(( مركز نور الإسلام للتعلم والتعليم ))Nur Al-Islam Center for Teaching and Learning
Open in Telegram
التعلم والتعليم
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
223
Subscribers
-124 hours
No data7 days
+830 days
Posts Archive
አል-አስማዒ ከተናገራቸው ውብ ነገሮች መካከል፦ "አንድ ወንድ በሚስቱ ላይ ያለውን ቁጣ ለ (40) ዓመታት ያህል አምቆ (ደብቆ) ለመያዝ አቅም አለው፤ ነገር ግን ለእሷ ያለውን ፍቅር ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን አውጥቶ ለማሳየት አቅም ያጣል። በአንጻሩ አንዲት ሴት ለባልዋ ያላትን ፍቅር ለ (40) ዓመታት ያህል ደብቃ ለመያዝ አቅም አላት፤ ነገር ግን በእሱ ላይ ያላትን ቁጣ ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን ደብቃ ለመያዝ አቅም ታጣለች።" 🪶
ሰዎች ሁሉ ደስታን እዚህም እዚያም ይፈልጋሉ፣ ለእሷም ልዩ ልዩ በሮችን ያንኳኳሉ፣ በእሷም ሰበብ የተለያየ መንገዶችን ይጓዛሉ፤ ከእነሱ መካከል ደስታ በሀብት ውስጥ ያለች የሚመስለው አለ፣ ከእነሱም መካከል በስሜት ፍላጎቶች (شهوات) መከተል ውስጥ ያለች የሚመስለው አለ፣ ደግሞም ከእነሱ መካከል በክብር፣ በስልጣን፣ በዝና ወይም በሕገ-ወጥ (ሀራም) ነገሮች ውስጥ ያለች የሚመስለው አለ፤ ነገር ግን ፈጽሞ አላገኟትም፣ ወደፊትም አያገኟትም፤ ምክንያቱም እነሱ እየፈለጓት ያሉት ከትክክለኛ ቦታዋ ውጭ በሆነ ስፍራ ነውና።
አዎ፣ ጊዜያዊ መዝናናትን (ደስታን) ሊያገኙ ይችላሉ፣ ነገር ግን እሷ ጊዜያዊ እንጂ ከአእምሮ ሰላም፣ ከልብ እረፍትና ከውስጥ መረጋጋት የራቀች ናት።
እውነተኛዋ ደስታ ግን፣ ለእሷ ከአንድ መንገድ በስተቀር ሌላ መንገድ የላትም፦
እሱም መለኮታዊው ራዕይ (ውሕይ) ይዞት የመጣውን መከተል ነው።
«ኢስቲግፋርን (ምሕረት መለመንን) አጥብቆ የያዘ ሰው፣ አላህ ለእሱ ከማንኛውም ጭንቀት መውጫን፣ ከማንኛውም ሃሳብም መቃለልን ያደርግለታል…»
በዚህም መሰረት ለደስታ ከራዕዩ (ከውሕዩ) መንገድ ውጭ ሌላ መንገድ የለም። በብርሃኑ የተመራና በቅኑ ጎዳናው ላይ የተጓዘ ሰው በልቡ ውስጥ መረጋጋትን፣ በነፍሱ ውስጥ ሰላምን፣ በሕይወቱም ውስጥ እርካታን ያገኛል።
ሪዝቅ... ከዱንያ አስደናቂ ነገሮች ሁሉ እጅግ አስደናቂው ነው!
እሱ በእጅህ (በቁጥጥርህ) አይደለም፤ በብልሃትህ ወይም በጥረቶችህ ብቻ የሚገኝም አይደለም። አንተ እሱን እንደምትፈልገው ሁሉ እሱም ይፈልግሃል፤ ወደ አንተም የሚመጣው በእሱ (በአላህ) ጊዜ ነው እንጂ በአንተ ጊዜ አይደለም።
ለስንቱ ደካሚና ጠንካራ ሰራተኛ ጠቦበት (አጥቶት) አላየንም! ለስንቱስ ዘንጊና ግድየለሽ የሲሳይ በሮች ሲከፈቱለት አልታዘብንም! ጉልበትና ጥንካሬ ወደ አንተ አያቀርበውም፣ ድክመትና አቅም ማጣትም ከአንተ አያርቀውም፤ ይህም ነገሩ ሁሉ በአላህ እጅ መሆኑን እንድታውቅ ነው።
💥🏠 አላህ ይዘንላችሁና፤ ልጆቻችሁ ለአቅመ-አዳም ሲደርሱ አጋቧቸው ⚡
✍ ኢብን አል-ጃውዚ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፦
