ch
Feedback
የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

前往频道在 Telegram

በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ላይ የነቢያችንን ﷺ ሶሂህ ሐዲሶችን የምንለቅበት ይሆናል። ኢንሻ አላህ!!!

显示更多
3 574
订阅者
-124 小时
-27 天
-1430 天

数据加载中...

相似频道
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服。
标签云
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服。
进出提及
---
---
---
---
---
---
吸引订阅者
10月 '26
十月 '26
+4
在0个频道中
九月 '26
+51
在13个频道中
Get PRO
八月 '26
+75
在3个频道中
Get PRO
七月 '26
+51
在0个频道中
Get PRO
六月 '26
+61
在1个频道中
Get PRO
五月 '26
+87
在37个频道中
Get PRO
四月 '26
+73
在24个频道中
Get PRO
三月 '26
+713
在35个频道中
Get PRO
二月 '26
+545
在35个频道中
Get PRO
一月 '26
+608
在52个频道中
Get PRO
十二月 '25
+1 250
在37个频道中
Get PRO
十一月 '25
+319
在9个频道中
Get PRO
十月 '25
+213
在12个频道中
Get PRO
九月 '25
+246
在16个频道中
Get PRO
八月 '25
+145
在13个频道中
Get PRO
七月 '25
+387
在9个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
04 十月+1
03 十月0
02 十月+1
01 十月+2
频道帖子
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ ያ ጀመዓ ዐፉወን ከዚህ በኋላ ለብዙ ጊዜ ያሕል ሐዲስ መልቀቅ አልችልም። ዒልም ፍለጋ ከሚዲያው አለም ለብዙ ጊዜያት ስለምርቅ ማለት ነው። እና ከዚህ በፊት ብዙ ሐዲሶችን መልቀቄ ይታወቃል። እና ወደኋላ በመመለስ ከዚህ ጀምራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።
👇
Amharic_Hadith Amharic_Hadith የአላህ ፍቃድ ከሆነ ለወደፊቱ በተሻለ መልኩ ለመምጣት እንሞክራለን ኢንሻ አላህ!! እና ይህን ደካማ ወንድማችሁን በዱዓ አትርሱት። ባረከላሁ ፊኩም።          የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith

2
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ ያ ጀመዓ ዐፉወን ከዚህ በኋላ ለብዙ ጊዜ ያሕል ሐዲስ መልቀቅ አልችልም። ዒልም ፍለጋ ከሚዲያው አለም ለብዙ ጊዜያት ስለምርቅ ማለት ነው። እና ከዚህ በፊት ብዙ ሐዲሶችን መልቀቄ ይታወቃል። እና ወደኋላ በመመለስ ከዚህ ጀምራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። 👇 Amharic_Hadith Amharic_Hadith የአላህ ፍቃድ ከሆነ ለወደፊቱ በተሻለ መልኩ ለመምጣት እንሞክራለን ኢንሻ አላህ!! እና ይህን ደካማ ወንድማችሁን በዱዓ አትርሱት። ባረከላሁ ፊኩም።          የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
2
3
ምድርን የሞላ ምህረት ከአነስ ኢቢኑ ማሊክ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿يقولُ: قال اللهُ: يا ابنَ آدَمَ، إنَّك ما دَعَوْتَني ورجَوْتَني غفَرْتُ لك على ما كان فيك ولا أُبالي، يا ابنَ آدَمَ، لو بَلَغَتْ ذُنوبُك عَنانَ السَّماءِ ثمَّ استَغفَرْتَني غَفَرْتُ لك ولا أُبالي، يا ابنَ آدَمَ، إنَّك لو أَتَيْتَني بقُرابِ الأرضِ خَطايا ثمَّ لَقيتَني لا تُشرِكُ بي شَيئًا، لَأَتَيْتُك بقُرابِها مَغفرةً.﴾ “የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ የኣደም ልጅ ሆይ! ከለመንከኝና ከከጀልከኝ ባንተ ላይ ላለው (ወንጀል) ደንታ አይኖረኝም እምርልሃለሁ፡፡ የኣደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመናን ቢደርሱ ከዚያም ምህረትን ከጠየቅከኝ እምርልሃለሁ፡፡ የኣደም ልጅ ሆይ! አንተ ምድርን ሊሞላ የቀረበ ወንጀል ጋር ብትመጣኝ፣ ከዚያ በኔ ላይ ምንም ሳታጋራ ካገኘሀኝ እሷኑ ሊሞላ የቀረበ ምህረትን ይዤ እመጣሀለሁ፡፡” (📚ቲርሚዚ ሀሰን ብለውታል 3540)          የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
