ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 387
订阅者
+124 小时
+757 天
+1 40730 天
帖子存档
ኩልመስክ ዙሪያ ላይ አንድ ዙ23 መሣሪያ መውደሙ ተሰምቷል! በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር በአርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ የምትመራው ተከዜ ክ/ጦር
ኩልመስክ ዙሪያ ላይ አንድ ዙ23 መሣሪያ መውደሙ ተሰምቷል! በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር በአርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ የምትመራው  ተከዜ ክ/ጦር ልዩ ዘመቻ አባላት ኩልመስክ ዙሪያ ልዩ ቦታው ቻይና ካምፕ አከባቢ ላይ ባደረጉት ተጋድሎ አንድ የጠላት ብልፅግና ዙ-23 መሣሪያን ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አሳውቋል። በተደረገው ተጋድሎ ከወደመው ዙ23 በተጨማሪ ከከባድ መሣሪያው ጋር የነበሩ አራት ወታደሮች ሲገደሉ ሦስቱ ቆስለዋል ብሏል ዕዙ ለጣቢያችን በላከው መረጃ። በተያያዘ ዜና! ጥቅምት 29/2018 ዓ/ም በተከዜ ክፍለ ጦር ስር የሚትገኘው አምስተኛ ሻለቃ ባደረገችው ተጋድሎ በደላንታ አከባቢ በግለሰብ አይሱዙ ይጓዝ የነበረን የጠላት ኃይል ልዩ ቦታው ዥጣ ወንዝ ላይ በመጠበቅ በፈፀመችው ጥቃት አምስት የፀረ አማራው ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ሲገደሉ ዘጠኙን አቁስላለች ብሏል ዕዙ።

አርበኛ ፋኖ ዶክተር አብደላ እና አርብኛ ፋኖ ዳግም ከሸዋ ሰማይ በጥቁር አስፓልት ወደ ፊት ብቻ ❤💪

#ዙ_23_በአናብስቶች_ወደመ‼️ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ልዩ ዘመቻ ባደረገው ትንቅንቅ ልዩ ቦታው ቻይና ካምፕ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ በተደረገ ትግል አንድ የአገዛዙ ዙ-23 ከጥቅም ውጭ የተደረገ ሲሆን እዛው የነበሩ አራቱ ሲደመሰሱ ሦስቱ ቆስለዋል። በተያያዘ መረጃ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በተከዜ ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው አምስተኛ ሻለቃ ባደረገው ተጋድሎ ከወደ ደላንታ በግለሰብ አይሱዙ ይመጣ የነበረውን ጠላት ዥጣ ወንዝ ላይ በመጠበቅ አምስቱን ሲደመስስ ዘጠኙን አቁስሏል። በዚህ የተናደደው የጠላት ኃይል የግለሰብ ባጃጅ አቃጥሎ ሄዷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጥራሪ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 29/ዐ2/2018 ዓ.ም

🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 ከ ሰፊ የሥራ አዝመራዎች መካከል ከ "አለም አቀፉ የ ዐማራ ማህበራት ህብረት" ተቀጣጣይ እና ቀጣይ ተግባራት ውስጦች ላይ ይቀጥላል... "የዐማሓራ እናቶች እንባ" የ
+2
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 ከ ሰፊ የሥራ አዝመራዎች መካከል ከ "አለም አቀፉ የ ዐማራ ማህበራት ህብረት" ተቀጣጣይ እና ቀጣይ ተግባራት ውስጦች ላይ ይቀጥላል... "የዐማሓራ እናቶች እንባ" የ ዐማራ እናቶች እንባ በሚል የጠራው አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ እየተካሄደ ነው!! የአማራን ሕዝብ ሰቆቃ የአማራ ፋኖን ተጋድሎ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ በማሳየት ዓላማ ላይ ያሰመረ የአማራ ሰልፍ። . . .