✅ "አንድ ልጅ ለአቅመ-አዳም ሲቃረብ፣ አባቱ ሊያጋባው (ሊድረው) ይገባል። የሚገርመው ግን፤ አባትየው እሱ ራሱ በወጣትነቱ የነበረበትን ሁኔታ፣ ከአቅመ-አዳም መድረስ በኋላ ምን ያህል እንደተፈተነና እንደተቸገረ፣ ወይም ደግሞ (በወቅቱ) በስህተት (በወንጀል) ውስጥ ወድቆ እንደነበር እንዴት አይታወሰውም?! ልጁም ልክ እንደ እሱ መሆኑን ማወቅ አለበት።"
📚 [ተንቢሁ አን-ናኢም አል-ገምር፡ 43]
📚 ሸይኽ አል-ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦
"የወጣትነት ዘመናቸውን የረሱ አንዳንድ አባቶች፣ ልጃቸው ጋብቻን በጠየቃቸው ጊዜ፦ 'ከግንባርህ ላብ አውጥተህ (ራሰህን ችለህ) አግባ' እንደሚሉት ሰምቻለሁ።
📌 ይህ ፈፅሞ የተፈቀደ አይደለም፤ (ለማግባት) አቅሙ እያለው ልጁን ባያጋባው በእሱ ላይ ሀራም (እርም) ይሆንበታል። አባትየው አቅም እያለው ሳይድረው ከቀረ፣ ልጁ በትዕግስት ቀን (በቂያማ ዕለት) አባቱን ይሟገተዋል።"
▪️ [ፈታዋ አርካነል ኢስላም፡ (440-441)]
✅ አል-ፋሩቅ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
"ልጆቻችሁ ለአቅመ-አዳም ሲደርሱ አጋቧቸው፤ የወንጀላቸውን ሸክም (ሀጢአት) እንዳትሸከሙ።"
📚 [አህካሙን-ኒሳእ ሊ-ኢብን አል-ጃውዚ፡ 304]
ይህ መልእክት የወላጆችን ኃላፊነት በተለይም በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚከሰቱ ስሜታዊ ፈተናዎችን በሃላል መንገድ በመቅረፍ ረገድ ያለውን ሚና በግልፅ ያሳያል።
💥🏠 አላህ ይዘንላችሁና፤ ልጆቻችሁ ለአቅመ-አዳም ሲደርሱ አጋቧቸው ⚡
✍ ኢብን አል-ጃውዚ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፦
✅ "አንድ ልጅ ለአቅመ-አዳም ሲቃረብ፣ አባቱ ሊያጋባው (ሊድረው) ይገባል። የሚገርመው ግን፤ አባትየው እሱ ራሱ በወጣትነቱ የነበረበትን ሁኔታ፣ ከአቅመ-አዳም መድረስ በኋላ ምን ያህል እንደተፈተነና እንደተቸገረ፣ ወይም ደግሞ (በወቅቱ) በስህተት (በወንጀል) ውስጥ ወድቆ እንደነበር እንዴት አይታወሰውም?! ልጁም ልክ እንደ እሱ መሆኑን ማወቅ አለበት።"
📚 [ተንቢሁ አን-ናኢም አል-ገምር፡ 43]
📚 ሸይኽ አል-ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦
"የወጣትነት ዘመናቸውን የረሱ አንዳንድ አባቶች፣ ልጃቸው ጋብቻን በጠየቃቸው ጊዜ፦ 'ከግንባርህ ላብ አውጥተህ (ራሰህን ችለህ) አግባ' እንደሚሉት ሰምቻለሁ።
📌 ይህ ፈፅሞ የተፈቀደ አይደለም፤ (ለማግባት) አቅሙ እያለው ልጁን ባያጋባው በእሱ ላይ ሀራም (እርም) ይሆንበታል። አባትየው አቅም እያለው ሳይድረው ከቀረ፣ ልጁ በትዕግስት ቀን (በቂያማ ዕለት) አባቱን ይሟገተዋል።"
▪️ [ፈታዋ አርካነል ኢስላም፡ (440-441)]
✅ አል-ፋሩቅ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
"ልጆቻችሁ ለአቅመ-አዳም ሲደርሱ አጋቧቸው፤ የወንጀላቸውን ሸክም (ሀጢአት) እንዳትሸከሙ።"
📚 [አህካሙን-ኒሳእ ሊ-ኢብን አል-ጃውዚ፡ 304]
ይህ መልእክት የወላጆችን ኃላፊነት በተለይም በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚከሰቱ ስሜታዊ ፈተናዎችን በሃላል መንገድ በመቅረፍ ረገድ ያለውን ሚና በግልፅ ያሳያል።
https://t.me/merkeznurilislam
💦 ሁላችንም እናዝናለን፤ ሁላችንም ደረታችን የሚጠበብባቸው፣ ልባችን የሚከብድባቸው እና የሚያልፍብን ነገር ሁሉ የሚከብደን ወቅቶች ያጋጥሙናል። ከዚህ የሚደነቅ (ነፃ የሚሆን) ማንም የለም፤ ሀዘን የሰው ልጅ ህይወት አካል ነውና። ደካማው ብቻ ሳይሆን ጠንካራውም ያልፍበታል፤ በዚህች ምድር ላይ ያለ ማንኛውም ልብም ያውቀዋል።
