ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多2 952
订阅者
+424 小时
+147 天
+38830 天
帖子存档
#ሰበር_የድል_ዜና
በሸዋ ከሁከቱ ኮሮች የተውጣጡ ጥቂት ሻለቆች እጅን በአፍ የሚያጭን ጀብድ ፈፀሙ:: ራሱን ጥምር ጦር ነኝ ብሎ የሚጠራው ቀይ ቦኔት ለባሹ የሀገር የመከላከያ ኮማንዶ, የአማራ አድማ ብተና እና የአማራ ሚሊሻ እንደ ቅጠል እየረገፈ ይገኛል::
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዛሬ እሁድ ከማለዳ 11:00 ጀምሮ ከሁለቱ ኮሮች በተውጣጡ ጥቂት ሻለቃዎች በደብረብረሃን ከተማ ዙሪያ እያካሔደ ባለው ጠንካራ የቅንጅት ኦፕሬሽኝ የአገዛዙ ሪፓብሊካን ጋርዶችን ጨምሮ በርካታ አየር ወለድ ኮማንዶ አባላት፣ የማራ አድማ ብተና እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ተደምስሷል።
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከአፄ አምደ ፅዮን ኮር እና ከአፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የተወጣጡ የክፍለጦር ውስን ሻለቆች የአንበሳውን ድርሻ በወሰዱበት አስደማሚ ልዩ መብረቃዊ ኦፕሬሽን ዘመናዊ ሹተርን (Shutter) ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ ጥርጥር ክላሽን ኮቭ እና በርካታ ተተኳሽ እንዲሁም የአገዛዙ ሰራዊት በምርኮ ሲያዙ፣ በርካቶች ተደምስሰዋል።
ጀግናው የፋኖ ሰራዊታችን የአውደ ውጊያ አድማሱን አስፍቶ በደብረብርሀን ዙሪያ እያካሔደ ባለው የተቀናጀ ውጊያ በአይነቱ ለየት ያለ ድል እየተጎናፀፈ ሲሆን ፣ በርካታ የአየር ወለድ አባላቱ ቁስለኛና አስክሬን በ 4 አንቡላንሶች ወደ ደብረብርሃንና አዲስ አበባ እያመላለሰ ይገኛል።
በሌላ የደፈጣ አውደ ውጊያ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አጼ ዘር ዓያዕቆብ አንደኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ትላንት ማታ ማለትም በቀን 23/08/208 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከአጣዬ ከተማ ተነስቶ ወደ ጨፋ ሲጓዝ የነበረ ሚሊሻ በጫነ ተሽከረካሪ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ዋናው አስፋልት ልዩ ቦታው እንቶሌ በሚባል አካባቢ ደፈጣ በመጣል ፋኖዎቹ ታሪክ ሰርተዋል። በዚህም በመኪናው ላይ ተጭነው የነበሩት ሚሊሻዎች በርካቶቹን መደምሰስ ተችሏል።
ዕዙ እየተካሄደ ያለውን የአውደ ውጊያ መረጃዎችን አሰባስቦ በዝርዝር የሚመለስ መሆኑን እየጠቆምን ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን በመግለፅ በድጋሚ ድል ለጀግናው የፋኖ ሰራዊታችን እንመኛለን።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 23/2018ዓ.ም
+9
➤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር በደብረ ብርሃን ዙሪያ ደማቅ አኩሪ ድል ተቀዳጅቷል !!! 💪🔥