588
4
ለሰላምህ ስትል ሰላምታን አብዛ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿السلامُ اسمٌ من أسماءِ اللهِ وضَعَهُ اللهُ في الأرضِ، فأفْشُوهُ بينَكمْ، فإنَّ الرجلَ المسلمَ إذا مَرَّ بقومٍ فسلَّمَ عليهم، فردُّوا عليه؛ كان لهُ عليهم فضلُ درجةٍ بتذكيرِهِ إيّاهُمُ السلامَ، فإنْ لمْ يرُدُّوا عليه رَدَّ عليه مَنْ هوَ خيرٌ مِنهمْ وأطْيبُ﴾ “አስ-ሰላም ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ስም ነው። አላህ በምድር ላይ (ሰላምታን ትለዋወጡበት ዘንድ) አስቀምጦታል። በመሆኑም በመካከላችሁ (ሰላምታን) አብዙ። አንድ ሙስሊም ሰው በሰዎች አጠገብ ሲያልፍና ቀድሞ ሰላምታ ሲያቀርብላቸው፣ እነሱም መልስ ከሰጡት፤ ሰላምታን በማስታወሱ ብቻ በእነሱ ላይ የአንድ ደረጃ ብልጫ (ተጨማሪ ምንዳ) ያገኛል። እነሱ መልስ ካልሰጡት ግን፣ ከእነሱ የተሻለና ይበልጥ የጠራው የሆነ አካል (መላኢካ) መልስ ይመልስለታል።” (📚 ሶሂህ አልጃሚ 3697)           የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
582
5
ጁሙዓ ሰለዋት ዱዓ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾ ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁሙዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለእኔ ይቀርብልኛልና። (📚አቡ ዳውድ ሰሂህ ብለውታል: 1531) ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ، فمَن صلّى عليَّ صلاةً صلّى اللهُ عليهِ عَشرًا.﴾ በጁሙዓ ቀንና ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በእኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል። (📚ሰሂህ አልጃሚ: 1209) ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ في الجُمُعَةِ لَساعَةً، لا يُوافِقُها مُسْلِمٌ، يَسْأَلُ اللهَ خَيْرًا، إلّا أعْطاهُ إيّاهُ.﴾ በጁሙዓ ቀን አንዲት ሰዓት አለች። በዛች ሰዓት አንድ ሙስሊም አላህን መልካምን ነገር እየጠየቀ አይገጥምም፤ ለእሱ የጠየቀው የሚሰጠው ቢሆን እንጂ። (📚ሙስሊም ዘግበውታል: 852) وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ። فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَاشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡ - «سُبْحَانَ اللهِ». - «الحَمْدُ للهِ». - «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ». - «اللهُ أكْبَرُ». - «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ». - «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ». - «رَبِّ اغْفِرْ لِي وَتُبْ عَلَيَّ إنَّكَ أنْتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ».       የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
675
6
ሽበት በኢስላም ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا تَنتِفُوا الشَّيْبَ، ما مِنْ مُسْلِمٍ يَشيبُ شَيْبَةً في الإسلامِ، إلّا كانَتْ لَهُ نورًا يومَ القيامَةِ﴾ “ሽበታችሁን አትንቀሉ። አንድ ሙስሊም በኢስላም ውስጥ ሆኖ አይሸብትም በቂያማ ቀን ለእሱ ብርሃን የሚሆንለት ቢሆን እንጂ።” (📚ሶሂህ አልጃሚዕ 7463)           የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
