✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Open in Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
193
Subscribers
-224 hours
-47 days
-630 days
Posts Archive
Repost from የወሎ ከዋክብት መናገሻ
አደራ ይነበብልን‼️‼️
👉ለመላዉ የሱና ወንድምና እህቶች የተላለፈ አስቸኳይ መልእክት‼️‼️
በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በ 05 ቀበሌ ጨፌ ላይ የሚገኙ የሱና ወንድሞቻችን ለብዙ አመታት በመስጂድ እጦት እየተሰቃዩ ይገኛሉ‼️
ከዚህ ቀደም አንድ ትልቅ አዛዉንት አባት ሞተዉ ዉሀቢያ ስለሆነ አንቀብርም የቀበረም ከእድር ወይም ከቅሬ ይባረራል በመባሉ ሬሳዉ ተጋድሞ የሚቀብረዉ ሲያጣ የወንድሞቻችን ልብ ክፉኛ ተሰብሮ የነበረ ቢሆንም ከሀይቅ፣ ከዉጫሌና ከአጎራባች አካባቢዎች ወንድሞች መጥተዉ በርካታ ጀመአ በተገኘበት ሊቀበር ችሏል። ጨፌ ላይ ከዚህም የከፋ ብዙ ብዙ ግፍ እንዳለ የአይን ምስክሮች ነን‼️
በዚህም መሰረት የጨፌ ወንድሞቻችን ከ3 አመታት በላይ ቤት ተከራይተዉ እየሰገዱም እየቀሩም ይገኛሉ‼️
አሁን ላይ ግን የቤት ኪራይ መክፈሉም እያዳገታቸዉ ስለሆነና ቋሚ የራሳቸዉ የሆነ መስጂድ መገንባት የግድ ስለሆነባቸዉ ከቦታ ግዢ ጀምሮ: ለመስጂዱ ግንባታ የሚዉል ገንዘብ ለማሰባሰብ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን አግዙን አሏህ ያግዛችሗል በማለት ወደ ሚዲያ ብቅ ብለዋል‼️
ለጊዜዉ ግንባታዉ የማይቻል ወይም ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ ቢያንስ ቦታዉን ብቻ ግዙልንና የራሳችን የሆነ ቦታ ካገኘን በሸራም ጋርደን ቢሆን እንሰግዳለን በማለት ተማፅነዋል‼️
📌በመሆኑም
የወንድሞቻችን ስቃይና ችግር የእኛም ችግር ነዉና ከ10 ብር ጀምሮ በገንዘብም፤ በሀሳብም፤ ፅሁፉን ሼር በማድረግም፤ አህለል ኸይሮችን በማስተባበርም እንተባባራቸዉ ዘንድ ጥሪ እናደርጋለን‼️‼️
⚡️ኢንሻአሏህ
እኛ እያለን ወንድሞቻችን ኪራይ ቤት ዉስጥ ረመዷንን አያሳልፉም‼️
👉የቻናል ባለቤቶች በየቻናላችሁ ሼር በማድረግ ትብብር አድርጉላቸዉ‼️‼️
♨️ለዚሁ አላማ ብቻ የሚዉል
✍በሸይኽ ሙሀመድ ነጂብ ጀማል
✍በወንድም ሙርሰል/አንሷር ሰይድ ሀሰን
✍በወንድም አወል ተሾመ ኢብራሂም ፈራሚነት በጨፌ አቅሷ መስጂድ ስም የተከፈቱ የባንክ አካዉንቶች
1 ♦️ሂጅራ ባንክ 👉1009061860001
2 ♦️ንግድ ባንክ 👉1000741733866
3 ♦️ዘምዘም ባንክ 👉0075749220101
📌ለዚሁ አላማ ብቻ የተከፈተ የቴሌግራም ግሩፕ
t.me/Yechefemesjidginbata
كيف نستقبل رمضان
ረመዳንን እንዴት እንቀበል ?
ቀደም ሲል በመርከዝ አልኢማም አሕመድ ለተማሪዎች የተሰጠ ምክር
25 ደቂቃ ያህል ነው
ሙሐመድሲራጅ ሙ-ኑር
https://t.me/msirage4
"የመልካም ስራ ምንዳዎችን ያልተገነዘበ እና ያልተረዳ ሁሌም ተግባሮችን መፈፀም ይከብደዋል።"
ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁሏህ
(ኢኽቲያር አልአውላ ገፅ 23)
ኢማሙ አልሙንዚረይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"ጠቃሚ እውቀትን ፅፎ የሚያሰራጭ፦
ለርሱም ሆነ ለአንባቢያን
ወይም ኮፒ አድርጎ ላስተላለፉት
ወይም ለተገበሩት በሙሉ ፅሑፉ እስካለ መልካም ምንዳ ያስገኝለቸዋል።"
[አተርጊብ ወተርሂብ (1/65)]
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
በነገራችን ላይ…ዛሬ ላይ የሰዎችን ማንነትና ሥነምግባር መስጂድ አካባቢ አትፈልጉ። እዉጭ በልብስና በአካላቸው ላይ በሚያንፀባርቁት ሁኔታቸው ላይም አትፈልጉ። ሶላትና ፆማቸው ዉስጥም አትፈልጉ።
ባይሆን በንግድ ቦታዎች አካባቢ እምነት ያላቸው ስለመሆኑ፣ አደራ ሲሰጧቸው ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በብድርና ዕዳ በጊዜ የሚመልሱ መሆናቸዉን፣ በዝምድና የሚቀጥሉ መሆናቸዉን፣ ዉርስ በሚከፋፈልበት ጊዜ ፍትሃዊ መሆናቸዉን ..በነኚህ ቦታዎች ላይ ይመልከቱ። በርግጥም እዚህ አካባቢ ተፈትነው ካለፉ -ኢንሻ አላህ-ኢማን ያላቸው ጥሩ ሰዎች ናቸው።
ሰው ከንቱ;…………
ሲታይ ከማያምር ፈሳሽ ይፈጠራል
በሆዱ ሰገራ ተሸክሞ ይዞራል
ነገም ይሞትና ጀናዛው ይገማል
እንዴት በዚህ መሃል………
ውበት አለኝ ብሎ በመልኩ ይኮራል??
منقول
«ቀባሪህ ይበዛል»
-----------------------
ምድር ላይ ሁሌ መልካም ብትሆንም፡
ሞት ካልመጣ በቀር አትመሰገንም፡
ህመም ስቃይህን የማያዳምጡ፡
ችግር ሰቆቃህን ለማየት ያልመጡ፡
ግፍ የፈፀሙብህ የዛን ቀን አያፍሩም፡
ከሩቅ ይመጣሉ ለቀብርህ አይቀሩም፡
ለሞት ያብቃህ እንጂ አፈር ያቀምሱሀል፡
ስለማትመለስ ሁሉም ይሸኙሀል፡
------------------------------
እድገትህን አይተው ደስ የማይሰኙ፡
በደስታህ ጊዜ ወደው ያልተገኙ፡
አገኘህ ስትባል ሁሌ እሚመቀኙ፡
አንተ ስትደሰት ብሶት የሚቀኙ፡
ሰወች ሲሸከሙህ ስትባል ሬሳ፡
ሁሉም ሰው ይመጣል ዝናህን ሊያነሳ፡
------------------------------
ተቀብረህ ከቀረህ እድገትህ ካቆመ፡
ጠላት ወዳጂህ ነው ኑሮህ ካከተመ፡
ቀኑን አመቻችቶ ነድፎ ፕሮፖዞል፡
ሞተ ሲባል ጊዜ ቀባሪህ ይበዛል ።
አብሮህ ላለመሆን ፈልጎ ሁሌም
ስህተቶችህን የሚለቅም ሰው እንዳለ ሁሉ..
ከአንተ ላለመለየት ሲል ብቻ ዘወትር
ስህተቶችህን እያየ ዝም ሳይልክ የሚመክርህም ሰው እንዳለ አትዘኝጋ
🔹ታድያ አንደ እነዚህ ያሉ ወለላ ልቦችን ያብዛልና።
ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"ንግግር በዕውቀትና በፍትህ ሲሆን አላህ ይወዳል። ሁሉንም ሰው የሚገባውን መብት መስጠት እና በደረጃቸው ልክ ማስቀመጥ እንዲሁ።"
(አልፈታዋ 12/205)
ስለዚህ ለአስገዳጅ ጉዳይ የሚፈፀሙ ነገሮች ከቢድዐ ፅንሰ-ሀሳብ ጋር ተጨፍልቀው አይታዩም። ምናልባት ለአንዳንዶች ዶሩራው አይታያቸው ይሆናል። እልፍ አእላፍ የቲሞችን መርዳት፣ ሙስሊሞች ደካማ በሆኑባቸው አካባቢዎች መስጂዶችን መገንባት፣ መሰናክል በሚበዙባቸው በተለይም ሙስሊም ባልሆኑ ሃገራት በፈቃድ ስር ሆኖ ማስተማር፣ በግለሰቦች ጥረት ለማቋቋም የሚከብዱ በድርቅ፣ በጎርፍ፣ በጦርነት የተጎዱ ወገኖችን መደጎም፣ … በግለሰብ ደረጃ የሚሞከሩ ስራዎች አይደሉም። እነዚህ ሃላፊነቶች የነፍስ-ወከፍ ግዴታ ባይሆኑም አማራጭ እስካለ ድረስ ችላ ቢባሉ ሙስሊሞች እንዳለ ተጠያቂ የሚሆኑባቸው ፈርዶል ኪፋያ ናቸው። ከፊሎች በህግ ጥላ ስር ሆነው ካልሰሯቸው በምን መልኩ ሊፈፀሙ ይችላሉ?! ጉዳዩን ከሰፈር አጀንዳ አውጥቶ አርቆ መመልከት ይበጃል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዕባን ዐ6/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
እውን ጀምዒያ ቢድዐ ነችን?
~
ጀምዒያን የሚያወግዙ፣ አልፈውም ይፈቀዳል የሚሉ አካላትን በቢድዐ የሚፈርጁ ወገኖች የተቃውሟቸው አንዱ መነሻ "ጀምዒያ ቢድዐ ነው" የሚል ነው። ለዚህም ማጠናከሪያ ይሆናቸው ዘንድ “ጀምዒያን ሰለፎች ያውቋታል ወይ?” የሚል ተቃውሞ አዘል ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲያነሱ ይስተዋላሉ። ለዚህ ተቃውሞ የሚነሳው ምላሽ እንደሚከተለው ነው፦
1ኛ፦ ዒባዳና መዳረሻ የተለያዩ ናቸው!
ጀምዒያኮ ዒባዳ አይደለም። ዒባዳ ካልሆነ በምን ሂሳብ ነው ከቢድዐ ጋር የሚገናኘው? የነዚህ ወንድሞች የተቃውሞ መነሻ መዳረሻንና ዒባዳን ከማቀላቀል የመጣ ነው። ሸሪዐዊ ግቦችን ለማሳካት የሚውሉ መዳረሻዎችን በአምልኮት መልክ ከሚፈፀሙ ቢድዐዎች ለይቶ ማየት ያስፈልጋል። ሺሃቡዲን አልቀራፊይ እንዲህ ይላሉ፡-
“እወቅ! መዳረሻዎች ሊዝዘጉ ግዴታ የሚሆንበት ቦታ እንዳለ ሁሉ ሊከፈቱ ግዴታ የሚሆንበትም አለ። የሚጠላበት፣ የሚወደድበትና የሚፈቀድበትም እንዲሁ። … ወደ ሐራም የሚያደርስ መዳረሻ ሐራም እንደሆነው ሁሉ ወደ ዋጂብ የሚያደርሰው ደግሞ ዋጂብ ነው። … የአሕካም መደቦች ለሁለት ይከፈላሉ። (አንዱ) ግቦች ናቸው። እነሱም በራሳቸው ጥቅሞችንና ጉዳቶችን ያካተቱ ናቸው። (ሌላኛው) መዳረሻዎች ናቸው። እነሱ ወደ ግቦች የሚያደርሱ ናቸው። ብይናቸውም (ጫፍ ላይ) የሚያደርሱት ነገር የክልከላ ወይም የፍቁድነት ብይን ነው፣ ምንም እንኳን ደረጃቸው ከግቦች ብይን ዝቅ ያለ ቢሆንም። ወደ ላቁ ግቦች የሚያደርሱ መዳረሻዎች የላቁ መዳረሻዎች ናቸው። ወደ መጥፎ ግቦች የሚያደርሱ መዳረሻዎች መጥፎ መዳረሻዎች ናቸው። ወደ መካከለኛ ግቦች የሚያደርሱ ደግሞ መካከለኛ ናቸው።” [ሸርሑ ተንቂሒል ፉሱል፡ 449]
2ኛ፦ ጃሚዐስ (ዩኒቨሲቲስ) ቢድዐ ነው ወይ?
ወሳኢልም (መዳረሻ)ም ቢሆን በሰለፎች ዘመን ያልነበረ ሁሉ ቢድዐ ነው የምትሉ ከሆነ በዚህ ስሌታችሁ መሰረት ጥንት ያልነበሩ ኢስላማዊ ተቋማትም ቢድዐ ናቸው ልትሉ ይይዛችኋል። ምክንያቱም ኢስላማዊ ሸሪዐ ተመሳሳይ መነሻ ላላቸው ነገሮች የተለያዩ ብይኖችን አይሰጥም። ጃሚዓት ኢስላሚያ (ዩኒቨርሲቲዎች)፣ መዓሂድ እና መራኪዝ በሰለፎች ዘመን አልነበሩም። እነዚህ ተቋማት ቢድዐ ያልሆኑት ወሳኢል እንጂ በራሳቸው እንደ ዒባዳ ስለማይቆጠሩ ነው። “ጀምዒያ በሰለፎች ዘመን አልነበረችም” የሚለውን ሙግታችሁን እዚህ ላይ አምጡትና የሚያዋጣችሁ ከሆኑ እዩት። እነዚህን ማስተማሪያ ተቋማታ “በሰለፎች ዘመን ስላልነበሩ ቢድዐ ናቸው” የሚል አንድም አታገኙም። ስለዚህ ከስሜት ውጡና ረጋ ብላችሁ መከራከሪያ ነጥባችሁን በኢንሷፍ ፈትሹት።
3ኛ፦ የዑለማኦች ተግባራዊ ምላሽ
በጣት ከሚቆጠሩ ውጭ ሁሉም ታላላቅና ታዋቂ የሱና ዑለማኦች ጀምዒያ መመስረትን ፈቅደዋል። አስታውሱ፤ ባለፈው ጀምዒያ የመሰረቱ፣ የጀምዒያ አባል የሆኑ፣ የጀምዒያ አመራር የሆኑ የህንድ፣ የፓኪስታን፣ የአልጀሪያ፣ የግብፅ፣ የሰዑዲያ ታላላቅ ዑለማኦችን ዘርዝሬያለሁ። ከነዚህ ውስጥ ከፊሎቹ ዛሬም በህይወት አሉ። ጀምዒያ ቢድዐ ቢሆን ኖሮ እነኚህ ሁሉ ዓሊሞች በዚህ ተግባር ውስጥ አይገቡም ነበር።
4ኛ፦ የዑለማእ ቀጥተኛ የቃል ምላሽ!
ተግባራዊ አካሄዳቸው በቂ ምላሽ ቢሆንም ከዚህም አልፎ ጀምዒያ ቢድዐ እንዳልሆነ በግልፅ የተናገሩ ዓሊሞችን አጣቅሳለሁ:-
4.1. አልባኒይ፡- “መተባበር ከሸሪዐ አንፃር የሚፈለግ ነው። መዳረሻዎቹ ደግሞ ከዘመን ዘመን፣ ከቦታ ቦታ፣ ከሀገር ሀገር ሊለያዩ ይችላሉ። ስለዚህም በዚህ መሰረት የሚቋቋምን ጀምዒያ በቡድንተኝነት (ሒዝቢያ) እና በቢድዐ መወንጀል ይሄ ይጓዙበት ዘንድ ቦታ የሚሰጠው አቋም አይደለም።” [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር፡ ካሴት ቁ. 590]
4.2. ኢብኑ ዑሠይሚን፡- ጀምዒያ “ቢድዐ ነው” “አይ አይደለም” በሚሉ ወጣቶች መካከል በተነሳው ልዩነት ሳቢያ የከረረ መሰዳደብ ውስጥ እንደተደረሰ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ለሸሪዐዊ ግብ መዳረሻ የሆነ በራሱ በመዳረሻው አምልኮት ካልታሰበበት በስተቀር ችግር የለበትም” ሲሉ መልሰዋል። [መጅሙዑ ፈታዋ፡ 18/465-466]
3. ሷሊሕ አሉሐይዳን፡- “እያንዳንዱ ሰው ምንም አይነት የቢድዐነት ቦታው በሌለበት ነገሮችን ‘ቢድዐ ናቸው’ እያለ ከመሞገት ሊታቀብ ይገባል” ብለዋል። [ሸርሑ ኪታቢ ተውሒድ፡ 15ኛ መጅሊስ]
ወጣ ያለ አቋም ካንፀባረቁ በጣም ጥቂቶች ውጭ ይሄ የሁሉም ዑለማእ አቋም ነው። እንዲያውም ኋላ ላይ አቋማቸውን ከመቀየራቸው በፊት ሸይኽ ረቢዕ በጀምዒያ መስራትን የሚቃወም ከዑለማእ አንድም እንደማያወቁ እንዲህ ሲሉ ገልፀው ነበር፦
“እኔ እስከዚህ ቀኔ ድረስ [በቁርኣንና በሱና ላይ የተመሰረተ የሆነን ጥንትም ዛሬም ሙስሊሞች ባሉበት ላይ ከሆነ] #ከሰለፍዮች አንድ እንኳን ሸሪዐዊ የሆነን ማህበራዊ ስራን የሚቃወም አላውቅም። … ለነሱ በህንድ፣ በፓኪስታን፣ በባንግላዴሽና በሌሎችም ሃገራት ማህበራት አሏቸው። … አንሷሩ ሱና በግብፅና በሱዳን በህብረት የሚሰሩ ትምህርት ቤቶች፣ መስጂዶችና ሌሎችም ስራዎች አሏቸው። … የተፈቀደ የሆነን ማህበራዊ ስራን የሚዋጋ፣ የሚከለክልና ባለቤቶቹን በቢድዐ የሚገልፅ አንድም ዐሊም ወይም ሰለፊ የሆነ የዒልም ተማሪ አልሰማንም።” [ጀማዐቱን ዋሒዳህ፡ 60]
ስለዚህ በዚህ ደረጃ በዑለማእ የሚደገፍን ጉዳይ በቢድዐ መፈረጅ ልክ አይሆንም። በተለይ ደግሞ ይህንን ሰበብ አድርጎ ሰዎችን ተብዲዕ ማድረግ ማንንም ሳይሆን ራስን ነው የሚጎዳው። እና ወንድሞቻችን ሆይ! ለራሳችሁ ኣኺራ ስትሉ ድፍረታችሁን ቀነስ ብታደርጉ መልካም ነው። ያላግባብ ሰዎችን በቢድዐ መፈረጅ ቀላል ነገር እንዳይመስላችሁ። ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ “ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ከባድ ነገር ነው” ይላሉ። [አስ-ሱናህ፣ አልኸላል፡ 1/373]
5ኛ፦ በአስገዳጅ ምክንያት የሚፈፀሙ ሰበቦች በቢድዐ አይገለፁም።
አንድ ሰው፡ “እነ ኢማሙ አሕመድ በዚያ ፈተና ዘመን እንኳን ማህበርን አልተጠቀሙትም” እያለ ሲሟገት ሰምቻለሁ። “ጀምዒያን ለአስገዳጅ ሰበብ እንኳን መጠቀም አይቻልም” ነው አባባሉ። ይሄ አቋም ጀምዒያን ከሚቃወሙ ዑለማእ ራሱ አንድም የሚጋራው የለም። ምክንያቱም አስገዳጅ ችግር ካጋጠመና ምርጫ ከጠፋ የማይፈቅድ አንድም ዐሊም የለምና። እነዚህን ቀዋዒዶች አስተውሉ፦
• “ችግሮች ያልተፈቀዱ ነገሮችን ያስፈቅዳሉ።” الضرورات تبيح المحظورات
• “ግዴታ ነገር ያለሱ የማይሳካበት ነገር እሱ እራሱ ግዴታ ነው።” ما لا يتم الواجب إلا به فهو واجب
• “ሁለት ጎጂ ነገሮች ባንድ ላይ ከመጡ ጉዳቱ የቀለለውን መፈፀም ይገባል።” إرتكاب اخف المفسدتين عند التزاحم
ደግሞ የማህበር አላማ በመንግስት እውቅና ስር ሆኖ አላማን ማሳካት ነው። ይህን አሰራር የዘመናችን መንግስታት እንዲቀበሉ ጫና ያሳደረባቸው እራሱን የቻለ ምክንያት አለ። እንዲህ አይነቱ አካሄድ በቀደሙት ዘመናት የተለመደ ቀርቶ የሚሞከርም አልነበረም። እነ ኢማሙ አሕመድ “ቁርኣን ፍጡር ነው” የሚለውን ጥመት እንዲቀበሉ ሲያስገድዷቸው የነበሩት መሪዎች አልነበሩምን እንዴ?! ታዲያ “ካልተቀበላችሁ” እያሉ የሚያሰቃዩበትን ጥፋት እንዲቃወሙ ነው እንዴ ፈቃድ የሚሰጧቸው?! ሙግታችንን ምክንያታዊም ህሊናዊም ብናደርገው መልካም ነው።
ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ(ረዲየላሁ ዐንሁ)እንዴት ነበር ረመዳንን የምትቀበሉት? ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም፦
"ከእኛ አንዳችንም ቢሆን በሙስሊም ወንድሙ ላይ የጎመን ዘር ታህል ቅሬታና ቂም ይዞ የወረሃ ረመዳን ጨረቃ ለመቀበል አይደፍርም ነበር።"
ወንድማዊ ወዳጅነት ይቀጥል ዘንድ አንዳንድ ጊዜ ጥፋትን ሆን ብሎ ችላ ያለ እና ስሕተትን የደበቀ አላህ ይዘንለት።
"ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል አሉ፤ ዩሱፍም (ይህችን ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት፤ ለነሱም አልገለጣትም፤ (በልቡ)፦ እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው አለ።"
[ሱረቱ ዩሱፍ (77)]
~ ወረደ አሉ ጥምቀት!
የመውሊዱ ንጉስ የዲቢው አርበኛ፤
የቃጥባሪው ኮተት የአብሬት ዘበኛ፤
የኑርሁሴን ባሪያ የዓብዱ ሞገደኛ፤
የዳናው አገልጋይ የጫሌው ወሬኛ፤
መቃብር አምላኪው የዶሪሑ እስረኛ፤
የቢድዓው አንጋሽ የሽርኩ ምርኮኛ፤
የተውሒድ የሱና የኢስላም ፀበኛ፤
የካፊሮች ኻዲም የሙስሊም ምቀኛ፤
ኢስላምን ተቃርኖ ካፊር ለማስደሰት፤
ምንም ቢያሸረግድ እነሱ ላይወዱት፤
ምንም ቢሽለጠለጥ ላያመሰግኑት፤
እስካልገባ ድረስ ወደ እነርሱ እምነት፤
"ወለን ተርዷ" ብሏል ግባና ተመልከት፤
ያ መውሊድ አክባሪ የሆነው የቁም ሙት፤
ያ የአሕባሽ ሙሪድ ተንቀሳቃሽ ሀውልት፤
ፎጣውን አጣፍቶ ወረደ አሉ ጥምቀት፤
Abu_lmran_Alaseriy
