ወደ ኢየሱስ ደረት
Open in Telegram
Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
276
Subscribers
-124 hours
-27 days
-630 days
Posts Archive
276
Repost from N/a
ወዳጄ
❤❤❤
በሰው መሃል ቆሜ እንደሆንኩ ብቸኛ
ሰው ስለየኝ ደግሞ እንደስደተኛ
መርፌ እንደሚሻ ታሞ እንደተኛ
ሁሌም እንዳስቸኳይ እንደ ድንገተኛ
እፈልግሃለሁ የልቤ ጓደኛ
ሆዴ ሞልቶ እያለ ረክቶ ውሃ ጥሜ
ስመላለስ ደህና ሆኖም ስጋ ደሜ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ በጎልማሳ እድሜ
ሌሊቱ ስነጋ ባይህም ደጋግሜ
ስመሽም ረሃቤ ነህ በእንቅልፍ በህልሜ
ሁሉ ሞላ ስሉ ባዶ ነኝ እላለሁ
በሰርግ በድግሱም ሆኜ እከፋለሁ
ቅቤ እየተቀባሁ እጠወልጋለሁ
እየበላሁ ስጋ ዘይት እገረጠለሁ
አውሬ በሌለበት በቀን እፈራለሁ
እስካገኝህ ድረስ
እያለሁ ጠፋለሁ እንድሁ ተንቦጅቡጄ
ህያው ሆኜ እንኳን
የህወቴ እስትንፋስ አንተ ነህ ወዳጄ
ወዳጄ...
በጥዋት እነሳለሁ ላገኝህ ማልጄ
እከተልሃለሁ እኔነቴን ክጄ
ይበልጥ እጠጋሃለሁ አምኜ ፈቅጄ
ምስጥሬን እነግርሃለሁ ማህተሙን ቀድጄ
ስትመጣ አትጣኝ አላጣህም ሄጄ
አንተ ካለህ ሁሉ በእጄ ነው በደጄ
ሌላውን እንዴት ልውደድ እኔ አንተን ለምጄ?
ወዳጄ...
የነፍሴ ብርሀን ህይወት የህይወቴ
ስበረታ ሀይሌ ስደክም ብርታቴ
ስሸነፍ አፅናኜ ሳሸንፍ ጉልበቴ
ስጓዝ የእኔ መሪ ስቀመጥ እረፍቴ
በሰላም መዝሙሬ በጦርነት ቀስቴ
በቀን ጀንበሬ ነህ ስመሽ መብራቴ
የመጣው ይምጣ እንጂ አልጣህ ከፊቴ
እኔኮ ባዶ ነኝ ወዳጄ ያላንተ
ወዳጄ...
ሳለቅስ ስከፋ ታበረታኛለህ
ስታመም ስቆስል ትፈውሰኛለህ
ስጨንቀኝ ሰጠበኝ ታሳርፈኛለህ
ስደክም ስርበኝ ትመግበኛለህ
ማስተዋል ስጎለኝ ትመክረኛለህ
ስፈራና ስቸር ትሸሽገኛለህ
ከሚጠሉኝ ሁሉ ትጠብቀኛለህ
ሳጠፋ ስሳሳት ትገስፀኛለህ
አባ አትሸሸኝም ካጠገቤ አለህ
ያየኛል ወይ ስልህ አዎን ታየኛለህ
ሌላው ሌላው ከቦት
ሰላሙ ስናጋ ውስጤ የሚያርፍብህ
የልቤን ነግረህ
ለልቤ ተናግረህ እፎይ የሚልብህ
ማንም ጥግ ቢይዝ
ለኔ የሚትቀርበኝ እኔም የሚቀርብህ
የኔ ያልኩህ የኔ
ወዳጄ አንተ ነህ የተማመንኩብህ
ወዳጄ...
አብሮነት ስሰማኝ እንደሆንክ ከጎኔ
ፍክት ይላል አይቶ የማይጠግብህ አይኔ
አንተ ማለት ለኔ ሁሉ ነገሬ ነህ
ትናፍቀኛለህ አብረሄኝም ሆነህ
ወዳጄ...
