en
Feedback
የልብ ጥበብ

የልብ ጥበብ

Open in Telegram

✨ This channel deeply explores eternal values ✨ Truth, Knowledge, Beauty, Thought, Life, Death, Love, Humility, and Purity.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
253
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+530 days
Posts Archive
መከተል ማባረር ሲሆን፤ መሄድ ማስከተል ይሆናል። በእርግጥ: ሰው የፈለገውን ከሚገኝበት ቦታ ሄዶ ቢፈልግ ስኬታማ ይሆን ነበር። ፀጋ ከሆነ ከባለፀጋው ሰላም ከሆነ ከባለ ሰላሙ ክብርንም ቢሆን ካክባሪው...... .......ቢፈለግ መልካምም፣እውነትም ነው። ይሁን እንጂ : በመንፈስም ሆነ በስጋ ተቃራኒ በሆንክበትና በማትግባባበት ስፍራ መቀመጥህ በመንፈስም ይሁን በስጋ ግጭት እንጂ ስምምነት እንድታተርፍ አያደርግህም! መሄድህ ለህልውናህ ጥሩ አማራጭ ሲሆን ማስከተልን ስታተርፍ ደግሞ መሄድህ የጥንካሬህና የእውነትህ ምልክት ይሆናል። እነሆ በልል ምሳሌ🫱 ቢራቢሮን ማሯሯጥ ትርፉ ድካም ነው። ይልቅ ያንተ ለማድረግ አበባ መሆኑ የተሻለ ነው። ጥበብም ብትሆን ስትጣራ እንጂ፤      ተጠርታ ስትመጣ አላየንም ፤ #መሄድ #ነጻነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ያላከበርከውን አታፈቅርም፤ ያላፈቀርከውን አታከብርም። ፍቅር እና ክብር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ሲሆኑ አንዱ ከሌለ ሌላው አይጸናም። ስለዚህ: ስለ ፍቅር ብለህ ክብር አትንካ! ስለ ክብር ብለህም ፍቅር አታጉድል! ፍቅር ሳትሰጥ ክብርን አትሻ! ክብርንም ሳትሰጥ ፍቅርን አትጠብቅ! ......... ውበትን የራስ የማድረግ ፍላጎት ቅጥፈት እንጂ ፍቅር አይባልም። የምትፈልጋትን አታፈቅራትም፤ የምታፈቅራትን አትፈልጋትም። #ፍቅር #ክብር #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

እውነት ተጫዋቿን እንጂ ተመልካቿን አትሸልምም። ከሩቅ ቆመህ የምትመለከታት እውነት፤ ቀንደኛ ደጋፊዋም ብትሆን አትሸልምህም። እውነት የምትገለጠው ለሚሳተፍ ነው። ለሚታገል ነው። ለሚያምን ነው። ስለእውነት ስለተናገርክ ብቻ እውነትን ከኖሩት ጋር ተሰላፊ መሆን አትችልም። ራስህን አትሸውድ በአፍህ የምታውቀውን እውነት፤ በኑሮም እወቀው። በእርግጥ እውነትን ለመኖር መመልከት መሠረት ነው! #እውነት #ተመልካች #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