ስለዚህ በሀዘንክ ጊዜ ነፍስህን ስሜቷን አትከልክላት (አትካዳት)፣ ከአቅሟ በላይም አታክብድባት። መረጋጋትን ለመሻት ጊዜ ስጣት፣ ማልቀስ ካስፈለገህም አልቅስ፣ ሃሳብና ጭንቀትህንም ወደ አላህ አምርረህ አዋይ ። ነገር ግን ሀዘን ዘላቂ መኖሪያህና የምትቀመጥበት ቤት እንዲሆን አትፍቀድለት።
ልብህ ካስፈለገው ጥቂት እዘን፣ ከዚያም ዳግም ቀና ብለህ ተነሳ! ህይወት በአንድ የህመም ቅጽበት አትቆምምና። አላህ ማንኛውንም በላእ (ፈተና) አላወረደም—ከእርሱ ጋር መውጫንና እፎይታን ያደረገ ቢሆን እንጂ፤ የማንኛውም ታጋሽ ባሪያ ነገር አልጠበበም—አላህ ከእርሱ በኋላ ስፋትንና (የልብ) ጥገናን የሰጠው ቢሆን እንጂ።
https://t.me/merkeznurilislam
🤲 የዱዓእ ( ታላቅነት እና የአላህ እገዛ
አንድ የአላህ ባሪያ፣ ዱዓእ ከእምነት (ከኢባዳ) በሮች ሁሉ ዝም ብሎ አንዲት ትንሽ በር ብቻ ሳትሆን፤ ይልቁንም ችግሮች የሚቀረፉበት እና ነገሮች የሚገሩበት (የሚቀሉበት) ከሁሉ የላቀው ትልቅ ሰበብ መሆኑን በእርግጠኝነት ማወቁ ምንኛ ታላቅ ነገር ነው! ሰዎች «ፈፅሞ አይሆንም፣ የማይቻል ነው» ብለው ያሰቡትን ስንት እና ስንት ነገር፤ አላህ እርሱን ከሚያስፈልገው እና ከተዋረደ ልብ በወጣች እውነተኛ ዱዓእ አማካኝነት እውን ሊሆን የሚችል አድርጎታል።
ልብ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን በሚያረጋግጥ እምነት (የቂን) ሲሞላ፤ ጋሬጣዎችና አስቸጋሪ ነገሮች ሁሉ በእርሱ ላይ ይቃለላሉ። ፍላጎቶችና ጉዳዮች ሁሉ የሚፈፀሙት በሰዎች ዘንድ ሳይሆን፣ ልቦችን በሚገላብጠው፣ ነገራትን ሁሉ በሚያስተናብረው እና ሰበቦችን ሁሉ በሚያገራው በአላህ ዘንድ መሆናቸውን ይረዳል ።
ስለዚህም፡ እርግጠኝነትህን (የቂንህን) ጨምር፤ ዱዓህንም አብዛ፤ በጌታህም መልካምን ጠርጥር (ጥሩ አስብ)። ቸር የሆነው አላህ ለባሪያው የዱዓእን በር ከከፈተለት፤ ዝም ብሎ በከንቱ አልከፈተውም። ነገር ግን ልቡ እንዲረጋጋና እንዲደሰት ለማድረግ፣ ከእርሱ የሆነውን አዘኔታውን እና ችሮታውን ሊያሳየው ስለፈለገ እንጂ።
🔄 ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ያጋሩት (ሼር ያድርጉት
🤲 የዱዓእ ( ታላቅነት እና የአላህ እገዛ
አንድ የአላህ ባሪያ፣ ዱዓእ ከእምነት (ከኢባዳ) በሮች ሁሉ ዝም ብሎ አንዲት ትንሽ በር ብቻ ሳትሆን፤ ይልቁንም ችግሮች የሚቀረፉበት እና ነገሮች የሚገሩበት (የሚቀሉበት) ከሁሉ የላቀው ትልቅ ሰበብ መሆኑን በእርግጠኝነት ማወቁ ምንኛ ታላቅ ነገር ነው! ሰዎች «ፈፅሞ አይሆንም፣ የማይቻል ነው» ብለው ያሰቡትን ስንት እና ስንት ነገር፤ አላህ እርሱን ከሚያስፈልገው እና ከተዋረደ ልብ በወጣች እውነተኛ ዱዓእ አማካኝነት እውን ሊሆን የሚችል አድርጎታል።
ልብ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን በሚያረጋግጥ እምነት (የቂን) ሲሞላ፤ ጋሬጣዎችና አስቸጋሪ ነገሮች ሁሉ በእርሱ ላይ ይቃለላሉ። ፍላጎቶችና ጉዳዮች ሁሉ የሚፈፀሙት በሰዎች ዘንድ ሳይሆን፣ ልቦችን በሚገላብጠው፣ ነገራትን ሁሉ በሚያስተናብረው እና ሰበቦችን ሁሉ በሚያገራው በአላህ ዘንድ መሆናቸውን ይረዳል ።