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ‼️
በአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ጊ/መንግስት አስተዳደር የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት:
64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
~~~
ኩሩው አማራ በመሠረታት እና በኖረባት ሀገሩ ዘሩ እንዳይቀጥል ለበርካታ ዘመናት ሙህራኑን እና የነቃ ዜጋውን ሁሉ ሲገብር ቆይቷል። ታሪካዊ ጠላት ነን ባዮች የሐሰት ትርክትን እየፃፋ ለብሄር ጥላቻም ዳርገውት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ ለመኖር አቅቶት ይባስ ብሎም በእድሜው ያፈራውን ቤት እና ሀብት ንብረት እየተወረሰ ጠላቶቹ ወደሠሩለት የብሔር አጥር ብቻ እንዲኖር ተፈርዶበታል።
ሆደ ሰፊነቱ ከልክ ሲያልፍ በሰላማዊ ሠልፉ አትግደሉኝ ቢልም እንደ ልማደኛ ሲቆጥሩት ይህን የጭቆና ቀንበር አሽቀንጥሮ ለመጣል ነፍጥ ካነሳ እነሆ 3 ዓመት ሞላው። በእነዚህ የትግል ዓመታት በዓለም ተፈፅሞ የማያውቅ የጦር ወንጀሎች ተፈፅመውበታል።
✍️ ንፁሀን በድሮን እና በከባድ መሳሪያ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፣
✍️ የሀይማኖት እና የህዝብ ተቋማቱ በሙሉ ወድመዋል፣
✍️ በሺዎች የሚቆጠሩ የነቁ ሙህራን አድራሻቸው ጠፍተው እስር ቤት ወርደዋል፣
✍️ብዙ ሺዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በድንኳን እንዲኖሩ ተደርጓል፣
✍️የኢኮኖሚ ፖለቲካዊ አሻጥር ተሠርቶበታል። ሞኝ መሳይ ገዥዎቹ ይህን ሁሉ ደባ እየፈፀሙበት ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ዘሩን ፈፅሞ ያጠፉ ዘንድ ሠላማዊ ምርጫ እያሉ ይላላጣሉ። ለዚሁም አንድም እውነተኛ ተፎካካሪ ፓርቲ በሌለበት ብል*ግና ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የምርጫ ቀን ብለው ቢወስኑለትም በተቆጣጠሯቸው ጥቂት የወረዳ ከተሞች የምርጫ ኮረጆዎች አስቀድመው ተሞልተው ተቀምጠዋል። ምክንያት የምርጫ ታዛቢም ሆነ የሚሞግት ተፍካካሪ ባለመኖሩ ነው።
በዚህም መሠረት የማይታጠፍ የትጥቅ ትግል የጀመረው ድርጅታችን አፋብን በተቆጣጠረው 80% ነፃ ግዛቱም ሆነ፣ ጠላት በተቀመጠበት ከተማ ምንም አይነት የማደናገሪያ ምርጫ መካሄድ ስለሌለበት፦
1ኛ.በከተሞች ያለ ማህበረሰብ የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣
2ኛ.በጊ/መንግስት አደረጃጅት ስር ያለው የጎበዝ አለቃ ጦር ለግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለትዕዛዝ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠባበቅ በጥብቅ እናሳውቃለን።
ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም!! አማራነት ወይም ሞት ድል ለአማራ ፋኖ !! ድል ለአማራ ህዝብ!!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !!