675
7
ቢያውቁ ኖሮ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي النِّدَاءِ وَالصَّفِّ الْأَوَّلِ ثُمَّ لَمْ يَجِدُوا إِلَّا أَنْ يَسْتَهِمُوا عَلَيْهِ لَاسْتَهَمُوا﴾ “በአዛንና በመጀመሪያ ሶፍ የሚገኘውን (ምንዳ) ሰዎች ቢያውቁ ከዚያም ዕጣ ካልተጣጣሉ የማይገኝ መሆኑን ቢረዱት ኖሮ ዕጣ ይጣጣሉበት ነበር፡፡” (📚ቡኻሪ 615 ሙስሊም 437 ዘግበውታል)           የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
692
8
ሰዎችን የምታሰግድ ከሆነ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِلنَّاسِ فَلْيُخَفِّفْ ؛ فَإِنَّ مِنْهُمُ الضَّعِيفَ، وَالسَّقِيمَ، وَالْكَبِيرَ، وَإِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِنَفْسِهِ﴾ “አንዳችሁ ሰዎችን የሚያሰግድ ከሆነ ቀለል ያድርግ (አያስረዝም)። በእነሱ ውስጥ ደካማ፣ በሽተኛና ባለ ጉዳይ ይኖራልና። አንዳችሁ ለብቻው ከሰገደ ግን የፈለገውን ያህል ያስረዝም።” (📚ቡኻሪ 703 ሙስሊም 467 ዘግበውታል)        የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
753
9
ሰባት አይነት ሰዎች ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ في ظِلِّهِ، يَومَ لا ظِلَّ إلّا ظِلُّهُ: الإمامُ العادِلُ، وشابٌّ نَشَأَ في عِبادَةِ رَبِّهِ، ورَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ في المَساجِدِ، ورَجُلانِ تَحابّا في اللَّهِ اجْتَمعا عليه وتَفَرَّقا عليه، ورَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذاتُ مَنْصِبٍ وجَمالٍ، فَقالَ: إنِّي أخافُ اللَّهَ، ورَجُلٌ تَصَدَّقَ، أخْفى حتّى لا تَعْلَمَ شِمالُهُ ما تُنْفِقُ يَمِينُهُ، ورَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خالِيًا فَفاضَتْ عَيْناهُ.﴾ “ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከእሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣ ምፅዋትን (ሰደቃ) የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።" (📚ቡኻሪ 1423 ሙስሊም 1031 ዘግበውታል)    የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 355
10
ሐዲሰል ቁድሲ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿قالَ اللَّهُ عزَّ وجلَّ: إذا تَحَدَّثَ عَبْدِي بأَنْ يَعْمَلَ حَسَنَةً، فأنا أكْتُبُها له حَسَنَةً ما لَمْ يَعْمَلْ، فإذا عَمِلَها، فأنا أكْتُبُها بعَشْرِ أمْثالِها، وإذا تَحَدَّثَ بأَنْ يَعْمَلَ سَيِّئَةً، فأنا أغْفِرُها له ما لَمْ يَعْمَلْها، فإذا عَمِلَها، فأنا أكْتُبُها له بمِثْلِها﴾ “የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ ‘ባሪያዬ መልካም ስራን ለመስራት አስቦ (በሆነ ምክንያት ሳይሰራው ቢቀር) እንደ አንዲት መልካም ስራ አድርጌ እጽፍለታለሁ። ከሰራው ደግሞ በአስር እጥፍ አድርጌ እጽፍለታለሁ። መጥፎ ስራን ለመስራት አስቦ እስካልሰራው ድረስ እምርለታለሁ፤ ከሰራው ግን ልክ እንደ እርሷ አንዲትን መጥፎ ሥራ ብቻ አድርጌ እጽፍለታለሁ።’” (📚ቡኻሪ 42 ሙስሊም 129 ዘግበውታል)          የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 100
11
ድንቅ ነቢያዊ ምክር ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ومَن يَسْتَعْفِفْ يُعِفَّهُ اللَّهُ، ومَن يَسْتَغْنِ يُغْنِهِ اللَّهُ، ومَن يَتَصَبَّرْ يُصَبِّرْهُ اللَّهُ، وما أُعْطِيَ أحَدٌ عَطاءً خَيْرًا وأَوْسَعَ مِنَ الصَّبْرِ.﴾ “እራሱን ከሐራም የቆጠበ አላህ ከሐራም ይጠብቀዋል። በራሱ ለመብቃቃት ጥረት ያደረገ አላህ የሚብቃቃበትን ነገር ይሰጠዋል። ትዕግስት ለማድረግ የጣረ ትዕግስትን ይለግሰዋል። ለአንድ ሰው ከትዕግስት የተሻለና እጅግ ሰፊ የሆነ ነገር እንደተሰጠው አይነት ለማንም አልተሰጠም።” (📚ቡኻሪ 1469 ሙስሊም 1053 ዘግበውታል)        የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
934
12
ስለ ቂያማ ዕለት የተነገሩ ሐዲሶች! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ثَلَاثَةٌ لَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ: شَيْخٌ زَانٍ، وَمَلِكٌ كَذَّابٌ، وَعَائِلٌ مُسْتَكْبِرٌ﴾ “ሶስት አይነት ሰዎች በቂያማ እለት አላህ አያናግራቸውም፣ ከወንጀላቸው አያፀዳቸውም፣ ወደነሱም አይመለከትም፣ አሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። እነሱም፦ የሽማግሌ ዝሙተኛ፣ የመሪ ውሸታምና የድሃ ኩራተኛ ናቸው።” (📚ሙስሊም ዘግበውታል፡ 107)         የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
956
13
እውነተኛ መመካትን በአላህ ላይ ብትመኩ ኖሮ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لو أنَّكم توَكَّلتم على اللهِ حقَّ توَكُّلِهِ، لرزقَكم كما يرزقُ الطَّيرَ، تغدو خماصًا، وتروحُ بطانًا.﴾ “እናንተ በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነ መመካትን ብትመኩ ኖሮ ወፎችን እንደሚመግበው ይመግባችሁ ነበር። ሆዷ ባዶ ሆኖ ጠዋት ትወጣና ከሰዓት በኋላ ሆዷን ሞልታ ትመለሳለች።” (📚ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል 2344)       የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
2 510
14
ሰባት አይነት ሰዎች ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ في ظِلِّهِ، يَومَ لا ظِلَّ إلّا ظِلُّهُ: الإمامُ العادِلُ، وشابٌّ نَشَأَ في عِبادَةِ رَبِّهِ، ورَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ في المَساجِدِ، ورَجُلانِ تَحابّا في اللَّهِ اجْتَمعا عليه وتَفَرَّقا عليه، ورَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذاتُ مَنْصِبٍ وجَمالٍ، فَقالَ: إنِّي أخافُ اللَّهَ، ورَجُلٌ تَصَدَّقَ، أخْفى حتّى لا تَعْلَمَ شِمالُهُ ما تُنْفِقُ يَمِينُهُ، ورَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خالِيًا فَفاضَتْ عَيْناهُ.﴾ “ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከእሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣ ምፅዋትን (ሰደቃ) የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።" (📚ቡኻሪ 1423 ሙስሊም 1031 ዘግበውታል)           የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 673
15
አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ... ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا تَزُولُ قَدَما ابنِ آدمَ يومَ القيامةِ مِن عندِ ربِّه، حتى يُسْأَلَ عن خَمْسٍ: عن عُمُرِه فِيمَ أَفْناه؟ وعن شبابِه فِيمَ أَبْلاه؟ وعن مالِه مِن أين اكتسبه وفِيمَ أنفقه؟ وماذا عَمِل فيما عَلِم؟﴾ “የአደም ልጅ በቂያማ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንዳጠናቀቀው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።” (📚ሶሂህ አልጃሚ፡ 7299)     የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 760
16
ወንጀል ከሰሩ በኋላ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما من عبدٍ يُذنِبُ ذنبًا فيُحسِنُ الطَّهورَ ثمَّ يقومُ فيُصلِّي ثمَّ يستغفرُ اللهَ إلّا غفر اللهُ له.﴾ “አንድ ባሪያ ወንጀል በሚፈፅምበት ወቅት ውዱእ በትክክል ያድርግ፡፡ ከዚያም ሁለት ረከዓዎችን ይስገድና አላህን ምህረት ይማፀን፡፡ አላህ ምህረትን ይለግሰዋል፡፡” (📚አቡ ዳውድ 1521 ቲርሚዚ 406 ዘግበውታል)         የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 691
17
ከኩራት ተጠንቀቁ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا يَدْخُلُ الجَنَّةَ مَن كانَ في قَلْبِهِ مِثْقالُ ذَرَّةٍ مِن كِبْرٍ قالَ رَجُلٌ: إنّ الرَّجُلَ يُحِبُّ أنْ يَكونَ ثَوْبُهُ حَسَنًا ونَعْلُهُ حَسَنَةً، قالَ: إنّ اللهَ جَمِيلٌ يُحِبُّ الجَمالَ، الكِبْرُ بَطَرُ الحَقِّ، وغَمْطُ النّاسِ﴾ “በልቡ ውስጥ የሰናፍጭ ፍሬ እንኳን ኩራት ያለበት ጀነት አይገባም። አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ ሰውዬው ልብሱ ቆንጆ ጫማውም ቆንጆ እንዲሆን ይወዳል’ ይህ ከኩራት ነውን? እሳቸውም እንዲህ አሉት፦ አላህ ቆንጆ ነው ቆንጆን ነገር ይወዳል። ኩራት የሚባለው ሐቅን አለመቀበልና ሰዎችን አሳንሶ መመልከት ነው።” (📚ሙስሊም ዘግበውታል 91)      የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 727
18
የሙዓዚንነት ምንዳ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿المؤذِّنُ يُغفَرُ لهُ مدى صوتِه، ويُصدِّقُه كلُّ رَطبٍ ويابِسٍ ولهُ مثلُ أجرِ مَن صلّى معَه﴾ “ሙአዚን ድምፁ በሚደርስበት ልክ (ወንጀሉ) ይማርለታል። እርጥብም ሆነ ደረቅ ነገር ሁሉ እውነትነቱን (በቂያማ ለት) ይመሰክርለታል። ከእርሱ ጋር የሰገደም ¹ ሰው አጅር (ምንዳ) ተመሳሳዩን ያህል ያገኛል።” (📚ሶሂህ አተርጊብ፡ 234) ¹ የሰጋጆች ምንዳ እኩልነት፡ ሙአዚኑ ሰዎችን ወደ ሶላት በመጥራቱ ምክንያት መጥተው ከእርሱ ጋር የሰገዱትን ሰዎች ያህል አላህ ተመሳሳይ አጅር ይሰጠዋል። ይህ የሚሆነው የሰጋጆቹ አጅር ምንም ሳይቀነስ አላህ ከራሱ ችሮታ ለሙአዚኑ ተጨማሪ እኩል አጅር ይሰጠዋል። ምክንያቱም “ወደ በጎ ነገር ያመለከተ ሰው የሰሪውን ያህል ምንዳ ያገኛል” የሚል የኢስላም መርህ ስላለ ነው።            የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 582
19
ያ ጀመዓ በዚህች ሳምንት በዒድ ምክንያት ለተወሰነ ቀናት ያህል ሚዲያ ላይ ተገኝቼ ነበር። አሁን ግን የእረፍት ጊዜዬን ስለጨረስኩኝ ከዛሬ ጀምሮ ለብዙ ጊዜ የለሁም። ከላይ በተቀመጠው ሊንክ መሠረት የተለቀቁ ሐዲሶችን ይመልከቱ።
914
20
ዋናው ነገር ጤና ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اسْأَلُوا اللَّهَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ ؛ فَإِنَّ أَحَدًا لَمْ يُعْطَ بَعْدَ الْيَقِينِ خَيْرًا مِنَ الْعَافِيَةِ﴾ “አላህን ይቅርታንና ጤንነትን ጠይቁት። ማንም በአላህ በእርግጠኝነት ከማመን ቀጥሎ እንደ ጤንነት መልካም ነገር አልተሰጠውም።” (📚ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል 3558)            የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
1 007