ስለዚህም፡ እርግጠኝነትህን (የቂንህን) ጨምር፤ ዱዓህንም አብዛ፤ በጌታህም መልካምን ጠርጥር (ጥሩ አስብ)። ቸር የሆነው አላህ ለባሪያው የዱዓእን በር ከከፈተለት፤ ዝም ብሎ በከንቱ አልከፈተውም። ነገር ግን ልቡ እንዲረጋጋና እንዲደሰት ለማድረግ፣ ከእርሱ የሆነውን አዘኔታውን እና ችሮታውን ሊያሳየው ስለፈለገ እንጂ።🔄 ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ያጋሩት (ሼር ያድርጉት
🤲 የዱዓእ ( ታላቅነት እና የአላህ እገዛ
አንድ የአላህ ባሪያ፣ ዱዓእ ከእምነት (ከኢባዳ) በሮች ሁሉ ዝም ብሎ አንዲት ትንሽ በር ብቻ ሳትሆን፤ ይልቁንም ችግሮች የሚቀረፉበት እና ነገሮች የሚገሩበት (የሚቀሉበት) ከሁሉ የላቀው ትልቅ ሰበብ መሆኑን በእርግጠኝነት ማወቁ ምንኛ ታላቅ ነገር ነው! ሰዎች «ፈፅሞ አይሆንም፣ የማይቻል ነው» ብለው ያሰቡትን ስንት እና ስንት ነገር፤ አላህ እርሱን ከሚያስፈልገው እና ከተዋረደ ልብ በወጣች እውነተኛ ዱዓእ አማካኝነት እውን ሊሆን የሚችል አድርጎታል።
ልብ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን በሚያረጋግጥ እምነት (የቂን) ሲሞላ፤ ጋሬጣዎችና አስቸጋሪ ነገሮች ሁሉ በእርሱ ላይ ይቃለላሉ። ፍላጎቶችና ጉዳዮች ሁሉ የሚፈፀሙት በሰዎች ዘንድ ሳይሆን፣ ልቦችን በሚገላብጠው፣ ነገራትን ሁሉ በሚያስተናብረው እና ሰበቦችን ሁሉ በሚያገራው በአላህ ዘንድ መሆናቸውን ይረዳል ።
ስለዚህም፡ እርግጠኝነትህን (የቂንህን) ጨምር፤ ዱዓህንም አብዛ፤ በጌታህም መልካምን ጠርጥር (ጥሩ አስብ)። ቸር የሆነው አላህ ለባሪያው የዱዓእን በር ከከፈተለት፤ ዝም ብሎ በከንቱ አልከፈተውም። ነገር ግን ልቡ እንዲረጋጋና እንዲደሰት ለማድረግ፣ ከእርሱ የሆነውን አዘኔታውን እና ችሮታውን ሊያሳየው ስለፈለገ እንጂ።🔄 ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ያጋሩት (ሼር ያድርጉት)
🤲 የዱዓእ ( ታላቅነት እና የአላህ እገዛ
አንድ የአላህ ባሪያ፣ ዱዓእ ከእምነት (ከኢባዳ) በሮች ሁሉ ዝም ብሎ አንዲት ትንሽ በር ብቻ ሳትሆን፤ ይልቁንም ችግሮች የሚቀረፉበት እና ነገሮች የሚገሩበት (የሚቀሉበት) ከሁሉ የላቀው ትልቅ ሰበብ መሆኑን በእርግጠኝነት ማወቁ ምንኛ ታላቅ ነገር ነው! ሰዎች «ፈፅሞ አይሆንም፣ የማይቻል ነው» ብለው ያሰቡትን ስንት እና ስንት ነገር፤ አላህ እርሱን ከሚያስፈልገው እና ከተዋረደ ልብ በወጣች እውነተኛ ዱዓእ አማካኝነት እውን ሊሆን የሚችል አድርጎታል።
ልብ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን በሚያረጋግጥ እምነት (የቂን) ሲሞላ፤ ጋሬጣዎችና አስቸጋሪ ነገሮች ሁሉ በእርሱ ላይ ይቃለላሉ። ፍላጎቶችና ጉዳዮች ሁሉ የሚፈፀሙት በሰዎች ዘንድ ሳይሆን፣ ልቦችን በሚገላብጠው፣ ነገራትን ሁሉ በሚያስተናብረው እና ሰበቦችን ሁሉ በሚያገራው በአላህ ዘንድ መሆናቸውን ይረዳል ።
ስለዚህም፡ እርግጠኝነትህን (የቂንህን) ጨምር፤ ዱዓህንም አብዛ፤ በጌታህም መልካምን ጠርጥር (ጥሩ አስብ)። ቸር የሆነው አላህ ለባሪያው የዱዓእን በር ከከፈተለት፤ ዝም ብሎ በከንቱ አልከፈተውም። ነገር ግን ልቡ እንዲረጋጋና እንዲደሰት ለማድረግ፣ ከእርሱ የሆነውን አዘኔታውን እና ችሮታውን ሊያሳየው ስለፈለገ እንጂ።🔄 ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ያጋሩት (ሼር ያድርጉት) https://t.me/merkeznurilislam
የባል ሚስት ማሰሮም ብትሆን መራራ ናት!
አል-በይሩቲ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፦
አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ለረጅም ዘመናት በትዳር አብረውኖረዋል። ነገር ግን ባለቤቱ ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር። አንድ ቀን ባለቤቱ ወደ እርሱ ቀረብ ብላ፦ “ለምን ሌላ ሚስት አታገባም? ምናልባት የምትወልድልህና ስምህን የሚያስጠራ ልጅ ታገኝ ይሆናል” አለችው።
እርሱም፦ “ሁለተኛ ሚስት ባገባ በመካከላችሁ ጠብና ፍትና (ችግር) ተፈጥሮ እኔም እረፍትና ሰላም እንዳጣ እሰጋለሁ” አላት።
እሷም፦ “በፍጹም! የፈለግከውን አግባ፤ እኔ ለእኔነቷ እታገሣታለሁ፣ ለአንተ ስልም ሁሉንም እችለዋለሁ” ስትል መለሰችለት። እርሱ ግን መጀመሪያ ላይ ንግግሯን ችላ አለው፤ እሷ ግን ደግማና ደጋግማ ወተወተችው።
በመጨረሻም አንድ ቀን ለጉዞ እየተነሳ እንዲህ አላት፦ “እነሆ ወደ ሌላ ሀገር እሄዳለሁ፤ ከዚያም አንቺን የማታውቅ፣ አንቺም የማታውቂያትን ባዕድ ሴት አግብቼ እመጣለሁ። ይህን የማደርገው በመካከላችሁ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይፈጠር ነው” አላት። እሷም፦ “ምንም ቢፈጠር በመካከላችን ጠብ ሊፈጠር አይችልም” አለችው።
ባሏም ተጓዘ፤ አላህ የሻለውን ያህል ጊዜ ከቆየ በኋላ በምስጢር ወደ ቤቱ ተመለሰ። ከመጣ በኋላም ከአንድ ክፍል ውስጥ በስውር ገባ። ይዞት የመጣው ግን ሴት ሳይሆን አንድ ትልቅ የሸክላ ማሰሮ (ጃራ) ነበር። ማሰሮዋን የሴት ቀሚስ አለበሳት፤ በሂጃብ (በጨርቅ) ሸፈናትና ልብሱ ወደ ታች እንዲወርድ አደረገው።
ከዚያም የመጀመሪያ ሚስቱን ጠርቶ፦ “እነሆ አዲሷ ሚስቴ አሁን ደርሳለች፤ በአሁኑ ሰዓት ተኝታ ስለሆነ እንዳትቀሰቅሻት፣ እረፍት ታድርግ። እኔ አሁን ወደ ስራዬ እወጣለሁ፣ በቀኑ መጨረሻም እመለሳለሁ” አላት። የክፍሉን በር ዘግቶላት ወጣ።
በቀኑ ማብቂያ ላይ ባልየው ወደ ቤቱ ሲመለስ፣ የመጀመሪያ ሚስቱ በደጃፉ ላይ ቆማ ስትረበሽና ስታለቅስ አገኛት!
ባለቤቱም፦ “ለምንድን ነው የምታለቅሽው?” ሲል ጠየቃት።
እሷም በምሬት፦ “ይህች አዲሷ ሚስትህ እኔን ሰደበችኝ፣ አናደደችኝ፣ እንዲህና እንዲያ አደረገችኝ! እኔ ግን ለአንተ ስል ታግሼ አንድም ቃል አልመለስኩላትም” ስትል ከሰሰቻት።
ባሏም፦ “በአላህ እምላለሁ! በአንቺ ላይ ይህ እንዲሆን አልፈቅድም” አላት። ከዚያም ዱላ ይዞ ወደ ክፍሉ ገባ፤ ዱላውንም አንስቶ አዲሷን “ሚስት” መታት፤ ማሰሮዋም ተሰባብራ ወደቀች!
ባሏም በመገረም፦ “ለመሆኑ የሰደበችሽ ሚስት ይህች ነበረች?!” አላት።
እሷም የተደረገውን ስታይ፦ “በሆነው ነገር አትውቀሰኝ፤ የባል ሚስት ማሰሮም ብትሆን መራራ ናት (ቀናትንና ቅናትን አትተውም)” አለች ይባላል።
📚 ምንጭ፦ [አል-ኪናሻህ ሊል-በይሩቲ — ቅጽ 2፣ ገጽ 4008]
https://t.me/merkeznurilislam
አስተማሪ እና አስገራሚ ታሪክ‼>>
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " كَانَ فِيمَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ رَجُلٌ اشْتَرَى عَقَارًا، فَوَجَدَ فِيهَا جَرَّةً مِنْ ذَهَبٍ، فَقَالَ : اشْتَرَيْتُ مِنْكَ الْأَرْضَ وَلَمْ أَشْتَرِ مِنْكَ الذَّهَبَ. فَقَالَ الرَّجُلُ : إِنَّمَا بِعْتُكَ الْأَرْضَ بِمَا فِيهَا، فَتَحَاكَمَا إِلَى رَجُلٍ، فَقَالَ : أَلَكُمَا وَلَدٌ ؟ فَقَالَ أَحَدُهُمَا : لِي غُلَامٌ. وَقَالَ الْآخَرُ : لِي جَارِيَةٌ. قَالَ : فَأَنْكِحَا الْغُلَامَ الْجَارِيَةَ، وَلْيُنْفِقَا عَلَى أَنْفُسِهِمَا مِنْهُ، وَلْيَتَصَدَّقَا ".
البخاري ومسلم
👇👇👇👇
በሚሻሻጡ ጊዜ የታማኝነታቸው ደረጃ።
አቡሁረይራ" ረደየሏሁ ዓንሁ" ባስተላለፉት ሀዲስ: ነቢዩ "ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰልም" እንድህ አሉ:
ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች,አንድሰው ነበር።
መሬት ገዛ በገዛት መሬት ውስጥ በቃ ውስጥ ያለን ወርቅ አገኘ።
ከዚያ መሬቱን ለሸጠለት ሰው ካንተ የገዛሁት መሬቱን እንጂ ወርቅ አልገዛሁም አለው።( ወርቅህን ውሰድ ማለቱ ነው)።
መሬቱን የሸጠለት ሰው እኔ መሬቱን የሸጥኩልህ በውስጧ እስካለው ጭምር ነው አለው ለገዢው ። ( ወርቁንም ጭምር ማለቱ ነው)
በዚህ ጉዳይ ለመፋረድ ወደ አንድ ሰው ሄዱ።
ያሰውም ልጆች አላችሁ አላቸው?
አንድኛው ወንድ ልጅ አለኝ አለ።
ሌላኛው ሴት ልጅ አለቺኝ አለ።
ከዚያም ሰውየው ወንዱን ልጅ እና ሴቷን ልጅ አጋቧቸው እና ይህን ወርቅ ለራሳቸውም ይጠቀሙ፣ ሶደቃም ይሰጡ ብሎ አላቸው።
ምንጭ
አልቡኻሪ" 3472/ ሙስሊም 1721"
ከዚህ ታሪክ ዋናው ቁምነገር ሻጭ እና ገዥ እንደት ያለ ጥንቃቄና ታማኝነት እንዳላቸው እንረዳለን።
እኛስ??‼
እስኪ እራሳችንን እንገምግም።
https://t.me/merkeznurilislam
ስለ ወደፊት ህይወትሽ ስጋትና ጭንቀት ሊያድርብሽ ይችላል፤ ነገር ግን የአላህን (ሱ.ወ) ይህንን ቃል ስታስተነትኒ ሁሉም በረሮ ሆኖ ይበናል፦
﴿أَلَیۡسَ ٱللَّهُ بِكَافٍ عَبۡدَهُ﴾
«አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን?» (አዝ-ዙመር: 36)
በዚህ ጊዜ ዱንያ በአላህ እጅ እንደሆነች፣ ሪዝቅ ከአላህ ብቻ እንደሚገኝ፣ እናም የወደፊት እጣ ፈንታሽ በእርሱ በብቸኛው እጅ መሆኑን በእርግጠኝነት ትረጃለሽ (የቅንነት እምነትሽም ይጨምራል)።
ስለዚህ የአላህን ውዴታ ከመፈለግ የበለጠ ታላቅ ጭንቀት በውስጥሽ አታሳድሪ፤ ምክንያቱም አንቺ አላህን ካስደሰትሺው፣ እርሱ በአንቺ ይወዳል፣ አንችንም ያስደስትሻል፣ ይበቃሻልም፣ ያበለጽግሻልም።
የጁሙዓ ኹጥባህ
✅ ርእስ: ከበአላት በኋላም በዒባዳ ላይ መጽናት አለብን።
✅ በላም በረት ራህመቶ ኑር መስጂድ የተደረገ ኹጥባ
👌በአቡ አህመድ
https://t.me/merkeznurilislam
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል)
«ከኡመቴ (ከተከታዮቼ) መካከል ቁርኣንን ልክ ወተትን እንደሚጠጡት አድርገው የሚጠጡ ሕዝቦች ይመጣሉ።»
(ሐሰን - ሶሒሕ አል-ጃሚዕ፡ 3653)
አል-ሙናዊ የሀዲሱን ትርጉም ሲያብራሩ እንዲህ አሉ፦ ስለ መልእክቱ ሳያስተነትኑና ስለ ሕግጋቱ ሳይመራመሩ በምላሶቻቸው ብቻ ያነበንቡታል (ያፈጥኑታል)። ይልቁንም ወተት በሚጠጣበት ጊዜ በጉሮሮ ላይ በፍጥነት እንደሚፈሰው ሁሉ፣ ቁርኣኑም በምላሶቻቸው ላይ እንዲሁ በፍጥነት ያልፋል (ወደ ልባቸው አይዘልቅም)።»
(ፊይዱል ቀዲር፣ 4/118)
📝 ምክር፣ ጊዜው ሳይረፍድ በፊት... 🫵
⚠️ ብዙ ትዳሮች (ቤቶች) የሚፈርሱት በድህነት ወይም በገንዘብ እጥረት ሳይሆን፣ ልብ በሚያቆስል ቃል፣ በንቀት አስተያየት ወይም ተደጋጋሚ በሆነ ቸልተኝነት ነው።
የባል ሚስቱን ማዋረድ የቤተሰብን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ ክስተት ሆኗል።
ከቤት ውጭ ከሰዎች ጋር ሲሳሳቅና ሲቀልድ ታየዋለህ፤ ነገር ግን ወደ ቤቱ ሲገባ ወደ ሌላ ሰው ይቀየራል፤ አጉረምራሚ፣ ተነካሽ፣ ሚስቱን የማያከብር፣ ይልቁንም ዋጋዋን የሚያሳንስ እና በዚህም ድርጊቱ ወንድነቱን ያስመሰከረ የሚመስለው! ❌
አይ ወንድሜ... ተጠንቀቅ!
🎀 አንዲት ሴት ስታገባ ከአባቷ ቤት የወጣችው የሚበላ ፍለጋ ተርባ ወይም የሚለበስ ፍለጋ እራቁቷን ሆና አይደለም፤ ይልቁንም የተከበረችና ንግሥት ሆና ነው የወጣችው። የመጣችው ካንተ ጋር አዲስ እስላማዊ ቤተሰብ ለመገንባት ነው።
የምትፈልገውም፦
ትኩረትንና እንክብካቤን 🌸
ውዴታንና ፍቅርን 💕
እዝነትን 🌹
ርኅራኄንና ቸርነትን 🤲
ሰላምና ደህንነትን 🛡️
እሷ የማይቻል ነገርን እየጠየቀች አይደለም... የሚንከባከባት ልብ እና ዋጋ የሚሰጣት ነፍስ (ሩሕ) ብቻ ነው የምትፈልገው።
ይህን በባሏ ቤት ካጣች፣ ቤቱ ለእሷ መተንፈሻ የሚያጣብብ ወህኒ ይሆንባታል። 🚫
👈🏻 እሷ ባዕድ (እንግዳ) አይደለችም... እሷ ሚስትህ፣ ፍቅረኛህ፣ የልጆችህ እናት እና የሕይወት አጋርህ ናት። ስለዚህ አትጨክንባት...
👶 አንተ ባል ሆይ! ልጆችህ ዝምተኞች ምስክሮች መሆናቸውን አስታውስ...
ድብደባን፣ ጩኸትን እና ውርደትን ሲያዩ፣ በልባቸው ውስጥ ፍርሃት ይሰርጻል፤ በውስጣቸውም ጥልቅ የሆነ የስነ-ልቦና ቁስል ይዘው ያድጋሉ።
እርጋታና ሰላም (ሰኪነህ) ሊሆን ይገባው የነበረው ቤት፣ በዓይኖቻቸው ፊት የዓመፅና የጠብ አደባባይ ይሆናል።
✋ ለአላህ ብዬ የምመክርህ፦
በሚስትህና በልጆችህ ላይ አላህን ፍራ! በአላህ (ሱ.ወ) ፊት አንተ ስለ እነሱ ተጠያቂ (መስኡል) ነህና።
ሚስትህና ልጆችህ አንተ በመምጣትህ እንዲደነግጡና እንዲፈሩ አታድርግ፣ ይልቁንም ባንተ መምጣት እንዲደሰቱ አድርግ።
ልጆችህ የሚኮሩብት አርአያ (ቁድዋህ) ሁን እንጂ ልባቸውን በእጅህ አትስበረው።
በአላህ ይሁንብኝ! ከእለታት አንድ ቀን ስለ አንተ “አባቴ አዛኝ ይቅርባይና ፍትሃዊ ነበር” ተብሎ ከመነገር በላይ ምን ታላቅ ክብር አለ!
ለባለቤቱ መልካም ያደረገ ሰው አላህ በዕድሜውና በቤቱ ላይ በረከትን ያወርድለታል።
በእሷ ላይ ክፉ የሰራ ግን በረከትንና የልብ ሰላምን ይነፈጋል።
♻️ ይህንን መልዕክት ለሌሎችም ያጋሩ (ሼር ያድርጉ)።
https://t.me/merkeznurilislam
🍔የስግብግብነት ጥግ🍔
ለአሽዓብ እንዲህ ብለው ጠየቁት ፦
የስግብግብነትህ (የስስትህ) ልክ ምን ያህል ነው?"
⚡እሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "ሙሽራ ሴት ስትሸኝ (ወደ ባሏ ቤት ስትሄድ) አይቼ እኔን ልታገባ የመጣች መስሎኝ ያልታሰበኝ ጊዜ የለም።
⚡ሬሳ (ጀናዛ) አይቼም የዚያ ሟች ባለቤት ለእኔ የሆነ ነገር አውርሶኝ (ኑዛዜ ትቶልኝ) ይሆን ብዬ ያላሰብኩበት ጊዜ የለም።
⚡አንድ ቀን ህፃናት ከበውኝ 'አሽዓብ ሆይ! አሽዓብ ሆይ!' እያሉ አስጨነቁኝ። እኔም ከእኔ ላይ ለማራቅ፦ 'የእገሌ ቤት እኮ ስጦታ እያደለ ነውና ፈጥናችሁ ሂዱ!' አልኳቸው። ልጆቹም ፈጥነው በሄዱ ጊዜ (በራሴ ውሸት ተሸውጄ) እውነት የተናገርኩ መሰለኝና እኔም አንድ ነገር ለማግኘት ተከትያቸው ሮጥኩ።
(ምንጭ፡ ጃምዑል ጃዋሂር ፊል ሙላሂ ወን ነዋዲር)
https://t.me/merkeznurilislam
💧የጧት መልእክት 👇👇
የአላህን የቀድሞ ውለታና ችሮታ ብታስታውስ ኖሮ፣ ምንም ነገር አትፈራም ነበር። የላቀውን ረቂቅ እዝነቱን፣ መጥፊያህ የመሰለህን መከራ ስንት ጊዜ እንዳሻገረህ፣ ከጉድለትህ ጋር እንዴት እንደሸፈነህ እና ካላሰብከው አቅጣጫ እንዴት ሲሳይህን እንደሰጠህ ብታስታውስ ኖሮ፤ ልብህ በእርግጥ ይረካ ነበር። ብቻህን እንደሆንክም ሆነህ ነገሮችህን ሁሉ እራስህ ለማስተካከል በመጨነቅ ባልተጠመድክ ነበር።
ስንት ጭንቀትን አስወገደልህ! ስንት መከራን አቀለለልህ! እናም ፈጽሞ ሳትጠብቀው ስንት ጸጋዎችን አወረደልህ! ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ፣ በሱ እዝነትና ቸርነት መከበባችንን አንዳንድ ጊዜ እንረሳዋለን፤ በዚህም ልባችንን በጭንቀትና በትክንት እንበክለዋለን።
ስለሆነም ጉዳይህን ሁሉ ለአላህ አደራ ስጥ፣ በእሱም ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑርህ፤ በጌታው የተንጠለጠለ (የተጠጋ) ልብ ፈጽሞ አይከስርምና። ዱንያ (ይህች ዓለም) ትልቁ ጭንቀትህ ከመሆን በአላህ ትጠበቃለህ ።
https://t.me/merkeznurilislam
ሚዛናዊነትና ብልህነት በማህበራዊ ህይወት
"መካከለኛና ሚዛናዊ ሁን፤ ለእያንዳንዱ ሁነታ የሚመጥነው፣ ለእያንዳንዱም ሁኔታ የሚስማማው ነገር አለና።"
ህይወት ከሁሉም ሰው ጋር በአንድ አይነት መንገድ ብቻ አትመራም፤ ይልቁንም በጥበብ፣ እያንዳንዱን ነገር በተገቢው ቦታው ላይ በማስቀመጥ እና ሰዎችንም እንደየክብራቸውና ደረጃቸው በማስተናገድ (ኢንዛሉን-ናስ መናዚለሁም) ⚖️ እንጂ።
📌 አንዳንድ ሁኔታዎች አሉ፦ ገርነት፣ ቃናነትና ልስላሴ (ሊን) ብቻ የሚስማማቸው።
📌 ሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ አሉ፦ ቁርጠኝነት፣ ግልጽነትና ጥብቅነት (ሀዝም) እንጂ ሌላ የማይበጃቸው።
📌 አንዳንድ ሰዎች አሉ፦ ለአንተ ሲሉ መስዋዕትነት ሊከፈልላቸው፣ ስህተታቸው ሊታለፍላቸውና ይቅር ሊባሉ የሚገባቸው።
📌 ሌሎች ደግሞ አሉ፦ ያንተን ጠንካራ ጎን ሊያዩ የሚገባቸው፤ መልካም ስነ-ምግባርህን እንደ ፍርሃት፣ የዋህነትህንም እንደ አቅመ-ቢስነት እንዳይተረጉሙት።
⚖️ ምክንያቱም መካከለኛና ሚዛናዊ መሆን (ኢዕቲዳል) የመብሰል ትልቁ ማረጋገጫ ሲሆን፣ ተጨባጭ መሆንም ማጋነን ከበዛበት ምናባዊ ፍጹምነት ይልቅ እውነተኛ ነው።
🌸 ደግና ሩህሩህ ሁን፤ ነገር ግን ማንም ሰው ደግነትህን ለግል ጥቅሙ እንዲበዘብዘው አትፍቀድ።
🌸 ልጋስና ቸር ሁን፤ ነገር ግን ይህ ልግስናህ በክብርህና ራስህን በማክበርህ ላይ እንዲመጣ አታድርግ።
ከመጠን ያለፈ የዋህነትንና ደግነትን ማረም ማለት ጨካኝ ወይም ራስ ወዳድ መሆን ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ለሌሎች መልካም በመዋል (ኢህሳን) እና የራስን መብትና ክብር በመጠበቅ መካከል ያለውን ሚዛን ማወቅ ማለት ነው።
https://t.me/merkeznurilislam
🪜ዛሬ ግንቦት 24/2018 ማስታወሻ‼
قال الله سبحانه وتعالى :
قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ
(ነቢዩ ሆይ!) በል፦ «የንጉሥና ሁሉ ባለቤት የሆንክ አላህ ሆይ! ለፈለከው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ...» (ሱረቱ አሊ-ዒምራን፡ 26)
የአንቀጿ ማብራሪያ (ተፍሲር)
ይህ ትዕዛዝ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን)፣ እንዲሁም በአላህ ለሚያምንና ለእውነት እጅ ለሚሰጥ እያንዳንዱ የቁርአን አንባቢ የተላለፈ ነው።
ትዕዛዙም፦ በዚህ ፍፁም እውነታ ላይ በመመስረት፣ አንደበቱን አውጥቶ ወደ አላህ (ሱ.ወ) እንዲማጸንና እንዲለምን ነው። ምክንያቱም ይህ በዚህ አጽናፈ ዓለም ውስጥ ያለ ፍፁም እውነት ሲሆን፣ አማኝም ከዚህ ውጪ ሌላ እውነትን አያውቅም።
በዚህ በተከበረው ዱዓ (ልመና) ውስጥ ያለው ዋና መልእክት የሚከተለው ነው፦
ፍፁም ባለቤትነት፦ አላህ በዚህ ዓለም ላይ ፍፁም የሆነ የሥልጣንና የንግሥና ባለቤት መሆኑን በመመስከር ለእርሱ መተናነስና መማጸን ነው። እርሱ የሥልጣን ባለቤት ብቻ ሳይሆን፣ የሥልጣን ምንጭና ራሱን ሥልጣኑን በባለቤትነት የሚገዛው እርሱው ራሱ ነው።
ሥልጣንን መለገስና መንሳት፦ ለፈለገውና ለሻው ሰው ሥልጣንን ይሰጣል፤ ከፈለገውና ከሻው ሰው ላይ ደግሞ ሥልጣንን ይገፍፋል (ይነጥቃል)። ማለትም ሥልጣን በእጁ ላይ ካለ ሰው ላይ ሙሉ በሙሉ ይወስድበታል።
ማስታወሻ፦ በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተጠቀሰው «አል-ሙልክ» (الملك) ማለት «ሥልጣን፣ ንግሥና እና የበላይነት» ማለት ነው።
https://t.me/merkeznurilislam
