ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
2 956
订阅者
+424 小时
+147 天
+38830 天
帖子存档
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሱት የ208ኛ ኮር የዘራይ እና የጭና ክፍለጦር አሃዶች በትናንትናው ዕለት እስከ ምሽቱ 6:00 ድረስ በዳባት ከተማ ላይ አስደናቂና ከፍተኛ ተጋ
+1
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሱት የ208ኛ ኮር የዘራይ እና የጭና ክፍለጦር አሃዶች በትናንትናው ዕለት እስከ ምሽቱ 6:00 ድረስ በዳባት ከተማ ላይ አስደናቂና ከፍተኛ ተጋድሎ የታየበት የጋራ ኦፕሬሽን አካሂደዋል። በዚህ የተቀናጀ ወታደራዊ እርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ የተቻለ ሲሆን፥ ከጠላት ወገን 03 ሲሞቱ 05 ደግሞ የቆሰሉ ሲሆን  በጀግኖቹ የክፍለጦር አሃዶች በኩል ግን በትንሽ መስዋዕትነት 02 ቀላል  ቁስለኞችን ብቻ በማስተናገድ ደማቅና ስኬታማ ገድል መፈጸም ተችሏል። ድል ለአማራ ህዝብ!!!

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 208ኛ ኮር ​የግዳጅ ግምገማን ማካሄድ እና የፋኖ ሰራዊት በአዲስ ሬጅመንት ማደራጀት ​በአርበኛ መለሰ ተሾመ ይመራ የነበረውና "ጭና ቁጥር 02" በመባል የሚታወቀው የአናብስቶች ስብስብ የሆነው የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 208ኛ ኮር ከአስመሳዩ የፋሽስቱ አብይ አህመድ አገዛዝ ምርጫ የማጨናገፍ ብቃቱን ባሳየበት ታሪክ እንዲሁም በአምባ-ጊዮርጊስ፣ በገደብጌ እና በወርቅደሞ ግንባሮች የጠላትን የውጊያ መልስ በመቀልበስ ያስመዘገባቸውን አስደማሚ ድሎች መሠረት በማድረግ በዛሬው ዕለት የግዳጅ ግምገማና አደረጃጀቱን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የማዘመንና የመከለስ ሥራ አከናውኗል። ይህ የአማራ ሕዝብ የነጻነት ኃይል በወገራና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱትን የፋኖ ሰራዊት አባላት የወቅታዊ የውጊያ ስልትና የግዳጅ አፈጻጸም ብቃታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ሬጅመንት ሁለት በሚል አዲስ ስያሜ በድጋሚ ያደራጀው ሲሆን ይህ ታሪካዊ የአደረጃጀት ሥራም የ208ኛ ኮር አመራሮችና የበላይ ዕዝ አመራሮች ግብረ-ኃይል በተገኙበት በታላቅ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። ​በጋራ ግብረ-ኃይሉ አጋዥነት የተሠራው ይህ አዲስ መዋቅር የተጣለባቸውን ሕዝባዊና ወታደራዊ አደራ በቁርጠኝነት ለመወጣት ሙሉ ዝግጁ የሆኑትን መሪዎች ያካተተ ሲሆን የአመራር መዋቅሩና ኃላፊነቱ በተራ ቁጥር ቅደም ተከተል ወደ ታች እንደሚከተለው ይፋ ተደርጓል፦ ​የሬጅመንት ሁለት ሙሉ የአመራር መዋቅር 1/ ​አዲሱ ሙሉ አለም ➡️ ዋና አዛዥ 2/ ​ቸኮለ ጋሻው ➡️ ም/አዛዥ 3/ ​አስንቆ ጌጡ ➡️ ግዥ 4/ ​አቅለው ተሾመ ➡️ ሕክምና ክፍል 5/ ​ግዛቸው ተቀባ ➡️ ወታደራዊ ስልጠና 6/ ​መሴ ውቤ ➡️ አደረጃጀት 7/ ​ለካው ይለፉ ➡️ ወ/አስተዳደር 8/ ​ጌቴ ተገን ➡️ ፖለቲካ 9/ ​------➡️ መረጃና ደህንነት 10/ ​ደሳለኝ ሞላ ➡️ ሕዝብ ግንኙነት 11/ ​ይላቅ አደራጅ ➡️ ፋይናንስ 12/ ​እይልኝ ተክሉ ➡️ ኦዲት 13/ ​አበባው አቡሃይ ➡️ ቀጠናዊ ትስስር 14/ ​እዘዝ ጌጡ ➡️ ም/ዘመቻ 15/ ​ዋኘው በቃሉ ➡️ ዘመቻ መሪ 16/ ​ሰማይ ደምሌ ➡️ ሕዝብ አስተዳደር 17/ ​ጠግኖ ቢምረው ➡️ የሰው ኃይል 18/ ​አማኑኤል አዳነ ➡️ መገናኛ 19/ ​አላዛር ተሰማ ➡️ ትምህርትና ስልጠና 20/ ​ማግኘት ገበየሁ ➡️ ልዩ ኦፕሬሽን 21/ ​ላቄ መርሻ ➡️ ሎጅስቲክስ መምሪያ ድል ለአማራ ህዝብ!!!

ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በ8 ወረዳዎችና በ186 ቀበሌዎች ምር*ጫ አልተደረገም ሲል 206ኛ ኮር አስታወቀ(ዝርዝሩ ቀርቧል) ግንቦት 25/2018 ዓ.ም ~~~ 206ኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ምስራቅ ጎጃም አገዛዙ የኩራዝ ምርጫ ለማድረግ አቅዶ የተንቀሳቀሰበት ትልቁ ደብረ ማርቆስ ከተማን ጨምሮ በ8 ወረዳዎች እና 186 ቀበሌዎች ምንም አይነት ምር*ጫ አለመደረጉን አስታወቀ። ግንቦት 24 /2018 ዓ.ም 206ኛ ኮር ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ 14ኛ ክ/ጦር በደብረ ማርቆስ አቅራቢያ ሊባኖስ፣ ደብረ ማርቆስ አየር ማረፊያ፣ ደብረ ዘይትና እነራታ ደብረ ኤልያስ፤ 24ኛ ክ/ጦር ረዕቡ ገበያ፣ የቦቅላ፤ 34ኛ ክ/ጦር ባሶሊበን ኮርክ፣ እነሞጨራ፣ ሉማሜና ወጀል፣ ጉብያ ፤ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ እና ባሶሊበን የላምገጅ በአደረጉት ጥቃት ሊደረግ የነበረውን የወንበዴዎችን ምር*ጫ ማስቆሙን አረጋግጧል። 206ኛ ኮር ከዚህ ዘፊት ነፃ የወጡ ቀጠናዎችን በማስጠበቅና በትልልቅ ከተሞች የተሳካ ኦፕሬሽን በመፈፀም ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የብልፅግና ምር*ጫ እንዳይከናወን ከተደረገባቸው መካከል ወረዳዎችና ያልተደረገባቸው ቀበሌዎች በዝርዝር ከስር ቀርበዋል። 