እንደዝናብ ከላይ ዝነብ አረስርሰኝ
ንካኝ በእጆችህ ዳስሰኝ ዳብሰኝ
ሹክ በልልኝ ማታ ሌሊትም ቀስቅሰኝ
እንደ ድምፅህ የለም ደስ የሚያሰኝ
እቀፈኝ በክንድህ ልቆይ በደረትህ
አይንህን እያየሁ ልፈግግ በፊትህ
ጠረንህን ልስማ ልዋል ሳሸትህ
ተለጥፌ ልደር ሳልለቅ በሰውነትህ
አንተም በኔ እኔም ባንተ ውስጥ ልሰንብት
ከቅፍህ ሳልነቃ ልከርም ልሸብት
ፀሀይ እንኳን ባትወጣ ጨረቃም ባትበራ
አንተ ብርሃኔ ነህ ያለሄው ከእኔ ጋራ
ወዳጄ...
በማይጠገብ ስፍራ ባንተ ህልውና
ስንሳፈፍ እውላለሁ በሐሴት ደመና
ሳልጠጣ እረካለሁ አይቼህ ሳልቀምስ ገና
አይርበኝ ከቶ እንደበላሁ መና
መንፈስህ ይሞላል ቤቴ አይሆንም ወና
ፀሐይ አይመታኝም ጥላ ነህ ስል ቀና
ማፅናናትህ አለ ነፍሴ አትቀርም አዝና
በመገኘትህ ውስጥ ሰላም አለ ጤና
እንቢ እንቢ እላለሁ ማንም ሰው ብለኝ ና
ወዳጄ...
ይከልለኝ ፍቅርህ እንደጠል ዳምኖ
ይውደድህ ሰውነቴ በራሱ ጨክኖ
በቃኝ አይበል አፌ ጮሆ አመስግኖ
አይራቅህ ስጋዬ በአለም ዘምኖ
ያክብርህ ምላሴ በቋንቋ ተክኖ
ይጥፋ ከውስጤ ውስጥ ትዕቢቴ መንምኖ
ይግለጥህ ያሳይህ ግጥሜ ተከሽኖ
አንተ ጎልተህ ታይብኝ እኔነት ታፍኖ
ድምፅህ ይሰማብኝ ድምፄ ተሸፍኖ
ፈቃድህ ይርጋብኝ ፈቃዴ ተንኖ
መላ እኔነቴ
ሳይላካ መዝኖ ሳይቀንስ መጥኖ
ይውደድህ ወዳጄ እስከሞት ወስኖ
ብቻ አትለየኝ ያም ሆኖ ይህም ሆኖ።
❤❤❤❤
✍Alazer Teshome
276
በጣም ጠንካሮች ልንመስል እንችል ይሆናል ግን ያለመንፈስ ቅዱስ እንደኛ ያለ ደካማ ዬለም ህይወታችን የሚቀጥለው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ነው።ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አንዲት ሰአትን ብንቆይ የአጋንንታት መሣሪ ነው የምንሆነው ያለመንፈስ ቅዱስ ማገልገል አደለም ማንችለው መኖር አንችልም መንፈስ ቅዱስ በኛ ውስጥ መኖር የእኛን ህይወት ይወስናል ስለዝህ በህይወታችን ላይ መንፈስ ከሚሰራው ብላይ እንድሰራ ዕለት ዕለት recognition እንስጠው በጉዳያችን በነገራችን ላይ......
መንፈስ ቅዱስ ሆይ አንተን ለመድረክ ድምቀት ወይም ለሞቅታ አደለም ምንፈልገው በህይወታችን ውስጥ ኢየሱስን እንድታደምቅልን ነው ምንፈልገው😔
276
በጣም ጠንካሮች ልንመስል እንችል ይሆናል ግን ያለመንፈስ ቅዱስ እንደኛ ያለ ደካማ ዬለም ህይወታችን የሚቀጥለው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ነው።ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አንዲት ሰአትን ብንቆይ የአጋንንታት መሣሪ ነው የምንሆነው ያለመንፈስ ቅዱስ ማገልገል አደለም ማንችለው መኖር አንችልም መንፈስ ቅዱስ በኛ ውስጥ መኖር የእኛን ህይወት ይወስናል ስለዝህ በህይወታችን መንፈስ ከሚሰራው ብላይ እንድሰራ ዕለት ዕለት እውቅና እንስጠው በጉዳያችን በነገራችን ላይ......
መንፈስ ቅዱስ ሆይ አንተን ለመድረክ ድምቀት ወይም ለሞቅታ አደለም ምንፈልገው በህይወታችን ውስጥ ኢየሱስን እንድታደምቅልን ነው ምንፈልገው😔
276
ማን_ለምን_እየፈለገን_ነው?
#ገላትያ 4
17፤ በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ።
18፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው።
19፤ ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል።
✏️ አለም በብርቱ ትፈልገናለች፤ እግዚአብሔር በብርቱ ይፈልገናል፣
✏️ አለም ራሷ ጋር ልታስቀረን ትወዳለች
እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንድንኖር ይወዳል
✏️ አለም ፈፅማ እግዚአብሔርን ማሸነፍ ብሎም መወዳደር አትችልም፣
➤ እኛ ግን ወይ ለእግዚአብሔር አሊያም ለአለም ተሸናፊዎች እንሆናለን‼️
✏️ አለም ለምን ትፈልገናለች?
እግዚአብሔር ለምን ይፈልገናል?
✏️ በእርግጥ በዚህ ምድር ላይ ስንኖር እጅግ በጣም ብዙ ቀልባችንን የሚገዛ የምንመኘውና ሁሌም ልናገኘው የምንፈልገው ነገር አለ፣
➤ ያ ነገር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከሌለበት በህይወታችን ላይ መልካም ድርሻ አይኖረውም
✏️ አለም ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ይድኑ ዘንድ የእግ/ር ፈቃድ ሲሆን
➤ ሁሉም ወደ ዘለአለም ጥፋት እንዲሄዱ የአጥፊው ፍላጎት ነው ለዚህ ሀሳቡም ዘወትር ይተጋል፤
✏️ አጥፊውም አዳኙም በህይወታችን ለመስራት ፈቃዳችንን ይሻሉ!!
✏️ እኛ ደግሞ በደም ተገዝተናል ዋጋችንን ካላረከስን በቀር ይህን ዋጋ ከፍሎ ማንም ከአብ እጅ አይነጥቀንም
👋
✏️ እኝ በአብ ቀኝ ነው ያለነው እኛው ካልወረድን በቀር ማንም አብ ዘንድ ሄዶ ሊያወርደን አይችልም!
✏️ ይህች ከንቱ አለም በብርቱ የምትፈልገን የምትከፍልልን ዋጋ ኖሯት ሳይሆን በፈቃዳችን በምድር ላይ በህይወት ዋጋ ከፍለን እንድንቅበዘበዝ ነው፣
✏️ በብርቱ የምትፈልገን በብርቱ እንድንፈልጋት ነው የምትከተለን እንድንከተላት ነው
✏️ ሰው የእግ/ር ሲሆን እግዚ/ር ራሱ ይመራዋል የሚናገረውም የእግ/ር መሆኑን ያሳያል፣
✏️ ሰው የእግዚአብሔር ሳይሆን ሲቀር ምንም ጥያቄ የለውም የሰይጣን ነው፤ ስለዚህ ንግግሩ ኑሮው ህይወቱ የሰይጣን መሆኑን ይገልፃል፣
✏️ ከክፉ ምንጭ መልካም ውሃ ሊፈልቅ አይችልምና።
✏️ አጥፊው ወደ ህይወታችን ለእኛ ድንገትና አጋጣሚ በሆነ መንገድ አቅዶና አስቦበት ይመጣል
✏️ ማነኛውም ሰው በብርቱ የሚፈልገን ለጥቅሙ ሲል ነው እንጂ ለእኛ ጉዳይ አይደለም
✏️ ሰይጣን ወደ ህይወታችን ሲመጣ በመጀመርያ ማድረግ የሚፈልገው ነገር እግ/ርን ከውስጣችን ማውጣት ነው ይህም ከተሳካለት በቃ የራሱ ያደርገናል!
👉 "ለመልካም አይደለም" ከጊዜ በኋላ ከተፈላጊነት ወደ ፈላጊነት ህይወት እንገባለን‼️
👉 "አለም ውብ በሆኑና ጣዕም ባላቸው ነገሮች የተከበበች መርዝ ናት"!!
✏️ ሰዎች ጣፋጩን ፍለጋ ሄደው መርዟን በልተው ይሞታሉ!!
✏️ #ህይወታችንን ለምንሰጠው እንወቅ የገዛን እግዚአብሔር ከእኛ ይልቅ ለእኛ ይጠነቀቃል ከእኛ የበለጠ እኛን ይፈልገናል
✏️ የሰጠንን ሰውነት ይዘን የፈጠረውን እየበላን ያፈለቀውነሰ እየጠጣን የእርሱን አየር እየተነፈስን በምድር ላይ የራሳችን የሆነ ምንም የሌለን እኛም ባለቤት ያለን ሰዎች ነን፤
✏️ ባለቤትነቱ የእግዚአብሔር ነው ባለቤቱ ያልሆነው ደግሞ ለጥቅሙ ይፈልገናል፣
✏️ ስለዚህ ጳውሎስ በሰዎቹ ላይ እምነት የለውም በአህዛብ መካከል ነው የሚኖሩት ለገዛቸው እንዲገዙ ይፈልጋል ክርስቶስ እንዲሳልባቸው ይፈልጋል ፍላጎቱ እርሱ ነው፤......