መኖርን ያላሸነፈ መሞትን ይፈራል። የሞት ፍርሀት በቃኝ (አልጠግብ ባይነት) ካለማለት ይነሳል። በቃኝ አለማለት ለአዕምሮ ስቃይ መነሻ ነው። ለአዕምሮ ስቃይ ምክንያት የሆኑት ደግሞ እነዚህ ናቸው : አለማወቅ : ከፍላጎት ጋር መጣበቅና : ጥላቻ ሞትን ላለመፍራት: - እውቀትን ሰብስብ (አንብብ ፣ፃፍ ፣አዳምጥ ፣አስብ) - ማወቅህን እወቅ(ፍላጎትህን በማወቅህግዛ) - አትቅና ( ቅናት የእኔነት (egoism) ውጤት ሲሆን ራስንና ሌሎችን ወደ መጥላት ያደርስሀል።) እነዚህን ስታደርግ በቃኝ ማለት ትጀምራለህ። ለምን? - የማወቅን አለማለቅ ትረዳለህ - የስጋህን ገደብና የመንፈስህን ምሉዕነት፣ የአለምን ድግግሞሽና አሰልቺነት ትረዳለህ - ፍቅር ፣ ትህትና ፣ እምነት የሰውነት መለኪያና የጥላቻ ጠላት እንደሆኑ ትረዳለህ። ሞትን የሚፈራው "በቃኝ" ማለት የማይችል ነው። በዓለም ላይ ፈሪ ሰው በቃኝ የማይል ሰው ሲሆን "አስፈሪው ሰው ደግሞ ሞትን የማይፈራ ሰው ነው።" #ሞት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ምንጭና ምክንያት የሌለው መኩራራት አስቂኝ እና አሳዛኝ ነው። በምን? ለምን? እንደሚኩራራ ምክንያት ሳይኖረው የሚኩራራ: ከሰውነት ዝቅ የማለት ወይም የአዕምሮ መዛባት (Mental Disorder) ተጠቂ ሊሆን ይችላል። ይህ አይነቱ ሰው ባዶ ሆዱን እንደሚነፋ ድሀ ሰው ሲመሰል ሳቅን ከሀዘኔታ ጋርም ያጭራል! በጥቅሉ ኩራት: ራስን ከፍ አድርጎ እንደማየት ሆኖ ሲተረጎም በተዘጋ ባዶ እቃ ይመሰላል። ኩራት: ራስን እኩል አድርጎ እንደማየት ሆኖ ሲተረጎም ጉርምስና ወይም ስጋዊነት ይባላል። ኩራት: ራስን ከሁሉ ዝቅ አድርጎ እንደማየት ሆኖ ሲተረጎም ሰውነት ወይም ትህትና ተብሎ ይጠራል። ይህ ከራስ ነፃ መውጣት ይባላል። ከራስ ነፃ መውጣት ጥቅሙ ደግሞ ዓለም በምትከለክልህ እና በማትሰጥህ ነገሮችም ሁሉ የማይነቀነቅ ሰላም ባለቤት ትሆናለህ። ከራስህ ነፃ ውጣ! #ከራስ ነፃ መሆን #የልብ ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

የሰው መድረሻው ወደ መነሻው ነው።             ትልቅነት ወደ ልጅነት ሲሆን: አዕምሮህ መሞገት የማይችለውን የፈጣሪ እውቀት ያለጥያቄ ማመን ትጀምራለህ።   ያለምክንያት ትሰ'ጣለህ፤ ትሰጣ'ለህ     ውበትን ሁሉ በንፅህና ታደንቃለህ..         ፍቅርህ በሁኔታ አይገደብም..    እውነትን ያለ ፍርሀት ትመሰክራለህ..        መነሻህን በቅርብ ርቀት ታያለህ .. ትልቅነት ማገልገል እንደሆን ትረዳለህ          ........ ሳትዋጋ ትነግሳለህ፤ሳትጣራ ትከበባለህ! ........ ሞትህ ይታደስና 1 ብለህ 2 የማትለውን   ያልተገደበ መኖር ትኖራለህ። ህይወት ለንፁሀን የምትፈርገው እውነተኛ የምልሰት ፍርድ ይህ ነው።              ወደ ልጅነት እደግ! #ትልቅነት #ልጅነት #የልብ_ጥበብ ©የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

