our family, or friends, colleagues. 2) ancient Christians were much stricter with those who distort the true teaching. They, actually guarded it with their lives. Not for us to destroy it now. 3) Orthodox Christian understands, that we can't pray together with non Orthodox for the sake of their salvation. Otherwise they will never know what's wrong. Of course we should do it with love and patience for this action to be fruitful.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ውድየልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች  እንደምን ቀያችሁ?አሜን!!! ነገ ማለትም ሐሙስ በቀን 14/01/2019 ዓ.ም እንኳን ደህና መጡ (WELL COME ) መርሐ ግብር በቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን እንደ ሁለቱም ግቢ ስለተዘጋጀ ። ስለዚህ ሶስተኛ እና አራተኛ ዓመት ኦርቶዶክሳዉያን ተማሪዎች በሙሉ ተቀሳቅሰን በመገኘት የመርሀ ግብሩ ተካፋይ እንድንሆን በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን። የዕለቱ መርሐ ግብሮች   1,ስብከተ ወንጌል   2 መዝሙር ⏰ሰዓት: ሰርክ 11:00 የምንጀምርብት ነው 🌍ቦታ: ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ማስታወሻ *መርሐ ግብሩ የተዘጋጀው እንደ ሁለቱም ግቢ ነው። *ማስታወሻ እንዳንረሳ *ስንመጣ ቢያንስ 10 ሰው እንቀስቅስ አዘጋጅ፡-ዋና ግቢ ጉባኤና ኦዳያ ግቢ ጉባኤ በጋራ በመሆን

photo content