(tesfa T)
276
የህይወቴን መልህቅ ሰሪው ተረከብከኝ
ከመንገዳገዴ ከእንቅፋት ያዳንከኝ
መንገዴን አልመርጥም ከንግዲ ብኋላ
በወደድከው ምኸራኝ ህይወቴን በሙላ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ወዳጄ ጌታዬ ኢየሱስ
መልካም እረኛዬ ኢየሱስ
ትሁቱ መምህሬ ኢየሱስ........🤲
276
ሆዳም አድርገኝ🤗
በልቼ በልቼ የማልጠግብ
እየበላው መብላቴን የምረሳ
እየጎረስኩ ሳልውጥ ሌላ የማነሳ
እኔ ነኝ እኮ ለሆዴ የምሳሳ
እባክህ ጌታዬ ለስጋዬ ሆዳም እንደሆንኩኝ
የድስት ጥርግራጋ ፈርፍሬ እንደበላሁኝ
እባክህ ጌታዬ ለቃልህ አፒታይቴን ክፈትልኝ
ምወዳትን ተስገብግቤ እንደበላው
አይኔን አፍጥጬ ሌላውን እንዳላስነካው
ሱስ ይዞኝ ሰአቴን ተብቄ እንደበላሁ
አባክህ አምላኬ
የፀሎትን አፒታይት ክፈት እልሀለው
ለሆዴ እጄን ከሩቅ ከሩቅ ከሩቅ
ወደ ትሪው አርዝሜ እንደዘረጋሁት
ለመጠቅለል 360° ጥሼ የምዝናና
አባክህ አምላኬ እንደዚያው አድርገኝ
የቃልህን አፒታይት ክፈትና
ቃልህን ተስገብግቤ የምበላ
ያልቅብኝ ይሆን እያልኩ አቀርቅሬ
ዘፍጥረትን ቁርሴ ዘፀአትን ግሞ
እንዳያንቀኝ አብዝቼ ጠጥቼ
ዘለዋዊያንን አቅርቤ በዕብራዊን አጣቅሼ
እስከ ዕራዕይ አንገቴን አድርሼ
በመንፈስ ቅዱስ ለትውልድ አግስቼ
አባክህ ልኑር ለቃልህ ሆዳም ሆኜ
በልቼ ደግሞ እንደምበላ
እየበላውም እንደሚለኝ ሌላ ሌላ
አቤቱ የቃልህን አፒታይት ከፈትልኝ
አስጠልቶት እንዳይለኝ ቧላ ቧላ
አባክህ ሆዳም አድርገኝ ለዘመናት
የቃልህን ርሀብተኛ አድርገኝና
✍Betsinat
276
🎵10 ጊዜ ባይህ🎵
🎤 : ዮሴፍ አስቻለው📌🙏
ሁል ግዜ ባገኝህ ሁል ግዜ ብርቅ ነህ
የየእለት መናዬ የቶሎቶሎ ነህ
ደረትህ ስር ምውል ወዳጄ ብትሆን
ምንም ያህል ባውቅህ ብነግርህ ምስጢሬን
አስር ግዜ ባይህ አስሬ ፈራለው
ሁል ጊዜም ባገኝህ እደነግጣለው
እንደቤተኛ ቅርብ እንደእንግዳ ብርቄ
ደጋግመህ ብትመጣ ሽር_ጉድ እላለው ወገቤን ታጥቄ
ለዮሃንስ ብትሆን አብሮ እንጀራ ቆራሽ
ደጋግሞ ስላየህ አይለምድህም ጭራሽ
በፍጥሞ ደሴት በእድሜ ፍጻሜው
ሲያገኝህ ወደቀ ልክ እንደሞተ ሰው
ውሎ አያቀልህም ትልቅ ነህ አባቴ
ሺህ አመት ብሰብክህ አይለምድህም ቤቴ
አስር ግዜ ባይህ አስሬ ፈራለው...
