en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Open in Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
193
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-530 days
Posts Archive
አጼ ዮሃንስ (1871-1889)  በራያ ሙስሊሞች ላይ የፈጸመው  አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል መለስ ብለን ስንዳስሠው...... በአከባቢው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው አህመድ ሙስጣፍ ወይም በቅጥያ ስማቸው አባ ግራጫ ማኻን በተባለ ቦታ ላይ ክርስትናን እንዲቀበሉ እና ማህበረሰቡም እንዲቀበል ማድረግ እንዳለባቸው እንዲሁም ይህን የማያደርጉ ከሆነ እንደሚገደሉ፤ ክርስትናን ከተቀበሉ ደግሞ ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም መኖር እንደሚችሉ ተነገራቸው፡፡ አባ ግራጫም ክርስትናን ለመቀበል ፍቃደኛ እንዳልሆኑና በኢስላም ላይ መሞትን እንደሚመርጡ አስታወቁ፡፡ በዚህ ግዜ የአፄ ዮሃንስ ጦር በሙስሊሞች ላይ ዘግናኝ ጥቃት አደረሰ በመጨረሻም አባግራጫ በቁጥጥር ስው ዉለው ህዝብ ፊት በህይወት እንዲቃጠሉተደረገ፡፡ የአባ ግራጫ ጀግንነት አሁን ድረስ በስፋት የሚወራና የራያ ሙስሊሞች በኢስላም እንደማይደራደሩ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በዚህ መልኩ ሙስሊሞችን ማሰቃየት ቀጠለ ቁጥሩ ጥቂት የማይባል ሙስሊም ሀይማቱን በልቡ ይዞ ክርስትናን ተቀበለ፡፡ ቀን ቀን ክርስትያን ሌሊት ደግሞ ሙስሊም በመሆን ይኖሩ ነበር፤ ክርስትያን መሆናቸዉን ለመሳየት አንገታቸው ላይ ክር እንድያስሩ በተጨማሪም የክርስትያን ስጋ እንዲበሉ ይገደዱ ነበር፡፡ ተክለጻዲቅ ሞክሪያ ሙስሊሞች የሚከተለውን ስንኝ ሲቋጥሩ እንደነበር አጼ ዮሃንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መፅሕፋቸው አስፍረዋል። ‹‹ታናሽ ታላቅ በላን ከርካ አደባባይ፤ ክርስትያን ሆይ፡ አለልብ ሥጋ ይጣፍጣል ወይ፡፡›› የአፄ ዮሃንስ የማጥመቅ ዘመቻው በቀላሉ የሚሳካ አልነበረም፤ ይህን የማጥመቅ ዘመቻ የተቃወሙ ሙስሊሞች ሰይፍ፣ጎራዴ እና ሽቶል በመታጠቅ እምነታቸውን ለመካከል ሸፈቱ፡፡ የአፄውን ጦር ፊትለፊት መጋፈጥ እንደማይችሉ ስላወቁ በድንገት አጥቅቶ የመመለስ አካሄድ በመከተል፤ አፄ ዮሃንስ ተረጋግቶ እንዳይገዛ ማድረግ ችለዋል፡፡ ይህን ራስን የመከላከል ዘመቻ በመሀመድ ቦርሼ እና አደም በይን የሚመራ ሲሆን በዉስጡም ብዙ ወጣቶች አዳራጅቶ ጨለማን ተገን በማድረግ በአፄው ወታደሮች እና አሽከሮች