en
Feedback
𝙸'ƚ𝚒dαℓ 𝙸мαи

𝙸'ƚ𝚒dαℓ 𝙸мαи

Open in Telegram

የፃፈ ሁሉ ደራሲ የተፃፈ ሁሉ ድርሰት አይባሉም !

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
2 891
Subscribers
-224 hours
-97 days
+4730 days
Posts Archive
. ኦርቶዶክሳዊቷ ክፍል 00:01 1hr left......... .

በደስታችሁ ወይስ በሀዘናችሁ የመጣ?? የቱ ነው ወዳጅ??? @rim_han .

. ኦርቶዶክሳዊቷ ( ቃሲዮን ) ይህ ፓስት 400❤+ ላይክ ሲኖረው ይጀመራል ግን ሰኞ መሆኑን አልቀይርም 😭
. ኦርቶዶክሳዊቷ ( ቃሲዮን ) ይህ ፓስት 400❤+ ላይክ ሲኖረው ይጀመራል ግን ሰኞ መሆኑን አልቀይርም 😭

. ነሃሴ ቀን 22 በዚህ አጭር ቀን ታሪክ የመፃፍ ሀሳብ የለኝም ግን ትምህርት ከተጀመረ ቡሀላ መፃፍ ስለማልችል እንዲሁም መስከረም ላይ ብዙም class ስለማይገባ አንድ ታሪክ ላስነብባችሁ 😭 50 ክፍል በላይ የመፃፍ ሀሳብ ይለኝም ግን ሊበልጥ ይችላል ነሃሴ 25 ሰኞ አዲሱን ታሪክ በተለመደው ሰአት እጀምራለሁ ግን ከእናንተ የምፍልገው ነገር አለ ቻናሉን ለአንባቢያን ሼር ማድረግ ዝግጁ ናችሁ ? @rim_han .

ለጥያቄዎቹ  መልስ 1ከዚህ ታሪክ እንድንማር የፈለግሽውን ነገር በአንድ አ/ነገር ግለጪ ብትባይ ....? « በቀድር እንመን ! »   ለምን እንደዚህ ሆንን አንበል በቃ የማይፈተን የለም ዱንያ ላይ እስካለን ድረስ የተፃፈልንን ነው የምንንኖረው ዱንያ ስትከብድብን አላህን ማማረር እናቁም ዋነኛ አላማው ይሄ ነው ( ላሳጥረው ብዬ ነው 🤭) 2 ታሪኩን ስትጀምሪ መጨረሻውን አስቀድመሽ ታውቂ ነበር? አዎ የታሪኩ ሴራዎችን ታሪኩን ሳልጀምር አስቢያቸው ነበረ 3 ከጉጉታችን አንጻር ሁሌ በታሪኩ መጨረሻ ላይ ግምት አለ በቃ ቀኑን ሙሉ በሚባል ደረጃ እና እስከ አሁን ድረስ በመጻፍሻቸው ክፍሎች ውስጥ አንቺ ካሰብሽው በተለየ በእኛ comment ምክንያት ያስቀየረሽ part አለ? commentochun አነባቸዋለሁ ምን አልባት የተዛባ ወይም ሳላስተውለው ያጋጨውት ሀሳብ ካለ ለማስተዋል ነበር የምጠቀምበት  እንጂ ሀሳቤን ያስቀየረኝ የለም 4 ስትፅፊ በጣም የተቸገርሽበት ነገር ነበር? ሀሳብ እየጠፋብኝ በጣም ተቸግሬ ነበረ በተለይ ትምህርት ላይ እያለሁ በዛ ላይ ፈተና ሰሞን ነበረ የዛን ጊዜ ተቸግሬ ነበረ 5  ዶዶላን በተለየ ሁኔታ ለምን መረጥሽ? ሌሎች ቦታዎች ነበሩ ከ 5 በላይ ያዘጋጀዋቸው ግን ዶዶላ አንድ የኖረ ሰው ሳገኝ እሱን እየጠየኩ ፃፍኩኝ ስሙም ለየት ስለሚል ደስ አለኝ 6ምዕራፍ ሁለት ትቀጥያለሽ…ሌላ ታሪክ ትጀምሪያለሽ …What's on your mind? በሌላ ታሪክ ነው የምንገናኘው መርሊን እዚህ ጋር ተቋጭቷል . 7 ታሪኩ ለምን መርሊን የሚል ስያሜ ተሰጠው ትርጉሙስ ምንድነው ? መርሊን አፈታሪክ ላይ ያለ አስማተኛ ነው ይባላል በታሪክ  እንዲሁም የንጉስ አርተር አማካሪ ነውም ይባላል በእኔ ታሪክ ግን በዚህ ስም የተሰየመ የአእዋፍ (ንስር ) አለ ይህን የንስሩን ባህሪ ለገፀባህሪያቱ አላበስኩት ንቁ ፣ጠንካራ ፣ አስተዋይ እንዲሁም አዳኝ  በሚለው ሀሳብ ነው መርሊንን ( ዛቪያርን ) የገነባውት የታሪኩም ርእስ ስያሜ ሆነ 8  የሆነ ክፍል ላይ ዛቪያር የሚከራ ሱቅ እየፈለገ ነበረ እና ለምን ነበረ ምንስ አደረገው አባቱ መስራት አለብኝ ብሎት ነበረ የአባቱን ጥያቄ ለማሟላት ከእሱ እይታ እንዳይርቅ ነበረ ከሆስፒታሉ ፉት ለፊት  ሱቅ የተከራየው ግን ያው የማይታወቅ ሰው አባቱን እንደሚፈልገው ሲረዳ ስራውም ቀረ ካለበት ቤት አውጥቶ ጥበቃ ያለበት ቦታ አስገባው በጠየቃችሁን መሰረት የገፀባህሪያቱ ስም ለየት እንዳለባችሁ ነግራችሁኛል አንባቢዎቼ ዘንድ የማይረሱ ገፀባህሪያት ለመፍጠር ነው ከስማቸው ጀምሮ ያልተለመዱ ያደረኩት ረዒፍ - ሩህሩህ (🤭 ፈርሀን ሲጠይቃት ትርጉሙን ተሳስታ ነው ልእልት ያለችው ) ዛቪያር - ደፋር                  አይላር  የጨረቃ ብርሀን   ረዒና _ ልእልት                      ኢሪዝ   ክብር ያለው ኒያዝ - ስጦታ                         ሊን  ግሩም ልብ ያለው    ሜይሊን -ውብ እና የተከበረች   ኒማል - የአላህ ስጦታ አይዛን -እንደ ብረት ጠንካራ ኑሃይዳ  -ትልቅ ኑሓይላ -አስተዋይ ሊበን -ንፁህ  ልብ ማዕቅበዝጊ -የአምላክ መጠጊያ ናዝኒን - ውብ ጁዌይሪያ  ወጣት ሴት ለየት ያሉትን መርጬ ነው ትርጉማቸውን የነገርኳችሁ  መመለስ ያስፈልጋቸዋል ያልኩትን ጥያቄዎቻችሁን  መልሻለሁ ብዬ አስባለሁ አፍናን .

‹‹አቤት ባየውህ ማሳዘኔ፣ ይህ ጎጆ ሲል ወና፣ ይፅናናብኛል ታማሚ፣ ህመሜን ያይና፡፡ ውዴ የቀልቤ ጀምበሩ፣ ፋኖስም ሻማዬ፣ ሳስብ ለዑመት መቅለጥሁን፣ ጠናኝ በሽታዬ፡፡ ባልመልስም ውለታሁን፣ እኔም በተራዬ፣ ከጥልቁ ቀልቤ ምንጩ ስር፣ ያንቱ ነው እንባዬ፡፡ ሰላቱሏህ ሰላሙሏህ፣ አላ ኑሪል ቁሉብ፣ ሙሀመዲን ወአሊሂ፣ ሃባኢቢል መህቡብ!››     اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ  ኸሚስ ነው ሰለዋት አውርዱ አህባቢ💚🤌 @rim han .

. አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ                      መርሊን መርሊን አጭር የሚባል ታሪክ አይደለም ከረዥም ልብ ወለድ ታሪኮች ውስጥ ይመደባል በወረቀት ወይም በሌሎች ነገራቶች ላይ ሰፍሮ ለእናንተ የቀረበ ታሪክ አይደለም  ከመጀመሪያው ስንኝ ጀምሮ እስከመደምደሚያው ድረስ ያሉትን ሀሳቦች ቃላት ሂደት ጭንቅላቴ ውስጥ ያለቀ እና ቀጥታ ከጭንቅላቴ ውስጥ ያለውን ታሪክ በየቀኑ ሳስነብባችሁ ቆይቻለሁ ለእኔ በጣም ፈታኝ ነበረ መጀመሪያ ክፍል ላይ ገፀባህሪያቱ የተናገሩት ቃላት ሌሎች ክፍል ላይ ተፅእኖ እና የሀሳብ መጣረዝ እንዳይመጣ በጥንቃቄ እና በማስተዋል እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ያሉትን ቃላት በማስታወስ ነበረ የተፃፈው ታሪኩ የተለመደ አይነት ሳይሆን Dark romance በምንለው የአፃፃፍ ስልትን የተፃፈ ነው ኢስላማዊ እሴቱን እንዲጠብቅ በተቻለኝ መጠን ሞክሪያለሁ በእኔ ቢህል የእኔ አንባቢዎች ደራሲዎች ናቸው ከእኔ እኩል ይጨነቃሉ ቀጣዩን ክፍል በምናባቸው ይስላሉ ምናባዊ ደራሲያን ናቸው አንባቢዎቼ ለዚህ ምስክር እራሳችሁ አላችሁ በእያንዳንዱ ክፍል የቀጣዩን ክፍል ግምት ሀሳብ ስታስቀምጡ ነበረ  በቻልኩት መጠን የአንባቢዎቼን ስነ-ልቦና ጠብቄ ተጠንቅቄ ታሪኩን ከጅምሩ ጀምሬ ለመፈፀም በቅቻለሁ ይህ ታሪክ ተጀምሮ እስኪያልክ ድረስ ከጎኔ ሆናችሁ ስትደግፉኝ ስታበረታቱኝ በስራዬ እንድኮራ ያደረጋችሁኝ  ሰዎችም ይሁን አንባቢዎቼ ለእናንተ ትልቅ ክብር እና ከልብ የመነጨ  ምስጋና አለኝ እንዲሁም ታሪኩ ከተፈፀመ ቡሀላ የሚገነባ የሚያበረታታ የሚደግፍ አስተያየት ለሰጣችሁኝ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ቃል የለኝም  ውድድ ነው የማረጋችሁ ❤️‍🔥 ከዚህ በተሻሉ ሌሎች ምርጥ ምርጥ ታሪኮእንገናኛለን ቤቴ ቤታችሁ ነው ጥያቄ አያስነሳም አልልም ታሪክ እሱ ጥያቄ ነው በታሪኩ ዙሪያ ያሏችሁን ጥያቄዎች በግልፅ  አስቀምጡልኝ መመለሾ ያለባቸውን ጥያቄ እመልሳለሁኝ     አፍናን  @rim_han .