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
ፋኖ ሞገስ ውዱ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ጊ/መንግስት ኃላፊ
ሰበር ዜና!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር ደባርቅ ከተማ በልዩ ኦፕሬሽን የአገዛዙን 53ኛ ክፍለጦር አመራር ከነ ሶስት አጃቢዎቻቸው ወደ ላይ ሽኝት አድርገውለታል።
በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጠላት ግን ወረዳ በዛሬው ዕለት በዝግ አዳራሽ ምርጫ መደረጉ ተረጋግጧል።
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~
በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጥላት ግን ወረዳ በቁይ ከተማ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ብቻ ብልፅግና ምርጫ ለማስፈፀም ወስኖ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ግንቦት 24 በቁይ ከተማ ውጊያ ይከፈትብኛል ብሎ በመስጋት የሁለቱን ቀበሌ ምርጫ አስፈፃሚዎችን በመጠቀም በዝግ አዳራሽ የምርጫ ወረቀት በኮሮጆ ሲያስገቡ ውለዋል።
በወረዳው ካሉ 25 ቀበሌዎች 22ቱ በፋኖ ቁጥጥር ስር በማዋላቸው ከቁይ ከተማ ውጭ መንቀሳቀስ የማይችለው የብልፅግና ስርዓት፦
- አርሶአደሮችን ( የመሬት ማረጋገጫ ደብተር መዝገብ ከመሬት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ)፤
- ነጋዴዎችን( ከንግድ ፍቃድ ማረጋገጫ - ከንግድ ፅ/ቤት ሰነድ በመውሰድ)
- የሐይማኖት አባቶችን (ከወረዳው ቤተ ክህነት መዝገብ በመውሰድ)
-ተማሪዎችን ( ከሁለተኛ እና አንደኛ ት/ቤት በተጨማሪም ከትምህርት ጽ/ቤት መዝገብ በመገልበጥ) ምዝገባና ድምፅ በኮሮጆ የማስገባት ሒደቱን መፈፀሙን አረጋግጠናል።
ይሁን እንጂ እስከ አሁን
ከቁይ- ደብረ ማርቆስ
ከቁይ- ቢቸና
ከቁይ- ናብራ ፣ ደብረ እየሱስ፣ የዳማ የሚወስዱ የትራንስፖርት መስጫ መንገዶች እንደተዘጉ ሲሆን በደባይ ጠላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማን ጨምሮ ካሉ 25 ቀበሌዎች ውስጥ ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ካሉ 25 ቀበሌዎች መካከል ፦
1.ደቤት
2.ገሜ.
3.አንገች
4.አጋምና
5.ወደብ ኢየሱስ
6.ይጥባቆ
7.ደብር ከተማ
8.ደብር ዙሪያ ቀቀሌ
9.ሽሜ
10.እነቆይ ቀበሌ
11.ናዝሬት መድሐኒአለም
12.ናብራ ሚካኤል
13.ናብራ የባላት
14.ናብራ ጎቻ
15.ቅድስቴ
16.የባባት
17.የዳማ
18.አፈራሜ
19.ጀረምስ
20.አራጆ
21.እመውላድ
22.ቁይ ዙሪያ ቀበሌዎች በ206ኛ ኮር 24/ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ ቁጥጥርስ ሲሆን የደባይ ጠላት ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት በሁሉም ቀበሌዎች መንግስታዊ መዋቅር በመዘርጋት እያስተዳደራቸው ይገኛል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
ጎጃሜ ቡዳ ነው አወ ቡዳ ነው፤
ቢበላ አይደለም ወይ ነጭ ያነካው፤
ቢበላ አይደለም ወይ ውጦ ያስቀረው።
ዛሬ በጠዋቱ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ በኦባማ መኪና ሲንቀሳቀስ የነበረውን ጠላት ከነተሽከርካሪው ከጥቅም ውጭ አድርገውታል።
ይህን ዘመናዊ ሹተር መሳሪያ የታጠቀው 64ኛ ክ/ጦር በፈፀመው ጥቃት በርካታ የጠላት ኃይል ደምስሷል። በቢቸና ከተማም ምርጫ አስፈፃሚዎች ቀብር አስፈፃሚዎች ሁነዋል። በከተማዋ የባንዳ ልቅሶና እሪታ እየቀለጠ ነው።
እናማ አው "ቡዳ" ነን !! በላይ እየመጡ በታች ሲጠበቁ ማለት አሁን ነው።
+9
"ምርጫ ብሎ ነገር የለም " ያለው የባሶሊበን ወረዳ ህዝብ ከ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጋር ውይይት አድርጓል።
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በአማራን ህዝብ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት ጦርነት የከፈተው የብልፅግና ስርዓት ያዘጋጀውን ምርጫ መንግስታዊ ውንብድና ነው ያለው የባሶሊበን ህዝብ ከ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጋር እየመከረ ይገኛል።
በባሶሊበን ወረዳ የአገዛዙ ሰራዊት ሴቶችን እየደፈረ ንፁሐንን እየረሸነ ፣ በድሮን፣ በመድፍ እና በታንክ የታገዘ ጦርነት እንደቀጠለ ባለበት ነባራዊ ሁኔታ ይደረጋል የተባለው ምርጫ በዲሽቃ፣ በሞርተር እና በአረመኔው ሰራዊት ታጅቦ በሁለት ቀበሌዎች ብቻ ለማከናወን መወሰኑ የብልፅግናን ወንበዴነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አንስተዋል።
አፋብን የጣለው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ሙሉ ለሙሉ የተተገበረ ሲሆን ህዝቡ ከትግሉ ጎን መቆሙን ያረጋገጠበት እንደሆነም ተገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር የሻላቃ መሪውን፣ ብሬን ተኳሽ ጨምሮ 10 የአድማ_ብተና፣ ፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በደፈጣ ኦፕሬሽን እስከወዳኛው ሲያስወግድ 7ቱ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል!!
64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~~~~~~
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሃንዲስ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ ቀበሌ የአገዛዙን የሐሰት ምርጫ እና አፋብን ያወጣውን የመንገድ ክልከላ በጣሰ ባጃጅ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ለማስፈፀም ከየትመን ከተማ ወደ ቢቸና ከተማ በአንድ ኦባማ በጉዞ ላይ የነበሩ አድማ_ብተና፣ፖሊስ እና ሚሊሻ የጫነ ተሽከርካሪ በወሰደው ልዩ የደፈጣ ኦፕሬሽን ድል ተቀዳጅቷል።
በክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ አባላት ቁጥጥር ስር የዋለው ባጃጅ ለማስለቀቅ ከየትመን ከተማ በአንድ ኦባማ በጉዞ ላይ የነበሩ አድማ_ብተና፣ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላትን በመያዝ ወደ ሁለት አንባ ዲቢሳ ቀበሌ ያቀና ቢሆንም በጀግኖቹ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጅች በፊደራል መንገድ ጥቁር አስፖልት ሁለት አምባ ዲቢሳ ልወያ ጎጥ ላይ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት የአገዛዙ ቅጥረኛ #ሚሊሻ አባላት ወደ አፈርነት ተቀይረዋል።
የ64ኛ ክ/ጦሩ ቀኝ እና መሃንዲስ በሰራው ልዩ የደፈጣ ኦፕሬሽን 10 የሞተ ሲሆን 7 ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ላለም ጌታነህ አድማ_ብተና ሻለቃ መሪ የሞተ
2ኛ. ፖሊስ ይታያል ሙሉቀን ብሬን ተኳሽ የሞተ
3ኛ. ቢያድግ አይችሉም የማህበራት ፅ/ቤት ኃላፊ ቀላል ቁስለኛ
4ኛ. ሚሊሻ ሰይድ ዳውድ ቀላል ቁስለኛ እና
5ኛ. ሚሊሻ ጌትነት ውበት
6ኛ. ሚሊሻ ስማቸው ይሆንስ
7ኛ. ሚሊሻ ይበልጣል ሽፈራው ከባድ ቁስለኛ በመሆን ደ/ማርቆስ ሆሲፓታል የገቡ ሲሆን ስማቸውን ለግዜው ማግኘት ያልቻልናቸው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት በአንድ ፖትሮል እና አንድ አንቡላስ ሙት እና ቁስለኛ ሆነው ቢቸና ከተማ መግባታቸው ተረጋግጦል። በዚህ የደፈጣ ጥቃት ሚሊሻዎችን የጫነ አንድ ኦባማ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
በፋኖ ሀይሎች ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ #ሹፊር አየለ ግሩም የተባለ የቢቸና ተወላጅ አስገድደው እንዲጭናቸው ከአደረጉ በሆላ ለፋኖ ቀድመህ መረጃ በመስጠት ነው በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ገለውታል። በየትመን ከተማ አቶ በላይነህ አድማስ የተባለ ንፁሀን በአራት ጥይት ተመቶ ከባድ ቁስለኛ የሆነ ሲሆን በደጀን የመጀመርያ ደረጃ ሆሲፒታል በመግባት ህክምና እያገኘ ይገኛል።
የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር ቀኝ እና መሃንዲስ በሰሩት ከባድ የደፈጣ ጥቃጥ አገዛዙ በድንጋጤ ውስጥ መግባቱ የተነሳ ከደ/ማርቆስ፣ ደጀን፣ የትኖራ፣ ጢቅ የሚገኝውን የሰው ሀይሉን ከከባድ መሳሪያዎች መድፍ፣ ዙ23፣ አራት ድሽቃ የመሳሰሉት በመያዞ በሸበል በረንታ መረገጭ ንዑስ ከተማ በመግባት ወደ አራጢ ከተማ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ ውሏል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት ዘግይተው የሚደርሱን ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝባችን፣ ለትግሉ ደጋፊ እና ለሰራዊታችን መረጃው እንደደረሰን በክ/ጦሩ ድር ገፅ የምንገልፅ መሆኑን እናሳውቃለን።
ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም!! ወጥር አማራ🔥
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ግንቦት22/2018 ዓ.ም
Yibeltal Getie Mitiku
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት
የአገዛዙ 103ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባላት መክዳትን ተከትሎ የፋኖ አመራሩ ወላጅ እናት በብልፅግናው አመራሮች መታሰራቸውን ኮሩ አስታወቀ።
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
ያለማቋረጥ በርካታ የ103ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባላት በየቀኑ ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ግንቦት 22 ቀን 2018ዓ.ም የክፍለጦሩ ጋንታ መሪ የኦሮሞ ብሔር ተወላጁ ፶ አለቃ ፈይሳ ገመቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦርን መቀላቀሉን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል።
የመከላከያውን ፍለሰት ተከትሎ "ልጅሽ ሰራዊታችንን እያስኮበለለብን ነው" በሚል የፈጠራ ወሬ ከቀጠናው ውጭ የሚገኘውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ምክትል ዘመቻ ኃላፊ የፋኖ መመኪያ መሸሻ ወላጅ እናት የሆኑትን ወ/ሮ አሳበች መንገሻ በአገዛዙ ኃይሎችና በመከላከያ አመራሩ ትዕዛዝ ሰጭነት ከግንቦት 18/2018ዓ.ም ጀምሮ በአጣዬ ከተማ ዝግባ ሰፈር የመከላከያ ካምፕ ውስጥ በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።
በዚሕ አረመኔ ድርጊቱ ያላቆመው የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል የኤፍራታና ግድም ወረዳ የመተኬ ሸረፋ ነዋሪ የሆኑትን የሁለት አባት አርበኞችን የአቶ አውራሪስ ማሞን ሁለት በሬዎች እና የሴት ልጁን ሳምሰንግ ዘመናዊ ስልክ እንዲሁም የአቶ ካሳዬ ክብረትን አንድ በሬ በመዝረፍ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት በማሰብ ለኢድ ዓል-አድሃ (አረፋ) በዓል ለመከላከያ ሰራዊቱ የተዘረፉትን 3 በሬዎች መታረዳቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
አገዛዙ እንደ ህዝብ የአማራን ህዝብ እየገደለና ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ውድቀት እየዳረገው መሆኑን መላው ህዝባችን ጠንቅቆ በማወቅ በውድቀቱ ዋዜማ ላይ የሚገኘውን አሸባሪ ስርዓት ለመጣል በሀሰተኛ የምርጫ ድራማ ላይ ባለመሳተፍ ከፋኖ ጎን ተሰልፎ ነፃነቱን እንዲያውጅ ሲል ኮሩ መልዕክቱን አስተላልፏል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 22/2018ዓ.ም
+3
ሰበር ዜና!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ አማራ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር በዘመቻ አንሻ ሰይድ ከወንድም 101ኛ ኮርና ልዩ ዘመቻ በጋራ ግንቦት 20/2018ዓ/ም በብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ በተኩለሽ ከተማ ዙሪያ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወቃል።
በመሆኑም አሁን በደረሰን መረጃ የ102ኛ ኮር የ65ኛ ከፍለጦር በወሰደችው የሞርተር 82 ኢላማውን የጠበቀ ድብደባ በማድረግ የአገዛዙን የ45ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሌኔል ተርፋታን ጨምሮ ድሽቃ ምደብተኞቾን ልዩ ቦታው አምዳምባ አቦ 026 ቀበሌ ላይ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል።
በተጨማሪም የጠላት 45ኛ ክፍለጦር ድሽቃ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ወጭ መሆኑን የውስጥ መረጃችን አድርሶናል።
ሌላው የብልፅግና ወንበር ጠባቂው የ45ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሌኔል ተርፋታ ዛሬ ግንቦት 22/2018ዓ/ም በሐራ ከተማ ከሌሎች የሬጅመንት አመራሮች ጋር የቀብር ስነ-ስርዓታቸው መከናወኑን የውስጥ መረጃዎቻችን ገልፀውልናል።
በመጨረሻም የጠላት 45ኛ ክፍለጦር ዙ-23 በቀድሞው ዞብል አምባ ክፍለጦር የአሁኑ 12ኛ ክፍለጦር ሜካናይዝ አልሞ ተኳሾች በወሰዱት ስብጥር የሞርተርና የድሽቃ ተኩስ ሙሉ በሙሉ እርምጃ ተወስዶበታል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብን ወሎ(ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃዉን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!!
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
የትውልዱ መሪ የአማራ ፋኖ ልዩ ምልክት አቢዮተኛው የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በስራ ላይ
እስኪ ለአንድ አፍታ ቆም በሉና የነጻነትን ዋጋ እናስተውል…
ዛሬ በአራቱም የአማራ ግዛቶች እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት በቃላት የሚገለጽ አይደለም። በምቾት ዓለም ውስጥ ሆነን ስልካችንን ስናነሳ፣ እዚያ ማዶ ግን ስንቱ የሚወደውን ሞቅ ያለ ቤቱን፣ ስንቱ ናፋቂ ልጆቹንና ውድ ቤተሰቡን በትኖ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል።
የአማራ ልጅ ፋኖ እንደ ማንኛውም ሰው “በርገር ልብላ፣ የደላኝ ሕይወት ልኑር” አላለም። የሚወዳትን አንዲት ነፍሱን ሳይሳሳ ለአማራ ሕዝብ ሕልውና አሳልፎ የሰጠው፣ የአረመኔው ሥርዓት ወገኑን ለማጥፋት ሌት ከቀን እየሠራ መሆኑን ስላወቀ ነው—ይህ ደግሞ ጥቁርም ነጩም የሚያውቀው የትውልድ ሐቅ ነው!
ነገር ግን... ልብን በሀዘን የሚሰብረው ትልቁ ሕመም ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እነሱ በረሃብና በጥም እየተቃጠሉ፣ የጥይት ናዳ እየተጋፈጡ ደማቸውን ሲያፈሱ፤ እዚህ ማዶ ግን አንዳንድ ወገኖች ለሚዲያ ፍጆታና ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅም ሲሉ የፋኖን ስም እየለዩ ይሰድባሉ። ይህ እጅጉን ልብ የሚሰብር አማራዊ ክህደት ነው!
📌 ቆም ብለን የምናስበው እውነት፡ አማራን ማዳን የምንችለው ጀግኖችን በመሳደብና ስም በመስጠት አይደለም፤ ጀግኖችን በዕውቀት፣ በሃሳብና በጉልበት በመርዳት እንጅ! ከታች ካለው ተዋጊ ጀሌ ጀምሮ እስከ ንጉሱ ዘሜ (ዘመነ ካሴ) ድረስ እያንዳንዱ የአማራ ልጅ የሚከፍለው መስዋዕትነት ለአንድ ዓላማ ብቻ ነው ለአማራ የመኖር ነፃነት!
እንደ ኢትዮጵያ ተወልደን፣ እንደ አማራ የምንታረድባትና የምንሞትባት ሀገር እንድትኖር የአማራዊ ተፈጥሯችንና የማንነት ክብራችን በፍጹም አይፈቅድልንም! ውድ በውስጥም በውጭም የምትኖሩ አማራውያን… ታሪክ ጥሪውን እያቀረበ ነው። ከቻላችሁ ኑ፣ ክንዳችንን አስተባብረን አብረን እንስራ። ካልሆነ ግን የጀግኖችን ሞራል አንስበር።
ይህ መልዕክት የሁላችንም የቤት ሥራ ነው። ትግሉ የጋራችን እንደመሆኑ መጠን፣ ከተመቻችሁ ለመላው የአማራ ፋኖ ትግል ደጋፊዎቻችን በሙሉ ሼር በማድረግ አድርሱልን! ✊❤️
#Dawit #Amhara ቀጥታ ከግንባር 👑 ከንጉሶች መንደር
Repost from ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
የጀግንነት ማህደር የዋልታ እና የማገሩ ስልጣኔ አርበኛ መከታው ማሞ፤
አማራ ማለት ለዚህች ውድ አገር ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ነው! ታሪክ የገመደው፣ ጀግንነት የወለደው ይህ ታላቅ ህዝብ፣ ለሀገረ መንግስቱ መመስረትና መጽናት የማይናወጥ አለት ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።
ከዳግማዊ አፄ ሚኒልክ መንገሻ፣ ከታላቋ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት... ታሪክ ደጋግሞ ከሚያነሳቸው የጀግኖች አውድማዎች መካከል የሸዋ መሬት ቀዳሚዋና ዋናዋ ነች። ይህች መሬት በአቀማመጧ አስደናሚ ናት ደመናን የሚቧጥጡ ተራራዎቿ፣ ቅዝቃዜያቸው አጥንት የሚሰረስር ብርዳማ ስፍራዎቿ፣ እና ታሪካዊ ሚስጥርን ያቀፉት ቆላማ ግዛቶቿ የጀግኖች መፈልፈያ እቶን ሆነው አገልግለዋል።
በዚሁ አስገራሚ መልክዓ ምድር በታላቁ ስምጥ ሸለቆ፣ በሸዋረቤት ዙሪያ ተፈጥሮ ካበቀለቻቸው እምቡጥ ጀግኖች መካከል ዛሬ የአንዱን ስም በወርቅ ቀለም እንድፅፍ አማራዊ ግዲታዬ ያስገድደኛል። እርሱ.የታላቁ የአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት የሆነው የድርጅታችን (የአፋብን) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ ነው!
እርበኛ መከታው ማሙ በንግግሩ መልካም፣ በአስተሳሰቡ እጅጉን ጥበበኛና አስተዋይ ሰው! ከመሆኑም በላይ የአርበኛው መከታው ማሙ ማንነት የሚገለጠው በቃላት ድርደር ብቻ አይደለም። የእርሱ መልካም ባህሪ፣ ለህዝቡ ያለው ተቆርቋሪነት፣ እና በጦር ሜዳ ላይ የሚያሳየው ስልታዊና አስደማሚ የሰራዊት እንቅስቃሴ እርሱ እውነተኛ፣ ባለማዕተብና ታማኝ የአማራ ልጅ መሆኑን በግልጽ ያሳብቃሉ።
እርሱ ለወገኑ ጋሻ፣ ለጠላት ደግሞ የማይሻገር የቁም ቅዠት ነው! በሸዋ ምድር የበቀለው ይሄ ጀግና፣ የአባቶቹን አደራ ተሸክሞ፣ የማንነትንና የነጻነትን ሰንደቅ አንግቦ በቁርጠኝነት እየተጓዘ ይገኛል።
ታሪክ ሁሌም ጀግኖቹን ያስታውሳል። የሸዋ መሬት ዛሬም እንደትላንቱ መከታዎችን ማፍራቷን ቀጥላለች! የአርበኛ መከታው ማሙ የጀግንነት ጉዞ ይቀጥላል! #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር!!
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