ላይ ጥቃት ያደርስ ነበር፡፡ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና ስቃይ ተጠናክሮ ቀጥሏል በዚህም ምክንያት ሀሼንጌ አብዛሃኛው አካባቢ ሙስሊሞች በግዳጅ እምነታቸው እንዲቀይሩ ስለተደረገ አማካይ ቦታ ላይ ቤተ ክርስትያን ለመገንባት ተወሰነ የተመረጠዉም ቦታ ፍሕራ ይባላል፡፡ ባለ 12 ምሶሶ ቤተ-ክርስተያነ ለመገንባት ተውስኖ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ አፄ ዮሃንስ በራያ ቆይታው ላይ ሀሼንጌን መኖርያው ራያ(ለም መሬት ያለው አከባቢ ማለትም ዋራባየ ፣ጋባተ…) እርሻዬ ‹‹ ሀሸንጌ ዓደይ፤ ራያ ግራተይ›› በማለት ነበር በሓሸንጌ ፋሕራ ላይ ቤተ ክርስትያን ግንብቶ ለመቆየት የወሰነው፡፡ ቤተክርስተያኑ ለማስገንባት ሙስሊሙ(በግድ ክርስትና እንዲቀበል የተደረገው) እንዲተባበረ ጥሪ ተደረገ፡፡ይህን የሰሙ መሀመድ ቦርሼ እና የትግል አጋሮቹ ይህንን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ለቤተ ክርስተያን ግንባታው ግብኣት በሚያሰባስቡት ላይ እርምጃ መውሰደ ነው፡፡ ምሶሶው በፅድ እንዲሆን ስለተፈለገ 12 ወታዶሮች ፅድ በብዛት ወደሚገኝበት ማይ ሁሴን አቀኑ፤ 12 ምሶሶ ቆርጠው መልምለው ሲያዘጋጁ ዋሉ፡፡ መሀመድ ቦርሼ እና ባልደረቦቹ በድብቅ ሲከታተሉ ስለነበረ ወታደሮቹ ስራቸዉን ጨርሰው ወደ ፋሕራ ለመመለስ በተዘጋጁበት ስዐት ጥቃት አደረሱ 12 ወታደሮችም እጁ ሰጡ፤ እጃቸው ታስረው አስራ አንዶቹ ባዘጋጁት የፅድ ግንድ እንዲታረዱ ሲወሰን አንዱ ደግሞ ወደ አፄ ዮሃንስ መልእክት ይዞ እንዲሄድ ተደረገ፡፡ ወደ አፄ ዮሃንስ የተላከው ወታደር ራያ ላይ በሰላም መኖር እንደማይችልና ቤተክርስትያኗም እንዳይሰራት አስጠንቅቀው ላኩት፡፡ ያላሰበው ሽንፈት የገጠመው አፄ ዮሃንስ ፋህራ ላይ ቤተክርስትያን መገንባት አስቸጋሪ መሆኑን በማመን ሌላ ራቅ ያለ ቦታ እንዲገነባ ወሰኑ፡፡ አመቺ ቦታ ተብሎ በታሰበው ደብሪ ላይ የመጀርያው ቤተ ክርስትያን ተገነባ፡፡ከዚህ ጥቃትብኋላ ለተወሰነ ግዜ ጥቃቱን በማቆም የራያ ሙስሊሞችን በቀላሉ ማንበርከክ የሚችልበትን መንገድመፈለግ ጀመር ለዚህ ይረዳው ዘንድ በራያ ማህበረሰብ ሰፊ ተቀባይነት ያላቸዉን ኡለሞችን በማጥቃት ህዝቡን በቀላሉ መቆጣጠር እንደሚችል በማሰብ ኡሎሞችን ለማጥቃት ወሰነ፡፡ ሀሼንጌ ላይ ተከታታይ ጥቃት ከደረሰባት ቡኋላ ፊቱን ወደ ጋባተ አዞረ፡፡ ጋባተ የሚባለው መሆኒ፣ህጂራ፣ኩከፍቶ መቻሬና በዙርያው ያለ አከባቢዎች ነው፡፡ አፄ ዮሃንስ ጋባቴን የወረረው ሶስት ግዜ ነው፤ በሶስቱም ድል ሳይቀነው ነው የተመለሰው፡፡አፄ ዮሃንስ የራያ ሙስሊሞችን በቃላሉ ማሸነፍ የሚችለው በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ኡለሞች በማጥቃት ከታቸለም ክርስትናንን እንዲቀበሉ በማድረግ እንደሆነ በማመን ኡለሞች ላይ ልዩ ቱክረት አድርጓል፡፡አፄ ዮሃንስ የራያ ዓዘቦ ሙስሊሞች በቀላሉ ሊበገሩ እንደማይችሉና በዉግያ በጣም የተካኑ መሆናቸው ስለተገነዘበ ሀሼንጌ ላይ እንዳደረገው ጦር አዝምቶ ክርስትናን እንዲቀበሉ ማድረግ የሚሳካ ስላልሆነ ወታደሮችን በመላክ በግዜው ታላቅ አሊም የነበሩት ከመላው ኢትዮጵያ ከኦሮምያ ፣ከስልጤ ፣ከአፋር፣ ከሀረር ተማሪዎች እየመጡ ሲማሩባቸው የነበሩትን የዳንዩል አዋል፣ የሸይኽ ዓሊ ዳንሳ አስተማሪ የሆኑትን ኢማም አልሙጃሂድ ጀማሉዲን አል-አኒይን (አቡዋ) በማጥቃት ተማርከው እንዲመጡ ማስደረግና በእሳቸው አማካኝነት የራያ ዓዘቦ ሙስሊሞችን ለማጥመቅ ወሰነ፡፡ ሸይኽ ጀማሉዲን አል አኒይ ላይ ልዩ ቱክረት የተደረገበት ምክንያት የሚከተሉት ናቸው። ሙስሊሞችን ማሰቃየት እና ክርስትና እንዲቀበሉ ማድረግ ባልጀመረበት ግዜ አፄ ዮሃንስ ወራባዬ ላይ ቁንቁራ ዱባርቲ በተባለው ቦታ ሰፍሮ የጦር ካምፕም አቋቁሞ ስለነበር ማህበረሰቡ ንጉሶች በሚመጡበት ግዜ የሚያደርጉትን አቀባበል ለአፄ ዮሃንስም የተለያዩ ስጦታዎችን በመስጠት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ ሸይኽ ጀማሉዲን አል አኒይ ዳጋጋ ላይ ነበሩ፤ለተከታዮቻቸውም እንዲህ አሏቸው፡ ‹‹ይህ ሰው ወደኛ መጥቷልና ስጦታ ይዛቹህ ወደርሱ ዘንዳ ሂዱ›› አፄ ዮሃንስ ስጦታዉን በመቀበል ስጦታው ይዘው የመጡ ሰዎችን ስለ ሸይኹ የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለሶስት ቀናት እንዳይንቀሳቀሱ አደረገ ይህም ያደረገበት ሸይኽ ጀማሉዲንአል-አኒይና ተከታዮቻቸው ፍራቻ እንድያድርባቸው በሚል ነበር፡፡ ሸይኽ አኒይ ባልደረቦቼ በንጉሱ ታግተው እኔ እዚህ ቁጭ ማለት አይገባኝም በማለት አንድ ሺህ ብር እና በወርቅ የተሰራ እቃ ስጦታ ይዘው ሄዱ፡፡ ይህ ስጦታ ኢንግሊዞች አፄ ቴድሮዎስን ለመግደል ሲመጡ እዚህ ቦታ ላይ ታላቅ አሊም መኖሩ ሲነገራቸው ለሸይኹ የሰጡት ስጦታ ነበር፡፡ ሸይኽ ጀማሉዲን ከአፄ ዮሃንስ ጋር ተነጋገሩ በመካከላቸው ስላለው ዝምድናም አወሩ፤ በሸይኹና በአፄ ዮሃንስ ስላለው ዝምድና ለማውቅ ፈታዋ ጀማሉዲን አል አኒይ ገፅ 117 መመልከትይቻላል፡፡ ጀማሉዲን አልነኢይ ስጦታበመስጠት አቀባበል ቢያደርጉለትም አፄው በሸይኹ ላይ ያለው ስጋት ሊቀንስ አልቻለም እንደዉም በማህበረሰቡ ያላቸዉን ተሰሚነትና ሶስት ባልደረቦቻቸውን ለማስለቀቅ ያደረጉት ጥረት እንደ ድፍረት በመቁጠሩ ለእሳቸው የነበረው አመለካከት የባሰ መጥፎ ሆነ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በሚከተሉት ምክንያት ሊሆንይችላል።

የሱና ኡለሞች በሱሪ እና በጀምዒያ ላይ ያላቸው አቋም ምን ይመስላል? ያውርዱ እና ያንብቧት!!!!!!

አጼ ዮሃንስ (1871-1889) በራያ ሙስሊሞች ላይ የፈጸመው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል መለስ ብለን ስንዳስሠው አፄ ዮሃንስ በትግራይ ክልል በማይበሀ ተንቤን በሐምሌ 5/1829 ተወለዱ፡፡ ስለ ልጅነቱ እና አስተዳደጉ መረጃዎች እምብዛም የሉም፡፡ አፄ ዮሃንስ በልጅነታቸው ድርቅ በመከሰቱ ወደ ራያ ተሰድቶ ልዩ ቦታው ሐሸንጌ የሚባል አከባቢ እንዳደገ የራያ አባቶችና በአረብኛ የተፃፉ ጽሁፎችይነገራሉ፡፡ አፄ ዮሃንስ 4ኛ በኢትዮጵያ ህዝብ ማሀል የመንግስታዊ አንድነት ስሜት እንዲፈጠር ጥረት ማድረጉ ይታወቃል፤ይህም አንድነት ሊፈጠር የሚችለው በየቀበሌው መካከል ያሉትን ቅራኔዎች በማስወገድ በመላ ሀገሪቱ አንድ ሀይማኖት እዲፀና በማድረግ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት የተዋህዶ ማህበረ መነኮሳት በኢትዮጵያ ብቸኛው ሃይማኖት ነው ተብሎ ታወጀ፡፡ ይህን እመነት ለማስፋፋት እንዲሁም እምነቱን በማይቀበሉት ላይ አሳማሚ ቅጣት እንዲቀጡ አስነገረ፡፡ ይህንን የታሪክ ፀሀፊያን እንደሚከተለው አስፈረዉታል ‹‹ ዮሃንስ 4ኛ የካራ እምነትን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋፋት ይጣደፍ ጀመር፡፡ ሁሉም ሰው ይህንን እምነት እንዲከተል፣ ትዕዛዙን የማይቀበል ቢኖር ቅጣት እንዲፈፀምበት የሚል ደንብ አወጣ፡፡ ትዕዛዙ የሚቃወሙ መሀመዳዉያን(ሙስሊሞች)፣ ባህላዊ እምነት ተከታዮች ሌሎችም የአካል ቅጣት ይፈፀምባቸው ጀመር፤ ወይንም ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ ተደረገ›› የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመርያ እስከ አሁኑ ዘመን ኢትዮጵያን በእምነት አንድ ለማድረግ የጀመረዉን ዉጥን ለማፋጠን እንዲሁም በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ ለማስፈፀም ከደሴ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ቦሩ ሜዳ ግንቦት 21 ቀን በ1870 ዓ.ል ‹‹የቦሩ ሜዳ ጉባኤ›› ተብሎ የሚታወቀው የህይማኖት ጉባኤ ተጀመረ ፡፡ በዚህም ጉባኤ የአፄ ዮሃንስ መሰረታዊ ሀሳብ በክርስትያኖች መካከል ያለዉን ልዩነት ‹‹የቅባት ተከታይ እና የፀጋ ልጅ›› የሚለዉ ተወግዶ ሁሉም ክርስትያን በተዋህዶ እንድያምን ነበር፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን በኢትዮጵያ ያሉትንሙስሊሞች በክርስትና እንዲጠመቁ በየአውራጃው ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በ1870ዓ.ልሙስሊሞች በያሉበት በጭቃ ሹም መልከኛ ወደ አቅራብያቸው ቤተክርስትያን በግድ እንዲቆርብ ተደረገ፡፡ አፄ ዮሃንስ ሙስሊሞች ላይ እጅግ በጣም የመረረ ጥላቻ ያለው እና ኢስላምን ለማጥፋት አልሞ ሲንቀሳቀስ የነበረ ፤ከላይ እንደተመለከትነው ሙስሊመችን በመግደል በማቃጠል ኢስላምን ለማጥፋት የጣረ መሪ ነበር፡፡ አፄው ራያ ሐሸንጌ ላይ እንዳደገ ይነገራል በዚህም የራያ ሙስሊሞች ሁኔታን በደንብ ያውቃል፤ ለዚህም ስልጣኑን በተቆጣጠረበት የመጀመርያ ሳምንታት የዘመተው በራያና አዘቦ ሙስሊሞች ነበር፡፡ የመጀመርያው ዘመን ዘመቻው ብዙ ሙስሊሞችን ጭፍጭፏል ዘመቻዉን ከዳር ሳያደርስ ያቋረጠው ራስ አዳል መሸፈቱን በሰማ ግዜ ትኩረቱን ወዳዛ በማድረጉ ነው፡፡የራያ ሙስሊሞች የአፄው ግፍ ገና በጧተ ነበር የተጫነባቸው፡፡ ራያ የክርስትና አገር እደነበረች እና ወደ ነበረችበት ሁኔታ መመለስ አለባት የሚል አዋጅ በማስነገር ህዝቡ እንዲገደል፣ እንዲሰደድ እና እምነቱን እንደለዉጥ አድርጓል፡፡ አፄ የሃንስ እንዲህ አለ ‹‹ ራያ አዘቦ ለረጅም አመታት የተቀደስች እና የብዙ አብተያክርስትያን መገኛ ነበረች፡፡ በአብያተ ክርስትያናቱም ብዙ ቀሳዉስቶች፣ዲያቆናት፣ሴቶች፣ወንዶች፣ህፃናት እና ትላልቆች ነበሩበት፡፡ ከረጂም ግዜያት ቡኋላ ግን ኦሮሞዎች መጥተውአንዳቸዉንም ሳያስቀሩ ገደሏቸው ምክንያቱም በእነሱ አመለካከት ሰዎችን መግደል የጀግንነት መገለጫ ነው፡፡ ክርስትያኖችን ካጠፉ ቡኋላ አብያተክርስትያንን በማቃጠል የጣኦት ማምለክያ ቦታወችን ገነቡ፡፡ራያን ለማጥቃት justification ያቀረበው ራያ ከኦሮሞዎች መምጣት በፊት ክርስትያኖች እንደነበሩ ቢሆንም ግን ከላይ እንደተመለከትነው ከኦሮሞ በፊት የነበሩ ዶብዓዎች ሙስሊሞች ነበሩ። ከመጀመርያው ጥቃት ብኋላ ራያ አዘቦን ለማጥቃት የተለያዩ ዝግጂቶቸን አደረጉ፡፡ የራያ ማህበረሰብ በቀላሉ የማይበገር፣ ማንነቱን አና ክብሩን አስጠብቆ የነበረ ማህበረሰብ እንደሆነ ስለምያውቁ የማጥመቁ ሂደት ቀላል እንደማይሆን ከወዲሁ ነበር የተገነዘበው፡፡ የወሎ ሙስሊሞችን እምነት አስለሙጠው፣ ኢስላምን አልተዉም ያለዉን ገድለው አገር ጥሎ እንዲሰደት አደርገው ፊታቸዉን ወደ ራያና አዘቦ አዘሩ፡፡ ራያን ለማጥቃት በሁለት አቅጣጫ ነበር የዘመቱት፤በማይጨው፣ሀሸንጌ፣ ኮሮም፤ ወራባያ፣ጋባተ አና በዙርያዉ ያሉትን አከባቢዎች በአፄ ዮሃንስ የሚመራዉ ጦር ተዘጋጀ፣ በቆላው በኩል ደግሞ ማለትም ጨርጨር፣ባላ፣አላማጣ፣ ዋጃ እና ቆቦ በደጃች ራስ አርኣያ የሚመራው ሰራዊት ለማጥቃት ተንቀሳቀሰ፡፡ በአፄ ዮሃንስ ሙስሊሞችን በግዳጅ ክርስትናን አንዲቀበሉ ሲያደርግያ ያልተቀበሉትን ደግሞ እንዲገደሉ ‹‹ ጋላ ይጥፋ፤ ዱሩ ይገፋ፡፡›› የሚል አዋጅ አስነገረ፡፡ በአፄ ዮሃንስ የሚመራው ሀይል ማይጨው፣መሆኒ፣ኤቦ እና በዙርያዋ ያሉትን ሙስሊሞች ክርስትናን እንዲቀበሉ አደረገ ክርስትናን አንቀበልም ያሉትን ደግሞ ተገደሉ መሳጂዶችም ወደ አብያክርስትያን ተቀየሩ፡፡ በእነዚህ አከባቢዎች የሚከላከል የታጠቀ ሀይል ባለመኖሩ አካባቢዉን በቀላሉ ተቆጣጥረው በሙስሊሞች ላይ ጭፍጨፋ አካሄዱ፡፡ መስጂዶችን እያቃጠሉ፣ ኢስላምን አንተዉም ያሉትን ደግሞ እየገደሉ ሀሸንጌ አከባቢ ደረሱ፡፡ ሀሸንጌ ላይ ሲደርሱ የማጥመቁ ሂደት እንደ ማይጨው በቀላሉ ሊሆን አልቻለም ለዚህም የሀሼንጌ እና አከባቢው ማህበረሰብ ኢስላምን እንደማይተውና ለእምነቱ መስዋእት መሆን ተቀዳሚ ምርጫው እንደሆነ አስረግጦ ተናገረ፡፡ ይህን የተረዳው አፄ ዮሃንስ በሀሼንጌ ሙስሊሞች ላይ በጣም ዘግናኝ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዘ፡፡ በሓሼንጌ ዙርያ ያሉ ሙስሊሞች ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ ተደረገባቸው፡፡ ኢስላምን አንተዉም ያሉ ሙስሊሞች እንዲገደሉ፤ ህዝቡ ፊት እስከ እንብርታቸው ድረስ እንዲዘለዘሉ ተደረገ፡፡ ከዚህ አልፎ የዓዲሽላ፣ ፋህራ፣ መንከረ ሙስሊሞች ብዙ ስቃይ አሳለፉ ሴቶቹ እና ህፃናትን ሳይቀር ቤታቸውን ጥለው ዱር ገቡ፡፡ ሙስሊሞችን ለማስፈራራት እና በቃላሉ ስነ ልቦናቸው ላይ የፍርሀት ሰሜት እንድያደርባቸው መሻይኾች እና የአገር ሽማግሌዎች ላይ በተለየ መልኩ ጥቃት ደረሰ፤ የሚወሰደው እርምጃም ህዝቡ እንዲመለከት ይደረግ ነበር፡፡ ይቀጥላል ..........

እስልምና ወይንስ ክርስትና መግደልን የሚያዘው???? ለማንኛውም መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል????

ምን አይነት አምላክ ነው በልመና እንጀራ ያደገ! ጌታችን ሆይ አንተ ከእንከን የጠራህ ነህ ጥራት ይገባህ!

ቀደምት ሙስሊሞች ለአለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ???! 1. ኻሊድ ኢብን ዘይድ ይባላል፡፡ በኬሚስትሪ ዘርፍ የተመራመረ ሙስሊም ሳይንቲስት ነው… 2.  ጃቢር ኢብን ሐያን፡፡ የኬሚስትሪ ሊቅ ለዘመናዊ ኬሚስትሪ ጠንካራ መሰረት የጣለ ሳይንቲስት ነው፡፡ በርካታ መጽሐፍት የደረሰም ምሁር ነው፡፡ በተለይ የኢን-ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ አባት ነው፡፡ 3. አል-አስመዒ፡፡- በሶስት የባዮሎጂ ትምህርቶች የተመራመረ ሳይንቲስት ነው፡፡ የእንስሳት ሳይንስ /Zoology/፣ የእፅዋት ሳይንስ /Botany/  እና የእንስሳት እርባታ ሳይንስ /Animal production/፡፡ 4.  አል-ኸዋሪዝሚ ይባላል- የሂሳብ ፕሮፌሰር እና የአል-ጀብራ (የሒሳብ ስሌት) ጥናት አባት ነው፡፡ በተጨማሪም በአስትሮኖሚ፣ በትሪጎኖሜትሪና በጂኦሜትሪ ጥናቶች የመጠቀ ሙስሊም ጠቢብ ነው፡፡ 9ኛው ክፍለ ዘመን 5. አል-ኪንዲ፡- የመጀመሪያው ተብሎ የሚገመተው ሙስሊም ፈላስፋ ነው፤ በአስትሮኖሚ  (ኦፕቲክስ) ና በፊዚክስም ድንቅ ሳይንቲስት ነው፡፡ 6. አል-ዲነዋሪ፡- በሂሳብ፣ በቋንቋና በባዮሎጂ ዘርፎች አስደናቂ ግኝቶች የነበሩት ሳይንቲስት ነው፡፡ 7. ሣቢት ኢብን ቁራ፡- በአውሮፓውያን ዘንድ ቴቤዝ በሚለው ስሙ ይታወቃል፡፡ በአስትሮኖሚና በሂሳብ ጥናቶች አንቱታን ያተረፈ ሊቅ ነው፡፡ 8. አጥ-ጦበሪ፡- በህክምና ሳይንስ፣ በህክምና ስነ-ምግባር፣ በህክምና ድርሳናትና በሂሳብ ትምህርቶች “ተዓምረኛ ነው” የተባለለት ሳይንቲስት ነው፡፡ 9. አል-ፈርጋኒ፡- የሲቪል መሃንዲስ ነው፡፡ በኤሮዳይናሚክስ ሥራዎቹ ሰዎች ተደምመውበታል፡፡ ከዳቪንቼ ስድስት መቶ ዓመታት በፊት የበረራ ሳይንስን ፈጥሮ አሳይቷል፡፡ 10. አል-ራዚ፡- በውስጥ ደዌ ህክምና ሳይንስ ለዘመናዊ ህክምና መሰረት የጣለ ዶክተር ነው፡፡ በ20 ቅፆች የተሞላ መጽሐፉ ለአውሮፓ የሰባት መቶ ዓመታት ማስተማሪያ ነበር፡፡ 10ኛው ክፍለ ዘመን 11. አል-ዘህራዊ፡- የቀዶ ህክምናን ሳይንስ በአውሮፓ የጀመረ ሳይንቲስት ነው፡፡ ህክምናን በተመለከተ ሰላሳ ቅፅ መጽሐፍ አለው፡፡ ሲሪንጅን (የሕክምና መርፌ) የፈለሰፈ ሳይንቲስትም ነው፡፡ 12. ሙሐመድ አል-ቡዝጃኒ፡- በአስትሮኖሚ፣ በአል-ጀብራና በጂኦሜትሪ ከዓይን ያውጣህ የተባለ ሊቅ ነው፡፡ 13. ኢብን አል-ሐይሠም፡- ከኒውተን በፊት የኒውተንን ሕግ የቀመረ፤ ከአንስታይን በፊት የብርሃንን ቁሳዊ ባህሪ የተናገረ በሰባት ቅፆች የፊዚክስን ፅንሰ-ሀሳቦች የነደፈ ሳይንቲስት ነው፡፡ 14. አል-ቤሩኒ፡- የሒሳብን ጥበብ የተረዳና በቀላሉ ማስረዳት የቻለ ፊት አውራሪ ጠቢብ ነው፡፡ 15. ኢብን ሲና፡- በህክምና ዘርፍ የጻፈው ግዙፍ መጽሐፍ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሱ ቃላት እንዳሉት ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ በህክምናና (መድሐኒት ቅመማ) የተባ ፈጠራ ያለው ሳይንቲስት ነው፡፡ 11ኛው ክፍለ ዘመን 16. ኢማም አል-ገዛሊ፡- የሳይንስ ሚዛን የሆኑ ሁሉ አቀፍ ተመራማሪ፡፡ 17. ኢብን ዙህር፡- በቀዶ ህክምና ሳይንቲስት ትልቅ ሥራ የሰራ ሳይንቲስት፡፡ 18. ኢብን በይጧር፡- የፋርማኮሎጂ (የመድኃኒት ምርምር) ሳይንቲስት፡፡ 19. አል-ኢድሪሲ፡- የጂኦግራፊ ሊቅ፡፡ የመጀመሪያውን ሉል (ግሎብ) የነደፈ ሰው ነው፡፡ 20.  ኢብን ባጃህ፡- የህክምና ሳይንቲስት 21. ኢብን ሪድዋን፡- የህክምና ሳይንቲስት 12ኛው ክፍለ ዘመን 22. ኢብን ጡፈይል፡- የህክምና ሳይንቲስት 23. ኢብን ዐሊ አልኪማዊ፡- የኬሚስትሪ ሊቅ 24. አል-ባግዳዲ፡- ኬሚስት፣ ሀኪምና የጂኦግራፊ ሳይንቲስት 25. አሱሪ፡- የእፅዋት ሳይንስ ተመራማሪ 13ኛው ክፍለ ዘመን 26. ነስረዲን አል-ቱሲ፡- የጂኦሜትሪ፣ የአልጀብራና የአስትሮኖሚ ሊቅ 27. ኢብኑ ነፊስ ፡- (የአናቶሚ አባት) ከዊሊያም ሀርቬ በፊት የደም ዝውውርን ያጠና ሳይንቲስት 28. ቁጥቡዲን አል-ሺራዚ፡- የአስትሮኖሚ፣ የጂኦግራፊና የሒሳብ ሊቅ 29. ኢብን አልበናህ፡- የህክምናና የሒሳብ ሊቅ 30. አቡል ፊዳ፡- የአስትሮኖሚና የሒሳብ ሊቅ 31. ኢብን ሩሽድ፡- የህክምና ሳይንቲስት 14ኛው ክፍለ ዘመን 32. ኢብን አሽ-ሻጢር፡- የአስትሮኖሚና የሒሳብ ሊቅ 33. አል-ፋሪሲ፡- የኬሚስትሪ ሊቅ ነው 34. ኢብን አል-መጅዲ፡- የሒሳብና የአስትሮኖሚ ሊቅ የኛው ዘመን ሙስሊም ወጣትስ?????

📚كتاب اعْتِقَادِ أَهْلِ السُّنَّةِ ✍الحافظ أَبِي بَكْرِ أَحْمَدَ بْنِ إِبْرَاهِيمَ الإِسْمَاعِيلِي 📚ሽም ኪታብ: ኢዕቲቃዲ ኣህሊ ሱና 🎤
📚كتاب اعْتِقَادِ أَهْلِ السُّنَّةِ ✍الحافظ أَبِي بَكْرِ أَحْمَدَ بْنِ إِبْرَاهِيمَ الإِسْمَاعِيلِي 📚ሽም ኪታብ: ኢዕቲቃዲ ኣህሊ ሱና 🎤ደርሲ ዝሃቦ: #ሸይኽ_ሙሓመድ_መኪን_ሙሓመድ በዝሒ ቕዳሕ ድምፂ:16 ➷➴➷ ናይ ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/Alikhlasderstat

t.me/Quran_Mp3_Collection 1 @mishary_rashid_al_afasi 2 @Yassen_Al_Jazairi 3 @Sheikh_Abu_Bakr_Al_Shatri 4 @Sheikh_Muhammad_Al_Luhaidan 5 @Abdulbasit_Abdussamed1 6 @Sheikh_Abdul_Rahman_Al_Sudais 7 Ali_Al_Huzaifi 8 @Khalifah_At_Tonaeijy 9  Ahmad_Al_Ajmy 10 @Sheikh_Saad_Al_Gamidi 11 Emad_Al_Mansary 12 @Abdullah_ibn_Al_Basfar 13 @Sheikh_Nasser_Al_Qatami 14 @Abdulhadi_Kanakeri 15 @Sheikh_Maher_Al_Muaiqly 16 @Sheikh_Adel_Rayan 17 @Khalil_Al_Hussary 18 @Sheikh_Muhammad_Ayyub 19 @Abdullah_Awad_Al_Juhany 20 @Abdul_Rashid_Ali_Sufi 21 @Mohamed_Siddiq_El_Minshawi 22 @Abdul_Rahman_Al_Ossi 23 @Sheikh_Saud_Al_Shuraim 24 @Yasser_Al_Dosarii 25 @Muhammad_Al_Kurdi1 26 @Fares_Abbad1 27 @Sheikh_Salah_Bukhatir 28 @Imad_Zuhair_Hafez 29 @Muhammad_AbdulKareem 30 Ahmad_Misbahi 31 @Abdulaziz_Az_Zahrani 32 @Ibrahim_Al_Asirii 33 @Abdulbosit_Qobilov1 34 @Abdullah_al_Matrood1 35 @Afzal_Rafiqov1 36  Hani_Ar_Rifai 37 @Abdullah_Ali_Jaber 38 @Sheikh_Muhammad_Jibril 39 Jazza_Alswaileh 40 Bandar_Balila 41 @Mohammad_Al_Tablawi 42 Wadee_Al_Yamani 43 @Ghassan_Al_Shorbajyi 44  Zaki_Dagistan 45 Ahmad_Al_Lahdan 46 @Abdullah_Xalif 47 @Yasser_Al_Qureshi 48  Nabil_Al_Rifai 49  Salah_Al_Hashem 50  Shirazad_Taher 51 @Tawfeeq_As_Sayeghh 52  Rashid_Al_Arkani 53 @Sheikh_Mustafa_Ismail 54  Ali_Yakupov 55 Abdullah_Kamel 56 @Mahmud_Ali_Albanna 57 @Sheikh_Idris_Abkar 58  Hassen_Saleh 59  Moeedh_Al_Harthi 60  Ahmed_Naina 61  Waleed_Al_Naehi 62 Saber_AbdulHakam 63 @Mohammad_Saleh_Shah 64 @AbdulMuhsin_Qasim 65 Salah_Al_Budair 66  Akram_Alalaqimy 67  Jamaan_Alosaimii 68 @Abdulmohsen_Harty 69 @Abdul_Wadood_Haneef 70 @Mohammad_Al_Abdullah 71  Yahya_Hawwa 72 @Hasanxon_Yahyo_Abdulmajid 73 Khalid_Al_Jaleel 74 @Noreen_Muhammad_Siddique 75 @Ahmad_Al_Shalabii 76 @Alzain_Muhammad_Ahmad 77 @Abdulmohsin_Al_Obeikan 78 @Ibrahim_AlAkhdar 79 @Rahmatulloh_qori_Obidov 80 @Muhammadloiq_qori_Aminov 81 @Shayx_Alijon_qori_Haydarov 82 @sheikh_badr_alturki © @Quran_Mp3_Collection

አደጋ‼ **** ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን ሐፊዞሁላህ እንዲህ ይላሉ: – · "አንዳንዶች እንደሚሉት ~ ' ዛሬ ዘመኑ ተቀይሯል፤ ~ በቁርአን እና በሱንና ማስተዳደር ዘመን ያለፈበት ነው፤ ~ ዛሬ ያለንበት ጊዜ ለዘመኑ የሚበጅ አስተዳደር ማቅረብ ያስፈልጋል፤ …' በማለት የሞገተ ሰው ይሄ ከኢስላም ሃይማኖት ማፈንገጥ ነው (ከእስልምና መውጣት ነው!!)" · [ሸርሑ ነዋቂዲል ኢስላም: 111]

+1
خطبةالجمعة بعنوان (فضل الصحابة).m4a59.66 MB

لروم الصراط المستقيم.m4a68.34 MB

+2
Ustaz idris Daqwa Qafar Afat

تفسير الأنعام125__135 (1).m4a82.07 MB

تفسير الأنعام 116__124.m4a106.03 MB

تفسير الأنعام 109__115.m4a122.89 MB

تفسير الأنعام97__108.m4a121.07 MB

تفسير الأنعا 91_96 (1).m4a85.79 MB

تفسبر الأنعام 84__90.m4a74.44 MB

تفسير الأنعام71__83.m4a48.93 MB