. ያቆየሁት ግማሹ ጠፍቶብኝ ነው 😭 አስተያየታችሁን በ comment እጠብቃለሁ .

  ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ወደ እቤት  ነበረ የሄድኩት ረዒፍ ተዘገጂጅታለች እሷን እየጠበኩኝ ሳሎን ቁሚያለሁ ÂŤ ዛቪያር ሜይሊን መታለች እኮ Âť ÂŤ እና የት አለች እመጣለሁ ብላኝ ነበረ» ÂŤ ምን አውቃለሁ አሁን እዚህ ነበረች የእሷ ነገር እብድ እብድ ነው Âť ÂŤ አሁን ቸኩያለሁ ሾመለሾ አገኛታለሁ Âť አልኩት ረዒፍ እና ኒማል መጡ የረዒፍን አነስተኛ ሻንጣ ከዃላው መኪና ውስጥ አስገባውት እሷ ጋቢና ገባች ኒማል ተሰናብታ እኔም መኪናውን አስነሳውት እና ከግቢ ወጣሁ ÂŤ ምነው የቸኮልክ ትመስላለህ Âť ÂŤ አይ አልቸኮልኩም Âť ÂŤ የምትወዳት ሴት እንዴት ነች Âť ዞር ብዬ አየዋት እና ዝም አልኩኝ ÂŤ መች ነው ታድያ የምትጋቡት እኔ ሰርግህ ላይ ላልገኝ ነው Âť ÂŤ አላገባም Âť ÂŤ መቼስ ቁመህ አትቀርም Âť ÂŤ ቁሜ እንዳልቀር ካልፈለግሽ ካዘንሽልኝ  አግቢኛ Âť አልኳት ምንም አልተናገረችም ፊቷን አዙራ ተቀመጠች የማይባል ነገር ያልኩ እስኪመስለኝ ድረስ ውስጤ ደንግጧል ግን ምንም አላልኳትም በዝምታ ከረዝም ደቂቃ ቡሀላ ወደ መርከዙ ደረስን አሁንም ምንም ወሬ የለም ቀድሚያት ወረድኩኝ እና ውስጥ ያሉትን ነገራቶች አስተካክዬ ተመልሼ ወደ እሷ ተመለስኩኝ ከዃላ ያለውን አነስተኛ ሻንጣዋን አወረድኩት እና የመኪናዋን በር ከፈትኩላት ወረደች መግቢያው ላይ አንድ ሴት እየጠበቀቺት ነው ÂŤ ዛቪያር አለችኝ Âť ከመግባቷ በፊት ÂŤ አቤት ምነው ችግር አለ Âť ÂŤ አግባኝ ብልህ ታገባኛለህ ከምትወዳት ሴት እኔን ትወደኛለህ Âť ÂŤ እብድ  ከእሷ ጋር እንኳን አትወዳደሪ እንዳገባሽ ገፈለግሽ አገባሻለሁ Âť ÂŤ እሷ ከእኔ ታምራለች ለዛ ነው Âť ÂŤ አንቺ ከእሷ ትበልጫለሽ መሰለኝ Âť ፈገግ አለች እኔንም ፈገ አስባለችኝ ÂŤ እና ከእሷ እኔን ትወደኛለህ Âť ÂŤ ምን አልባት Âť ÂŤ እርግጠኛ ሁን Âť ÂŤ ከእዚህ ስትወጪ እርግጠኛ እሆናለሁ Âť ÂŤ ታገባኛለህ ?Âť ÂŤ እንቢ ብትይም መጥለፌ አይቀርም ድሮ የቀረውን ጠለፋ አሁን እጀምረዋለሁ Âť ፈገግ በላ ጀርባዋን ሰጠችኝ መልሳ ወደ እኔ ዞር አለች ÂŤ ደሞ ያን ጊዜ  ስቀልድ ነው እሺ ፈገግታህ ያምራል Âť አለችኝ በሹክሹክታ መልሴን ሳትሰማ ፈጠን ፈጠን ብላ ወደምትጠብቃት ሴ። ሄደች እና አብረው ገቡ ።ብቻዬን እየሳኩኝ ወደ መኪናዬ ገባሁኝ ሞተሩን አስነስቼ መንገዴን ቀጠልኩኝ በረዒፍ ሁኔታ ብቻዬን ፈገግ እያልኩ ነው ምን አልባት የተፃፈችልኝ እሷ ትሆን ይሆናል ብቺዬን እያወራው ÂŤ ዛቪያር Âť ሹክሹክታ በጆሮዬ ሾር ትንፋሽ ከመደንገጤ የተነሳ መኪናውን እንዴት እንዳደረኩት አልውቅም አስፓልቱን ዞረው መኪና አለመኖሩ ጠቀመኝ እንጂ የማይሆን ጉዳት ማድረሴ ነበረ እንደምንም መኪናውን አቆምኩት ልቤ በአፌ ልትወጣ ነበረ ዞር አልኩኝ ወደ ዃላ ወንበር ወድቃለች ÂŤ ተጎዳሽ Âť ድምፄ ልሹ እየተንቀጠቀጠ ነው ÂŤ አዎ ደህና ነኝ Âť ÂŤ አልሀምዱሊላህ ግን እብድ ነሽ ሙተን ነበረ እኮ Âť ÂŤ ትደነግጣለህ ብዬ እንደዚል አልጠበኩም Âť ÂŤ እንዴት ገባሽ ሲጀመር አንቺ እብድ» ÂŤ አንተ ሳሎን የነበርክ ሰአት ተደብቄ ነው የገባውት Âť እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩኝ ÂŤ እኔን አገባሻለሁ ብለኸኝ አነበረ አሁን ደሞ እሷንም ስትል ሰማሁ» አለች እየሳቀች ሜይሊን የሊን ታናሽ እህት ነች ከልጅነትብ ጀምሮ ነው የምናውቃት ÂŤ 18 አመት ሞላሽ እንዴ Âť ÂŤ 16 አመት Âť ÂŤ እኮ 18 አመት እስኪሞላሽ እሷ ሚስቴ ትሁን ከዛ ሁለተኛ አገባሻለሁ» አልኳት እየሳኩኝ ÂŤ ኧረ እኔ ሁለተኛ አልሆንም ግን አፈሰችኻ Âť አለች እየሳቀች ÂŤ አንቺ እብድ ኧረ በህግ Âť ÂŤ የምር ተመልሽር ልንገራት እንዴ Âť አለች የመኪናውን በር እየከፈተች ÂŤ ጤና የለሽም ነይ ተመለሺ አንቺ Âť እየሳቀች በሩን ዘግታ ተስተካክላ ተቀመጠች ÂŤ ለዚህ ጥፋትሽ እቤት እናወራለን ትቀጫለሽ Âť አልኳት እና መኪናዬን አስነሳዋት በዛ ሰፊ አስባልት አስወነጨፍኳት                          ╔═ ═  𑁍  ═ ═╗                             ታሪኩ  አልቋል                           á‰ľá‹á‰łá‹  ቀርቷል                          ╚═ ═   𑁍   ═ ═╝   áŠĽáŠ” ፀሀፊዋ ጨረስኩ የገፀባህሪያቶቹ ህይወት ግን  ትቀጥላለች እንደምንም ብላ ትቀጥላለች             ═══════•|   |•════════                                       Š  አፋናን ሩማን                    ቃላት የማይሞትበት አለም                  Augsꫀt  19 E.C                     αℓℓ ɾỉghƚѕ ɾꫀѕꫀɾvꫀd              â•â•â•â•â•â•â•â€˘|   |•════════ .

