en
Feedback
የልብ ጥበብ

የልብ ጥበብ

Open in Telegram

✨ This channel deeply explores eternal values ✨ Truth, Knowledge, Beauty, Thought, Life, Death, Love, Humility, and Purity.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
253
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+530 days
Posts Archive
✨✨✨     🌅 ዓይን እና እውነት 🌅                            ✨✨✨       ☀️ ዓይን ሲሰፋ እይታ የማያጠበው                 እውነት አለ። ☀️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💫 ገዝፈው ፣ ደምቀውና ጣፍጠው የሚታዩህ ነገሮች በመረዳት የተቃኘ እይታ ሲኖርህ ይደቅቃሉ ፣ ይደበዝዛሉ ይመራሉ። 💫 ሰው ስለሚመለከተው ያስባል፤ ስለሚያስበው ይመለከታል! 💫 ለዚህም ነው ዓለም ተቆነጃጅታ ከዓይንህ ፊት የምትቀርበው፤በዓይንህ እንድትመለከታት የሆነው ፤ ዓይንህንም እንዳትነቅል የተጠመድከው። ➡️ ይህ የዓይን ወጥመድ ደግሞ የሞት ቀስት ነው!                    ነገር ግን:- 💫  እመነኝ ዓይንህን ክፈት፣ አስፋ ለእይታህ የማይደቅቅ አንድ እውነት ታገኛለህ እርሱም ፍቅር ❤️‍🔥 ይባላል!            እርሱም ታሞ መፈወስ ነው!          እርሱም የህይወት መንገድ ነው!           እርሱም ፍትህና እውነት ነው!           እርሱም ፅኑ ሰላማዊነት ነው!          ........ 💫 እውቀትም ጥበብም ሀብትም በማብዛት የማይደርሱበትን እውነት የዋህ ፣ ቅን ፣ ትሁትና ንፁህ ልቦና ይደርስበታል!🫡 #ዓይን #እውነት #የልብ_ጥበብ                   ✨✨✨ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab                    ✨✨✨

✨✨✨ 🌅 ዓይን እና እውነት 🌅 ✨✨✨ ☀️ ዓይን ሲሰፋ እይታ የማያጠበው እውነት አለ። ☀️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💫 ገዝፈው ፣ ደምቀውና ጣፍጠው የሚታዩህ ነገሮች በመረዳት የተቃኘ እይታ ሲኖርህ ይደቅቃሉ ይደበዝዛሉ። 💫 ሰው ስለሚመለከተው ያስባል፤ ስለሚያስበው ይመለከታል! 💫 ለዚህም ነው ዓለም ተቆነጃጅታ ከዓይንህ ፊት የምትቀርበው፤በዓይንህ እንድትመለከታት የሆነው ፤ ዓይንህንም እንዳትነቅል የተጠመድከው። ➡️ ይህ የዓይን ወጥመድ ደግሞ የሞት ቀስት ነው! ነገር ግን:- 💫 እመነኝ ዓይንህን ክፈት፣ አስፋ ለእይታህ የማይደቅቅ አንድ እውነት ታገኛለህ እርሱም ፍቅር ❤️‍🔥 ይባላል! እርሱም ታሞ መፈወስ ነው! እርሱም የህይወት መንገድ ነው! እርሱም ፍትህና እውነት ነው! እርሱም ፅኑ ሰላማዊነት ነው! ........ 💫 እውቀትም ጥበብም ሀብትም በማብዛት የማይደርሱበትን እውነት የዋህ ፣ ቅን ፣ ትሁትና ንፁህ ልቦና ይደርስበታል!🫡 #ዓይን #እውነት #የልብ_ጥበብ ✨✨✨ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab ✨✨✨

✨✨✨         🌱 ሙሉነት እና ትህትና 🌱                     ✨✨✨       ☀️ ሙሉ ሰው የመሆን መሰረታዊ                 ግብአት ትህትና ነው። ☀️         💫 ያለ ትህትና ሙሉነት አይጠናቀቅም፤            ያለ ሙሉነት ትህትና አይመሰረትም።                                         ━━━━━━━━━━━━━━━ 💫 ልክ እንደ ሕንፃ መሠረት ትህትና ሙሉነት የሚገነባበት መሠረት ሲሆን ራሷ ደግሞ ፍቅር ነው ፤ እንግዲህ ይህ መሰረት ሲሰፋ ከፍታ ከፍ  ይላል።       ⚡ ትህትና የነከሱትን እኔነት መትፋት ነው። ⚡ ትህትና ከታች ወደ ላይ መመልከት ነው። ⚡ ትህትና የማያልቅ የማወቅ ዝግጅት ነው። ⚡ ትህትና የማይቆም መከተል ነው።             ..............      እነኚህ በሰውነት ሚዛን የተለኩ ናቸው!            እንጅ ትህትና የማይደረስባት                  የሰማይ ዙፋን ናት!                                     ✨✨✨     #ትህትና #ሙሉነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab                      ✨✨✨

🌤️ እውነተኛ ደስታ 🌤️ ☀️ በስጋት ደስታ ውስጥ መቀመጥ ከመከራ አያንስም። ☀️ ⚡በስጋት ውስጥ ሆኖ መደሰት፤ ⚡በነፋስ ውስጥ ሆኖ በሻማ ብርሀን እንደ መጓዝ ነው። ⚡እሳት በሆነ ብርሀን ውስጥ ገብቶ በስጋት እየተቃጠለ በሚስቅ ትውልድ አትቅና!           💫የእውነት ፀሐይን ተስፋ አድርገህ በድቅድቁ የተጨመትክ! አንተ ፅና እንጂ አትቅና!  🌟 : -"ለሞት ነው"በሚያስብል አኗኗር አትኑር! -"ለልቅሶ ነው" በሚያሰኝ ሳቅም አትሳቅ! -"ለፀፀት ነው" በሚያስብል እርካታ አትርካ!      የስጋት ደስታን "በቃኝ" በል! 💫 በምንኖርበት አለም ያለ ስጋት መኖር ባይቻልም ፤ ፍፁም ሰላምና ደስታ ባለበት በማይጠፋ የእውነት ብርሀን ውስጥ ግን መኖር ይቻላል! ተችሏልም። እሱም ከ"እኔነት" መነጠል ነው፤ እሱም ከራስ "ነፃ" መውጣት ነው! እሱም የመንፈስ ፍሬ ነው፤ እሱም ፍ..ቅ..ር ነው! ✨✨✨ #እውነተኛ_ደስታ #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab ✨✨✨

✨✨✨ ⚖️ ሁለቱ ኃይሎች ⚖️✨✨✨     ☀️ ሰው በሰጭና በወሳጅ ኃይሎች           የተወጠረ ነው። ☀️ 🌟 ሰጭ ኃይል — ፍቅር፣ ምሕረት፣ ትህትና፣            መጋራት ዋና መገለጫዎቹ ናቸው። 🌟    በዚህ ሀይል ያለ ገደብ በእውቀት ላይ መንቃትን ታተርፋለህ!   ይህ ሁለንታን የፈጠረ በሰው ልብ ውስጥ የተዳፈነ ሀይል ነው።               ⚡ ወሳጅ ኃይል — ምኞት፣ ኩራት፣ ራስ ወዳድነት፣ መያዝ መገለጫዎቹ ናቸው ⚡ በዚህ ሀይል ደግሞ ከራስህ የተወሰደን ሀይል በዋጋ የምትደርስበት  የተገደበና የተዳፈነ ንቃተ እውቀት ነው።     አሁን አለም የደረሰችበት ስልጣኔ የዚህ ምሳሌ ነው!         💫 ወደ ሰጭ ኃይል ስታዘነብል           ነጻ ትሆናለህ! 💫     💫 ወደ ወሳጅ ኃይል ስታዘነብል           ባሪያ ትሆናለህ! 💫     ⚖️ ምርጫው ያንተ ነው!           ነጻነትን ወይስ ባሪያነትን? ✨✨✨#የልብ_ጥበብ✨✨✨ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

✨✨✨ ⚖️ ሁለቱ ኃይሎች ⚖️✨✨✨ ☀️ ሰው በሰጭና በወሳጅ ኃይሎች የተወጠረ ነው። ☀️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌟 ሰጭ ኃይል — ፍቅር፣ ምሕረት፣ ትህትና፣ መጋራት ዋና መገለጫዎቹ ናቸው። 🌟 በዚህ ሀይል ያለ ገደብ በእውቀት ላይ መንቃትን ታተርፋለህ! ይህ ሁለንታን የፈጠረ በሰው ልብ ውስጥ የተዳፈነ ሀይል ነው። ⚡ ወሳጅ ኃይል — ምኞት፣ ኩራት፣ ራስ ወዳድነት፣ መያዝ መገለጫዎቹ ናቸው ⚡ በዚህ ሀይል ደግሞ ከራስህ የተወሰደን ሀይል በዋጋ የምትደርስበት የተገደበና የተዳፈነ ንቃተ እውቀት ነው። አሁን አለም የደረሰችበት ስልጣኔ የዚህ ምሳሌ ነው! ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💫 ወደ ሰጭ ኃይል ስታዘነብል ነጻ ትሆናለህ! 💫 💫 ወደ ወሳጅ ኃይል ስታዘነብል ባሪያ ትሆናለህ! 💫 ⚖️ ምርጫው ያንተ ነው! ነጻነትን ወይስ ባሪያነትን? ✨✨✨#የልብ_ጥበብ✨✨✨ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

እውነት እጅግ መራራ ምትሆነው አህዮች ሲቀምሷት ነው። "እውነት ለንጹህ ልብ ከማርም ሸገር ብላ የጣፈተች ናት። ለርኩስ ልብ ግን መራራ ናት።" #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

በንጹህ መስታወት እውነተኛ ፀሐይ ይገለጣል። በንጹህ መስታወት እውነተኛዋ ፀሐይ እንደምትገለጥ በልብ ውስጥም ያለው እውነተኛ ሀይል በአካላዊና በመንፈሳዊ ንፅህና ይገለጣል። - ያልጠራ ዓይን እውነተኛ
በንጹህ መስታወት እውነተኛ ፀሐይ ይገለጣል። በንጹህ መስታወት እውነተኛዋ ፀሐይ እንደምትገለጥ በልብ ውስጥም ያለው እውነተኛ ሀይል በአካላዊና በመንፈሳዊ ንፅህና ይገለጣል። - ያልጠራ ዓይን እውነተኛ ምስልን ማየት እንደማይችል። - ያልጠራች ልብም እውነተኛ እውነትን አታይም።     ሰዎች በልባቸው መቆሸሽ ልክ እኔነታቸውም በዚያው ልክ ጨምሯል። ........ ->በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች የአንድን ነገር ትክክለኛነት ወይም እውነተኛነት በስጋዊነታቸውና በፍላጎታቸው ይለካሉ። ይህም እውነትን የምናዳምጥበትን የህሊናችንን ጓዳ ቆልፎታል።       ለዚህም ነው እውነቱን እያወቅነው ውሸት መስማት የሚያስደስተን!😂 *በልብ ንፅህና መሰረቷን እምነት ያደረገች ነፍስ እውነትን ታያለች ሐሴትንም ታደጋለች። #ንጽህና #መስታወት #fyp #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ላለመጓዝ በምትጓዝ አለም ውስጥ ዘላለማዊ ጉዞ መመኘት ቅዠት ነው። ኑሮ ማቅለል የሚልን የስልጣኔ መርህ እኔ "የስንፍና መርህ" እለዋለሁ። ለምን? ምቾትን መሰረት አድርጋ ሰለጠነች በምትላት ዓለም ውስ
ላለመጓዝ በምትጓዝ አለም ውስጥ ዘላለማዊ ጉዞ መመኘት ቅዠት ነው። ኑሮ ማቅለል የሚልን የስልጣኔ መርህ እኔ "የስንፍና መርህ" እለዋለሁ። ለምን? ምቾትን መሰረት አድርጋ ሰለጠነች በምትላት ዓለም ውስጥ ሆነህ ዘላለማዊነትን መመኘት ንቃትን መኝታ ቤት ውስጥ እንደ መፈለግ ነው። ሀሳቦች ሁሉ ላለማሰብ ከሆኑ ፤ መሮጥ ሁሉ ለመድረስ ከሆነ ፤ ማወቅ ሁሉ ላለማወቅ ከሆነ ፤ ድካም ሁሉ ለማረፍ ከሆነ -> ደስታ ሁሉ ለሀዘን ይሆናል ፤ ሰላም ሁሉ ለሁከት ይሆናል ፤ ወደድክም ጠላህም መኖርም ሁሉ ላለመኖር ይሆናል! ስለዚህ ዘላለማዊነትን ->ለመጓዝ በምትጓዝ ዓለም ውስጥ ፈልጋት! 😇 #ጉዞ #fyp #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ደስታን የምታጣው በቃኝ የማለት አቅም ስታጣ ነው። ጭንቀት እጅግ ከበዙ ነገሮች ይወለዳል። ገደብ ከሌለው : ሀሳብ - ውበት - ሀብት..... እንዲሁም ገደብ የሌለው ጥሩ ምግብ የመብላት ፍላጎትም አዕምሮን ከረቂቅ እውቀቶች ከመግታቱ ባሻገር ጭንቀትን ይፈጥራል። "በቃኝ" ከማለት ግን ርካታ ይገኛል። "በቃኝ" ማለት ከማይችል ሰው ልብ ውስጥ፤ ሕይወት የማትጠናቀቅ ናት፤ ደስታና ሰላምም ሩቅ ናቸው። #በቃኝ #ደስታ #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

የፍቅርን ኃይል የተረዱ ጥቂቶች በምድር ላይ አሉ። ብዙ ሰዎች ስለፍቅር ከመናገር፣ ከማዜም፣ ከመፃፍና ከመመኘት ሸገር ያለ መረዳት የላቸውም። ያም የልብን መቀዝቀዝና የህይወት መስከርን አስከትሏል። የ
የፍቅርን ኃይል የተረዱ ጥቂቶች በምድር ላይ አሉ። ብዙ ሰዎች ስለፍቅር ከመናገር፣ ከማዜም፣ ከመፃፍና ከመመኘት ሸገር ያለ መረዳት የላቸውም። ያም የልብን መቀዝቀዝና የህይወት መስከርን አስከትሏል። የፍቅር ሀይል ሁለንታን ፈጥሯል ፤ ይህን ሀይል የተረዱ ደግሞ :- ልባቸው እሳት ነው። - ዘላለማዊነትንም ያሳድዳሉ ፤ በቀኟም ይቆማሉ ።    #ፍቅር #ኃይል #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ውበት በርዕዮተ ዓለም ላይ ትልቅ ሚና አለው። የምንመለከተው ውበት የምናምነውን ያሳያል። የምናደንቀው ውበት የምንኖረውን ይገልጻል። የምንፈልገው ውበት የምንሆነውን ያሳያል። ውበት ማለት መልክ ብቻ አ
ውበት በርዕዮተ ዓለም ላይ ትልቅ ሚና አለው። የምንመለከተው ውበት የምናምነውን ያሳያል። የምናደንቀው ውበት የምንኖረውን ይገልጻል። የምንፈልገው ውበት የምንሆነውን ያሳያል። ውበት ማለት መልክ ብቻ አይደለም። ውበት ማለት ስምምነት፣ ትርጉም እና እሴት ነው። ርዕዮተ ዓለምህን ማወቅ ከፈለክ፣ ውበትን እንዴት እንደምትመለከት ተመልከት። በውበት ውስጥ ያለ ጥልቅ የማሸነፍ ጥበብ የዓለምን ዓይን ላይለወጥ ቀይሯል! #ውበት #ርዕዮተ_አለም #እሴት #fyp #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ምግባር ተግባራዊ የልብ ህግ ነው። ልብ ተፈጥሯዊ ህግ አለው። እምነት፣ ትህትና፣ ፍቅር ወይም እውነት የመሳሰሉት...... ይህ በውስጥ ተደብቆ ያለ ህግ ደግሞ በውጭህ ሲገለጥ መልካም ምግባር ይባላል። ምግባር የልብ ህግ ተግባራዊ መገለጫ ነው። ልብህን ማወቅ ካሻህ፤ ምግባርህን ተመልከት። ምግባርህን ማሻሻል ከፈለክ፤ ልብህን አንጻ ፣ እውነተኛውንም ህግ በልብህ ላይ ትከል። ተጠንቀቅ! ድንች መብሰሉ በቅጠሉ እንዲታወቅ: - የሰው ልብም እንዲሁ በምግባሩ ይታወቃል! - የሰው ንፅህናውም በሽታው ይታያል! ልቡን ያነፃ አፋ ይነፃል! #ምግባር #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ሁለንታ የጸናችው በተቃርኖ ነው። የውሀ አካላት ከየብስ አካላት ጋር ሲመጋገቡ፤ በምድራዊ ዕፅዋቶች ትንፋሽ ሰማይ ስታደምን፤ የሰማይ ደመና ምድርን በዝናብ ሲያረሰርስ... ሁለንታ አንድ ሆና ሳለ እንዲህ በውስጧ ባሉ ልዩነቶች ፀናች። የሰውንስ ባህርይ አትመለከትም:- ነፋስነቱን መሬትነቱ ሲቋቋም፤ እሳትነቱን ውሀነቱ ሲያቀዘቅዝ። ሴት ከወንድ ገጥሞ፤           ሰው ሰውን ሲወልደው።    ደግሞ በልቅሶ ዘርቶ በሳቅ ሲያጭድ፤     በድካም ውስጥ አልፎ ሲጠነክር... ለዚያኮ ነው በልዩነት ውስጥ ባለ አንድነት ያይደል ባንድነት ውስጥ ባለ ልዩነት ዓለም ትፀናለች የምልህ። እናም እንዳገራችን በልዩነት ውስጥ አንድነት "unity in diversity" በሚል ፖለቲካዊ መፈክር በልዩነት ውስጥ አንድነትን አትቅበር! ወደ አንድነት በማይወስድ ልዩነት ውስጥም አትቀመጥ! #አንድነት #ልዩነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ስለገባህ ብቻ አትናገር! ባልኖርክበት ህይወት ወስጥ ገብተህ ስለገባህ ብቻ ሀሳብ ለመስጠትህ ሕይወት ሀሳብ በሰጠህበት ቦታ ላይ አስቀምጣ ያልኖርከው ለነበረው ህይወት የውዴታ ግዴታ ክብርን እንድትሰጥ ታስገድድሀለች። ስለዚህ ሀሳቦችህን ከመናገርህ በፊት በመኖር ፈትናቸው። ............ ብዙ መናገር የመስራት ደስታን ያሳጣል! ለዛም ነው ተናጋሪ ሰዎች የማይፀኑት! ቃል ከተግባር ያንሳል! ታላቁ ጬኸትም ዝምታ ነው! በዝምታ ጩኽ! #ዝምታ #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

የሰው የመኖር ምክንያት......ነው።
Anonymous voting

አብሮነትን ለማፅናት? ተቀራርቦ መተዋወቅ ወይንስ ተዋውቆ መቀራረብ
Anonymous voting

ብልጥ ከሆንክ የዋህ ሁን።   በቅንነት ሂሳባዊ ግንኙነት የለም! ቅንነት ገንዘብ የማይገዛው ሀብት ነው።     ሁከት የማይነጥቀው ሰላም፤     መጠላት የማያሸሸው ፍቅር፤     መነጠቅ የማይቀማው ደስታ፤     መረገጥ የማይገታው የልብ ትህትና።         ጥበብም እውቀትም ፣እውነትም ፣ገንዘብም ሊኖርህ ይችላል ቅን ካልሆንክ ግን አሁንም ድሀ ነህ። ጥበብ ቢኖርህ ቅን ካልሆንክ ሀዘንተኛ ነህ። እውቀት ቢኖርህ ቅን ካልሆንክ ግብዝ ነህ። እውነት ቢኖርህ ቅን ካልሆንክ ሰነፍ ነህ። ገንዘብ ቢኖርህ ቅን ካልሆንክ ብቸኛ ነህ። በቅንነት እና በትህትና ታጥቦ የሚሰጥ ስጦታ ፍቅር ይባላል እሱ ደግሞ ሀያላኑን ሁሉ ያንበረከከ ጥልቅ ማንነት ነው።   ዓለምን መግዛት ካሻህ ቅንና ትሁት ሁን🤝 #ቅንነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ጥሩ ካልታየህ ቀናተኛ ነህ፤ መጥፎ ካልታየህ አስመሳይ ነህ። - በሌሎች ወይም በሁኔታዎች ውስጥ ጥሩውን ማየት ካልቻልክ ልብህ በቅናት ወይም በጥላቻ ተሞልቷል የልብ ንፅህናህም ጥያቄ ውስጥ ይገባል። - በሌሎች ወይም በሁኔታዎች ውስጥ መጥፎውን ማየት ካልቻልክ እውነታውን ለማየት ፈቃደኛ አይደለህም በዚህም አስመሳይ መሆን እጣፈንታህ ይሆናል። ከእያንዳንዱ ሰው ላይ 1 መልካም ነገር ካልታየህ ፤ መቶ ክፋ ነገር በአንተ ውስጥ አለ። ከእያንዳንዱ ሰው ላይ 1 መጥፎ ነገር ካልታየህ ፤ በእርግጥ መቶ ጥሩ ነገር በአንተ ውስጥ ሊኖር ይችላል ግን አሁንም አስመሳይ ነህ። ሁለቱንም ማየት እውነት ነው። ሁለቱንም ማየት ጥበብ ነው። #ጥሩ #መጥፎ #እውነት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab

ህይወት ተጨባጭ ብትሆን ሁሉም ይጥላት ነበር። ህይወት ውብ ጭምብሎቿን ትቀያይራለች እንጂ እሷ አትቀየርም። ህይወት ውብ የሆነችው ምክንያታዊ ስለሆነች አይደለም። ውብ የሆነችው ባዶነቷን እንደ ትልቅ ምስጢር አድርጋ ስለምታሳይ ነው። ህይወት : - ልጆቿን ባዶ ስጦታ በመጠቅለያ ተቅልላ እንደምታጓጓ እናት ትመስላለች። - እንደ ተዋበች ታሪካዊ መንገድ ስትመሰል ሰው ደግሞ በጌታው እንቁላል በማንኪያ እንደተሰጠው ቱሪስት ባላደራን ይመስላል። * እንግዲህ በጉብኝቱ ከፈዘዝክና ውቧን ታሪካዊ መንገድ ከተመሰጥክባት እንቁላሉን ትሰብራለህ የጌታህንም አደራ ትበላለህ። ምርጫው ያንተ ነው!🫡 ወይ መጠንቀቅ ወይ በውበት መማረክ! #ህይወት #የልብ_ጥበብ © የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab