የአኺራ ተጓዦች☁️
Open in Telegram
ኢንሻአላህ በዚህ ቻናል ላይ ሱናን የሚደግፉ - ሴቶች እህቶቻችንን የሚያነቃቁ እና አሪፍ አሪፍ የሆኑ ስንቆችን እንለቃለን inshallah የሱና ቻናሎች መገኛ @bahruteka @shakirsultan @alateriqilhaq @abdulham
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
935
Subscribers
No data24 hours
+327 days
+13830 days
Posts Archive
935
🌸🌱 ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን – አላህ ይጠብቃቸው – እንዲህ ይላሉ፦
“አንዳንዶች የሴት በቤቷ ውስጥ የምትሰራውን ሥራ ትንሽ ቢያዩትም፣ እሱ ግን ትልቅ ሥራ ነው። በውስጡ ብዙ ዓይነት ሙያዎችና ክህሎቶች ይገናኛሉ።
ይህ ሥራ እንደ አንድ መንግሥት የሚፈልገውን ያህል ዕውቀት፣ አስተሳሰብ፣ ትክክለኛነት፣ አስተዳደር፣ ኢኮኖሚን መረዳት፣ ርህራሄና ስሜት ይፈልጋል።
ሴትየዋ ይህን ትልቅ ሚናዋን በአቂዳ መሠረት መረዳቷ አስፈላጊ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ﴾
“በል፦ ሶላቴ፣ አምልኮቴ፣ ሕይወቴና ሞቴ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው።”
ስለዚህ ይህ ኢባዳ (የአምልኮት ሥራ) ነው። ሴትየዋ የምትሠራው በግዴታ የሚደረግ ሥራ ወይም ተደጋጋሚ የዕለት ተዕለት ሥራ ብቻ አይደለም። የሕይወትን ዓላማና የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ምስጢር ለተረዳች ሴት፣ ይህ ሥራ መንፈስና ትልቅ ዋጋ ያለው ሥራ ነው።”
እና ምን ልላችሁ ነው አብሽሩ
ሀያ ጉዞ ወደ ኪችን🙌
@light_of_sunnah
935
☁️ ሀቢቡና ﷺ ምን አሉ
«مَن صَمَتَ نَجَا»
<<ዝም ያለ ነፃ ወጣ>> አሉ
በሰው ህይወት ላይ በማይመለከታችሁ
ነገር ውስጥ እየገባችሁ እሱኮ እንዲህ ነው
እሷኮ እንዲህ ናት እያላችሁ ወሬ አታዋስዱ
የራሳችሁን ሀያት ኑሩ ዝም በሉና
አሁንም ዝም በሉ 🙌
@light_of_sunnah
935
በእንደዚህ አይነት ጫማ ላይ ፊጥ ብላችሁ
የምትሄዱሙስሊም ሴቶች ተአደቡ🫵
በተለይ ሙተነቂቦች አላህን ፍሩ ይህ
ጫማ እንደሀቂቃው ከሆነ ሂሉ
ትልቅ ስለሆነ ባላንስሽን
ለመጠበቅ አካሄድሽን
ለመቀየር ትገደጃለሽ ስለዚህ
ከዚህ ጫማ ራቁ በተለይ
ሙተነቂብ የሆነች
ሴት ላይ በጣምምም ያስጠላል🙌
@light_of_sunnah
935
🌓ወንድ ልጅ እንደፈለገ ቦዝኖ ፣ አለሙን ቀጭቶ ፣ አተራምሶ ፣ ጠጥቶ ፣ አጭሶ ሁሉንም አዳርሶ ... ወደ ቀልቡ ሲመለስ በማህበረሰቡ ይከበራል። በሳል ሰው ይደረጋል። ለውጡ ምሳሌ ተደርጎ ለሌሎች ማስተማሪያ ይሆናል።
🌓ሴት ልጅ ቦዝና ፣ አለሟን ቀጭታ ፣ አተራምሳ ሁሉንም አዳርሳ ወደ ቀልቧ ስትመለስ ደግሞ ... በማህበረሰቡ ማላገጫ ትሆናለች።
🔴ጨፍራ እንደፈለገች ሆና ሲበቃት ደህና ነው ሰው ለመምሰል ትጣጣራለች ... የማናውቃት መሰላት እንዴ .. ትባላለች።
🌓ይህ ስሟ እድሜ ልኳን ይከተላታል። አግብታም አደቧን ገዝታም መጠቋቀሚያ ያደርጋታል። ይህንን ሚስኪን ሰው አገኘው ብላ ትጫወትበታለች ይባላል።
🛑ምን ለማለት ፈልጌ ነው ... የሴት ልጅ ትልቁ ገፀበረከቷ ክብሯ ፣ ስክነቷ ፣ ባህሪዋ ፣ አስተዋይነቷ ፣ መሰብሰቧ ፣ ስርዓቷ ፣ አደቧ ነው። ይህንን ፀጋ ሁሌም ጠብቃ መኖር አስፈላጊዋ ነው። የሴት ልጅ ክብር በምንም አይተካም !!
በድጋሜ የተፖሰተ
T.me/abduselam_addalochy11
T.me/abduselam_addalochy11
935
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ
በጠዋት ያሲሩናን ጋበዝኳችሁ
سورة المؤمنون || ياسر الدوسري
935
وَعَلَيْكُم السَّلَام وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ
በጠዋት ያሲሩናን ጋበዝኳችሁ
سورة المؤمنون || ياسر الدوسري
935
🇸🇦ሰለፊዮች ሆይ የምርጥ የሰለፊይ መሻይኮች ኡስታዞች እንዲሁም ወንድሞች ቻናል እያለላቹ በየሙብተዲእ ቻናል ምን ትሰራላቹህ?
አሁን ጉዳዬ ላሳጥርላቹህ እና ከታች ጆይን የምትለዋን ምልክት ስትፈልጉ በአውራ ጣታቹ ስትፈልጉ በቀለበት ጣታቹ ብቻ በፈለጋቹት ጣታቹ ጆይን(JOIN) የምትለዋን ምልክት በመንካት ወደ ኢትዮጵያ የሰለፊዮች ቻናል ተቀላቀሉ🇸🇦
935
🌳Pov:- ከጓደኛሽ ጋር መድረሳ
ውስጥ አኢሻ ረዲየላሁ አንሀ
እንዲህ ብላለች ኧረ አስማ
ረዲየላሁ አንሀም እንዲህ ብላለች
እያልሽ ስትከራከሪ(ስትወያዩ)
ያለው feeling አላህ አላህ🙌👌
@light_of_sunnah
935
ነብዩ ﷺ 'የተሰደቡበት"
"የተሰደዱበት"
" የተጎዱበት"
"እብድ የተባሉበት"
"ጠንቋይ የተባሉበት"
በመንገዱም ላይ ብዙ መከራን የተቀበሉለት
ዲን ነው የእኛ ዲን።
ሰሓቦችም ለዚህ ዲን ብለው ንብረታቸውን፣ ቤታቸውን እና አገራቸውን ትተው ተሰደዱ። አንዳንዶቹም ሕይወታቸውን ከፍለው አለፉ።
ይህ ነው የእኛ ዲን… ዛሬ ግን እኛ የት ነን?
ለዲናችን ስንል ምን እንተዋለን? ምን መስዋዕት እናደርጋለን? ሱናን ለመከተል ስንት ነገር እንተዋለን?
እነሱ ዲናቸውን ለመጠበቅ መከራን ተቀበሉ፤ እኛ ግን ዲናችንን ለመጠበቅ የዱንያን ትንሽ ደስታ መተው እንኳን እንቸገራለን።
አላህ ኢማናችንን ያጠናክርልን፣ በዲኑ ላይ ያጽናን፣ እንደ ነብዩ ﷺ እና ሰሓቦች ዲናችንን እንድንከተል ያድርገን። አሚን👍
@light_of_sunnah