በአንተ ወዳጅ ተብሎ አብረሃም ቢጠራ
ለእርሱ ሳትነግረው ምንም ባትሰራ
አንድ ልጅክን ሰዋልኝ ብለህ ስትጠይቀው
አልነጋለት ብሎት የወጣው ማልዶ ነው
ጉብኝትህ ሁሌ ትኩስ ነው ይለያል
መላልሰህ ብትመጣ የክብር አቀባበል ይደረግልሃል
አስር ግዜ ባይህ....
እንደልማድህ ቤቴ ብትመጣም
እንደ ልማዴ አልቀበልህም
አንድ ዜና ነህ ግን ሁሌ ሰበር
የማትለመድ ግን ማትቀየር
ለሁሉም ሃዘን አንድ የምስራች
ለሁሉም ዝግ ደጅ ብቸኛ ከፋች
አንተ ኢየሱስ ነው ቁም ነገራችን
ደባል ማትሻ መድሃኒታችን
276
በውሎዋችን እግ/ር መልካም ነበር በክፉ እጅ አልወደቅንም አሁንም አንደበት በምስጋና ቀና ብላ ታመሰግንሀለች እግ/ር ሆይ ተመስገን🙌🙂↕️
276
መዝሙር 126
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።
² በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።
³ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።
⁴ አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።
⁵ በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።
⁶ በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።
ይህ አመት ጌታ የድል ዘንባባ የምንይዝበት አመት ይሁንልም🙏🙏🙏🙏
276
ውዶቼ አንድ ነገር ላካፍላችሁ በዚህ ምድር ላይ የሚደግፈን ማን እንደሆነ ታቃላችሁ እግ/ር ነው።ህይወታችን miserable ውስጥ ሲገባ መንፈስ ቅዱስ እንዲ ይደግፈናል አናንተ ሚገርም እኮነው በውስጣዊ ህይወታችን መንፈሳችን ያለ ልክ ሲወርድ ለካ ተሸካሚ እጅ አለ ምንም አቅም አተን ሳለን ግን መንፈስ ቅዱስ ደግፎ ያቆመናል አይዞዋችው ደጋፊ እጅ አለላችሁ ደሞ ድካማችሁን አደባባይ የማያወጣ እንደገና ጥግንግን የሚያደርግ ነው።ድካማችሁን የሚሸፍንላችሁ ጌታ አለላችሁ ስለዚህ በርቱ ምስሉ ላይ እንዳያችሁት ተደግፋችዋል አትወድቁም🤗
276
ኢየሱስ እየጠበቀህ ነው.......
በውሎዋችው ከብዙዎች ጋር ውላችዋል ተነጋግራችዋል እና ኢየሱስም አሁን ብቻችሁን ባላችሁበት እንደ አባት ድምፃችሁን ሊሰማ ጓግቶ ይጠብቃችዋል እናንተ እና እሱ በምታውቁበት ስፍራ ሚስጥር በሆነችዋ ቦታ ይጠብቃችዋል በል ተነስ ምክንያትህን ተው እግሮችህ ሲዞሩ ውለዋል ለጌታ ይንበርከኩ ለቀጣይ ጉዞ ስንቅን ትቀበላለ መንፈስህ እንዳይደርቅ በል ከቃሉ ወተት ጠጥትህ አሰላስል
ኢየሱስ ኢየጠበቀህ ነው🧎➡️🧎♂➡️
276
መባከን አደለም
ማባከንም አደለም
ከኢየሱስ እግር ስር መቆየት
ከኢየሱስ እግር ስር መሆን መባከኛችን ሳይሆን መጠገኛችን ነው።ኢየሱስ ጋር ስለሆንን በአለም ባሉት ያልገባቸው ያልሰለጠኑ ልንባል እንችላለን ኢየሱስ የሌለበት ዕውቀት፣ ቅልጥፍና ፣ብልዕግና ምንም ነው ግድ አይለንም። እኛ ከብዙ ነገር ኋላ ቀርተን ሊሆን ይችላል ነገር ግን ቀድሞ የሄደ ሁሉ መድረሻው ከፂዮን አደለም ከሲኦል እንጂ አርፍደንም ቢሆን ከሱ ጋር ይሻለናል ይበጀናል እኛ ኢየሱስ እግር ስር ያለን ለዘመናዊነት የዘገየን ብንሆንም ከዘላለማዊ ህይወት ግን አልጎደልንም
ሁሌም ከኢየሱስ እግር ስር መቆየት።