« ደሞ አንድ ነገር አደርጋለው ብትል ያው ፓሊሶች መተው ካለህበት ቦታ ይዘውህ እንደሚሄዱ እያሰብክ ብዙ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው እቃዎች እንደ መድሀኒት ሌሎች ነገራቶች ወደ ሀገር ውስጥ  እንዳስገባህ የሚገልፅ ሰነድ እጄ ላይ አለ ይሄ ደሞ ሀገርን ከመካድ አይተናነስም አስብበት  መልካም ህይወት ማለቴ  ስቃይ ይሁንልህ እንግዲህ » ፈገግ ብዬ አየውት ድብዝዝ አለ ጥዬው ከሬስቶራንቱ ወጣሁ የጩኸት እና የእቃ መሰበር ድምፅ እየሰማሁ ነው ምንም ሳይመስለኝ ቀጥታ መኪናዬን  ወዳቆምኩበት ቦታ ሄድኩኝ   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── ዛሬም ስራ አልገባችም አይዛን ጋር ቁጭ ብላለች « ማማ አባቴ በመምጣቱ ደስ አላለሽም » አላት አይን አይኗን እያየ « ኧረ ደስ ብሎኛል » « ለምን እንደ ድሮው ከእኛ ጋር አልተኛም ታድያ አንቺ ደስ ቢልሽ እኮ ይተኛ ነበረ » የምትመልሰው ግራ ገባት « አይደለም የእኔ ልጅ አሁን ሂድ ተጫወት እሱ ጋር » አለችው ከጥያቄዎቹ ለመዳን የስልኳን ጥሪ ሰማችው  ከአልጋው ላይ አንስታ አየችው ፈገግ አስባላት የደዋዩ ማንነት « ሄሎ ዛቪያር » « ረዒና መገናኘት እንችላለን » « አዎ ምነው በሰላም ነዋ » « አዎ በሰላም ነው ሆስፒታሉ  አቅራቢያ ያለው ሬስቶራንት እጠብቅሻለሁኝ » « እሺ እመጣለሁ » ብላ ስልኩን ዘጋችው ውስጧ ፈራ ድምፅ ቅላፄው ተቀይሮባታል « ምን አሰብሽ » አላት ኑሃይድ በር ላይ ቁሞ ደንገጥ ብላ አየችው « ስለምኑ » « ትላንት ስላወራንበት ጉዳይ እኔ እና አንቺ አብረን ሁነን ልጇችንን እናሳድግ መለያየታችን ለሁለታችንም እንዲሁም ለልጃችን አልጠቀመውም ቆም ብለሽ አስቢ » « የማይሆን ነገር አታውራ ኑሃይድ የሚሆን አይደለም » « ይሆናል ረዒና ውሳኔሽን እስክትቀይሪ እጠብቅሻለሁኝ » በመገረም አይን አይታው እልፍ ብላው ሄደች   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── « ምነው ዝም አልክ ፈርሀን እፈልግሻለሁ ብለኸኝ አይደል ከስራ የቀረውት » « አሁን ልወቅስሽ አልፈልግም የምነግርሽም እውነታውን እንድታውቂ ስለምፈልግ ነው  ናዝኒን መደባበቁ ይብቃን ኢሪዝ የእኔ ልጅ እንዳልሆነ አውቃለሁኝ ይሄን ማወቄ ነበረ እንድንለያይ የፈለኩት እንዲሁም እኔ መሀን ነኝ መውለድ አልችልም ይሄንን አውቀሽ ከእኔ ጋር መሆን ከፈለግሽ አሁን ላይ በሬ ክፍት ነው ኢሪዝ ልጄ ነው  እኔም አባቱ ይሄ አይቀየርም ግን  በዱዐ ነገራቶች  መስተካከል ይችላሉ ብዬ አስባለሁ እና አንቺም እንደ እኔ ካሰብሽ አብረን እንሁን » አንገቷን ደፍታ ዝም አለች « ፈርሀን በጣም ይቅርታ » አላስጨረሳትም « ናዝኒን ሁሉንም እርሺው እና ፍላጎትሽን ንገሪኝ » « እሺ ፈርሀን ለልጄ አባት ላሳጣው አልፈልግም » « አላህ ከእኛ ጋር ነው ናዝኒን እጆቻችንን ወደ አላህ እንዘረጋለን እስከዛሬ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ላስከፋውሽ አውፍ በይኝ » እንባ ከአይኖቿ ዝርግ አለ  « እኔ ነኝ ብዙ ጥፋቶችን ያጠፋውት ፈርሀን ወላሂ አውፍ በለኝ» እግሩ ስር ድፍት አለች « ተነሺ ናዝኒን አውፍ ብዬሻለሁ እኔ ከአላህ ምህረትን ጠይቂ   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── ልቤ ቀጥ ማለት ነው የቀራት ሰአቱ አልደርስ አለኝ ለእናቴ ደውዬ ሁሉንም ነገር አስረዳዋት ለረዥም ደቂቃ ነው በእንባ ደስታዋን የገለፀችልኝ ምርቃት አዘነበችብኝ ብቻ በጣም ነው ደስ ይላት ይዤ የመጣሁትን ልብስ ኒማል በስርአት አስተካክላልኛለች የዛቪያርን መምጣት ብቻ ነው እየጠበኩኝ ያለውት « ረዒፍ ግን ብቻዬን እንደምሆን ሳስበው ትንሽ ከፋኝ » « ትንሽ ጊዜ ነው ትምህርት ስትጀምሪ እራስሽን ቢዚ ታደርጊያለሽ ትለምጂዋለሽ » « ደሞ አንድ ነገር ልንገርሽማ » አይን አይኗን አየዋት እንድትነግረኝ « ኒያዝ ትላንትና ስንመጣ ኡስታዝ ጋር ሽማግሌ ልላክ አለኝ ቀልዱን ነበረ የመሰለኝ » አለች አንገቷን ድፍት እያደረገች የእሷ መሽኮርመም እኔንም አሽኮረመመኝ ጉድ እኮ ነው ፈገግ አልኩ « ደስ ብሎሻል አይደል » አይኗን ጨፍና  ቀና አለች በአንገቷ አወንታዋን ገለፀች « ኦ ሰርግ ልንበላ ነዋ መቼስ የመጀመሪያ ሚዜ እኔ ነኛ  » አልኳት በሂጇቧ ፊቷን ሸፈነችው አቤት መሽኮርመም ሁኔታዋን ላየ ኒያዝ ፊት ለፊቷ ተቀምጦ የሚያሽኮረምማት ነው የሚመስለው « አትፈሪ እዚህ እኮ ኒያዝ የለም » ብዬ ሳኩባት   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── ከቀጠርኳት ሰአት ቀደም ብዬ ስለተገኘውኝ ብዙ ደቂቃዎችን ተቀመጥኩኝ እሷ በሰአቷ ያልኳት ቦታ ተገኘች ፈገግ ልል እየሞከርኩኝ ነው ግን እንዴት ፊት ለፊቴ ወንበር ሳብ አድርጋ ተቀመጠች «ፊትህ ልክ አይደለም ዛቪያር » ገና ከመምጣትብ ውስጤን አነበብችው « አይ አንድ ነገር ላወራሽ ነበረ ከየት እንደምጀምር አላውቅም ብቻ ፍቅር የሚባለውን ስሜት ያወኩት ባንቺ ነው በሀራሙም ቢሆን ሀላል ላደርገው ግን አልቻልኩም አልቻልሽም አላህ አልፈቀደውም አብረን እንድንሆን አልተፈቀደልንም እና አንቺም የራስሽን ህይወት ቀጥይ እኔም የራሴን መንገድ ልመራ « ዛቪያር ምን እያልክ ነው » ውብ አይኖቿ ስር እንባ ኩልል አሉ ግን ውስጤ ደርቋል « አዎ ለልጅሽ ታስፈልጊዋለሽ ልጅሽ ደሞ በእናት አባቱ ፍቅር እቅፍ የማደግ መብት አለው ይሄን መብቱን ልጅሽን አትንፈጊው » አንገቷን ደፋች ምንም አላለችም « ይሄን ልነግርሽ ነው የቀጠርኩሽ ላሳለፍናቸው ጊዜያት አመሰግናለሁ ደህና ሁኚ » እራሴን ሳላዳምጥ ባለችበት ጥያት ሄድኩኝ ልታስቆመኝም ሆነ ልታወራ አልቻለችም ።                       ~ እቤት እንዴት እንደደረሰች አታውቀውም የሆነ የምትጮህበት ድምፅ አውጥታ የምታለቅስበት ቦታ ነው የፈለገችው ግቢው ውስጥ እንደገባች እየሮጠች ወደ ክፍሏ ሄደች ፈርሀን እና ኑሃይድ ሳሎን ቁጭ ብለው ነበረ በድንጋጤ ተነስተው ተከተሏት አልጋው ላይ ድፍት ብላለች በሩን ስላልዘጋችው ለመግባት አልተቸገሩም ግራ እና ቀኝ ሁነው ምን እንደህሽነች ይጠይቋታል ግን ምንም አልመለሰችም እስኪወጣላት ተንሰቅስቃ አለቀሰች እነሱም ዝም አሏት ብድግ ብላ ቁጭ አለች አይኗ ቀልቷል ቀይ ፊቷ ቲማቲም መስሏል « ኑሃይድ » አለች ሳግ እያነቃት « ወዬ ረዑ ምን ሁነሽ ነው ». « በድጋሜ አብረን እንድንሆን ትፈልጋለህ ».“ « አዎ አዎ እፈልጋለሁኝ» « እንደቀድሞው አይነት ስህተት አትሰራም በእኔ እና አንተ መሀከል ማንንም አታስገባም » « አዎ ረዑ ቃል እገባልሻለሁኝ ማንንም አላስገባም ልጃችንን በሰሊም እናሳድጋለን ያገባዃትን ሴት ፈትቻታለሁ እሷ ለሚስትነት ብቁ አይደለችም ውጪ ውጪውን እንጂ ቤቷን መያዝ አልቻለችም « እንመለስ » ፊቱ በደስታ ፈካ ፈርሀንን አየው እሱም ደስ ብሎታል