እውነት-እውነት እልሀለው እውነት-ሀሰት የሆነ ህይወት ካለመኖር ያነሰ ነው።                                     ለምን ? ካንዳንድ ሳቅ ማልቀስ ስለሚሻል   ካንዳንድ ጥጋብ መራብ የተሻለስለሚሆን   ካንዳንድ መሮጥ መቆም መሮጥ ስለሆነ             ካንዳንድ መዋደድ ጥላቻ ፍቅር ስለሆነ ካንዳንድ ማወቅ አለማወቅ የሻለ ስለሆነ      ካንዳንድ መሰብሰብ መበተን ስለሚሻል     ካንዳንድ ልማት መፍረስ ስለሚሻል        ካንዳንድ መኖር ሞት ህይወት ስለሆነ              እውነት በእውነት ስትደበቅ "እውነት" ዘላለም የተደበቀች ትሆናለች!               #እውነት-ሀሰት #የልብ-ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ምህረት እድል እንጂ ድህነ"ት አይደለም። ብዙዎች ምህረትን ድክመት አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን ምህረት ታላቅ ጥንካሬ ነው። ምህረት ከበቀል ነጻ መውጣት ነው። ምህረት ከጥላቻ መላቀቅ ነው። ምህረት ዋነኛ የፍቅር መገለጫ ነው።         ምህረት ማድረግ ማለት፦ ምህረት ሰቶ መራቅ ወይም መሸሽ አይደለም ፤ ይህ የልብ ምህረት አይሆንም። ያለፈውን ረስቶ እንደ ሌለ ማሰብም አይደለም ፤ አዲስ እምነትን ለመገንባት እድል መስጠት ነው እንጂ። ምህረት አዲስ መነሻ እንጂ አዲስ ማብቂያ አይደለም! #ምህረት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ቃል እንደ ውሃ ነው! ውሀ ሲፈስ ልብን እንደሚያረሰርስ፤ የለዘበ ቃልም እንዲሁ ነው። ውሀ ሲደርቅ ሰንጥቆ ይጥላል፤ ደረቅ ቃልም ልብን ይሰብራል። ንፁህ ውሀ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእውነት ቃልም ጨለማን ያበራል። የተበከለ ውሀ ግን ሞትን ይጠራል፤ የሀሰት ቃልም ፍዳን ያመጣል። ያለ ውሀ መኖር እንደማይቻል፤ ያለ ቃልም መኖር ዲዳነት ነው። ውሃ ተንጠባጥቦ ድንጋይን ይሰነጥቃል ፤ ቃልም ቀስ በቀስ ልብን ይለውጣል። #ቃል #ውሃ #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ሰው ሲተኛ ይነቃል ሲነቃ ይተኛል! ሥጋ ሲተኛ ነፍስ ከፍ ወዳለ ዓለም ትነቃለች። ሥጋ ሲነቃ ነፍስ በግርግር ፣ በጭንቀት ፣ በስጋ ምኞት ውስጥ ዝላ ትተኛለች። እውነተኛ ንቃት ሁለቱም ሲነቃቁ ነው፤ ነፍስም ስጋም እንደ ፍህም ብረት ሲሆኑ፤ ተኝተህ ስትነቃ ሳይሆን! ነቅተህ ስትተኛ። እንዲያ ሲሆን:   ስጋህ በነፍስህ ምሉዕነትን ያገኛል፤        ይህ ሲሆን ደግሞ:- ሳይነግሩህ! ያልነገሩህን ማወቅ ይቻልሀል፤  በቆምክበት ቦታ ሆነህ! ባልቆምክበት ቦታ መገኘት ይቻልሀል። "ይህ እንዴት ይሆንልኛል?" ንፁህ ሁን ! ሀሳብህን ተቆጣጠር ! ነቅተህ ተኛ ! #ንቃት #ነፍስ #ሥጋ #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

የማሰብ ፍላጎትህ የቀነሰው የመብላት ፍላጎትህ ሲጨምር ነው። የማሰብ ፍላጎት ወደ ላይ ይወስዳል። የመብላት ፍላጎት ወደ ታች ይስባል። ሁለቱን ሚዛናዊ ስታደርግ: ነፍስህ በእውቀት ትመራለች። ስጋህን የነፍስ ዕውቀት ይመራታል። የነፍስ እውቀት፤የስጋን ድካም ይቀንሳል! #ማሰብ #የልብ ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

አልማዝነትህን ማየት የሚችሉት በእሳቱ ዙሪያ መኖር ሲጀምሩ ብቻ ነው። አልማዝ መሰረቱ ሙቀት እና ግፊት ነው። ስለ አልማዝነት ከመናገር ባለፈ ማየትና ማጣጣምም ያልተቻለው ዙሪያው እሳት መሆኑ ብቻ ነው። አልማዝ የሆኑ ሰዎችንም ችላ አትበል! ሌሎች አጊጠውበት ያየህ ቀን ከማድነቅ ያለፈ ስልጣንን አታገኝም። በትልቅ ሙቀት ፣ ግፊት እና ጥልቀት ውስጥ መኖር የአልማዝነት ምልክት ነው። ማንነትህን ማወቅ ከፈለክ እና አልማዝ መሆንም ካሻህ ከመቅረብ ባለፈ ወደ እሳቱ ግባ። ማንነትህን ስላጣጣሉ አትበሳጭ እዘንላቸው እንጂ ፤ አንተ በቆምክበት አልፈው የመጡት ጥቂቶችና አንፀባራቂዎች ናቸውና። የአልማዝ አድናቂ ሆነህ መዳብ ተከታይ ከሆንክ ክፉ አንተነትህ ውስጥህ ተቀብሮ እየጎተተህ ሊሆን ይችላል እና ተጠንቀቅ! #አልማዝ #እውነተኛ ማንነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ውሃ በሌለበት በእሳት አትጫወት። እሳት ኃይል ነው። ሊጠቅም ይችላል፣ ሊያጠፋም ይችላል። ያለ ውሃ ከእሳት ጋር መጫወት ጥፋት ነው። በሕይወትህም እንደዚሁ፦ አደገኛ ነገር ማድረግ ከፈለክ፣ መጀመሪያ መከላከያህን አዘጋጅ። እሳትነቱ ከውሀነትህ ከበለጠ ውሀነትህን ጨምረህ ና ያኔ አሸናፊ ትሆናለህ። ደህንነትህን አረጋግጥ። ከዚያ በእሳት ተጫወት። ውሀ ታጥቀህ ሞግት ጥልን እንዳታተርፍ። #ጥበብ #ደህንነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

የማታውቀውን ለማወቅ የምታውቀውን አድርግ። አዲስ ነገር ለማወቅ ቀድመህ የምታውቀውን ተግብር። ያለመተግበር እውቀት ሙት ነው። የምታውቀውን በምታደርግ ቁጥር ፣ ወደማታውቀው የሚከፈትልህ በሮች ብዙ ይሆናሉ። እውቀት በተግባር ይበረታል። መረዳት በሥራ ይገነባል። ስለዚህ ዛሬ የምታውቀውን አድርግ። ነገ የማታውቀውን ታውቃለህ። #እውቀት #ተግባር #እድገት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

እንደ ነፋስ አትሁን እንደ መሬት ሁን። እንደ ነፋስ ስትሆን - መፍጠንህ ጥበብ ይመስልሀል -ሁካታህ መሬትን የሚያስጨንቅ                  ይመስልሀል። መሬት ያመቀችው ነፋስ ፣እሳት ፣ውሀ ቢገለበጥ ግን መኖርን ወደ አለመኖር ይቀይራል። ነፋስ ማፍረስ መለያው ነው። መሬት ግን ሁሉንም ትሸከማለች። ስለዚህ ባሕርይህ እንደ መሬት ይሁን፦ ጸንቶ መቆየት፣ የማይለወጥ፣ ሁሉንም የሚሸከም። ስሜትህ እንደ ነፋስ ቢሆንም፣ አንተ ግን እንደ መሬት ቁም። #ጽናት #መረጋጋት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