ፋኖ በሰሜን ጎንደር አዳርቃይ እና ዛሬማ አካባቢ ታላቅ ድል ፈፅሟል። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ  የራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር ድብ ጠለምት ተከዜ እና ጭና ክፍለጥር በጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ ድል መቀዳጃታቸዉን አስታዉቀዋል። ከጥቅምት 26/2018 ዓ.ም እስ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም ድረስ በነበረዉ እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ በመደርዘን የሚቆጠር የስርአቱ አገልጋይ ሰራዊት ድል ተደርጓል። የአገዛዙ ብልፅግና የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሶስት ክፍለጦር ሰራዊት በአዳርቃይ እና ዛሬማ ቢሰማራም አብዛኛው ሰራዊት መደምሰሱ ተገልጿል።ለአራት ተከታታይ ቀናት በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ ከ90 በላይ የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ 80 የነፍስወከፍ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ደግሞ ምርኮ ተደርጓል። ጥቅምት 27 ለጥቅምት 29 አጥቢያ ሌሊቱን የድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦርን የከበበዉ የአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛ የሆነ ሽንፈትን አስተናግዷል።በለሊቱ በተደረገዉ አዉደዉጊያ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰራዊት መደምሰሱን የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ራስ አሞራዉ ዉብነህ ሶስተኛ ኮር ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ እሸቱ መለሰ ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግሯል። አዉደዉጊያዉ ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፋኖ በርካታ ወታደራዊ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል ።በፋኖ ከፍተኛ ምት ያስተናገደዉ እና አብዛኛው ሰራዊት የተደመሰሰበት የብልፅግ ጡት ቆራጭ ሰራዊት በሰላማዊ ዜጎች ሀብት እና ንብረት ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።

በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በዕዙ የተሰጡትን የስራ አቅጣጫዎች ተቀብሎ ወደ ስራ ተገብቷል። ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ
+1
በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በዕዙ የተሰጡትን የስራ አቅጣጫዎች ተቀብሎ ወደ ስራ ተገብቷል። ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮሶ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በከፍተኛ የዕዙና የከር አመራሮች የተሰጡትን የስራ አቅጣጫዎች በመቀበል በዛሬው ዕለት በአዲሱ አደረጃጀት የክ/ጦሩ አመራር ስብሰባ በማድረግ አሀዱ ብሎ ስራውን በይፋ ጀምሯል።በዚህም ስብሰባ የተሰጡትን የትኩረት የስራ አቅጣጫዎች ልቅምአድርጎ  በመያዝ ባሉት ሁሉም ሻለቃዎች የክ/ጦሩ  አመራሮች ስምሪት በመያዝ ተለያይተዋል!!!!    መልካም የስራ ዘመን!!!!! አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ

ከአርሲ ጥቃቶች የደረሱን ፎቶዎች ናቸው። ጥቅምት 29/2018 ዓ/ም
+3
ከአርሲ ጥቃቶች የደረሱን ፎቶዎች ናቸው። ጥቅምት 29/2018 ዓ/ም

ከዛሬ ጀምሮ እኛ ከትግል ሚዲ ከመሪዎቻችን ሃሳብና የመላው አማራ የነፃነት ትግል የውይይት ቀን ይሁንና ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ እንወያይ! 1, ትግሉ አሁን እየሄደ ካለበት ፍጥነት አኳያ እንዴት ትገመግሙታላችሁ? ከዚህ በተሻለ ፍጥነት እንዲሄድ ከማን ምን ይጠበቃል ? እኛስ ምን እናድርግ? 2, ለትግሉ ዋና ማነቆዎች ምን ምን ናቸው? እንዴትስ እናስወግዳቸው? 3, የ ሳይበር ወይም የሚዲያ ጦርነቱ እና ፕሮፖጋንዳው በቂ ነው ወይስ አይደለም?  ካልሆነስ ክፍተቶች ምን ምን ናቸው እንዴትስ የሚዲያ የበላይነትን እንፍጠር? 4, በሚዲያዎቻችን ላይ የሚታዩ ችግሮች ምንድን ናቸው ? እንዴት ይስተካከሉ? እና ሌሎችም መነሳት ያለባቸው ጉዳዮች ካሉ አንሷቸው እና እንወያይበት! በንቃት ተሳተፉ ! ውይይቱ በመወያያ ግሩፓችን ላይ ነው ያልገባችሁ ሊንኩን ነክታችሁ ግቡ! ዛሬ የውይይት ቀን ይሁንና ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ እንወያይ! 1, ትግሉ አሁን እየሄደ ካለበት ፍጥነት አኳያ እንዴት ትገመግሙታላችሁ? ከዚህ በተሻለ ፍጥነት እንዲሄድ ከማን ምን ይጠበቃል ? እኛስ ምን እናድርግ? 2, ለትግሉ ዋና ማነቆዎች ምን ምን ናቸው? እንዴትስ እናስወግዳቸው? 3, የ ሳይበር ወይም የሚዲያ ጦርነቱ እና ፕሮፖጋንዳው በቂ ነው ወይስ አይደለም?  ካልሆነስ ክፍተቶች ምን ምን ናቸው እንዴትስ የሚዲያ የበላይነትን እንፍጠር? 4, በሚዲያዎቻችን ላይ የሚታዩ ችግሮች ምንድን ናቸው ? እንዴት ይስተካከሉ? እና ሌሎችም መነሳት ያለባቸው ጉዳዮች ካሉ አንሷቸው እና እንወያይበት! በንቃት ተሳተፉ ! ውይይቱ በመወያያ ግሩፓችን ላይ ነው ያልገባችሁ ሊንኩን ነክታችሁ ግቡ! 👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

በአማራ ክልል እጃችንን አናስገባም የሚመሩት አማራዎች ናቸው ብሏል አብይ አህመድ። ይህንን የሚለው የአማራ ክልልን በአስቸኳይ አዋጅ ስር በወታደራዊ አገዛዝ የክልሉን መንግስትነት ተረክቦ የሚያስተዳድረ
+1
በአማራ ክልል እጃችንን አናስገባም የሚመሩት አማራዎች ናቸው ብሏል አብይ አህመድ።   ይህንን የሚለው የአማራ ክልልን በአስቸኳይ አዋጅ ስር በወታደራዊ አገዛዝ የክልሉን መንግስትነት ተረክቦ የሚያስተዳድረው ኃይል ነው መሪ ነው:: እጃሁን ብቻ ሳይሆን እግራቸውን ነው ያስገቡት:: ለነገሩ በዛው ንግግሩ ላይ በደቂቃዎች ልዩነት ከጎንደር ጎርጎራ በወታደር ነው የምንቀሳቀሰው ፣ልማትም የምንሰራው ሲል ይደመጣል:: ለምን? አማራ ለምን አማራ መራኝ ብሎ ነው? © በቃሉ አላምረው

ፋሽስቱ አገዛዝ በአንጎት ወረዳ የግለሰብ ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና እንስሳቶችን አወደመ። ስርዓቱ  የግለሰብ ባጃጅ  ያቃጠለ ሲሆን፤እንስሳዎችን ደግሞ ተኩሶ ገሏቸዋል። ጥቅምት 29/2018 ዓ/ም የፋሽስቱ ስርዓት ከአስር በላይ ላም፤በሬና በጎች በአገዛዙ ሰራዊት ሲገድሉ፤አንድ ባጃጅ ደግሞ ሙሉ በሙሉ አቃጥለውታል። ለብልፅግና ስርዓት የአማራ ህዝብ አይደለም እንስሳቱም፤እፅዋቱም፤ንብረቶችም ጥላት ናቸው ብሎ የዘመተባቸው ስርዓት በአንጎት ወረዳ የህዝቡን ንብረት በዛሬው እለት አውድሟል። ባጃጆች ማንነት አላቸው፤እንስሳዎችም አማራ ናቸው። የአማራ ህዝብ ህይዎቱ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውም መውደም አለበት ብሎ የሚያስበው የበሻሻው ስብስብ አፀያፊ ድርጊት በእንስሳቶችና በተሽከርካሪ ንብረቶች ላይ ፀያፍ ድርጊት ፈፅሞባቸዋል። መዳረሻችን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልወና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ህልውናችን በተባበረ ክዳችን አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም

ሰበር መረጃ በአቡነ ሳዊሮስ የሚመራው ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ አጥቢያዎች ለአገዛዙ በቢሊዮን የሚቆጠር ድጋፍ ማድረጋቸው ታወቀ። ከጠቅላይ ቤተ ክህነት 200 መቶ ሚልዮን ብር ወጪ ተደርጓል። ከመላ
ሰበር መረጃ በአቡነ ሳዊሮስ የሚመራው ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ አጥቢያዎች ለአገዛዙ በቢሊዮን የሚቆጠር ድጋፍ ማድረጋቸው ታወቀ። ከጠቅላይ ቤተ ክህነት 200 መቶ ሚልዮን ብር ወጪ ተደርጓል። ከመላው የአዲስ አበባ አድባራት ደግሞ ከዝቅተኛው ደብር 2 ሚልዮን ከከፍተኛው ደብር ደግሞ 10 ሚልዮን ወጭ ተደርጓል። በጥቅሉ 275 አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ የተጣለባቸውን ኮታ ወጪ አድርገዋል። ይሄ ድጋፍ በድምሩ በሚልዮን የሚቆጠር ሳይሆን በቢልዮን የሚቀጠር ንዋይ ነውም ተብሏል። እነ አባ ሳዊሮስ ሥራ አስኪያጅ ሁነው የገቡት እንዲህ ያለ ድጋፍ እንዲያደርጉና የምእመናንን ሞት እንዲያሳልጡ ነው ሲሉ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

👉ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጥቃት ኢላማ  ከሆነች ሰባት የሞት ዓመታት ተቆጥረዋል። 👉የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስተያንን የዘር የማጽዳት ጥቃት ተፈጽሞባታል እየተፈጸመባት ይገኛል። 👉የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድ  የሃይማኖት ሥርዓታዊ ተቋም ለማዳከምና ተከታዮቿ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ግልጽ፣ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃት ከተጀመረባት ከባለፉት ሰባት ዓመታት እስከ ዛሬ ድረስ ጥቃቱ በአብዮት፣ በብሔር እኩልነት፣ በለውጥ እና በግጭት ስም ተሸፍኖ ሲካሄድ ቆይቷል። 👉በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች እልቂት፣ መፈናቀል፣ ስደት፣ከሰብአዊ ህልውና መነጠል ተፈጽሞባቸዋል አሁንም እየተፈጸመም ይገኛል። 👉ኦርቶዶክሳዊንን ማግለል፣ መግደልና ሁለገብ ጥቃት ሥር ማዋል በግልጽ ቢካሄድም አጥፊዎች ሲቀጡ አልታየም። 👉እንዲያውም ፍትህ ለማግኘት ሲጠይቁ ፍትህ መጠየቅ ትምክህተኝነት ነው ብለው እንደገና ያስሯቸዋል ወይም ይገድሏቸዋል። 👉ኦርቶዶክሳዊያንን በገዛ አገራቸው በዘር በቋንቋ እየከፋፈሉ፣ ድብቅ የዘር ፖለቲካ አጀንዳን ወደ ፖለቲካዊ ርዕዮት በማሳደግ፣ በመደራጀት፣ በመዋቀር አመራር በመሥጠትና በመቀበል ከምድረ ገጽ እያጠፉን ይገኛሉ። 👉ኦርቶዶክሳውያንን የማጥፋት ድርጊት የተለያዩ ሰበቦች እየተሰጡ፣ ክሥተት በሚመስሉ ነገር ግን  ተከታታይነት ባላው ስልታዊ አካሄድ የተፈጸመ ነው፡፡ 👉በሞት የተረፉ ከጥላ ያረፉ ኦርቶዶክሳውያንም የዜግነት ጥበቃ ተነፍገው፣ በሕይወት የመኖር መብታቸው ተጥሶ በተለያየ  አሰቃቂ ሁኔታዎች ሥር ይገኛሉ፡፡ 👉ለዚህ ደግሞ በአደባባይ የሚፈጸመውን ይህን የኦርቶዶክሳውያንን ዘር ማጥፋት ድርጊት ማስቆም እየቻሉና ኃላፊነት እያለባቸው ዝምታን የመረጡ አካላት የጥፋቱ ባለቤቶች ናቸው፡፡ 👉እንደ ዜጋ  ሊጠብቁን የሚገባቸው፣ግብር የምንከፍላቸው አካላት መዋቅሮቻቸውን በሥልጣን ውግንና ማኒፌስቶ ቀርጸው ሞታችንን ሲያውጁ ይውላሉ።   👉ጥቃታችንን ማጋላጥና መሞገት የነበረባቸው ብዙኃን መገናኛዎች ግብራችንን እንጂ ሕይወታችንን አልፈለጉትም። 👉ሁሉም በኦርቶዶክሳዊያን ሁለገብ ጥቃት እልቂት የተስማሙ በሚመስል ደረጃ ስለ እልቂታችንና ስደታችንን አንዳች አይናገሩም። 👉ወይንም ሕማማችን አልተሰማቸውም። 👉ወይንም እኛም አንደሚገባ ለራሳችን ቆመን ጥቃታችን እና እልቂታችንን ለሚመለከታቸውና መረጃ ለተነፈጉት አላሳየንም። 👉እዚህ ላይ ይበቃል ማለት ይገባል  የምትሉ ሁላችሁ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እና በሰው ልጅ እኩልነትና ክብር የምታምኑ የሌላ እምነት ተከታዮችም ሁሉ ለሰብአዊነት መቆማችሁን አሳዩን። © የኔታ ገብረ መድኅን እንየው

ሰበር መረጃ!! ሸዋ በመንዝ ምድር አንድ ገበሬ ልጅህ ፋኖ ነዉ በሚል ትጥቁን ሊያስፈቱ ከቤቱ ድረስ የሄዱ 6 የአገዛዙ ሰራዊት አባላትን ገ*ድሎ የጦር መሳሪያቸዉን መማረክ ችሏል።

በአማራ ሕዝብ ስለደረሰው ሰቆቃ ዓለም አቀፍ የዘመቻ ጥሪ: ዓለም አቀፍ የአማራ ንቅናቄ (iAM) ከዓለም አቀፍ የአማራ ግብረ ኃይል  እና ከሌሎች የአማራ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ህዳር 1 እስከ ህዳር 30 ቀን ድረስ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ ዘመቻ በድጋሚ ጥሪ ያደርጋል ። ይህ ዘመቻ በዓለም ዙሪያ ያሉ የአማራ ድርጅቶችን: ግብረ ኃይሎችን እና ደጋፊዎችን ሁሉ በአንድነት በማሳተፍ ተቀናጀ ስራ ላይይገኛል ። ይህ ጥሪ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ሰፊ እና ስልታዊ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የተጀመረ ሲሆን፥ በመንግሥት ድጋፍ የሚካሄድ ጥቃት፣ የጅምላ ግድያ፣ የግዳጅ መፈናቀል እና የዘር ማጽዳት ወንጀልን የምናደርገው ትግል ነው። ዘመቻው ዓለም አቀፍ ግንዛቤን ለመፍጠር፣ የአማራ ዳያስፖራን ለማሰባሰብ እና እነዚህን ቀጣይ ወንጀሎች ለመፍታት ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት እንዲደረግ ለማበረታታት ያለመ ነው። የዘመቻው ዓላም ዓለም አቀፉን የአማራ ማኅበረሰብ በማሰባሰብ እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በጋራ የድጋፍ ጥሪ በማሳተፍ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ ማስቆም ነው። ይሄውም: 1ኛ በአማራ ክልል ውስጥ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶች እና የአየር ድሮን ድብደባዎች ማስቆም። 2ኛ በአማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ እና የጅምላ ግፍ በተመለከተ ዓለም አቀፍ ግንዛቤን ከፍ ማድረግ። 3ኛ በአማራ ሲቪሎች ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግ እና ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ መጠየቅ። 4ኛ ለፍትህ፣ ለእኩልነት እና ለሰብአዊ ክብር መከበር ዓላማ ሲባል አንድ ወጥ የሆነ የአማራ ትብብር ማሳየት። 5ኛ በጥላቻ ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲዎች እና ተጠያቂነት የጎደላቸው ድርጊቶች ላይ ቆራጥ እርምጃ እንዲወሰድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንን፣ የሰብአዊ መብት ተቋማትን እና የፖሊሲ አውጪዎችን ማሳተፍ። በኢትዮጵያ የሚኖሩት የአማራ ሕዝብ በመንግሥት ድጋፍ የሚካሄድ ጥቃት፣ የግዳጅ መፈናቀል፣ ስደትና የዘር ማጽዳት ገጥሞታል። እነዚህ ጥሰቶች ከባድነት ቢኖራቸውም፥ ዓለም አቀፉ ምላሽ ዝምታን መርጧል። በመሆኑም፥ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተጨማሪ ግፍ እንዳይከሰት ለመከላከል እና በአማራ ክልል የሚገኙትን ሲቪሎች ለመጠበቅ እንዲቻል፥ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ፣ በዘር ማጥፋት ወንጀል ስምምነት (Genocide Convention) እና በሰብአዊ መብት ግዴታዎች መሠረት እንዲንቀሳቀስ ጥሪ እናቀርባለን። ዓለም አቀፍ ጥረትእና ትብብራችም  በሚከተሉት የተቀናጁ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ተግባራዊ ይሆናል፦ 1ኛ ቀውሱን ለማሳየትና ከተጎጂው ሕዝብ ጋር ያላቸውን ትብብር ለመግለጽ በዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰልፎችን ማዘጋጀት። 2ኛ የህዝብ ድጋፍን ለማሰባሰብ እና በፖሊሲ አውጪዎች ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር ያለሙ የተቀናጁ ዲጂታል ዘመቻዎች፣ የፊርማ ማሰባሰቦች: ኢሜይሎች፣ የፌስቡክና የትዊተር ግንኙነቶች። 3ኛ የአማራን ቀውስ ለማሳወቅ ዓለም አቀፍ እና ክልላዊ የመገናኛ ብዙኃን በጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ በቃለ ምልልሶች እና በሕዝባዊ ስብሰባዎች ማሳተፍ። 4ኛ ለገለልተኛ ምርመራዎች እና ለሰብአዊ ዕርዳታ ጣልቃ ገብነቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ መንግሥታትን፣ ተቋማትን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አካላትን ኢላማ ያደረገ የድጋፍ ጥሪ ማቅረብን የሚያካትት ይሆናል:: ዘመቻችን ተቀላቀሉ: ትብብራችን ይበልጥ ይጠናከር: የቁጭታች ያህል አምርረን እንታገል: በየግዛቱ: በየሀገሩ እና በየአህጉራቱ እንደራጂ: እንቀራረብ:: ዓለም አቀፍ የአማራ ንቅናቄ ሕልውናችን በክንዳችን!

ብዙ አልፈናል እናልፈዋለንም! የዐማራ የሆነውን ሁሉ ማፍረስ፣ የዐማራ ትግልና የዘር ጭፍጨፋ በጥናትና ምርምር እንዳይደገፍ፣የዐማራ አደረጃጀቶችና ማህበራት የራሳቸው ደንብና መተዳደሪያ እንዳይኖራቸው፣ አታጋይና ታጋይ ድርጅቶችም በጥቃቅን ነግሮች ላይ በማተኮር ዘላቂ ግባቸውን በግርድፉ የሚጠቁምና ለውይይት የሚጋብዙ ማኒፌስቶዎችን እንዳያወጡ እንዲሁም የዐማራ ምሁራን ማህበራት በሰፊው እንዳይደራጁ፣ የሴቶች ወጣቶችና ሙያ ማህበራትም ለዐማራ ህዝብ ዘላቂ የደህንነትና የኢኮኖሚ ዋስትና የሚሆኑ መፍትሄዎች ላይ አተኩረው እንዳይሰሩ ለማድረግ በበጀት የተደገፈ እናፍርሰው ፕሮግራም አሁን አሁን የዐማራን ስትራቴጂክ ጭራ መያዝ ባቃተው የማህበራዊ ሚዲያ ግሪሳ ከንቱ ጩኸት ብቻ እንደሚመራ እየታየ ነው።.የቤተመንግስቱ ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ነጋ ጠባ ተረት ይነግረናል የጠቅላይ ሚንስትሩን የመስክ ጉብኝት ወደ ተረት ይቀይረውዋል፤ የዐማራን የህልውና ተጋድሎም ተረት ይስራበታል፣ የአብይ አህመድን ብልጽግና በተረት እየሸነገለ ዐማራን ለመግደል የሄደው ሰራዊት በእየሄደበት መቅረትም ተረት እያደረገው ራሱም ወደተረትነት የሚቀየርበትን ጊዜ እየጠበቀ ነው።ይዘት (content) አልባ ጩኸት። ምን ይሄ ብቻ የአገዛዙ ብቁና ከፍተኛ የሚባሉት ካድሬዎችም (high level intellectual cadres) በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተመረቱ የቪዲዮና የፎቶ ምስሎችን በየገጾቻቸው በመፖሰት የሰራዊታቸውን ብዛት፣ የልማቱን አይነትና ያገኙትን የህዝብ ድጋፍ ለማሳየት ሲጋጋጡ ይውላሉ። ከሁሉ የሚገርመው ግን መሬት ላይ የሚፈጠሩ ተጨባጭ እውነቶችን ለመካድና ጥላሸት ለመቀባት የሚያደርጉት ሙከራ ሁሌም ራሳቸውን ዞሮ ሲመታቸው ማየቱ ያዝናናል። አከሌ የተባለ የዐማራ ሚዲያ ተከፋፈለ፣ አከሌ የተባለው የዐማራ ድርጅት ፈረሰ፣ ያኛው ከመንግስት ጋር እየተደራደረ ነው ይሄኛው ጠፍቷል ወዘተ ልብ ዎለዶቻቸው የሚሳለጡት ከፍተኛ በሚባሉ (high level cadres) ቢሆንም ውሃ ቢዎቅጡት እምቦጭ ብቻ። እነሱ ጠላትን ለማዎናበድ መጣላት እንዳለ፣ አንድነትና ህብረት ያልተማከለ በሚመስል ውብ ስንሰለት ሊታሰር እንደሚችል፣ትውልድና እውነታዎች በሚገባ እየተሰነዱና የማይናዎጥ መሰረት እየተጣለ መሆኑ በእርግጥ እየገባቸው አይደለም። አሁን ሁሉም ስልቶቻቸው ክብር ጥበብን ላስተማሩን አባቶቻችን ይሁንና ታውቀዋል ። በእርግጥ ብዙ ስራ አለ፤ ጉዞውም ረዥም ነው ትግሉም መራራ። አንዳንዴ ቁጭ ብለንባቸው የነበሩ ታላላቅ ድንጋዮችን መፈንቀል የግድ ይሆናል በስር አፈር ለብሰው ጊዜ ጠብቀው ሊነድፉን የሚያደቡትን እባቦች ጭንቅላታቸውን ለመምታት። ያኔ ድንጋጤዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ነገር ግን ከሁሉም በላይ የዐማራ የዘር ጭፍጨፋና ዘላቂ ጥቅም ይቀድማልናል። ያም ሆኖ ዐማራ በትክክለኛው አውራ ጎዳና ላይ ነው። ተዋቸው ይንጫጩ። የፈሰሰው የዐማራ ደም ፍትህ ያገኛል! ክብር ጥበባቸውን ላውረሱን አባቶቻችን! ክብር በዱር በገደሉ ለዐማራ ህልውና እየተሰውና ዋጋ እየከፈሉ ላሉ! ውርደት በሆዳቸው ለሚያስቡ ጸረ ዐማራ ሃይሎች!