1 ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር 2.የጎዛምን ወረዳ 1 .የጋግና ቀበሌ 2. እነራታ ቀበሌ 3. የጥጃን ሸባልማ ቀበሌ 4. ባላርፍ ቀበሌ 5. ሊባኖስ ቀበሌ 6. ግራራም ቀበሌ 7. ቸርተከል ቀበሌ 8. ለቅለቂታ ቀበሌ 9. ማይ አገታም ቀበሌ 10. አማሪት ቀበሌ 11. የውያን ቀበሌ 12. ደባ ቀበሌ 13. ገደማላ አመሻቀበሌ 14 .የዛግራ ቀበሌ 15 .አመሻ ቀኝአቦ ቀበሌ 16 .የቦቅላ ዙሪያቀበሌ 17 .የነብርና ቀበሌ 18. ወንማ ገራሞ ቀበሌ 20. ወንቃ 21. ፈንድቃ 23. ቀቢ 3.ስናን ወረዳ 1.ደ/ዘይት ቀበሌ 2. አምስትያ ቀበሌ 3. የጸድ ቀበሌ 4. ዳጉሌ ቀበሌ 5. ግድምል ቀበሌ 6. ዋሻሚካኤል ቀበሌ 7. ጠለዛሞ ቀበሌ 8. አበዛዢ ቀበሌ 9. ሺዋ ኪዳንብርት ቀበሌ 10. ጉድያሜ ቀበሌ 11. ስናን ማሪያም ቀበሌ 12. ጣማይት ገደል ቤት ቀበሌ 13. ገዳማዊት ቀበሌ 14. ካብ ጨባ ቀበሌ 15. ዚላን ቀበሌ 16. ወለጨ ሚካኤል ቀበሌ 17. ረቡዕ ገበያ ቀበሌ 01 18. ረቡዕ ገበያ ቀበሌ 02 4. ደብረ ኤልያስ ወረዳ 1. ደብረ ኤልያስ ከተማ 01 ቀበሌ 2. ደብረ ኤልያስ 02 ቀበሌ 3. ደብረ ኤልያስ ዙርያ ቀበሌ 4. አበሸብ እማበባ ቀበሌ 5. የሜዘኝ ቀበሌ 6. የጓራት ቀበሌ 7. ጫጎ ቀበሌ 8. የደንበኝ ቀበሌ 9. ግብፃዊት ቀበሌ 10. የግዳድ ቀበሌ 11. ጥጃ ጎጠር ቀበሌ 12. ጎፍጭማ ቀበሌ 13. ደጎልማ ቀበሌ 14. ገነት ቀበሌ 15. ጃቢ ገነት ቀበሌ 16. ጓይ ታዳጊ ከተማ 17.  ጓይ ዙሪያ 18. ዋሜት ቀበሌ 19. የቀጋት ቀበሌ 20.  ደጅባ  ቀበሌ 5. አዋበል ወረዳ (ሉማሜ) 1. እነሞጨራ ቀበሌ 2. ስኩት እነጋትራ ቀበሌ 3. ምንዳ የሽሚት ቀበሌ 4. የሰንበት ቀበሌ 5. የቃንዳች ቀበሌ 6. ለቁማ አሪራ ቀበሌ 7. ዝንዳ የጌደረ ቀበሌ 8. አምባሻም እነድንግረ ቀበሌ 9. የኬየት ቀበሌ 10. ሉማሜ 01 ቀበሌ 11.  ሉማሜ 02 ቀበሌ 12. ጣባ የጎደና ቀበሌ 13. ዱቄ ቀበሌ 14. ወጀል አንቅራቅ ቀበሌ 15. እነቢ ጭፍረ ቀበሌ 16. ለጋ ቀበሌ 17. ኩታይ እንደገት ቀበሌ 18. ፅድማሪያም ቀበሌ 19. መቅደስ አፍቀራ ቀበሌ 20. ደረቅ አፈረ ቀበሌ 21. ኩራረ ገነት ቀበሌ 22. አድስ አንባ ጨለያ ቀበሌ 23. ሚዛን ዋሻ ቱሉ ቀበሌ 24. ድማ መለሴ ቀበሌ 25. ጡረት ገዳም ቀበሌ 26.ጊትባረ አንባ ቀበሌ 27. አማያ ሀልጌ ቀበሌ 28. ወጀል ከተማ ቀበሌ 29. ሸብላ አበቀስቲት ቀበሌ 30. ጉንግ የዳበና ቀበሌ 6. አነደድ ወረዳ (አምበር) 1. ምስአዋሽ ቀበሌ 2. ሰንደባ ደማሞ ቀበሌ 3.ገነቷ ቀበሌ 4. ወንጋ ንፋሣም ቀበሌ 5. ሻፎ ጉዳለማ ቀበሌ 6. አምበር 01 እና 02 ቀበሌ 7.  ጃማ ዙሪያ ቀበሌ 8. ጃማ ከተማ ጎጥ 9. ዳገት የዘለቃ ቀበሌ 10. እናሥካይ የላምጪቃ ቀበሌ 11. ማልጋሽ ቀበሌ 12. ታላቅ አምባ ቀበሌ 13. ጥቁር አድብር ቀበሌ 14. አድስጌ የጎራ ቀበሌ 15. የሳምቻ ሽምቡርማ ቀበሌ 16. ጨንደፎ አይደብስ ቀበሌ 17. ዘንጎባ ደንጉማ ቀበሌ 18. ዝንቅር መሌ ቀበሌ 19. የወቢ እነችፎ ቀበሌ 20. አምበር ከተማ ቀበሌ 21. የውሽ ቀበሌ 7.ባሶሊበን (የጁቤ) ወረዳ 1. የጁቤ 01 ቀበሌ 2. የጁቤ 02 ቀበሌ 3. ምችግ ቀበሌ 4. የለመለም ቀበሌ 5. 4ቱ-አንባ ቀበሌ 6. ደን ቀበሌ 7. ዶገም ቀበሌ 8. ድንጓም ቀበሌ 9. አንጅም ቀበሌ 10. ጉንድሊሚት ቀበሌ 11. እነተመን ቀበሌ 12. ጭድ ማሪያም ቀበሌ 13. ዘንቦል ቀበሌ 14. የላምገጅ ከተማ ቀበሌ 15. የላምገጅ ገጠሩ ቀበሌ 16. የዱግ ቀበሌ 17. ልምጭም ቀበሌ 18. የገለው ቀበሌ 19. ደንደገብ ቀበሌ 20. ኮርክ ከተማ ቀበሌ 21. ኮርክ ገጠሩ ቀበሌ 22. የንስቻ ቀበሌ 23. ደጃት ቀበሌ 24. ጎበጥማ ቀበሌ 25. ቤተ ንጉስ ቀበሌ 26. ኮሜ ዘሜ ቀበሌ 8.ደባይ ጥላት ግን ወረዳ 1. ደቤት ቀበሌ 2. ገሜ ቀበሌ 3. አንገች ቀበሌ 4. አጋምና ቀበሌ 5. ወደብ ኢየሱስ 6. ይጥባቆ ቀበሌ 7. ደብር ንዑስ ከተማ 8. ደብር ዙሪያ ቀቀሌ 9. ሽሜ ቀበሌ 10. እነቆይ ቀበሌ 11. ናዝሬት መድሐኒአለም ቀበሌ 12. ናብራ ሚካኤል ቀበሌ 13. ናብራ የባላት ቀበሌ 14. ናብራ ጎቻ ቀበሌ 15. ቅድስቴ ቀበሌ 16. የባባት ቀበሌ 17. የዳማ ቀበሌ 18. አፈራሜ ቀበሌ 19. ጀረምስ ቀበሌ 20. አራጆ ቀበሌ 21. እመውላድ ቀበሌ 22. ቁይ ዙሪያ ቀበሌ 23. ቁይ 01 ቀበሌ 24. ቁይ 02 ቀበሌ 9. ደጀን ወረዳ 1. ገልገሌ ቀበሌ 2. ግብግብ ቀበሌ 3. ኩራር ቀበሌ 4. ምንጅ ይብዛ ቀበሌ 5. ጠደን አማሪት ቀበሌ 6. ብያን ቀበሌ 7. አንበር እናምቡር ቀበሌ 8. ቦርቦር ሸንቻ ቀበሌ 9. ቆንቸር ሳሳበራይ ቀበሌ 10. ዘመትን ቀበሌ 11. ጢቅ ቀበሌ 12. የትኖራ ቀበሌ 13. ጥርጭ ጀባ ቀበሌ 14. እናጅማ የዝባ ቀበሌ 15. ሰብሸንጎ አለክታም ቀበሌ 16. በርጭ ወ/አምባ ቀበሌ 17. ቆቅውሃ-ቆሰቆስ ቀበሌ 18. የናኛት ላገኔ ቀበሌ 19. ሀገረሰላም ፅድም ቀበሌ 20. ውብላት ገትም ቀበሌ 21. ሙያን ተዝካረ ማርያም ቀበሌ 22. ሙ/ድ አንበጤ ቀበሌ 23. ቆል ቀበሌ 24. እንዝጎሽ ቀበሌ በድምሩ 9 ወረዳዎችና 186 ቀበሌዎች በጀግናው ሰራዊታችን ምር*ጫ ሳይደረግ ቀርቷል

በቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ኮ/ጦር ፍኖተሰላም ሆዳንሽ ላይ ግንቦት 24/2018 ከጥዋቱ 12:00 የተጀመረው አውደ ውጊያ አድማሱን አስፍቶ ፍኖተሰላም ከተማ ላይ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2:00 ከፍተኛ የሆነ የእጅ በእጅ የጨበጣ ውጊያ የተደረገ ሲሆን  የአገዛዙን የጨረቃ ምርጫ ከማስቆም ባለፈ በርካታ የአገዛዙ ሀይል ተደምስሷል። በውጊያው 19 ሚሊሻ፣11 ፓራ ኮማንዶ፣6 ፖሊስ እና 8 የመከላከያ አባላት  በድምሩ ከ44 በላይ የጠላት ሀይል ተደምሷል። ውጊያው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን ከፍኖተሰላም ወጣ ብሎ የሚገኝ አብሸት ፉንክት የተባለ ቦታ ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ ተደርጓል።  የፍኖተሰላም ሆስፒታል በቁስለኛና አስከሬን ተጨናንቆ የዋለ ሲሆን በሁለቱም ቀን በተደረገ አውደ ውጊያ በርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ በተርቦቹ 77ኛ ክ/ጦር ተማርኳል። #አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አሰተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት   ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ምርጫ ለመታዘብ በመወሰኑ ከፍተኛ ትችት እየቀረበበት ይገኛል፤ ይህም ውሳኔ በብዙ ታዛቢዎች እና አንቅስቃሴ አድራጊዎች ዘንድ በሲቪል ጦርነት እና በፖለቲካዊ ጭቆና የተበላሸን የምርጫ ሂደት ህጋዊ ለማስመስረት እንደተደረገ ተደርጎ ተወስዷል።የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን መላክን የሚቃወሙ ወገኖች ነጥቦችበአማራ ክልል ያለው የሲቪል ጦርነት፦ በፌዴራል መከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ቀጣይነት ያለው ውጊያ ሁሉንም ያካተተ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ እንዳይካሄድ እንቅፋት ሆኗል።ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፦ የለንኪን ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ይጠቅሳሉ።የሲቪክ ምህዳር መጥበብ፦ ዋና ዋናዎቹ የአገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአብይ አህመድ መንግስት ተዘግተዋል።በፕሬስ ነፃነት ላይ የሚደረግ ጭቆና፦ ነጻ ጋዜጠኞች በዘፈቀደ ለእስር፣ በድብቅ ቦታዎች ለመታሰር እና ለስቃይ (ቶርቸር) እየተዳረጉ ሲሆን፥ ይህም አገሪቱን በዓለም የፕሬስ ነፃነት ደረጃ 145ኛ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።የተቋሙ ተባባሪነት፦ የአፍሪካ ህብረት ድምጽ አሰጣጡን እውቅና በመስጠት የራሱን የዴሞክራሲ፣ የዲፕሎማሲ እና የቅን አገዛዝ ቻርተር ጥሷል በሚል ተከሷል።የአፍሪካ ህብረት ውጥረትበዚህ አሰጋጅ ጉዳይ ላይ የአፍሪካ ህብረት ገለልተኝነት በትልቅ ፈተና ውስጥ ወድቋል። በአንድ በኩል ህብረቱ የሕገ-መንግስታዊ ሂደቶችን የመደገፍ እና በአባል አገራት መካከል በምርጫ ታዛቢነት እና በውይይት የፖለቲካ መረጋጋትን የማምጣት ግዴታ አለበት። በሌላ በኩል ደግሞ በሰፊው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ዝምታን መምረጡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተአማኒነት ያሳጣዋል። የህብረቱ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ መሆኑም ጫናውን የሚያበረታው ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ውስብስብ እና ስትራቴጂካዊ ያደርገዋል።

ግንቦት 25/2018 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በሚያስተዳድራቸው አካባቢዎች ሁሉ አገዛዙ በሰሞኑ ህዝባዊ ቅቡልነት ማጣት ብስጭት ውስጥ በመግባቱ በሸዋ ከተሞችና ወረዳዎች የምርጫ ቲያትሩ የከሸፈበት በመሆኑ ህዝብን ወደ ማሽብር ተሸጋግሯል !! መንገዶች ሁሉ ተዘግተው ህዝባዊ ቁጣዎች ተነስተዋል፣ገበያውች ተበትነው፣ መናኸሪያዎች ዝግ ሆነው ውለዋል ። ከአዲስ አበባ ደብረብርሃን ፣ ሸዋሮቢት ፣ምንጃር አረሪቲ ፣ መርሐቤቴ አለምከተማ ፣በይፋት አንፆኪያ እና አጣዬ፣በመንዝ ቀጠና እና በሌሎች ወረዳዎች ተመሳሳይ እቅስቃሴዎችን በማገድ በበቀል ሹፌሮችን በማሰር፣ህዝባችንን በማንገላታትና በማሰር የበቀል ብትሩን እየሰነዘረ መሆኑ ታውቋል። ነገር ግን ከዚህና መሰል እኩይ ተግባራቸው የማይፋቱ እንደሆኑ ብናውቅም የህዝባችንን ዕለታዊም ሆነ ዘላቂ መብትና ህልውና ለማስከበር በአገዛዙ ሰራዊት እና ካድሬ ላይ ከወትሮው የበለጠ እርምጃችን ይቀጥላል ሲሉ የግንባር መረጃችን ምንጭ ጠቅሰዋል። ለዚህም በአንዳንድ ወረዳዎች ህዝቡ ጥያቄው ወደቁጣ በመቀየር ፋኖ ለህልውናችን እና ለአማራ ነፃነት የሚታገል በመሆኑ የድርጅታችን አፋብንን ትዕዛዝ ስላከበርን እና የአገዛዙን የምርጫ ድራማ ባለመታደማችና ባለ መምረጣችን ከክልል እስከ ወረዳ መንግስትነቱን ያጣው አገዛዝ እና አስፈፃሚ ካድሬዎች መክረው ያደረጉት እንደሆነ ገልፀው፤በዚህ ድርጊታቸውም መንገድ ፣ መገልገያ ተቋማት እና አንቡላንስ ሳይቀር ስለተዘጉ ህመምተኞች ዛሬ ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል ብለዋል። ድል ለአማራ ህዝብ ! ድል ለፋኖ!

ሰበር ዜና!!! መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር በሁሉም ቀጠናዎች የጨበራ ምርጫው ተሰርዟል፣ የአገዛዙ ሰራዊቱም ድባቅ ተመቷል!!! እንደ አፋብን የወረደው ግዳጅም በተሻለ ጥምረት የተሻለ ግዳጅ ተፈፅሟል። ከግንቦት 20/2018_ግንቦት 24/2018 በማዕከላዊ ጎንደር ሻሁራ ከተማና አፀደማርያም ከተማ ሊደረግ የታሰበው የጨበራ ምርጫ በአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ነበልባሏ አድዋ ክ/ር በሶስት ማዕዘን አውደውጊያውን በማፏፏም የጠላትን የምርጫ ዕቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከፍተኛ ድልን መጎናፀፍ ተችሏል። ሁለተኛው አውደውጊያ አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አይሸሽም ብርጌድ በሻለቃ አሌ መጋቢያውና በሻለቃ አምሳያው የኋሌ ልዩ ጥምረት በማድረግና ከ5ኛ ኮር ታድሎ ብርሀን ክ/ር ጋር በመተሳሰር ከአይንባ እስከ አዘዞ ካምፕ እንዲሁም አዘዞ ዙሪያ ቀበሮ ሜዳ፣ ጉንብሪትና አጣጥ እና መሰል በርካታ ቦታዎች ልዩ ድባብ በመፍጠር  የአገዛዙን የጨበራ ምርጫ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል እንዲሁም የአገዛዙ ሰራዊት በርካታ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዷል። ሶስተኛው የአውደውጊያ ውሎ በተመሳሳይ በአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር 1ኛ ሬጅመንት በመተማ ወረዳ ኩመርአውላላ እና ሌሎች ሬጅመንቶች አዳኝ አገር ጫቆ ነጋዴ ባህርና አካባቢው ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ የጨበራ የምርጫ ሂደቱን እንዲቋረጥ ሆኗል እንዲሁም ነጋዴ ባህር ከተማ ውስጥ ሰርጎ በመግባት በልዩ ተልዕኮ አስፈላጊ ድርጊቶችን በመፈፀም ውጤታማ ስራ ተሰርቷል። የጠላት ሀይል የፋኖን ከፍተኛ በትር አስተናግዶ በርካታው ሙትና ቁስለኛ ሲሆን የምርጫውን መጭበርበር በውል የተረዱ 6 የአድማ ብተና አባላትም እስከ ሙሉ ትጥቃቸው ክ/ሩን ተቀላቅለዋል። አራተኛው አውደውጊያ ከሱዳን ጠረፍ ጀምሮ ሽንፋንና ቋራን ባማከለ የአገዛዙ የምረጡኝ ህልም ከመክሸፉ ባሻገር የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት በአይበገሬዎቹ የካራማራ ክ/ር እና የኦሜድላ ክ/ር በጣምራ በተሰራ ኦፕሬሽን ድባቅ ተመቷል። በዚህም በርካታ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዷል። ሌላኛው አውደውጊያ ከመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አቅራቢያ በቀጠና መረጃዎችን በተገቢው በመለዋወጥ ጣና ብርጌድ ከታላቁ አርበኛ ልቡ መስዋትነት በኋላ በተጠናከረና በተደራጀ መንገድ ከእንዳሁን ቀደሙ በተሻለ በጠላት ላይ ብርቱ ክንዳቸውን በማሳረፍ ጀግንነታቸውን በማስመስከር እረገድ በማዕከላዊ ጎንደር ጣቁሳ ወረዳ ከድኩላርባ እስከ ደልጊ ከተማ መግቢያ ጫፍ ድረስ የአብይን የምርጫ ድራማ ሙሉ በሙሉ አክሽፈውታል፤ የጠላት ሀይልም አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ ለምርጫ ስምሪት የወጣው ሰራዊቱና የብልፅግና ካድሬዎች ኮረጆውን አንጠልጥሎ ምንም አይነት የማስመረጥ ስራ ሳይሰራ ቀጠናውን ለቆ በመፈርጠጥ ላይ እያለ በመከታተል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሰራዊት አፈር ከድሜ በልቷል በርካታ ቁጥር ያለውም ቁስለኛ ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በነዚህና ቀሪ በርካታ ቦታዎች በኔት ወርክ ችግር ሙሉ መረጃዎችን ማግኘት የተቸገርን ቢሆንም ለምሳሌ በቋራ፣ በሽንፋ፣ አዳኝ አገር ጫቆ አገዛዙ እንደ አማራጭ ተግዳሮት ቢፈጥርም በዲሞክራሲ ስም የአማራን ህዝብ እየገደለ በጎን ደግሞ ተጨማሪ የፈቃድ የግዞት ጊዜ ስጡኝ በማለት የሆረር ፊልሙ ተዋናይ አብይ አህመድና የግብረአበሮቹ ህልም በጀግናው የህዝብ ልጅ በሆነው በፋኖ ብርቱ ክንድ ከሽፏል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ ክፍል      ግንቦት 25/2018

ሳይሆን ለራስም ህልውና ሲባል አገዛዙን በህብረት መታገል ተገቢ እና አስፈላጊ በመሆኑ በያለህበት ትግሉን ፖለቲካዊ እና የሞራል ድጋፍ ከመስጠት ባሻገር የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ይህን ዘር አጥፊ አገዛዝ ለማስወገድ በሚደረገው ትግል በባለቤትነት እንድትሳተፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፫) ጥሪ ለዲያስፖራው የአማራ ዲያስፖራም ሆነ ህዝባዊው መላው የኢትዮጵያ ዲያስፓራ በሀገር ቤት የሚደረገውን የህልውና ትግል ለመደገፍ ከፍተኛ ጥረት ስታደርጉ መቆየታችሁ ይታወቃል። በዚህም ለትግሉ ትልቅ አቅም ሆናችሁ ቆይታችኋል። ትግሉ ወሳኝ እና አዲስ ምዕራፍ ለመሻገር በሚንደረደርበት በዚህ ወቅት ከቀደመው ድጋፍ የበለጠ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። ከዚህም አንጻር ድርጅታችን ባስቀመጣችው የድጋፍ መስመሮች በመግባት እና በመደረጃት የሚጠበቅባችሁን እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፬) ጥሪ ለሚዲያ ሰወች በአማራ ትግል ውስጥ ሚዲያ ትልቅ አቅም በመሆን መረጃ በማድረስ እና ህዝባዊ ንቅናቄ በማነሳሳት አግዟል። ይህ የትግላችን አንዱ መስክ እንደመሆኑ በተደራጀ አኳኀን የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ ሊሰራ ይገባል። ከዚህ አኳያ በቀጠናው ያለው አደረጃጀት አንድነት ከማብሰር ባሻገር አንድነትን የሚያጠናክር ስራዎች በመስራት የበኩላችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን፤ በቀጠናችን ያለውን ልዩ የትግል ባህርይ ያገናዘበ ዘገባዎች እንዲቀርቡም ለማሳሰብ እንወዳለን። እንዲሁም የወለጋ -ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝ ተከታዩን ምስጋና ያቀርባል። ፩) ምስጋና ለድርጅታችን: እናት ድርጅታችን አፋብን ሁላችንን