በማይታይ አካል የሚታይ አካልን ከማይታይ አካል ስታዋህድ ሙሉ ሰው ትባላለህ!       ነፍስህ ሥጋህን ስትመራ፣ ሀሳብህ ተግባርህን ስትቀድም፣ ልብህ ቃልህን ሲወልድ፣ ቃልህ በመንፈስህ ሲቃኝ፣ በቃልህ ልብህ ሲታይ! ያኔ ነው ሙሉ ሰው የምትሆነው። ሙሉ ሰው ማለት ውስጡ እንደ ውጩ      ነው ፤ውጩም እንደ ውስጡ ነው። ስለዚህ በውስጥህ ያለው እውነት በውጭህ ይገለጥ። በውጭህ ያለው ተግባርህ ወደ ውስጥህ ያመልክት። ያኔ ሙሉ ሰው ትባላለህ። እንዴት ይህ ይሆናል?       ልብህን አንፃ! ፍላጎትህን በማወቅህ ግዛ!      #ሙሉ_ሰው #አንድነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

በመኖር ያልፈተኗት እውነት ሀይል የላትም ሰይጣን የደበቀብን እውነትን ሳይሆን መኖርን ነው።          እንዴት ያለ ጥበበኛ¡ ነው ባካችሁ።     ምን ማለቴ መሰላችሁ: ያልጠነከረ ቅርንጫፍ ፍሬ ሲያዝል ለገበሬው አስከፊ ነው ፍሬዎቹን ሳይበስሉ ያረግፋልና! ሌሎችን መሸከም የሚፈልጉ ግን ያልጠነከሩ ቅርንጫፎች፦ ነፋስ ያወዛውዛቸዋል                   - ማንም በቀላሉ ይሰብራቸዋል         - ፍሬያቸውንም ሳይበስሉ  ያወድቃሉ ስለዚህ ኃላፊነት ከመውሰድህ በፊት ጠንክር። ሌሎችን መደገፍ ከመጀመርህ በፊት ራስህን ገንባ። "አለማወቅህን ለተማሪዎችህ ንገራቸውና ናና  ተማር" #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ብርሃን ካልተከተልክ ጥላ ተከታይ ትሆናለህ። ሕይወት ምርጫ ናት። በየቀኑ ትመርጣለህ። ግን ብርሃንን ስትመርጥ፦ እውነትንና ትጋትን፣ ቅንነትንና እምነትን፣ ተስፋንና ፍቅርን መርጠሀል።    ይህ አይደለም የሚያስደንቀው ከብርሀን በራቅህና ጥላን በተከተልክ ቁጥር ጨለምተኝነት እውነተኛ ባህርይህ እየሆነ ይመጣል። ለጥላህ መሪ ሁን ያኔ እውነትንም ታገኛለህ! #ብርሃን #ጥላ #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

የትኛውም አገልግሎት ፍቅር ከሌለው ግብዝነት ነው። ለሰው ልትታወቅ ስታገለግል፣ ግብዝ ነህ። ለምስጋና ስታገለግል፣ ግብዝ ነህ።       እውነተኛ አገልግሎት ከፍቅር ብቻ ነው የሚመነጨው። እሱም: ከተግሳፅ ማፅናናትን ያስቀድማል      በማፅናናትም ይፈፅማል። ይህ ደግሞ ፍቅር ይባላል። #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

እኔነት ሁሌም ተበዳይ ነው። ለዛም ነው ፍርደኛ የጠፋው።     ሁሉም: "እኔ ተጎጂ ነኝ" "በእኔ ላይ በደል ተፈጽሟል" "ሰዎች ጎድተውኛል" የሚል ከሆነ ማን በዳይ ማን ተበዳይ ሊሆን ነው? እውነተኛ ጠቢብ ግን ሁሌም ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው።            እኔነትህ በተበዳይነት ውስጥ ጠልቆ ፍርደኛነትን ያስረሳል። ራስህን ከተበዳይነት አውጣ። ለራስህ ፍርድ ስጥ። #እኔነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab