የልብ ጥበብ
Open in Telegram
✨ This channel deeply explores eternal values ✨ Truth, Knowledge, Beauty, Thought, Life, Death, Love, Humility, and Purity.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
253
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+530 days
Posts Archive
253
✨✨✨
መቅረብ ያለብህን ስትቀርብ ፤
መራቅ ያለብህን ትርቃለህ!
💫 ደግነት ከሆነ ደግነትን ቅረብ
ክፋት ካንተ ይርቃል!
💫 እውነት ከሆነ እውነትን ውደድ
ሀሰት ካንተ ይርቃል!
⚡ ላለማሰብ ማሰብ
ያለማሰብን ስኬት አያስገኝም!
⚡ ይልቅ ሌላውን ማሰብ እንድታስብ
ያልፈለከውን እንዳታስብ ያደርግልሀል።
🌅 የምትቀርበው ከሌለ የምትርቀው የለም!
ብርሀንን ቅረብ ከጨለማ ትርቃለህ
#መቅረብ #መራቅ #fyp
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
👁️ የማይታየውን እይ! 👁️
ከሚታየው ጀርባ ያለውን
የማይታየውን እይ!
💫 እንዲህ ያደረግህ እንደሆነ ሁሌም በተጨበጠ ተስፋ ላይ ቆመህ የሚጨበጥ ተስፋን ትወጥናለህ!
💫 እህቴ ሆይ ብዙ አፍቃሪ ወንዶች ሊኖሩሽ ይችላሉ ፤ ውበትሽም ድንቅ ሊሆን ይችላል! ነገር ግን እነዚያ በፍቅርሽ የወደቁት ወንዶች በቀረቡሽ ቁጥር የሚያፈቅሩት ራሳቸውን ነው።
💫 እነርሱ ከራሳቸው እንኳን የተሻለ እድሜ የሌለውን ውበትሽን ያፈቀሩ ናቸው።
⚡አንቺ ሴት የማይታየውን የሚያየውን
አፍቅሪ!
⚡እርሱ ሁሌም ለራሱ ሳይሆን ለራስሽ ያፈቅርሻልና።
⚡ እርሱ አንቺ ያላየሺውን ዘላለማዊ ውበትሽን አፍቅሯልና!
🌅 ነፍስሽ የሚንቀጠቀጥለትን አፍቅሪ!
🌅 ሰው በልቡ በፈጠረው ውበት በፍቅር ይወድቃል በዚያም አምላካዊ ፍርድን በራሱ ላይ ያውጃል!
⭐ ሥጋ በፈጠረው ውበት መውደቅ! ቅጥፈት ሲሆን ነፍስ በፈጠረው ውበት መውደቅ ደግሞ ልምላሜ ነው።
#ውበት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🕊️ ነጻነት በማይታይ አካል 🕊️
✨✨✨
ነጻነት በማይታይና በማይጨበጥ አካል ውስጥ መኖር ነው።
ነጻነት "ፍላጎትንና ምኞትን ያለገደብ ማድረግ ነው" የሚሉ ብዙዎች ናቸው ነገርግን ሞት የማይገድበው ፍላጎትና ምኞት እስከሌለ ድረስ ነጻነት አሁንም ጥያቄ ውስጥ ነው።
ነጻነት ያለ ጥያቄ መልስ የሚያገኘው ግን:-
በማይታይና በማይጨበጥ አካል ውስጥ በመኖር ነው።
እርሱም በመንፈስ ፍሬ ውስጥ መኖር ነው።
መንፈስ አይታይም አይጨበጥምና!
በዓለም ውስጥ አንዱ አንዱን ይገድበዋል!
ለጠንካራው ሌላ ጠንካራ አለው ለብርቱው ሌላ ብርቱ አለው : በምሳሌ :-
ፅኑን ብረት እሳት ያቀልጠዋል ፣ ፅኑን እሳት ውሀ ያጠፋዋል ፣ ፅኑ ውሀን ደመና ይሸከመዋል ፣ ፅኑ ደመናን ነፋስ ይበትነዋል ፣ ፅኑ ነፋስን መሬት ይሸከመዋል ፣ ፅኑ መሬትን የአዳም ልጅ ያገዛዋል ፣ የአዳምን ልጅ ሴት ታሸንፈዋለች ከዚህ ሁሉ ግን እሷ በድል ነሺነት በልጣ ትገኛለች።
ሴት አሸናፊዎች ሁሉ የሚሸነፋባት
ጦረኛ ናትና !!!
እርሷም የመጨረሻው የፍላጎትና የምኞት ደስታ መገኛ ናት ስለዚህ ከእርስዋ የበለጠ የደስታ ምንጭ ስታገኝ ነፃ ትሆናለህ።
ይህም በስጋ እየጠወለጉ ፤
በመንፈስ ማፍራት ነው።
ከከፍተኛው የስጋ ደስታህ የበለጠ ደስታን መፍጠር ስትችል በሳልና ነፃ ትባላለህ።
ምክንያቱም የስጋ ነፃነት ከሞት አያልፍምና!
#ነጻነት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🌱 ፍሬን ዘር ይቀድመዋል! 🌱
ፍርሀትን መገዛት ይቀድመዋል!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫እነዚያ በዙሪያህ የከበቡህ የሚመስሉህ በራስህ ኮቴ የምትርበተበትላቸው-እነርሱ የምትገዛላቸው ባሪያ ያደረጉህ መሆናቸውን ላረጋግጥልህ እወዳለሁ!
⚡እናም ልበ ሙሉ መሆን ከፈለክ ለፍቅር ተገዛ!
⚡ እርሱም በሞትና በጨለማ ውስጥ እንኳን ብትሄድ የሚጠብቅህና ደስታና ሰላምን የሚሰጥህ እንጂ ማስደንገጥን የሚያደርግብህ አይደለምና !
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌅 ሀሳብን እይታ ይቀድመዋል ፤
ድርጊትን ሀሳብ ይቀድመዋል!
🌅 ማንኛውም የተንከባከብከው የልብ ሀሳብ እንደ ዛፍ አድጎ ሰውነትህን ፈልቅቆ ከወጣና ከተላበሰህ በኋላ->ባንተ ላይ ፍሬ ያፈራልና!
⚠️ ምን እንደ ምትመለከት ተጠንቀቅ!
✨✨✨
#ሀሳብ #ድርጊት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🌪 ባዶነት ብቻ ሲሞላ አይቻለሁ! 🌪
✨✨✨
ትንሽ የተባሉ ብቻ ታላቅ ሲሆኑ አይቻለሁ ፤
የተናቁ ብቻ ሲከበሩ አይቻለሁ ፤
የተራቡ ብቻ ሲጠግቡ አይቻለሁ ፤
የተቸገሩ ብቻ ሲታደሉ አይቻለህ ፤
የታመሙ ብቻ ሲድኑ አይቻለሁ ፤
የሞቱ ብቻ ሲኖሩ አይቻለሁ ፤
አልችልም ያሉ ብቻ ሲችሉ አይቻለሁ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 እውነተኛው ሀይል - ሀይል በሌላቸው ላይ ብቻ ሲገለጥ አይቻለሁ።
✨✨✨
#ባዶነት #fyp #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
⚠️ እውነትን አትጣ። ⚠️
✨✨✨
💫 ግልጽነት በሚል ስም ሰውን ማዋረድ
አስመሳይነት ነው።
💫 በይቅርታ ተስፋ ሰውን መበደል ሌላ ይቅርታ የሚፈልግ ጥፋት ነው።
💫 በየኔነት ስሜት ያንተ የሆነውን
ቸል አትበል።
⚡ ሰውን ክፋ ያደረገው ሰው ነው! የሚሉ ክፋትን በስምምነት ማፅደቅ የሚፈልጉ ናቸው።
🌅 ለክፋትህ ስላልተመቹህ "ወግ አጥባቂ" ብለህ ደጋግ ልቦችን አትራቅ!
🌅 እውነት በሚመስሉ ምክንያቶች
እውነትን አትጣ።
⭐ ግልጽነት ማዋረድ አይደለም!
⭐ ይቅርታ መብት አይደለም!
⭐ እውነት መሸሸጊያ አይደለም!
✨✨✨
#እውነት #አስመሳይነት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
⚠️ እውነትን አትጣ። ⚠️
✨✨✨
💫 ግልጽነት በሚል ስም ሰውን ማዋረድ
አስመሳይነት ነው።
💫 በይቅርታ ተስፋ ሰውን መበደል ሌላ ይቅርታ የሚፈልግ ጥፋት ነው።
💫 በየኔነት ስሜት ያንተ የሆነውን
ቸል አትበል።
⚡ ሰውን ክፋ ያደረገው ሰው ነው! የሚሉ ክፋትን በስምምነት ማፅደቅ የሚፈልጉ ናቸው።
🌅 ለክፋትህ ስላልተመቹህ "ወግ አጥባቂ" ብለህ ደጋግ ልቦችን አትራቅ!
🌅 እውነት በሚመስሉ ምክንያቶች
እውነትን አትጣ።
⭐ ግልጽነት ማዋረድ አይደለም!
⭐ ይቅርታ መብት አይደለም!
⭐ እውነት መሸሸጊያ አይደለም!
✨✨✨
#እውነት #አስመሳይነት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🎵 የራስህን ዜማ ፍጠር! 🎵
✨✨✨
ሰው ከታጠረበት የምንነት አጥር ይልቅ
የማንነቱን አጥር ቢያፈርስ መልካም ነው።
💫 ከተመሰረትክበት አፈጣጠር ፣ እምነትና አስተምህሮት አጥር ውስጥ መውጣት ያለ ስንቅ በምድረ በዳ እንደመሰደድ ነው።
💫 ነገር ግን በማንነት አጥር ውስጥ መቆየትም እንደ በቀቀንና እንደ ገደል ማሚቶ መሆን ነው።
ስለዚህ:-
⚡ ከተመሰረትክበት የምንነት ቅኝት ሳትወጣ የራስህን የማንነት ዜማ ፍጠር!
✨✨✨
#ማንነት #ምንነት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
አስመሳይነት ከአዕምሮ አስመሳይነትና ፍራቻ የፈለቀ ነው።
✨✨✨
⚡አዕምሮህ የሚሞግተው የትኛውም ሀሳብ የውድቀት መነኛ ነው።
⚡አዕምሮ አካላቶችን የማዘዝ እንጂ ሀሳብን የመመርመር ፀጋ የለውም።
ሀሳብን የሚመረምር ልብ ነውና።
⚡ ለመቀበል የተፈሩ ማንነቶች በአዕምሮ በፈለቁ የውሸት ማንነቶች ይሸፈናሉ።
አሁን አሁንማ:
- በአፋቸው "አላዋቂ ነኝ" እያሉ በልባቸው "አዋቂ ነኝ" የሚሉ የውዳሴከንቱ ጥመኞች በዝተዋል።
- "ሀጥያተኛ ነኝ" እያልንም "ጻድቅ ነኝ" የምንል እጅግ ብዙዎች ነን!
አስተውል!
💫 ውዳሴከንቱ የስጋን ስንፍና የሚያፅናና የአዕምሮ አስመሳይነትና ፍርሀት ነው።
- ለዚያም ነው አዋቂነት "አላዋቂ ነኝ" በማለት የሚገኝ የሚመስለን ፣ ጻድቅነት "ሀጥያተኛ ነኝ" በማለት የሚገኝ የሚመስለን።
በልብህ ትሁት ሁን!
💫 አላስፈላጊ ቦታ ላይ ራስን ዝቅ ማድረግ ያልተገባ የሹመት ፍላጎት ነውና!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✨✨✨
#ልብ #አዕምሮ #ፍርሃት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
ከልብ ያልፈለቀ ሁሉ ከአዕምሮ አስመሳይነትና ፍራቻ የፈለቀ ነው።
✨✨✨
⚡አዕምሮህ የሚሞግተው የትኛውም ሀሳብ የውድቀት መነኛ ነው።
⚡አዕምሮ አካላቶችን የማዘዝ እንጂ ሀሳብን የመመርመር ፀጋ የለውም።
ሀሳብን የሚመረምር ልብ ነውና።
⚡ ለመቀበል የተፈሩ ማንነቶች በአዕምሮ በፈለቁ የውሸት ማንነቶች ይሸፈናሉ።
አሁን አሁንማ:
- በአፋቸው "አላዋቂ ነኝ" እያሉ በልባቸው "አዋቂ ነኝ" የሚሉ የውዳሴከንቱ ጥመኞች በዝተዋል።
- "ሀጥያተኛ ነኝ" እያልንም "ጻድቅ ነኝ" የምንል እጅግ ብዙዎች ነን!
አስተውል!
💫 ውዳሴከንቱ የስጋን ስንፍና የሚያፅናና የአዕምሮ አስመሳይነትና ፍርሀት ነው።
- ለዚያም ነው አዋቂነት "አላዋቂ ነኝ" በማለት የሚገኝ የሚመስለን ፣ ጻድቅነት "ሀጥያተኛ ነኝ" በማለት የሚገኝ የሚመስለን።
በልብህ ትሁት ሁን!
💫 አላስፈላጊ ቦታ ላይ ራስን ዝቅ ማድረግ ያልተገባ የሹመት ፍላጎት ነውና!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✨✨✨
#ልብ #አዕምሮ #ፍርሃት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
👂 ጆሮ ካለህ ስማ!
💛 ልብ ካለህ አድምጥ!
✨✨✨
አንድ ሰው ሰውን ወደደ የሚባለው
ያ ሰው የወደደውን መውደድ፣
የጠላውን መጥላት ሲችል ነው።
💫 እኔን የጠላኸኝ! የጠላሁትን መጥላት የወደድኩትን መውደድ ስላልቻልክና ስለከበደህ ነው።
💫 አንዳንዴም የምትወደኝ! የሚመስልህ
እኔ የምወደውን ከኔ ማግኘትና መውደድ ስለሚናፍቅህ ነው።
⚡እኔን ግን አትጠራጠረኝ በዚያን ወቅት ለመክዳት እንደመጣህም እያወቅሁ እቀበልሀለው!
- ምክንያቱም አንድ ቀን መክዳት እየሰለቸህ ፣ የወደድኩት እየጣፈጠህ የጠላሁትንም እየጠላህ እንደምትመጣ አውቃለሁና!
🌅 ጥርጥር የሌለው አንድ እውነታም
ላሳውቅህ!
⭐ አንድ ቀን እኔ የወደድኩትን በፅናት ትወዳለህ!
⭐ አንድ ቀን እኔ የጠላውትን በፅናት ትጠላለህ!
⭐ እኔንም ትወዳለህ!
አስተውል!
💫 ይህ ሁሉ ቢቀርም እንኳን:-
ያለጥርጥር አንድ ነገር ያንገበግብሀል እሱም:
እኔ የወደድኩትን መውደድ አለመቻልህ፤
እኔ የጠላውትን መጥላት አለመቻልህ፤
እኔንም መውደድ አለመቻልህ ነው!
⚡ አንተ ማነህ እንዳትለኝ!
እኔ ሁልጊዜም የምትሸሸኝ የህሊናህ
ድምፅ ነኝና!
⚡ አዎ! አንተ ማነህ እንዳትለኝ!
ስለ እኔ የምጣውቀው ብቸኛው! ሰው
አንተ ነህና!
💛 ይህን ስልህ:- በታላቅ ፍቅር፣ ርህራሄ፣
ፈገግታና ልበ ሙሉነት ነው!
💛 ይህም የሆነው:- እኔ ፅኑና ህያው
ስለሆንኩ ነው!
⭐ ጆሮ ካለህ ስማ! ልብ ካለህ አድምጥ!
✨✨✨
#ህሊና #ፍቅር #እውነት #ጥላቻ #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🌍 ባልፈጠርከው ዓለም ውስጥ
እንደ ፈጣሪ አትኑር!🌍
✨✨✨
💫 ስታጣ ማቀርቀርህ፤
ስታገኝ ማቅራራትህ....
💫 ኪስህ ባዶ ሲሆን:
በመስጠት ፍላጎት መቃተትህ....
💫 ኪስህ ሲሞላ:
-በስስት መለከፍህ....
⭐ ባልፈጠርከው ዓለም ውስጥ እንደ ፈጣሪ የመታየት የውዳሴከንቱ ጥማት እና ፍቅር ሰቅዞ ስለያዘህ ነው።
።
⚡ ማንም የተቀበለውን እንጅ ያስገኘውን ሰጥቶ አያውቅምና መስጠት ለመሰጠት ግዴታ መሆኑን አስተውል!
፣
⚡ ሀላፊነትን ሳይወጡ! በሌሎች ሀላፊነት ላይ ዋና መስሎ የመታየት ፍላጎትም ለመጥፋት መነሳሳት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል!
።
🌅 አንድ ነገር ሳትፈጥር
ስለ ፈጣሪ ህልውና አትሞግት!
፤
🌅 ማንኛውም የሀሳብ ተቃርኖ፤
የሙግት መገለጫ ነውና፤
ከፈጣሪህ ሀሳብ አትውጣ!
፤
⭐ አቅምህን እወቅ
ወይም ትሁት ሁን!
✨✨✨
#ትህትና #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
ባደባባይ የምትሰብካቸውን እውነቶች
በጓዳህም ስበካቸው!
አፍህ እንደ ልብህ ካልሆነ ልብህ
እንደ አፍህ ይሆናልና።
✨✨✨
አንድ ምሳሌ መዝዘን እንየውና ሀሳቡን አስረን እንፍታው:-
💫 ሸክላ እንስራን በመቱት ጊዜ እንደሚያፈስ በውስጡ ክፋትን ያዘለ ፍቅርም እንዲሁ ነው።
እስኪ ራሳችንን በዚህ የፍቅር ሚዛን በትወስታ እንየው:-
"አሙን" ብለን ባኮረፍናቸው ሰዎች ፤
"አልጠቀሙንም"ብለን ባራቅናቸው ሰዎች
በቃላት አጠቃቀማቸው በናቅናቸው ሰዎች
"አልታመኑም" ብለን በገፋናቸው ሰዎች ፤
በስካር ሽታቸው በጠላናቸው ሰዎች ፤
ለምፃቸውን አይተን ቤት በዘጋንባቸው ፤
ነውርና ሀጥያታቸውን ቆጥረን- በፈረድንባቸው ሰዎች።
💫 እንግዲህ ፍቅርህ እንዲህ ቁስልህ እስኪነካ ከሆነ ተሸክመህ የምትዞረው ልብ ከሸክላ አይተናነስም ለማለት ያስደፍራል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
በደጅ የሰበክኸውን በቤት ስበክ፤
የውጭ ትህትናህ በውስጥም ይሁን፤
በደጅ የሰጠኸውን በቤት ስጥ!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✨✨✨
#ልብ #እውነት #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
🌓 ኮከብ ያልተቋቋመው፤
ፀሐይ ያልገለጠው ጨለማ የለም! 🌓
ማታ የደበቀውን ቀን የገለጠውን አትርሳ!
ክፋ ሲመጣ ደጉን ፤
ደጉ ሲመጣ ክፋውን አትርሳ።
💫 ህመምን ያላለፈ መዳን የለም፤
ሳቅን ያላለፈ ልቅሶም የለም፤
ችግር ያላለፈ ተድላ የለም፤
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
አስተውል
💫 ብርሀን ከብርሀን የአንድነት እንጂ የልዩነት ትብብር የለውም!
ጨለማም ከጨለማ እንዲሁ ነው።
💫 ነገር ግን ጨለማ የሚያሞተው
ኮከብ እንደሌለም አስተውል!
ጨለማ በብርሀን ይሸነፋል እንጂ -
ብርሀን በጨለማ አይሸነፍም!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 ስለዚህ የንፁሀን ህመሞች ብርሀንነት ያላቸው የጨለማ ህመሞች መሆናቸውን አትዘንጋ!
⚡ ባለንበት ሶላር ሲስተም ውስጥ ማንኛውም "ተከለከልኩ ፣ ተነፈግሁ ፣ ተሰደብኩ ፣ ተጠለሁ...." የምትላቸው ህመሞች ከጨለምተኝነታቸው ጋር ትብብር ስለሌለህ የደረሱብህ መከራዎች እንደሆኑ ልትገዘብና በደስታ ብርሀንህን የምትጠብቅ ኮከብ እንደሆንክ ልታውቅ ይገባል!
💫 በዚህ የንጥቂያ ዓለም ላይ እንደ ኮከብ ጭላንጭል ብርሀኑን ተጠቅሞ የጨለማ ቀማኞችን በዝምታና በማዘን እያየ የእውነት ፀሐይን የሚጠብቅ ሰው እርሱ እውነተኛ ፣ ንፁህና አሸናፊ ይባላል።
⚡ ፅና ፣ በርታ ጨለማ ያዳከመው እንጂ ያሞተው ኮከብ የለምና
⚡ ፅና ፣ በርታ ብርሀን ያልመጣለት ኮከብ የለምና!
✨✨✨
#የእውነት_ኮከብ #የልብ_ጥበብ
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
⏳ ዛሬን አትበድል! ⏳
✨✨✨
የሰው ህልውና በዛሬ ብቻ! ነው
የሚረጋገጠው!
✨✨✨
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
በትናንት ሐዘንህ ዛሬን አትጫን...
በዛሬ ጭንቀትህም ነገን አታበላሽ...
በነገ ፍራቻ አትደንግጥ...
በነገ ጉጉትም አትመሰጥ....
ዝም ብለህ፤
ዛሬን ትሁት ሁን፤
ዛሬን ፍቅር ስጥ!
⚡ ዛሬ ምትኖረው እውነት ብቻ
ነገ ዘላለምን ይገነባልና!
🌟 ማንነትህን በቆምክበት ቦታ ላይ ሆነህ ብቻ በእውነት እና በፍቅር መዝን ያኔ እውነተኛ አንተነትህ ይገለጥልሀል።
🌟 ሙገሳ የማያዘልለውና ትችት የማያስቆመው ጠንካራ ሯጭ ስትሆን አሸናፊ ትሆናለህ።
🌟 እንደ ሞኝ ሯጭ የቀደምካቸውን እያየህም አትሩጥ ትወድቃለህና! ይልቅ - ያለፈውን እየረሳህ! የፊትህን እያየህ! ሩጫህን ቀጥል።
🌟 ሰዎች እንደ ጅል! በትናንትና ጥሩ ስራቸው ሲመሰጡ ነው የነገ ቦታቸውን ያጡት እና አትፍዘዝ!
በትናንት እና በነገ ላለመታሰር...
ዛሬን አትበድል! 🧠💛
#ዛሬ #የልብ_ጥበብ
✨✨✨
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🔥በምትጠራጠርበት መንገድ ማንንም አትምራ🔥
✨✨✨
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 ምክርህ የማይደመጠው ለምን ይመስልሀል?
ሰው የሀሳቡ ውጤት ስለሆነ አይደለምን?
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
⚡ በሻማነትህ ላይ ብርሃን ሳትለኩስ እንዴት "አትደናቀፍ" ብለህ ወንድምህን ትመክራለህ?
⚡ በውስጥህ ያለውን ግብዝነት ሳትገድል
እንዴት? በግብዞች ላይ ትቆጣለህ!
⚡ በአንተ ውስጥ ያለውን የመስራት ስንፍና ደብቀህ ሰውን ስለ ስንፍና አትምከር!
⚡የፍቅር ማጣታችንም መንስኤ ያልተረዳነው ውስጣዊ የልብ ጥላቻችን ነው።
⚡ ሁሌም እይታህ ወደ ውስጥህ ይሁን ችግሩም መፍትሄውም ውስጥህ ነውና!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌅 ልብ ሲጠራ ገፅ ይበራል፤
ገፅ ሲበራ ዙሪያ ይበራል።
🌅 የሚያስተቹት የልብ ማንነትህንም ፍቀህ ሳትጥል "ለምን ተቹኝ" አትበል!
⭐ እንድትተኝ ያደረገህን የልብ ተንኮል አጥፋ እንጂ "ለምን ተተቸሁ!" አትበል!
⭐ አንተ መሆን የምትፈልገውን ግን መሆን ያልቻልከውን መሆን ባልቻሉ ሰዎች ላይ መቆጣት እብሪተኝነት ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🔥 ጥርጥር የሌለው ሰውን የመምራት መፍትሄ ገፅን በብርሃን መለኮስ ነው!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💀 ያልኖሩትን ምክር መምከር የማያውቁትን መድሀኒት እንደመስጠት ነው!
ይህ ደግሞ ወንጀል ነው!
#ራስን_ማወቅ #የልብ_ጥበብ
✨✨✨
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🔥በምትጠራጠርበት መንገድ ማንንም አትምራ🔥
✨✨✨
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 ምክርህ የማይደመጠው ለምን ይመስልሀል?
ሰው የሀሳቡ ውጤት ስለሆነ አይደለምን?
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
⚡ በሻማነትህ ላይ ብርሃን ሳትለኩስ እንዴት "አትደናቀፍ" ብለህ ወንድምህን ትመክራለህ?
⚡ በውስጥህ ያለውን ግብዝነት ሳትገድል
እንዴት? በግብዞች ላይ ትቆጣለህ!
⚡ በአንተ ውስጥ ያለውን የመስራት ስንፍና ደብቀህ ሰውን ስለ ስንፍና አትምከር!
⚡የፍቅር ማጣታችንም መንስኤ ያልተረዳነው ውስጣዊ የልብ ጥላቻችን ነው።
⚡ ሁሌም እይታህ ወደ ውስጥህ ይሁን ችግሩም መፍትሄውም ውስጥህ ነውና!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌅 ልብ ሲጠራ ገፅ ይበራል፤
ገፅ ሲበራ ዙሪያ ይበራል።
🌅 የሚያስተቹት የልብ ማንነትህንም ፍቀህ ሳትጥል "ለምን ተቹኝ" አትበል!
⭐ እንድትተኝ ያደረገህን የልብ ተንኮል አጥፋ እንጂ "ለምን ተተቸሁ!" አትበል!
⭐ አንተ መሆን የምትፈልገውን ግን መሆን ያልቻልከውን መሆን ባልቻሉ ሰዎች ላይ መቆጣት እብሪተኝነት ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🔥 ጥርጥር የሌለው ሰውን የመምራት መፍትሄ ገፅን በብርሃን መለኮስ ነው!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💀 ያልኖሩትን ምክር መምከር የማያውቁትን መድሀኒት እንደመስጠት ነው!
ይህ ደግሞ ወንጀል ነው!
#ራስን_ማወቅ #የልብ_ጥበብ
✨✨✨
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
☀️ መግጠም ከሚችል ልዩነት ጋር
ህብረት አድርግ! ☀️
✨✨✨
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 አንድነት ያለ ልዩነት አይፀናም!
ነገር ግን ለአንድነት በማይመች ልዩነት ውስጥም አብሮነት የለም!
☀️ ይህ ማለት:-
ባለማወቁ ሳይሆን ማወቅ ባለመፈለጉ ፤ በኢ-አማኒነቱ ሳይሆን አማኝነትን በመጥላቱ ፤
ድሀ በመሆኑ ሳይሆን ለሀብት ባለመጣሩ ፤
በሀጥያተኛነቱ ሳይሆን ጽድቅን በመጥላቱ ፤ .............................. እንዲህ ያለውን ሰው በሰፊ ርቀት ልዩነት ራቅ!
💫 ምክንያቱም እንዲህ ባለ ክፋ የመንቻካነት ባህር ውስጥ የገቡ ሰዎች በሰው የመዋኘት አቅም ከገቡበት የመውጣት እድል የላቸውም!
ስለዚህ
⚡ ልትዋኘው በማትችለው ባሕር ውስጥ አትግባ፤
⚡ ልትገጥመው በማትችለው ልዩነት አትቀላቀል፤
⚡ አብረህ በማትዘልቀው መንገድ ጉዞ አትጀምር!
🤝በማይገጥምህ ግጣም አትገጠም!🤝
#ልዩነት #አንድነት #የልብ_ጥበብ
✨✨✨
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🌿 ገርነት 🌿
✨✨✨
☀️ ገርነት ልብን የሚከፍት
ምግባር ነው። ☀️
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 የተዘጋ ልብን የሚከፍተው ገርነት ነው እንጂ ኃይል አይደለም።
⚡ ገርነት ለሁሉ የተመቸ ፣ ያልከበደ ፣ ያልቀለለ ሰላማዊ ምግባር ነው።
💫 ገርነት ሌሎች እንዲያምኑ፣ እንዲቀረቡ ፣ እንዲወዱ የሚያደርግ ልል የሆነ ቅን ማንነት ነው።
☀️
- ልል ስትሆን የህይወት ባሕርን ትሻገራለህ!
- ልል ስትሆን እንደ ርግብ ሰማይ ትቀዝፋለህ!
💫 ልፋትን ከትጋት ፣ብልጠትን ከብልሀት፣ መውደድን ከማፍቀር...የመሳሰሉትን ስትለይና ስታስተውል ስለ ገርነት በጥልቅ ትረዳለህ።
💫 እውቀት የማያስታብይህ ፣ ዘለጌታ የማያንጠራራህ ፣ መልከኛነት የማያኮራህ ፣ ሀብት ሰውነትህን የማያስረሳህ.......ልል ሰው ሁን!
#ገርነት #የልብ_ጥበብ
✨✨✨
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
253
✨✨✨
🌿 ገርነት 🌿
✨✨✨
☀️ ገርነት ልብን የሚከፍት
ምግባር ነው። ☀️
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💫 የተዘጋ ልብን የሚከፍተው ገርነት ነው እንጂ ኃይል አይደለም።
⚡ ገርነት ለሁሉ የተመቸ ያልከበደ ያልቀለለ ሰላማዊ ምግባር ነው።
💫 ገርነት ሌሎች እንዲያምኑ፣ እንዲቀረቡ ፣ እንዲወዱ የሚያደርግ ልል የሆነ ቅን ማንነት ነው።
- ልል ስትሆን የህይወት ባሕርን ትሻገራለህ!
- ልል ስትሆን እንደ ርግብ ሰማይ ትቀዝፋለህ!
💫 ልፋትን ከትጋት ፣ብልጠትን ከብልሀት፣ መውደድን ከማፍቀር...የመሳሰሉትን ስትለይና ስታስተውል ስለ ገርነት በጥልቅ ትረዳለህ።
💫 እውቀት የማያስታብይህ ፣ ዘለጌታ የማያንጠራራህ ፣ መልከኛነት የማያኮራህ ፣ ሀብት ሰውነትህን የማያስረሳህ.......ልል ሰው ሁን!
#ገርነት #የልብ_ጥበብ
✨✨✨
© የልብ ጥበብ - t.me/Ye3773ab
✨✨✨