 .                 ╔═══ ೋ 𔘓 ೋ  ═══╗                                  𝙼ҽɾℓỉɳ                          ፀሐፊ  « አፍናን ሩማን »                   ╚═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╝ .                       ━─━─  𓍯  ─━─━                              ραɾƚ    0:76                         ━─━─  𓍯  ━─━─ ወደ ግቢ ገባሁኝ ማንንም ማውራት አልፈለኩም በቀጥታ ወደ ክፍሌ መሄድ ብቻ ደስ የሚለው ሳሎን ማንም የለም ቀጥታ ወደ ክፍሌ ሄድኩኝ እና ልብስ ቀየርኩ « ትመጣለህ ብዬ አንተን አይደል የምጠብቀው» ኒያዝ ወደ ክፍሌ እየገባ « ማንንም ማውራት ስላልፈለኩኝ ነው  ኒያዝ» አልጋ ውስጥ ገባሁ እሱም ጫፍ ላይ ተኛ «ኧረ ባክህ እኔ ስንከራተት ነው የዋልኩት ወላሂ በቃ ይሄ ብር የማይሰራው ነገር የለም የብር ሀይልን በደንብ ዛሬ አየውት ለማንኛውም የኒማልንም የረዒፍንም ጉዳይ በሚገባ ጨርሼዋለሁ ረዒፍ ነገውኑ መግባት ትችላለች » «እሺ ነገ ከአሱር ቡሀላ  ይዣት እሄዳለሁኝ» « ምን ሁነህ ነው እንደዚህ የቀዘቀዝከው» «ዛሬ ፈርሀንን አጊንቼው ነበረ እና የሆኑ ነገራቶችን ነገረኝ ስለራሱ ምናምን» «እና እሱ ነው ያስደበረህ» « አይደለም ረዒና ባለትዳር እንደነበረች እና አንድ ልጅ እንዳላትም ነገረኝ ትንሽም ቢሆን ውስጤ ተስፋ ነበረ አሁን ግን በሷ ጉዳይ የመጨረሻ ተስፋዬ ሙጥጥ ብሎ አለቀ በቃ ከህይወቴ ለአንዴም ለመጨረሻ ጊዜ አስወጣዃት ግን ውስጤ ሰላም አቷል» « እኔም ይሄንን ፈርቼ ነበረ አብሽር ወንድሜ እሷን ላንተ አላላትም ለምን ብለህ አትሟገት ለአንተ የተፃፈችው በጊዜዋ በሰአቱ ትመጣለች አሁን ብቻህን ሁን ልሂድ ቁርአን አዳምጥ ውስጥህን ለማረጋጋት » ከተቀመጠበት ተነሳ ስልኩን አቀብሎኝ ክፍሉን ለቆ ወጣ አንድ የቁርአን ቲላዋ ከፈትኩኝ ኡፍፍፍፍፍ ሰላምምምምም   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── አለምን በእጅ መጨበጥ የሆነ ከአቅም በላይ የሆነ ደስታ ከእንቅልፏ እንደነቃች ያየችው እጇ ላይ ያለውን ቀለበት ነው አስተውላው የማታውቀው እጇ ዛሬ ሳሳችለት « ታውቃለህ ሊበን በጣም በጣም ደስተኛ ነው ያደረገኝ ቃል የለኝም » አለች እና በተኛበት አይኑን ግንባሩን ጉንጩን የቀራት የለም በደንብ ሳመችው ግን አይኖቹን እንደጨፈነ ነው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላሳየም ደጋግማ ሳመችው አሁንም አይኖቹ እንደተጨፈኑ ናቸው ነገራት ኮሽ ባሉ ቁጥር እንደ ንስር አይኖቹ የሚነቁት ውዱ የሷ ሊበን አሁን አይኖቹ እንደተጨፈኑ ናቸው ልብ ምቷ በጣም ጨመረ ከአልጋው ተስፈንጥራ ተነሳች እጇ እግሯ ውሀ ሁኗል ምንም የማይንቀሳቀሰውን አይኑን የጨፈነውን ሊበን ወደ ታች አዘቅዝቃ ተመለከተችው እንደ ምንም ወደ እሱ ተጠግታ የልብ ምቱን ለማዳመጥ ደረቱ ላይ ተለጠፈች « ሊበን አይሆንም ትተኸኝማ አትሄድም ቀን እኮ ይቀረናል ልንጋባ እኮ ነው ፈጣሪዬ ሆይ ምን ተፈጥሮ ነው » ወደ አፉ እና አፍንጫው እጇቿን ላከች እስትንፋሱን  ለማረገጋገጥ ግን ሁሉም ነገር ዝም ያለ ነው በእጇቿ ወዘወዘችው ግን እንደ ቅድሙ ነው የተለየ ነገር የለም እንባዋ መቆም አልቻለም ህልም እንዲሆን እየተመኘች ነው ክፍሉን ለቃ ወደ ውጪ ሮጠች « እባክህ  እርዳኝ ሊበን የሆነ ነገር ሁኗል እባክህ » እየጎተተች በሚባል ደረጃ ወደ ውስጥ ይዛው ገባች አገልጋዩ በፍጥነት አልጋው ላይ ሄዶ የሊበንን ሁኔታ አየው « አዝናለሁ እመቤቴ  የልብ ምቱም ይሁን እስትንፋሱ ቆሟል » አላት ወደ እሷ እየዞረ « አይሆንም አይሆንም እኔ ይሄንን አላምንም » እንባ የተቀላቀለበት ሳቅ እንደ እብድ አደረጋት « አዝናለሁ እመቤት ግን አለቃ ይሄንን እንድሰጥሽ አዞኝ ነበረ » አላት አንድ ወረቀት በእጁ ይዛ የእሱን ህይወት የሚተካ ተአምር ይመስል ተስገብግባ ወረቀቱን ተቀበለችው የኔ ውድ በመጀመሪያ ከእናቴ ከጣይ ብቸኛ የወደድኳት ሴት መሆንሽ እወቂልኝ ከልቤ ነው ደሞ ሞተ ብለሽ አትዘኚ ሁሌም ልብሽ ውስጥ እኖራለሁኝ ትሞታለህ ከተባልኩበት ቀን ተጨማሪ ቀን እንደውም ፈጣሪ ጨምሮልኛል ተደስቼ እንድሞት ስላደረግሽኝ በጣም አመሰግናለሁ አትዘኝ በእኔ ስም ያሉትን ሀብቶች ሁሉንም በስምሽ አዙሬልሻለሁ የራስሽን ህይወት ጀምሪ ደስተኛ ሁኚልኝ አንቺ እንዳይከፋሽ  ሁሌም አወድሻለሁ   ያንቺው ሊበን አቅም አንሷት በቆመችበት ዘጭ ብላ ወለሉ ላይ ተቀመጠች « እመቤት አይዞሽ ተረጋጊ » እጇን ይዞ ሊያስነሳት እየሞከረ « ህይወቴ እኮ አንተ ነህ ደስታን ፍቅርን ያየሁት እኮ ባንተ ነው ለምን ለምን ሊበን » ትኩስ ትኩስ እንባ ከአይኖቿ ተንከባለሉ   ─‌──‌   ⪩⪨  ───   ከመስጅድ ከተመለስን ቡሀላ እንደተለመደው በጀምአ ቁርስ ላይ ቀረብን « ዛቪያር 2:30 ላይ ተቀጣጥረናል ዶክተር ጋር » « እሺ እናቴ » ቁርስ ተመግበን ጨረስን ኒያዝም ስራ መግባት ስላለበት ወደ ክፍሉ ሄደ አባቴም ወደ ክፍሉ ኒማል እቃዎችን እያነሳሳች ነው «ረዒፍ ሁሉንም ነገር ተስተካክሏል ቡሀላ እንሄዳለን » አልኳት « እሺ » አለች ፈገግ ብላ ኩስትር እንዳልኩኝ ጊቢ ለቅቄ ወጣሁኝ በቅድሚያ ዶክተር ሀሪስን ማግኘት አለብኝ ሰነዱን እንደያዝኩ አረጋገጥኩኝ እናቴ ወደ ነገረችኝ ሬስቶራንት አመራሁ በተባለው ሰአት ደረስኩኝ መኪናዬን አቁሜ ወረቀቶቹን ይዜ ወደ ሬስቶራንቱ ገባው ብዙም አይኔን አላንከራተትኩትም የሚታይ መልኩ አምሮበት ከእነ ግርማሞገሱ ተቀምጧል ይሄ በራስ መተማመኑ ከደቂቃዎች ቡሀላ ኩሽሽሽ ሲል በሀሳቤ አስቤው ፈገግ አልኩኝ ፊት ለፊቱ ያለውን ወንበር ሳብ አድርጌ ተቀመጥኩኝ ግራ መጋባቱ እና መደናገጡ ያስታውቃል « እንዴት ነህ ዶክተር ሀሪስ » « አልሀምዱሊላህ  ዶክተር ዛቪያር ምን እግር ጣለህ ወደ እዚህ » « እንዴ ሚዜ አይደለው እንዴ ግን እናቴን አግብተህ ለእንጀራ አባቴ ሚዜ እንደምሆን እያሰብኩት ነበረ » « ምን አልገባኝም ምን እያልክ » ግራ መጋባቱ ግልፅ ነው አንድ ፎቶ አውጥቼ ጠረንጴዛው ላይ ወደ እሱ አስጠግቼ አስቀመጥኩለት « ይህቺን ሴት ታውቃታለህ » ከጠረንጴዛው ላይ ፎቶውን አንስቶ ትኩር ብሎ ተመለከተው ከእዛ እኔን አየኝ ከዛ ፎቶውን « ያስታወስካት ይመስለኛል ሚስትህ የነበረች ሴትን እንዴት አታስታውስም ነገሩ ባሏ እንደ ሞተ እንድታምን አድርገህ ብዙ ብዙ ነገር አድርገህ አገባኻት ከዛ  ንብረቷን ወሰድከው ከዛ ፈተዃት ... ከዚህ በላይ ያለውን ታሪክ በደንብ ታውቀዋለህ እንድታስታውሰው ያህል ነው  ኑሓይላ የእኔ እናት የጁዌይሪያ ታላቅ እህት የአባቴ ሚስት ባንተ ምክንያት ለብዙ ጊዜ ታመመች እሷን ማሳከሚያ ብር እስክናጣ ድረስ ባዶ እጃችህን አስቀረኸን ሞተች በአንተ የተነሳ እናቴን አጣሁኝ ይገባኻል አይደል ይሄ ሁሉ ያንተ ሀጥያት ነው እራስህን በራስህ እንድታጠፋ ነበረ ምኞቴ ግን ሞት እረፍት ነው ቅጣት አይሆንም ይልቅ እንዲህ የምትመፃደቅበት ንብረት በአባት እናቴ እንዲህ ያደክበት ሀብት በእጄ ገባ » ንብረት ያዘዋወረበትን ሰነድ ኮፒውን ወደ እሱ ወረወርኩት «አንተ ውሻ ታውቆኝ ነበረ ሲጀመር እሷንም አንተንም አጠፋችዃለሁ እኔ ሀሪስ አይደለውም » ፊቱ በአንዴ ቅይርይር አለ ድንፋታውን እስኪጨርሽ ጠበኩት  « አሁን እኮ አንተ ጎዳና ላይ እንዳለህ ውሻ ነህ ቤት የለው ምግብ የለው በቃ ሲንቀዋለል የሚውል ውሻ ማለት ነህ እስትንፋስህን ስላልነጠኩህ አመስግን ከዜሮ ተነስተህ መኖር ጀምር አይዞህ እንግዲህ » ከተቀመጥኩበት ተነሳው

. መርሊን የመጨረሻ ክፍል 1:00 hr .......left @rim_han .

https://t.me/whatif_34_44 ቻናል ልጋብዛችሁ ቢያንስ 500 አስገቡት ለኔ ብላችሁ ፓሚሊ 🫶

. ውድ አንባቢዎቼ መርሊን ሊያልቅ አንድ ክፍል ብቻ ነው የቀረው 🥹 አንድ እህቴ በሰጠችኝ አስተያየት ስለ ታሪኩ አስተያየት መስጫ እና ጥያቄ መጠየቂያ ቀናት አዘጋጅቼ ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም በታሪኩ ዙሪያ ጥያቄ ታነሳላችሁ .😭😭 ሊያልቅ በመሆኑ የከፋኝ እኔ

እና ተጨማሪ ደሞ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ያለ የሴቶች መርከዝ ፈልግ Âť ÂŤ እንዴ ለምን Âť ÂŤ ለረዒፍ Âť ÂŤ መርከዝ ልትገባ Âť በአይኔ ቆጣ አልኩት ÂŤ እሺ በቃ እንዳልከኝ አደርጋለሁ ኒማል ተዘጋጂ ቁርስ በልተን እንሄዳለን Âť አላት ቁርስ ከበላን ቡሀላ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ከቤት ወጣሁ ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ ፈርሀን ማታ ረዒፍን ስልኩን ብዬ ተቀብያት ነበረ ባይዋጥላትም ሰጠችኝ ቁጥሩን ፈልጌ ደወልኩለት ÂŤ ሄሎ ፈርሀን አሰላም አለይኩም ዛቪያር ነኝ Âť ÂŤ ዋለይኩም አሰላም እሺ ዛቪያር እንዴት ነህ Âť ÂŤ አልሀምዱሊላህ አሁን ከቻልክ መገናኘት እንችላለን Âť ÂŤ አዎ እችላለሁ የት ልምጣ Âť ÂŤ ከሆስፒታሉ አቅራቢያ ያለ ካፌ እጠብቅሀለው Âť አልኩት እና ስልኩን ዘጋውት ዣንግ መኪናውን ወደ ካፌው ዘውሮ አቆመው የካፌው በር አከባቢ እንድታየው ሁኜ ተቀመጥኩኝ ውስጤ ግን ምን ሊለኝ ነው ይሆን የሚል ጥያቄ መጠየቁን አላቆመመ ከደቂቃዎች ጥበቃ ቡሀላ መጣ ከውጪ ሁኖ በመስታወቱ አሻጋሪ ነው የተመለከተኝ ቀጥታ ወደ እኔ ጋር መጣ እና ተቀመጠ ÂŤ ቆየውብህ Âť ÂŤ እይ ትንሽ ደቂቃ ነው  የሆነ ነገር እዘዝ Âť ÂŤ አሁን ነው ቁርስ የበላሁት ሰአተን እንዳልሻማህ ቶሎ ወደ ጉዳዬ ልግባ». ÂŤ እሺ ካልክ Âť ÂŤ እሺ እየሰማውህ ነው Âť. ÂŤ ዛቪያር ባልጠበኩት እና ባላሰብኩት ሁኔታ ረዒፍን ወድጃታለሁ Âť ክው ነው ያልኩት ቀጣይ ምን ሊለኝ እንዳሰበ ግልፅ ነው ÂŤ እና እኔ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልገው ፈርሀን ይሄንን ለልሡ ብትነግራት አይሻልም Âť ÂŤ አዳምጠኝ ዝም ብለህ ግን እኔ እና እሷ አብረን መሆን አንችልም  ታውቃለህ ለእሷ የነገርኳት ታሪክ ሌላ ነው ምን አልባት አሁን የምነግርህ ነገር ከእኔ ቀጣይ አንተ ብቻ የሰማኸው ጉዳይ ነው ዶክተር ናዝኒንን ታውቃታለህ መቼስ እሷ የእኔ ሚስት ነበረች እናም አንድ ልጅም አፍርተናል ደስተኛም ባለትዳሮች ነበርን አሁን ግን ተፋተናል በምን እንደተለያየን ልንገርህ በተጋባን 7ወር ባልሞላ ጊዜ ነው የመጀመሪያ ልጅ የወለድነው በሰአቱ አላሰብኩትም ግን ማንኛውም ሴት በ7 ወሯ ልትወልድ የምትችልበት አጋጣሚ አይኖርም 8 ወር እንደውም ይሻላል ከ 7 ወር በቃ ጊዜ በሄዱ ቁጥር ይሄ ነገር ውስጤን ይበላኝ ጀመረ ውስጤን ለማሳረፍ DNA አስመረመርኩ የልጁ አባት እኔ እንዳልሆንኩ እና እኔ መውለድ እንደማልችልም የሚሰብር ዜና ሰማው ለሳምንት ድንዝዝ ብዬ ነበረ የማደርገውን አላውቅም ነበረ መፍትሄ ብዬ ያሰብኩት ነገር ቢኖር ናዝኒንን መፍታት አደረኩት ለውራት ከእቤት አልወጣሁም ነበረ በቃ ስራም ምንም አቆምኩኝ ከዛ ሁሉ ነገር ቡሀላ አገግሜ ወደ ልሴ ተመለስኩኝ ለሾል ወደ ውጪ ወጣሁ እና ለወራት ከራሴ ጋር ለመሆን በስራ እራሴን ቢዚ አድርጌ ወደ ኢትዮጵያ ሾመለሾ ረዒፍን ባጋጣሚ አገኘዋት እንደቀልድ ሳያት ደስ ስላለኝ ነበረ ደፈር ብዬ ያወራዋት እሷም ቀላል ባትሆንም ተግባባን ግን እወዳታለሁ ብዬ አስቤ አልነበረም ውስጤ ግን ፍቅር ጀመረ  ይሄ ስሜት እንደማይሆን እያወኩት አስቀጠልኩት ግን በቃ ሁልን ነገር ሳስበው ጭራቃዊ የማይሆን ነገር ነው ስለዚህ ረዒፍን ያለጥፋቷ በማይሆን ነገር  እንድትከፋብኝ አድርጌ ከራሴ አገለልኳት Âť ዝም አለ ÂŤ ፈርሀን ምን እንደምልህ አላውቅም ከባድ ነገር ነው የነገርከኝ ግን በአላህ ተስፋ አይቆረጥም ሁሉም ነገር እኮ በዱዐ ይስተካከላል አይደል እንዴ Âť ÂŤ ልክ ነህ እኔም ጥፋቶቼን ማረም አለብኝ ለዛ ነው ላንተ የነገርኩህ ረዒፍን አደራ እዚህ ሀገር ከእኔ ውጪ አንተን ነው የምታውቀው እኔ ከእሷ ጋር መሆን አልችልም አላህ አልፈቀደውም ÂŤ ግን እኮ ፈርሀን Âť አላስጨረሰኝም ÂŤ እንድታዳምጠኝ ነው የምፈልገው ዛቪያር ሌላው ደሞ ያንተ እና የረዒና ጉዳይ ነው የአጎቴ ልጅ እንደሆነች ታውቃለህ ሾለ አንተ አውርታ አትጠግብ በጣም ነው የምትወድህ ምን አልባት ከዚህ በፊት አግብታ እንደፈታች ነግረሀለች ግን ልጅ እንዳላት አልነገረችህም ይመስለኛል» ÂŤ ምን ልጅ አላት Âť ድንጋጤዬን ማንም ቢያይ ይመሰክራል ÂŤ አዎ ፈርሀን እሷ በዚያ ሁኔታዋ እንደማትነግርህ ስለገባኝ ነው ይሄን ልነግርህ ነው ስላዳመጥከኝ አመሰግናለሁ Âť ደንዝዣለሁ ከተቀመጠበት ቦታ ተነስቶ ወጣ ያኔ ልጅ እያለን እንለያይ ስትለኝ የነበረው ስሜት   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ቀናቶች ተቆጥረዋል ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ እያሳለፉ ነው  ከኪሱ አንድ ነገር አውጥቶ ጠረንጴዛው ላይ አስቀመጠው ÂŤ ምንድነው Âť ÂŤ እይው ከፍተሽ Âť አንስታ ከፈተችው ውስጡ ቀለበት ነበረው ፈገግ አለች ÂŤ ድጋሜ እንጋባ ያኛው ወረቀት ላይ ነው Âť ÂŤ ይሄስ Âť ÂŤ ይሄ ፍቅርም አለው» ከተቀመጠበት ተነሳ እና እጇን ሳብ አድርጎ ቀለበቱን አደረገላት ግንባሯን ሳማት አይኖቿ በእንባ እረጠቡ   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ ነው የዋሉት የኒማልንም ጉዳይ ተሯሩጦ ሁሉን ነገር አስተካከለው ዛቪያር እንዳለውም የሴቶች መርከዝ ፈልጎ ያለውን ሁኔታ አጣርቶ የሚያስፈልገውን ነገር አድርጎ ሁሉን ነገር አጠናቋል ÂŤ አሁን ወደ ቤት እንሂድ አይደል Âť አላት መኪናውን እያንቀሳቀሰ ÂŤ አዎ ምን ቀረ ጨረስን አይደል Âť ÂŤ አዎ በጣም ደክሞኛል እኔ ልሹ Âť. ÂŤ ስላረጀህ ነዋ የሚደክምህ »አለችው ÂŤ ገና አንድ ልጅ ሳልወልድ አርጅተሀል አልሽኝ Âť ÂŤ ሚስት ሳታገባ ሾለ ልጅ ወይስ ሚስትየዋ አለች Âť ÂŤ ኧረ የለችም ፈልጊልኝ እስኪ» ÂŤ ከየት ልፈልግልህ እኔ ብለህ ነው ግን ምን አይነት ትሁንልህ Âť ÂŤ ያው እንዳንቺ ትሁን Âť ÂŤ ምን ኒቃቢስት ነው Âť ÂŤ አዎ ፀባይም ትሁን Âť ÂŤ እንደ እኔ አይነት እማ የለም እኔው ነኝ Âť ÂŤ እና አንቺን ላግባ ምን አማራጭ አለኝ Âť ÂŤ ሽማግሌማ አላገባም ያው አባቴን ጠይቅ እና እሱ ሽማግሌ እንዳገባ ከፈረደብኝ ምን አማራጭ አለኝ Âť ÂŤ እኔ ቀልድ አላውቅም አምርሪያለሁ እንዳይቆጭሽ ቡሀላ ሽማግሌ እንዳልክ ወደ ኡስታዝ Âť ÂŤ ላክ እንግዲህ ምን ይባላል ሌላ  Âť ብላ ሳቀች   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ሰአቱ ሂዷል ልጇ ከአባቱ ጋር እየተጫወተ ነው ህመሙን ሁሉ እረስቶታል ኑሃይድ ሰረቅ እያደረገ እያያት ነው እሷም ገብቷታል ብቻቸውን እንዲሆኑ ሳሎኑን ለቃላቸው ወደ ክፍሏ ሄደች ÂŤ ረዒና Âť ወደ ዃላ ዞር ስትል ኑሃይድ ተከትሏታል ÂŤ አቤት ምንድነው Âť ቆጣ ብላ ÂŤ አንዴ እናውራ Âť በልምምጥ አይን እያያት ÂŤ ስለምን Âť ÂŤ ሾለ እኔ እና አንቺ  ለትንሽ ደቂቃ Âť ÂŤ እሺ Âť አለችው እየሸከካትም ቢሆን   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ሆስፒታል ቆየ እንጂ በጣም ደብሮታል ፈርሀን የነገረው ነገር ቀኑን ነው ያበላሸው ስልኩ ጠራ ከኪሱ አውጥቶ አየው እና አነሳው ÂŤ ሄሎው Âť ÂŤ ሄሎ ባልየው ምን ሁነህ ነው ስልክ የማታነሳው Âť ÂŤ ሜይሊን ትንሽ ጥሩ ሙድ ላይ አይደለውም Âť ÂŤ ምን ሆንክብኝ ወንድሜ እኮ ሾል ቢዚ አድርጎት ነው ብሎኝ ነበረ Âť ÂŤ ሊን ልክ ነው ትንሽ ቢዚ ሁኜ ነበረ Âť ÂŤ እሺ ነገውኑ እመጣለሁኝ Âť ÂŤ ኢትዮጵያ መጣሽ እንዴ Âť ÂŤ አዎ ነገውኑ እቤት እመጣለሁ እንደዚህ ባሌን ያስደበረውን ነገር ድራሹን ነው የማጠፋው Âť ሳልፈልግ አሳቀችኝ ÂŤ እሺ ውዷ ሚስቴ በይ ቻው» ስልኩን ዘጋውት ይቀጥላል .  . . . @rim_han .

 .                 ╔═══ ೋ 𔘓 ೋ  ═══╗                                  𝙼ҽɾℓỉɳ                          ፀሐፊ  « አፍናን ሩማን »                   ╚═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╝ .                       ━─━─  𓍯  ─━─━                              ραɾƚ    0:75                         ━─━─  𓍯  ━─━─  « በሉ አውሩ እኔ ልግባላችሁ» አለ ኒያዝ እየሳቀ ወደ ውስጥ ገባ «ረዒፍ በሰላም ነው» አለኝ «አዎ በሰላም ነው  አንድ የማወያይህ ጉዳይ አለ» « እሺ ረዒፍ አሁን ግን ሰአት እየሄደ ነው ከመስጅድ ስመለስ እናወራለን » ብሎ ጥሎኝ ገባ እኔም ወደ ክፍሌ ሄድኩኝ ኒማል እየሰገደች ነበረ እስክትጨርስ ጠበኳት እንዴት ለዛቪያር እንደምነግረው እያሰብኩኝ ነው ግን ለእሱ መናገር ይኖርብኛል እንዴ ስል አሰብኩ በድጋሜ « ረዒፍ ምን አለሽ» አለች ኒማል መስገጃዋ ላይ እንደተቀመጠች « አይ አልነገርኩትም» « የተጨነቅሽ ትመስያለሽ ወይ እኔ ልንገረው» « እንደሱ ይሻላል» « አዎ ሲመጣ እኔ እነግረዋለሁ አታስቢ» አለችኝ   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── እራት እንብላ ስላላት መግሪብን እዛው ፋውንዴሽኑ ውስጥ ባለ የመስገጃ ቦታ ሰግዳ ወደቀጠራት ቦታ ሄደች እንደ ሁልጊዜው ቀድሟት ተገኝቷል ፈገግ ብላ ከፊት ለፊቱ ተቀመጠች « ደክሞሻል መሰለኝ ዛሬ» «አዎ እንዳየኸኝ ዛሬ ስደክም ነበረ የዋልኩት » « አዎ ልክ ብለሻል እኔማ ቤተሰቦችሽ ጋር መች ሽማግሌ ልላክ በሚለው ጉዳይ እንድናወራ ነበረ» « ነገ የማስተካክለው ጉዳይ አለኝ ከነገ ቡሀላ በደንብ ቁጭ ብለን እናወራለን እ ተረዳኸኛ» «እሺ ችግር የለውም እረዳሻለሁ የሚያስቸኩል ነገር የለንም» ለአፉ እንደዚህ ይበላት እንጂ ፊቱ መከፋቱን ይገልፃል እሷም ከማብራሪያ ይልቅ ዝምታን መረጠች ለአስተናጋጇ የሚፈልጉትን ነገራቶች አዘዙ   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── «እናቴ አልመጣችም እንዴ » አልኳት ኒማልን ወደ ውስጥ እየገባሁ « አዎ አልመጣችም » አለች ኒያዝ መጅሊሱ ላይ ተቀመጠ «ዛቪያር አንዴ ና » አለች ለመቀመጥ ስንደረደር ረዒፍ እፈልግሀለው ያለችኝም ትዝ አለኝ ኒማል ተከትዬ ወደ ላይ ወጣሁኝ ከእኔ እርቀቷን ጠብቃ ነው የምትሄደው « ይኸውልህ ዛቪያር ከረዒፍ ጋር አውርተን አንድ ሀሳብ አስበናል እንዴት እንደሚነገር አላውቅም ግን ረዒፍ ዲናዊ እውቀቷ ላይ እራሷን ማሻሻል ትፈልጋለች  እናም ኢስላማዊ እውቀት የምታገኝበት ቦታ ልትሄድ ነው » « ማሻአላህ ታድያ ይሄ እኮ ምርጥ ሀሳብ ነው » « አዎ እሷ ይሄንን ልትነግርህ ፈልጋ ነው እና ግራ ስለገባት ነው » አለችኝ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እንድገባ ይሄ ምን ያስፈራል እያልኩኝ በውስጤ ወንበሩን ሳብ አድርጌ ተቀመጥኩኝ ኒማልም ወደ ታች ወረደች « ወይዘሪት ረዒፍ አሁን እንደማያውቅ ሰው ምን ነበረ አልልሽም ሀሳቡን ኒማል ነግራኛለች እኔም በሀሳብ እስማማለሁ ለዚህ ደሞ እኔ አመቻችልሻለሁኝ ያሳሰበሽ ይሄ ከሆነ» « አመሰግናለሁ ግን እኔ እዛው ሁኜ ከእዚህ ወከባ መውጣት ነው የምፈልገው ትኩረቴ ሁሉ ኢልም ላይ እንዲሆን ብቻ » « ይሄማ መርከዝ ነዋ እርግጠኛ ከሆንሽ እና ያ ከሆነ ፍላጎትሽ የሴቶች መረከዝ መግባት ትችያለሽ ግን ከተሻለኝ ቡሀላ ውጪ እሄዳለሁ ነበረ ያልሽኝ » « ሀሳቤን ቀይሪያለሁ ቅድሚያ ያልኩህ ነገር ይበልጣል» « ማሻ አላህ ሀሳብሽን ደግፈዋለሁ እኔም አሁን ሌላ የምትነግሪኝ ከሌለ ልሂድ » « እሺ መቼ » « በደንብ ተሽሎኛል ካልሽ ነገ ሁሉን ነገር እናስተካክላለን ከነገ ወዲያ ምናምን » « እሺ » ብላ ፈገግ አለች እኔም ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከክፍሉ ወጣሁ   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── ከግዙፉ አየር መንገድ መኪናውን አቁሟል መምጣቱን ለማንም አልተናገረም እራሱ ሊቀበለው ስለፈለገ ከረዥም ጊዜ በፊት ያየው ወንድሙ ሻንጣ እየገፋ  ብቅ አለ እና ወደ እሱ መጣ ተቃቀፉ « ኦ ወንድሜ » በድጋሜ ተቃቀፉ የተለያየ እናት ቢኖራቸውም እነሱ በፍቅር ነው ያደጉት የሚጠያየቁ ወንድማማቾች ናቸው ፈርሀን ሻንጣውን አንስቶ መኪና ውስጥ አደረገው ኑሃይድ ጋቢና ገብቶ ተቀመጠ ፈርሀንም ገብቶ ቀበቶውን አሰረ ንጋት ላይ ነው « ኑሃይድ አምሮብሀል » አለው ፈርሀን « ቀልደኛ እንደውም ከሳው እንጂ አታየኝም እንዴ ያ ሸበላው ኑሃይድ የት አለ አሁን ረዒና ታውቃለች እንዴ መምጣቴን » « አሁንም ኧረ ሸበላ ነህ ኧረ ለማንም አልተናገርኩም አታውቅም መምጣትህን» « ነገሩ ልታየኝ ነው አሁን አንድ ነገር እንድትተባበረኝ እፈልጋለሁ » « ምን » « ረዒና አንተን ትሰማኻለች እና እንድታስታርቀኝ በድጋሜ አብረን ሁነን ልጇችንን እንድናሳድግ እንድታሳምናት እፈልጋለሁ » « ይሄ ከባድ ነው ኑሃይድ እሷ የምትስማማ አይመስለኝም » « አንተን እሺ ትልሀለች አንተ ብቻ ፍቃደኛ ሁን እንጂ » «ኑሃይድ ከባድ ነገር ነው የጠየከኝ ግን እሺ እንሞክራለን » የፈርሀን ፍቃደኛ መሆን ኑሃይድን አስደሰተው እና ፈገግ አለ ከኤርፖርት ወደ እቤት እስኪደርሱ 1:00ሆኗል ጨለማው ተገፎ ንጋት ሁኗል የመኪና ክላክስ ሲያሰማ  ዘበኛው በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ ከመኪናው ወረዱ ሻንጣውን አወረደለት በፈርሀን መሪነት ወደ ቤት አመሩ መጥሪያውን ተጭኖ ረዒና በሩን ከፈተችው ፈገግ ብላ ነበረ በር ላይ የቆመውን ሰው ስታይ ፈገግታዋ ኩሽምን አለ ፊቷ ኩስትርትር አለ « ረዑ እንግባ ወደ ውስጥ » አላት ፈርሀን ሁኔታዎች ስላላማሩት እልፍ እያላት  ኑሃይድም አንገቱን ድፍት አድርጎ ፈርሀንን ተከትሎ ወደ ውስጥ ገባ  አይኗ ማመን አልፈለገችም ምን ሊሰራ መጣ ብላ አሰበች በውስጧ በሩን ዘግታው ወደ እነሱ ተቀላቀለች ቁርስ አቀራርባባ ነበረ የፈርሀን እናት እና አይዛን ቁጭ ብለዋች አይዛን የአባቱን መምጣት ሲያይ ድክምክም ያለው ሰውነቱ ሀይል አገኘ  ቁዝም ያለው ፊቱ ፍክት አለ ከፈርሀን እናት እቅፍ ውስጥ ወቶ አባቱ ላይ ተጠመጠመበት እሱም እቅፍ አደረገው እና ተቀመጠ ለደቂቃዎች ልጅ እና አባት ናፍቆታቸውን ለደቂቃ ተወጡ ረዒና ጥግ ላይ ቁማ የልጇን ሁኔታ አስተዋለች ጭንቅ ብሏት ነበረ እንዲህ ሲደሰት እሷም ደስ አላት « ኧረ በቃ ቁርስ እንብላ እኔ እርቦኛል » አለ ፈርሀን ሁሉም ወደ መአዱ ቀረቡ በዝምታ ተበላ « አንተ አይጥ አባትህን ስታገኝ እኔን ተውከኛ » አለች የፈርሀን እናት « አይ አያቴ አንቺንም አባቴንም እወዳችዃለሁ ባባ አትሄድማ ከዚህ ቡሀላ » « አዎ አልሄድም » አለ ረዒና በዚህ ጊዜ ገልመጥ አደረገችው « የአባትህን ሰርግ አስመልክቶ ነው የመጣኸው ኑሃይድ » አለች የፈርሀን እናት « አዎ » አላት ረዒና ውስጧ እርፍ አለ ተመልሶ ይሄዳል የሚል ሀሳብ አሰበች   ─‌──‌   ⪩⪨  ─── « ይኸው ዛቪያር ሀብቱን ወደ እኔ እንዳዘዋወረው የሚገልፀው ወረቀት» ብላ ሰጠችኝ ተቀበልኳ እና አነበብኩት « ስለዚህ አሁን እሱ በእጄ ላይ ነው ማለት ነው » « ልክ ብለሀል ኢላማህ ላይ ደርሰኻል ከዚህ ቡሀላ መተኮስ ወይ አለመተኮስ ያንተ ምርጫ ነው አሁን ቁርስ እንብላ ሆስፒታል ትሄዳለህ እንዴ ?» « አዎ ዛሬማ ስራ መግባት አለብኝ» ወረቀቱን ጠረንጴዛው ላይ አስቀመጥኩት እና ተያይዘን ወደ ታች ወረድን ኒማል እንደ ሁሌው ቁርስ እያቀራረበች ነው ኒያዝ እና አባቴ ተቀምጠዋል እኛም ተቀላቀልናቸው « ኒያዝ የኒማልን ነገር አስተካክለው ዛሬ አብራችሁ ሂዱ

9 ክፍል እየተማርኩኝ ነው እና መስኮት አጠገብ ነው የምቀመጠው  ከመስኮቱ አሻጋሪ ያለው ሁለተኛው የትምህርት ቤታቸው  ፎቅ 12&11 ናቸው እና 11-07 የምትማር  ልጅ አለች ቆንጆ ነች ምናምን ብቻ ሁሌ ምሳ ሰአት ከአንድ ልጅ ጋር ቁማ ነው የማያት 5 ደቂቃ አልፈጀብኝም ፍቅረኛሞች እንደሆኑ ለማወቅ በቃ ሌላ ትእይንት የሚሰሩት ይነካካታል ብዙ ቡዙ ነገር ብቻ ገብቷችዃል ለማለት የፈለኩት ልጅቷ ሙስሊም ነች ልጁም እንደዛው ግን አለ የተባለ ሱሰኛ ነው  አምና አንድ ታሪክ እንድ ቻናል ላይ አነበብኩኝ ስለ ሀራም ግንኙነት በደንብ የሚያስተምር የታሪኩን ርእስ እና ያለበትን ቻናል ብናገር ታውቁታላችሁ ሁላችሁም ታሪኩ ሲፈፀም ከስር comment አድናቆት ምናምን አለ እሱ እያነበብኩ የፀሀፊዋን አካውንት አየውት እና ወደ ውስጥ ስገባ ያቺ ሁሌ ከወንድ ጋር የማያት ልጅ ነች  መጀመሪያ ተመሳስሎብኝ ነው ብዬ አስቤ አወራዋት የት እንደምትማር ስጠይቃት የእኛ ትምህርት ቤት ተማሪ ነች  ሌላ ደሞ አንድ ልጅ አለ  አሁን 12 ተፈታኝ የሆነ በጣም ዲኑ ላይ ጠንካራ የሆነ ልጅ በቃ መድረሳ ውስጥ ኡስታዝ ባይኖርኝ ኡስታዝን ሊተካ የሚችል ሰው ነው ትምህርት ቤት ውስጥ ከሴት ስር የሚይጠፋ ከሱሰኞች ስር የማይጠፋ እንደ ሴት ጆሮ ላይ ጆሮ ጌጥ የሚያደርግ ሰው እና ዋናው ምን ልላችሁ ነው አሁን ላይ ወጣቱ  የእውቀት ማነስ የለበትም ቢኖር እራሱ አሁን ላይ ብዙ አማራጮች አሉት ለማወቅ ምን አልባት መርሊን የሚለው ታሪክ አስተማሪ  ላይሆንላችሁ ይችላል ግን እኔ የምፅፈው ፁሁፋ አሁንም ወደ ፊት የሚታየውን ችግር በፁሁፍ እፅፋለሁ አላህ ያድርሰን እንጂ እያንዳንዱን ችግር ከጓዳ እስከ በረንዳ እናወጣታለን እኔ እፅፋለሁ እናንተ ታነባላችሁ  የእኔ ችሎታ መፃፍ ነው  ይሄ ምን ይባላል ትውልዱን በቋንቋው ማውራት እኔ አንድ ጠቃሚ ሀዲስ ብለቅ የማያነበው ይበዛል አንድ ሀዲስ ከአንድ ፁሁፍ ጋር  አዋዝቼ ባቀርብላችሁ ልዩነቱን እራሳችሁ ታውቁታላችሁ ልብ ወለድ የማይጠቅም የሚመስላችሁ ሰዎች ደሞ በቀጣይ ፁሁፎች በሌሎች ታሪኮች ስመጣ ጥቅሙን ታዩታላችሁ እንግዲህ አላህ ያለ ምክንያት አልሰጠኝም ችሎታውን እኔም ጥሩ ነገር ላይ ላውለው የማይጠቅም ከመሰላችሁም ችግር የለውም 1 ሰው ከጠቀመ ይበቃኛል ለእኔ አንድ አህቴ ዲኑ ላይ ብታተኩሪ የሚል ሀሳብ ስላመጣች ነው .

አንድ ታሪክ ልንገራችሁ ? አሁን አንድ comment አይቼ ነው ትዝ ያለኝ .

የረቢዕ ንጋት ሳይፀድቅ ያ ጀንበር ያኔ አለም መልኳ ገፆ እንዴት ነበር ማን ያርዳኝ ገፁን የወቅቱን ሁነት ፍትህ ወዴት ነው ሴት ልጅ እንዴት ናት🥺 @rim_han

ÂŤ የታወቀ እኮ ነው ዛቪያር ለወሬ ነው ስልጣን የያዙት በቃ አለ ለመባል እንጂ አሁን እኛም እንቀላቀላቸው Âť ካለንበት ቦታ ወተን እንደ ማንኛውም ሰው ገባን እና ቦታ ያዝን ከፊት ለፊት ወንበር ፕሮግራሙ ተጀመረ የተዘጋጁት ፕሮግራሞች በአስተባባሪዎች አማካኝነት ወዙን ጠብቆ በሂደት ተጠናቀቀ ባቀድነው እቅድ መሰረት አዳዲስ ለጋሾችን አገኘን ከበፊት ለጋሾቻችን ምስጋና ቀረበልን ከብዙ ሂደት ቡሀላ ፕሮግራሙ ተጠናቆ ሰዎች እናቴ ጋር እየሄዱ ለትንሽ ደቂቃ እያወሩ ከአዳራሹ ይወጣሉ እኔ እና ኒያዝ ወንበር ላይ ተቀምጠናል በአይኖቼ ሀሪስን ስፈልገው ነበረ ከሁሉም ሰው መጨረሻ ወደ እሷ ሄደ እንዳላየኝ እርግጠኛ ነኝ ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ እኔም ወደ እሷ አቅጣጫ ሄድኩኝ ÂŤ ድንቅ ሴት ድንቅ ሾል እመቤት ጁዌይሪያ በጣም ነው ያስደነቅሽኝ ያስደመምሽኝ Âť ÂŤ በጣም አመሰግናለሁ ዶክተር ዛቪያር Âť ÂŤ እንዴ ዶክተር ዛቪያር እዚህ አለህ እንዴ አላየውህም ነበረ Âť እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ ግን አይኑ ንዴቱን እንደሚገልፅ ያስታውቃል ÂŤ እኔ ነኝ የጋበዝኩት Âť አለችው ፈገግ ብላ ÂŤ ለአድናቆት ቸኩዬ እኮ ነው ይቅርታ ዶክተር  Âť ብዬ እጁን ጨበጥኩት   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ሾል መግባት ግዴታ ስለሆነበት ከስራ ቡሀላ ቀጥታ ወደ ቤቷ ነው የሄደው ዘበኛው በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ መኪናውን አስገባው እና ከመኪና ወረደ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተጠግቶ ደውሉን ደገምገም አድርጎ ተጫነው ÂŤ መጣህ ፈርሀን Âť አለች በረን ከፍታ እያየችው ÂŤ አዎ ምነው ቆየው እንዴ Âť አለ ወደ ውስጥ እየገባ ትንሹ ልጁ የአባቱን ድምፅ ሲሰማ ከሳሎን እየሮጠ ተጠመጠመበት እግሩ ላይ ከእግሩ አንስቶ ወደ ላይ አቀፈው እና ወደ ሳሎን ገቡ ናዝኒኒ ተከትላቸው ገባች ÂŤ ባባ ለምን እኛ ጋር አትኖርም Âť አለ በሚጣፍጠው የልጅ አንደበቱ ÂŤ እየኖርኩአይደል እንዴ Âť አለው ጉልበቱ ላይ እያስቀመጠው ÂŤ እንደዚል አደለማ ማታ ና እኔ ጋር ተኛ» ÂŤ አልጋህ ላይ ታስተኛኛለህ Âť ÂŤ አዎ አንተንም ማማንም አስተኛችዃለሁ እኔም እተኛለሁ አብረን» ÂŤ እንደዛ ከሆነ ማታም እመጣለሁ በቃ ግን ስንትኛ እንዴት ነው የምታቅፈኝ Âť ጭምቅ አድርጎ እያቀፈው ÂŤ እንደዚህ Âť አለ እና በትትሽ ከንፈሮቹ ጉንጩን ሳመው ÂŤ ኡፍፍፍ የእኔ ጣፋጭ Âť ብሎ አንገቱ ሾር ሳም አደረገው ÂŤ ኢሪዝ በቃ አባትህን አታድክመው ሂድ ወደ ክፍልህ Âť አለችው እናቱ ÂŤ አትሄድማ Âť ÂŤ አዎ አልሄድም አንተ ጋር ነኝ አሁን ሂድ ተጫወት Âť ብሎ ከጭኑ ላይ አወረደው እየሮጠ ሳሎኑን ለቆ ወደ መኝታ ክፍሉ ሄደ ÂŤ ምሳ እንብላ ፈርሀን Âť አለችው ወደ ምግቡ እየጠቆመች እሱም ተነስቶ ምግቡ ጋር ተቀመጠ እና ሁለቱ ብቻ በዝምታ ተመገቡ ÂŤ  ዛሬ እዚህ ልታድር ነው እንዴ Âť ÂŤ አይ አላድርም Âť ÂŤ እና ለኢሪዝ ለምን ቃል ገባህለት» ÂŤ እሱ እስኪተኛ ድረስ እዚሁ ነኝ የረዑን ልጅ አሞታል ከጎኗ አስፈጋግለሁ Âť ÂŤ ምን ሆነ አሁንስ እንዴት ነው Âť ÂŤ አልሀምዱሊላህ ደህና ነው Âť ድርቅ ያለ መልስ ከዛ በላይ ጥያቄ አላቀረበችም   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ዝም ፀጥ ያለ መናፈሻ ቦታ እቅፉ ገብታ ተፈጥሮን ታደንቃለች በአሻጋሪ አንድ እናት አባት ሁለት ልጆችን ታቅፈው ሲሄዱ ሁለቱም አይን ውስጥ ገቡ ምን አለ አንድ ልጅ ወልጄለት ቢሆን ስትል አሰበች በውስጧ እነዛ ጥንዶች ከአይኗ እስኪርቁ ድረስ አይኗ አብሮ ሄደ ÂŤ ደስ ይላሉ አይደል Âť ÂŤ አንተም እያያሀቸው ነው Âť አለችው አንገቷን ቀና አድርጋ ወደ እሱ ÂŤ አዎ አይኔ ውስጥ ገቡ እንደ ድንገት እኔም እድል ኑሮኝ ይሄንን ህይወት ባየው አልኩኝ Âť መልስ ሳትሰጠው አንገቷን ደፋች እና ደረቱን ተንተረሰች   ─‌──‌   ⪊⪨  ─── ይሄን ሁለት ቀን መንቀሳቀስ ጀምሪያለሁ በደንብ ዛቪያር ካየውት 24 ሰአት ሞላኝ ከእቤት አልፎ ግቢ ውስጥ መዟዟር ጀመርኩኝ ሰአቱ እየመሸ ነው ግቢው ሰፊ እና ውብ አረንጓዴ ነው ብየቦታው ግብብዳ ጠባቂዎች አሉ ብቻዬን ስዟዟር በጓሮ በኩል ሄድኩኝ ዝም ተብዬዎች ለማየት እንድ ተለቅ ያሉ ረው ናቸው ከዚህ በፊትም አይቻቸዋለሁ  የዛቪያር አባት ናቸው ÂŤ ነይ ልጄ ወደ እዚህ Âť እንዴት አዩኝ ደንገጥ አልኩኝ እና ወደ እሳቸው ጠጋ አልኩኝ ÂŤ ቤቱ ሊበላሽ ደረሰ አይደል ባዶ ትልቅ ቤት ያለሰው ይመጣሉ  አሁን ሁሉም Âť አሉኝ ወሬያቸው የአነጋገር ለዛቸው እራሱ ደስ ይላል ከእሳቸው ራቅ ብሎ ያለው ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ ÂŤ ስምሽ ማነው Âť «ረዒፍ Âť ÂŤ ለየት ያለ ስም ነው የዛቪያር ጓደኛ ነሽ Âť ÂŤ አዎ Âť ÂŤ አላህ መጨረሻቸውን ያሳምረው እንግዲህ Âť አሉኝ ምን ያልኳቸው መስሏቸው ነው ጥያቄ ልጠይቃቸው ፈራሁ እና ዝም አልኩ እያየናት ፀሀይ አዘቀዘቀች መሸት አለ ÂŤ ብርድ መጣ መሰል እንግባ ሰላትም ደረሰ Âť አሉ ከረዥም ዝምታ ቡሀላ ተነስተው ሄዱ እኔም ተከተልኳቸው የቤቱ መግቢዪ ጋር ስንደርስ ከውጪ ወደ ውስጥ መኪና ገባ እነ ዛቪያር ናቸው ከመኪናው ወረዱ እየተሳሳቁ እና ወደ እኛ መጡ እኔ ዛቪያርን ለጥብቅ ጉዳይ ስለፈለኩት ቆሜ ጠበኩት ይቀጥላል .    .     . @rim_han .