አሰባስቦ የቀጠናውን ትግል አንድ የሚያደርግ ስራ በመስራት ረገድ ለተወጣው አይተኬ ሚና ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን። በዚህ ስራ ረጅም ጉዞ ተጉዘው በአካል ተገኝተው በማወያየት በትጋት አብረውን ለነበሩት እና በተሳካ መልኩ ግዳጃቸውን ለፈጸሙት የድርጅታችን የፖሊት ቢሮ አባል በልዩ መልኩ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። ፪) ምስጋና ለትግሉ ደጋፊዎች:- የትግላችን ደጋፊዎች ተቀራርበን እንድንነጋገር እና እንድንወያይ በጎ ግፊት ስታደርጉ በመቆየታችሁ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። በመጨረሻም የወለጋ -ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝ ቀጥሎ የተቀመጠውን ቃል ይገባል። እኛ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወለጋ(ቢዛም)- አንሻ ሰይድ እዝ ስራ አስፈጻሚ አባላት በቀጣናችን ሲደረግ በቆየው ትግል የተገኙ ድሎችን ለማሳደግ፣ ፈተናዎችንም በጽናት ታግሎ ዕዙን ለቀጣዩ የስራ ሀላፊነት ብቁ ሆኖ እንዲመጣ ለማስቻል በከፍተኛ ጓዳዊ ሞራል በተለይም ቅንነትን፣ የድርጅትን ህገ ደንብ እና ርዕዮተ አለማዊ መስመር ገዢነትን የሚያሰፍን፣ በአጠቃላይ ድርጅታችን አፋብን ያስቀመጠውን ዓላማ የሚያሳካ እና በሂደቱም ሆነ በውጤቱ 'የድርጅትን' አሸናፊነት በማረጋገጥ ለአዲስ የትግል ምዕራፍ የምስራች እንዲሆን፤ የተጣለብንን አደራ ፦ በእውተኛነት፣ በፍትሀዊነት፣ ሀቅ ላይ በተመሠረተ ምክንያታዊነት ለመፈጸም በህዝባችን፣ በጓዶቻችን፣ በተሰውት ሰማዕታት እና በምናምነው እውነተኛ እና ጻድቅ አምላክ ስም ቃል እንገባለን። በአፋብን የወለጋ-ቢዛሞ አንሻ ሰይድ ዕዝ

Mereja TV: ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወለጋ(ቢዛም)- አንሻ ሰይድ እዝ የተሰጠ የአንድነት መግለጫ ለዘመናት የጅምላ ሰቆቃ እና የዘር ማጽዳት ቤተ ሙከራ ሆኖ የባጀው የወለጋ-ቢዛሞ አማራ ራሱን ለመከላከል በተለያዬ ጊዜ እና ሁኔታ ተጋድሎዎች ሲያደርግ ቆይቷል። የአማራ ህዝብ የመንግስት እና የሀገር ባለቤትነትን መቀማቱ አማራ ክልል ከሚባለው ውጭ ላለው አማራ ማህበረሰብ ከፍተኛ የህልውና ስጋት እንዳመጠበት በተጨባጭ የታዬ ሀቅ ነው። በተለይ በቢዛሞ/ወለጋ ቀጠና ያለው ማህበረሰብ አማራ መሆንን ተከልክሎ ከመኖር ባሻገር ለዘመናት ከኖረበት አካባቢ ከአስተዳደራዊ በደል ጀምሮ ሰፊ የማንነት ጥቃት ተፈጽሞበታል። አማራ ነኝ እና አማራ አይደለህም በሚለው ተቃርኖ ውስጥ በስጋት ሲኖር የቆየው ማህበረሰብ በተለይ ከብልጽግና አገዛዝ መምጣት በኋላ መንግስታዊ እውቅና ባለው ይፋዊ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ተገድለዋል፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ተለያዬ አካባቢ ተፈናቅለዋል፣ ተበትነዋል። ይህን የዘር ማጥፋት አዋጅ መከላከል የህልውና ጉዳይ በመሆኑም የቢዛሞ አማራ ተደራጅቶ ራስን የመከላከል እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። ይህ እንቅስቃሴ የፋኖነት እና የአማራ ትግል በሀሳብ እና የአላማ አንድነት በማግኘቱ የፖለቲካ መስመር እየጠራ መምጣትን ተከትሎ ደግሞ ትግልን የሚመጥን አደረጃጀት በመፍጠር ከሌላው የአማራ ወገን ጋር ህልውናን መታደግ እና ጠላትን የመመከት አላማን ይዞ እየታገለ ይገኛል። በዚህም ህዝባዊ አቅሞችን በማሰባሰብ እና መሬት የተከለ ትግል በማድረግ ሰፋ ያለ አካባቢ ላይ በመንሳቀስ እና የማደራጀት ስራ በመሰራቱ የጠላትን የማጥፋት አቅም ማዳከም እና በጠላት ላይ ሰፊ ጉዳት ማድረስ ችሏል። ይሁንና ፈተናው ከምቹ ሁኔታዎች የሚልቅ በመሆኑ በሁለት አደረጃጀቶች የታቀፈውን ሀይል ወደ አንድ በማምጣት ብሎም በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አደረጃጀት መዋቅር ውስጥ በመግባት የጋራ ህዝባዊ አቅም በመፍጠር የተቀናጀ ትግል ማድረግ ግዴታ ነው። እስካሁን ድረስ በአካባቢው የነበረው አደረጃጀት ሁሉንም የአካባቢው የፋኖ ኃይል ማቀፍ ባለመቻሉ ምክንያት የአደረጃጀት ስራችን ሣይጠናቀቅ ቢቆይም እነሆ ዛሬ ድርጅታችን አፋብን ባደረገልን እገዛ እና ክትትል የአማራ ፋኖ ቢዛሞ ቀጠና አንሻ ሰይድ እዝ እና የአማራ ፋኖ በወለጋ በሚል አደረጃጀት ስር የቆዬን ታጋዮች በሁለታችንም የስራ አስፈፃሚ ሙሉ ኮሚቴ ቀናትን በወሰደ የአካል ውይይት በአፋብን የወለጋ-ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝን መስርተናል፤ የእዙ የስራ አስፈፃሚ አባላትንም:- 1. አርበኛ ንጉሴ ዋለልኝ- ሰብሳቢ 2. አርበኛ አደም ተፈራ -ምክትል ሰብሳቢ 3. አርበኛ ሐብታም ጥላሁን -ወታደራዊ አዛዥ 4. አርበኛ አለፈ ሽባባዉ -ምክትል ወታደራዊ አዛዥ 5. አርበኛ ዳዊት አማረ -የሕ/ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ 6. አርበኛ ተስፋዬ አቻሜ - የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ 7. አርበኛ ወንድ-ወሰን ተገኑ -የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 8)አርበኛ ምኒበል እንዳለ -አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ 8. አርበኛ ክንዱ ስጦታው -ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ 9. አርበኛ ክንዱ አቸነፍ -ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ 10. አርበኛ ጥላሁን ሰብስቤ -ጤና መምሪያ 11. አርበኛ ታለልኝ ደርሶልኝ -ፅ/ቤት ኃላፊ 12. አርበኛ ሮቤል ወ/ምካኤል -የፋይናንስ እና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ 13. አርበኛ አህመድ አበባው - ሎጅስቲክ መምሪያ ኃላፊ 14. አርበኛ አንዳርጌ በለጠ -መካናይዝድ ጦር መምሪያ ኃላፊ 15. ••••መረጃ እና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ 16. አርበኛ እንዳለው ተስፋዬ -ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ 17. አርበኛ ዘመን መላክ -ወታደራዊ መረጃ እና መገናኛ ኃላፊ 18. አርበኛ አስናቀው ቸርነት -ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ 19. አርበኛ አዲሱ አላምረው -ሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ 20. አርበኛ አማረ በለጠ-ህግ እና ስነ ምግባር መምሪያ ኃላፊ 21. አርበኛ በረከት አይናዬ -ልዩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 22. አርበኛ ካሳሁን ወርቁ -የሰው ኃብት መምሪያ ኃላፊ 23. አርበኛ ሙላት ከፌ -ኢንዶክሪኔሽን መምሪያ ኃላፊ 24. አርበኛ ደረጀ ወርቄ -ሐብት አፈላላጊ መምሪያ ኃላፊ 25. አርበኛ አስማማው ግርሙ-ጥናት እና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ 26. አርበኛ አይሸሽም አሞኘ -ወታደራዊ ጥናት እና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ 27. አርበኝት ወርቅሰው ጌጤ - የሴቶች ጉዳይ በማድረግ የስራ ስምሪት እና ምደባ ሰጥተናል። እንኳን ደስ አላችሁ ! ትግላችን የአማራን ህልውና የመታደግ እና እንደ አማራ በምንኖርበት አካባቢ ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የመተዳደር ወይም ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የመጎናጸፍ ነው። ይህ የአማራ የብሔርተኝነት ርዕዮተ አለማዊ የትግል መስመር የአማራ ህዝብ ለዘመናት የተነፈገውን መብት የቦታ ልዩነት ሳይኖረው እንዲከበር የማረጋገጥ ነው። ይህ መብት መከበር እኛ በምንኖርበት አካባቢ ከሚኖረው ወንድም የኦሮሞ ህዝብ እና ከሌላው ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መሠረት ሲሆን የመብት መከበር ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥም ብቸኛው መፍትሔ እንደሆነ እናምናለን። ከዚህም በመነሳት ለህዝባዊ ህልውና መረጋገጥ እና መብቶች መከበር ከኦሮሞ ወንድሞቻችን እና ሌሎች ጎረቤት ህዝቦች ጋር የጋራ መግባባት እየፈጠርን አገዛዙን ከሚታገሉ የኦሮሞ ኃይሎች ጋርም በትብብር በመስራት ቀድሞ የነበሩ ተቃርኖዎች እየፈታን፣ የነበሩ መልካም ግንኙነቶችንም እያጠናከርን መሄድ የትግላችን አካል ነው። በመሆኑም የወለጋ -ቢዛሞ አንሻ ሰይድ እዝ ተከታዩን ጥሪ ያቀርባል። ፩) ጥሪ ለሰራዊታችን የወለጋ(ቢዛም)- አንሻ ሰይድ እዝ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በቀጠናችን አንድ ትግል አንድ አደረጃጀት መፈጠሩን እያበሰርን በአማራዊ ወንድማማችነት እና በትግል ጓዳዊነት መንፈስ የጀመርነውን የህልውና ትግል የፖለቲካ መስመሩን በማጽናት እና የሚሰጡ ግዳጆችን የአንድነት አቅምን ተጠቅመን በበለጠ ጽናት እንድንፈጽም ለማሳሰብ እንወዳለን። ከዚህ በተጨማሪም በድርጅታችን ካሉ ሌሎች ዕዞች ጋር በሚኖሩ የጋራ ግዶጆች የሚጠየቀውን በቁርጠኝነት እንድትፈጽሙ በድጋሚ እናሳስባለን። ፪) ጥሪ ለአማራ ህዝብ የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የመጥፋት አደጋ ለመዳን እና ጠላትን ከመመከት ባሻገር ጨርሶ ለማስወገድ ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ላይ መድረሳችን ይታወቃል። ይህ ምዕራፍ ከቀደሙት የትግል ወቅቶች የበለጠ መራር ትግል የምናደርግበትም ነው። በቀጠናችን በዛሬው ዕለት የተጠናቀቀው አደረጃጀት ደግሞ በነባሩ አቅም ላይ ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ አቅም እንደሚሆን ሙሉ እምነት ያለን ሲሆን ይህን ህዝባዊ ጦርነት በህዝባዊ ውጊያ መክተን ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል በባለቤትነት እንደ እስከዛሬው የሚጠበቀውን ለማድረግ በየአደረጃጀቱ እንድትተጋ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፫) ጥሪ ለኢትዮጵያዊያን የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራ ህዝብ የተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመመከት ላለፉት ሦስት አመታት ሰፊ ህዝባዊ ትግል እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የአማራ የህልውና አደጋ የራሱ ልዩ ባህርያት ቢኖሩትም ሌላውም የኢትዮጵያ ህዝብ ተመሳሳይ ቅርጽ ያለው የህልውና ስጋት ውስጥ እንዳለ እሙን ነው። ይህ ጸረ ህዝብ የብልጽግና አገዛዙ በተርታ ህዝቦችን ለማጥፋት የጀመረውን ጦርነት በጋራ መመከት ደግሞ የሁሉም ህዝቦች ተፈጥሯዊ ግዴታ እንደሆነ እናምናለን። ስለዚህም የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል መደገፍ ብቻ

አርሲ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል'የንጹሃን ጭፍጨፋው ቀጥሏል' እስካሁን ቦታው ላይ የደረሰ መከላከያ ሀይል አልተገኘም። ከ49 በላይ ንጹሃን ክርስቲያኖች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። 230 የሚሆኑት ደግሞ ታ
አርሲ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል'የንጹሃን ጭፍጨፋው ቀጥሏል' እስካሁን ቦታው ላይ የደረሰ መከላከያ ሀይል አልተገኘም። ከ49 በላይ ንጹሃን ክርስቲያኖች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። 230 የሚሆኑት ደግሞ ታፋነው ተወስደዋል ያሉበት አይታወቅም ብለዋል የአይን እማኞች። ነዋሪዎቹ የደራሽ ያለሽ እያሉ ቢሆንም አጋዥ ሀይል እንዳላገኙና አሁን በምስራቅ አርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ ታጣቂዎች ቀበሌዎችን ከበው መስመር በመዝጋት ህዝቡ እንዳይወጣ በማድረግ ጥቃት እየፈጸሚበት መሆኑም ተነግሯል። ግንቦት 25/2018

#303ኛ_አሳምነው_ኮር💪 በምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር ትናንት ግንቦት 24/2018 ባደረገው ተጋድሎ የማረከው የጦር መሣሪያና የጠላት ሰራዊት! 25/ዐ9/2018 ዓ.ም
+7
#303ኛ_አሳምነው_ኮር💪 በምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር ትናንት ግንቦት 24/2018 ባደረገው ተጋድሎ የማረከው የጦር መሣሪያና የጠላት ሰራዊት! 25/ዐ9/2018 ዓ.ም

አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነዉ ኮር በትናንትናው  ዕለት በዘመቻ አይሻ ሰይድ የተገኙ ምርኮወች!! ዝርዝር ዘገባዉን በትላንትናዉ ዕለት ያደረስን ቢሆንም  ሙሉ የምርኮ ምስሎችን በኢንተርኔት ችግር ወደ እናንተ ያላደረስን መሆኑ ይታወቃል ከተገኙ ምርኮወች የተወሰኑትን  የ303ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ያደረሰን ሲሆን አሁንም ኢንተርኔት ባለመመቻቸቱ ሙሉዉ ሰላልደረሰን አሁንም ቀሪወቹ እንደደረሱን እናጋራለን። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!! ግንቦት 25/2018ዓ.ም

59 ቦታዎች ላይ ውጊያ  በመክፈት ምርጫውን አስቁመናል። ቀትናንትናው ዕለት  በጎጃም ምድር ብቻ 59 ቦታውች ላይ ውጊያ  በማድረግ ታሪክ ሰርቷል። ምርጫውን ማድረግ ያልቻለው ስርዓት ሌሊት ካቢኔዎችን ሰብስቦ የምርጫ ካርድ ሲመዘግብ አድሯል። በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና የቡድን መሳሪያ በመማረክ ምሽጎችን በመደረማመስ ጠላትን በመደምሰስ ከተማን መቆጣጠር ተችሏል። 105ኛ ኮር =11 ቦታዎች ላይ ውጊያ ከፍቷል። ሰከላ ፣አዲስ ቅዳም ፣ ቲሊሊ፣ኮሶበር ፣ዳንግላ ፣ዱርቤቴ ፣ይስማላ፣ ዲላሞ  ፣ወርቅ ሜዳ ፣ ዳዊ ፈንድቃ፣ ደቅ  ላይበመዋጋት ድል ቀዳጅቷል። 102ኛ =18 ቦታዎች ውጊያ ከፍቷል። አዴት፣ ቆቀር፣ ጋላ ወልዴ  ፣ ገርጨጭ ፣ብራቃት ፣ፒኮሎ ፣ አንዳሳ ፣ጭስ አባይ ፣ሮቢት ፣ደናማርያም ፣ ጎንጂ ፣ቋሪ ወይበይኝ፣ መሸንቲ ፣ቅንባባ፣ይጎዲ፣ ሰባታሚት ፣ዘንዘልማ    ላይ  በመዋጋት ድል ቀዳጅቷል። 109ኛ =9 ቦታዎች ላይ ውጊያ ከፍቷል። ደንበጫ ፣እንቡሊ ፣ አማኑኤል፣ ሆንዳንሽ፣ ሽንዲ ፣ እሁዲት፣ ጁቤራ፣ ፍተሰላም ከተማ  ፣ቁጭ   ላይ በመዋጋት ድል ቀዳጅቷል። 201ኛ=10 ቦታዎች ላይ ውጊያከፍቷል። ሞጣ፣ግንደወይን፣ ፈለገብርሃን ፣መርጦለማርያም ፣ደብረወርቅ፣ ቢቸና ፣ወይራ፣ የዱሃ ፣የትመን፣ ድጎ   ላይ በመዋጋት ድል ቀዳጅቷል።   206ኛ= 11 ቦታዎች ላይ ውጊያ ከፍቷል። የቦቅላ ፣እነራታ ፣ረቡዕ ገብያ ፣ ኮርክ ፣ ወጀል፣ ሊባኖስ ፣ደብረማርቆስ አየር ማረፊያ፣ ጎፍጭማ ፣ ቁይ ፣ጉዳልማ፣አንበር     ላይ  በመዋጋት ድል ቀዳጅቷል። በአማራ ምድር 5ቱም ዕዞች ትንቅንቅ በማድረግ ጠላት  ምርጫ ማድረግ አይደለም መቀመጥ የማይችልበት  ደረጃ ላይ አድርሰነዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ    ግንቦት 25/ 2018ዓ.ም

ሰበር የድል ዜና! ለጊዜው የትኛው እዝ፣ ኮር፣ ክፍለ ጦር ከመግለፅ ተቆጥበናል። በጥዋቱ አካባቢውን አሰሳ አደርጋለው ያለው የአገዛዙ ሃይል በጀግናው አይበገሬው የአማራ ፋኖ ደፈጣ በማድረግ የአገዛዙን
ሰበር የድል ዜና! ለጊዜው የትኛው እዝ፣ ኮር፣ ክፍለ ጦር ከመግለፅ ተቆጥበናል። በጥዋቱ አካባቢውን አሰሳ አደርጋለው ያለው የአገዛዙ ሃይል በጀግናው አይበገሬው የአማራ ፋኖ ደፈጣ በማድረግ የአገዛዙን ሃይል ሙት እና ቁስለኛ አድርጎ እረፍርፎታል። * 1ፓትሮል ወደ አመድ ቀይሯታል * 19 የተማረከ መከላከያ *  02 ስናይፐር *  39 ክላሽ * 03 ብሬን *የክላሽ ጥይት 11,212 *የብሬን ጥይት 2,241....ሸንሸል 03 *የስናይፐር ጥይት 845 ተማርኳል።

የ106ኛ ኮር አሃዶች  የውሎ ተጋድሎ!!! ግንቦት 24/2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ106ኛ ኮር አሃዶች የውሎ ተጋድሎ ጀብዶች!!!   የ106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር እና የ303ኛ ኮር 81ኛ ክፍለ ጦር በጋራ በመቄት ወረዳ የጥላትን ሰራዊት ሲያነጥፉት ውለዋል።በሁለቱም ክፍለ ጦሮች ጥምረት በመቄት ወረዳ በ36 ቀበሌዎች 79 የምርጫ ጣቢያ ሲኖር፤ በዚህ ጣቢያ ከአንዱ የምርጫ ጣቢያ ውጭ በፋኖዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ ሲውል፤  አንዱም የምርጫ ጣቢያ ህዝቡ ገዳይን አንመርጥም በማለት በራቸውን ዘግተው ውለዋል።በዚህ የውሎ ተጋድሎ የተገኘ ድል፦    *የተደመሰሰ የጥላት ሰራዊት ሶስት ፓትሮል ሲያመላልሰው የዋለ    *አምስት ፓትሮል ቁስለኛ የተጫነ    *አንድ ሻለቃ መሪ የተደመሰሰ ሲሆን በጥላት ላይ ሙሉ በሙሉ የበላይነቱን የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ልጆች  ተቆናጥጠዋል!!     #የ31ኛ ክፍለ ጦር የውሎ ተጋድሎ፦ በደላንታና በዳውንት ወረዳ የጥላትን ሰራዊት ሲያራዉጡት ውለዋል። ለአብይ አህመድ የስልጣን እድሜ ሲባል የተገበሩ የድሀ ልጆች ቁጥር በርክቷል።በሁለቱም ወረዳዎች የአማራን ህዝብ እጅግ ያስደሰተና አመርቂ ስራ የተሰራ ሲሆን  በዚህ የውሎ ተጋድሎ የተገኙ ድሎች፦    በዳውንት ወረዳ ካሉት የምርጫ ጣቢያዎች ከአንዱ ማለትም ከኩርባ ውጭ ሙሉ በሙሉ በፋኖዎች ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፤  በወረዳው ሙሉ በሙሉ የምርጫ እንቅስቃሴን ማስቆም ተችሏል። በብአዴን ሎሌዎች ቅዠት ታስቦ የነበረው የምርጫ መቋመጥ በግስላዎቹ ክንድ ዶግ አመድ ተደርጓል።             በዚህ የውሎ ተጋድሎ የተገኙ ድሎች፦      *ከ24 በላይ የተደመሰሱ!      *ከ35 በላይ ቁስለኛ ተደርገዋል!      *በርካታ የጥላት ትጥቅና ተተኳሽ ተማርኳል!       *በርካታ የምርጫ ቁሳ ቁሶች ማውደም ተችሏል! #በደላንታ ወረዳ የተገኙ የውሎ የተጋድሎ ድሎች፦      በወረዳው ውስጥ ካሉ የምርጫ ጣቢያዎች ጥላት አንድ ቀበሌ ወገልጤና ጣቢያ ብቻ ሲሆን በወገልጤና ጣቢያም ከሎሌ እና ከወታደር አካላቶች ውጭ የመረጠ የለም። በዚህም ወረዳ ከባድ የሆነ ጦርነት የተካሄደ ሲሆን በክፍለጦሩ ተናዳፊ ተርቦች  የጥላት ሰራዊት ሲረሸረሽ ውሏል፤ በውሎ ተጋድሎዎች የተገኙ ድሎች፦   *ዙ-23 ተኳሹን ጨምሮ 23 የተደመሰሱ!   *ሁለት  አስመራጭ የተደመሰሱ!   *በሶስት ፓትሮል ሲመላለስ የዋለ ቁስለኛ!   *በርካታ የምርጫ ቁሳቁሶች የወደሙ...     #በጋዞ ወረዳ የ34ኛ ክፍለ ጦር የውሎ ተጋድሎ፦ በጋዞ ወረዳ ከጠዋቱ የአገዛዙ የስርዓት ማስጠበቂያ ላቃዎች የሞትን ብራቅ መትፋት የጀመሩ ሲሆን በክፍለ ጦሯ አናብስቶች የጥላት የሞት ላንቃ ሲዘጋ በጋዞ ወረዳ በርካታ የጥላት ሰራዊቶች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል። ያለ የለለውን ሰራዊት ጥላት ያሰለፈ ቢሆንም የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት ፋኖዎች የውሎ ተጋድሎን በድል ቋጭተውታል። በዚህ አውደ ውጊያም፦    *37 የተደመሰሱ     *ለጊዜው ማዕረጋቸው ያልታዎቁ ሶስት አመራሮች የተደመሰሱ!    *27 ቁስለኛ የተደረጉ    *ከ2000 ሽህ በላይ የክላሽንኮቭ ተተኳሽ የተማረከ    * በርካታ የምርጫ ቁሳቁሶች የወደሙ ሲሆኑ በወረዳዉ ሙሉ በሙሉ የአገዛዙ የይስሙላ የምርጫ ጨዋታ እንዳይካሄድ ማድረግ ተችሏል።     #በዋድላ ወረዳ የ22ኛ ክፍለ ጦር አናብስቶች የተጋድሎ ውሎ እጅግ አመርቂና ውጤታማ ነበር። በኮን ከተማ ሰፍሮ የነበረን የስርዓቱ ጠባቂ ሰራዊት ላይ ከቋና ተነስተው እንደ ንብ ሲነድፉት በጥቅም የተገዛው አላማቢስ የብልፅግና ሰራዊት ሲፈረጥጥ የዋለ ሲሆን ለምርጫ ድራማው ሙሉ ያሰበው የጥላት እቅድ እንዲከሽፍ ተደርጓል። የወረዳው ህዝብም ገዳይ ስርዓትን አንመርጥም በማለት ቤት ሱቁን ዘግቶ የዋለ ሲሆን አንዳችም የጥላት እቅድ እይዳይፈፀም ግስላዎቹ አድርገዋል። እሽክትር ሲል የዋለው የብልፅግና ስርዓት ጠባቂ ሰራዊት ፋይዳ ቢስ ተደርገዋል። በርካታ የጥላት ውድመትን ማድረስ ተችሎ እሽከ ምሽት ጥላትን አገቱን በማስደፋት የውሻ ቅልውጥ በራፉን አነፍናፊ ማድረግ የቻሉት ፋኖዎች ታሪክ ሰርተዋል። በጠቅላላ የ106ኛ ኮር በሚቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ የአገዛዙን የጥፋት እጆች መቁረጥ ተችሏል። በእየአንዳንዷ የወረዳ አብራክ ቀበሌዎች እና የወረዳ ከተሞችን የጥላት የጥፋት ድርን በመጣጠስ ዘመን አይሽሬ ታሪክንና ጀብድን መፈፀም ችሏል። የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ አጠፋለሁ ብሎ ደንፍቶ ወደ ክልሉ የገባው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት የጅብና የአሞራ ሲሳይ ሆኖ ለወላጅ ቤተሰቦቻቼው መርዷቸው ሳይደርስ የውሀ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። ወላጆች ልጆቻችሁን ከዚህ አስከፊ አገዛዝ ልትጠይቁ ይገባል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ106ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር ቢቸና ደብር፣ ወይራ ጠልማ፣ የቀጋን፣ የትመን፣ የዕድውሃ፣ መርገጭ ቀሌዎች ላይ የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ተልዕኮ አስፈፃሚ የነበሩ መከላከያ፣ አድማ በትን፣ ሚሊሻ አባላት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ ድል ተቀዳጅቷል። 64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 25/2018 ዓ.ም ~~~~~~~~ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር በእነማይ ወረዳ ቢቸና ደብር፣ የቀጋን፣ ወይራ ጠልማ፣ የትመን እና ሸበል በረንታ የዕዱውሃ፣ መርገጭ ንዑስ ከተማ እና ደጀን ወረዳ እናጅማ አካባቢ የሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጋር በመቀናጀት ከባድ ተጋሃድሎ አድርጓል። ክፍለ ጦሩ በስሩ ያሉ ሻለቃዎች በማናበብ ባአካሄደው ውጊያ ድል የተቀዳጀ ሲሆን የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ የነበሩ መከላከያ ሰራዊት፣ አድማ በትን እና ሚሊሻ ደምስሶል። በእነማይ ወረዳ ቢቸና ደብር፣ ወይራ እና ጠልማ ቀበሌ በተደረገው ከፍተኛ ተጋሃድሎ የተገኙ ድሎች:- 🕳1 መከላከያ የሞተ 4 የቆሰለ 🕳2 ሚሊሻ የሞተ 4 የቆሰለ 🕳2 አድማ በትተ የሞተ 3 የቆሰለ ሲሆን በድምሩ 5 (አምስት) የአገዛዙ ስረዓት ተልዕኮ አስፈፃሚ የነበሩ መከላከያ፣ አድማ በትን እና ሚሊሻ ሲወገዱ 11(አስራ አንድ) የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት አባላት ቁስለኛ ሆነዋል። በእነማይ ወረዳ ዴንሳ እነቆራ ቀበሌ አገዛዙን ተልዕኮ ተቀብለው መንገድ በመምራት የብዙ ንፁሃን ነጋዴዎችን ሀብት ንብረት የዘረፉ፣ ያዘረፉ እና ንፁሃንን እየጠቆሙ ያስገድሉ ከነበሩት ቀንደኛ ባንዳዎች ውስጥ #ሞሳየ_አቡከረ የተባለ ቀንደኛ #ሚሊሻ እና ጓደኛው በቢቸና ደብር ጮለሚት አካባቢ በተደረገው ከፍተኛ ተጋሃድሎ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ መንፈስ የተላበሱት የክፍለ ጦሩ ሰራዊት አባላት ተወግደዋል። የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ለማካሄድ በተዘጋጀባቸው ቦታዎች የክ/ጦሩ አመራሮች በአይን ጥቅሻ በመናበብ የክ/ጦሩ የቡድን መሳሪያዎች እና እንደ ንብ የሚናደፍ የአባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ልጆች ጠላት ወደ አለባቸው ካንፖች በመጠጋት የሞርተር ቅንቡላ ወደ አገዛዙ ካንፕ በመወረወር ትንኮሳ እና ውጊያ በማካሄድ የሐሰት ምርጫው እንዳይከናወን ተደረጓል። በእነማይ እና ሸበል በረንታ አገዛዙ ያዘጋጀው የሐሰት የምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍል የአገዛዙ የሐሰት ምርጫን በተመለከተ ፋኖ ያወጠውን መግለጫ ወደ ተግባር በመቀየር ይህንን ስረዓት ነቅሎ ለመጣል በከተማ የሚኖረው ማህበረሰብ ቤቱን በመዝጋት፣ ወደ ገጠር በመውጣት ለፋኖ ያላቸውን አጋርነነት በተግባር አሳይተዋል። "ህዝብን በድሮን እና በከባድ መሳሪያ እየጨፈጨፉ ሰላማዊ ምርጫ አለ እንዴ" አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!! ግንቦት25 /2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት