ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 387
订阅者
+124 小时
+757 天
+1 40730 天
帖子存档
የወደቅህ ሲመስለው , የሚረዳህ ብታጣ , አለኝ ያልከው ሲከዳህ , ብቻህን ስትቆም ለክፋት ቢተባበሩብህ , ክፉ ጊዜያት በአንተ ላይ ሲያንጃብቡ , መንገድህን እንዳታቆም , ማንነትህን እንዳትቀይር የፀና ነው የሚያሸንፍ ወዳጀ !! ዴቭ ነኝ ከትግል ሚዳ

👌አስጨናቂው ዘሜ👏👏 የብልፅግና ሟርተኞች በማህበራዊ ሚዲያ ቢሟረቱብዎትም፤ እኛ ግን 24/7 ስራ ላይ ነን። አብይ አህመድ አሊ ወንበሬን ያፀኑልኛል ያላቸው ወታደሮቹ አልቀዋል። በቀተለይ በአማራ
+1
👌አስጨናቂው ዘሜ👏👏 የብልፅግና ሟርተኞች በማህበራዊ ሚዲያ ቢሟረቱብዎትም፤ እኛ ግን 24/7 ስራ ላይ ነን። አብይ አህመድ አሊ ወንበሬን ያፀኑልኛል ያላቸው ወታደሮቹ አልቀዋል። በቀተለይ በአማራ ክልል ከፋኖ ጋር ያለው ጦርነት ተስፋ ያስቆረጠው ይመስላል። የብልፅግና ውታፍ ነቃይ ከሆኑት ሐሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩት መካከል ናትናኤል በመኮንን ይገኝበታል። 👉በ2017 ዓ.ም አርበኛ ዘመነ ካሴን ከዚህ በኋላ አታገኙትም። እርማችሁን አውጡ ብሎ ለልሳኖቹ የተናገረውን ማስታወስ ይቻላል። በርቱ አርበኞቻችን ድል ለአማራ ፋኖ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

#ኮማንዶ_አብርሃም_መብራት(ዝምተኛዉ ሚሳኤል) ማነዉ? #ከሃይቁ_ስር_የፈለቀው_ወርቅ︎‼ ብላቴናዉ አዛዥ ኮማንዶ አብርሃም መብራት በልጅነቱ ታምር የሰራ፣ አለምን ያስደመመ ጀብድ የፈፀመ፣ በፋኖነት የትግል ዘመን ተስተካካይ የሆነ ታሪክ እስካ ያልተፃፈ ታሪክ በውቀት በክህሎት በጀግንነት በሞት አይፈሬ በልበሙሉነት ልዩ የሆነ ከወርቅ የደመቀ የድል ታሪክ ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድን እየመራ መፃፍ የቻለ ጥንቅቅ ያለ ጦር መሪ ነዉ። የ24 አመቱ ብላቴናው አዛዥ የጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ቲሊሊ ዘንገና ከብርጌድን እየመራ ከ65 በላይ አዉደ ዉጊያዎችን በልጅነቱ ተዋግቶ ያዋጋ አስደማሚ ድሎችን መፈፀም የቻለ የጠላት ራስ ምታት ለወገን መመኪያ አለኝታ የክፍለ ጦሩ ቋሚ አምድ ነዉ። በጦሩ የታፈረ የተከበረ የሚሳሱለት ከአይነ ልቦና የማይጠፋ  ስዕል ያለው፣ ሲናገር የሚጣፍት፣ ሰርቶ የማይታክት፣ ዝቅ ብሎ የሚያገለግል፣ ብሩህ አዕምሮ ያለዉ ልዩ ፍጥረት፣ ከባህሪ እስከ ሞራል ከእዉቀት እስከ ጀግንነት ተስተካካይ የሌለዉ የዘመናችን ጀግና #የወርቁ_ህዝብ_አብራክ....‼ የጠላትን ጦር ደረት እየበሳ፣ ግንባር እየበረቀሰ አንገት ድረስ የተሰራ ምሽግ እየደረመሰ፣ ግምባር ቀደም ተሰላፊ ፣በሔደበት ሁሉ ወገን አሳላፊ ፣ ፊት አዉራሪ፣ አንገት ደፊ ፣አንሰላሳይ መሪ፣ የጀግኖቹ ቁንጮ ማንም የሚመሰክርለት ልበ ሙሉ ብላቴና ነዉ። #ኮማንዶ_አብርሃም_መብራት(ዝምተኛው_ሚሳኤል) 1, ከሶማ የወታደራዊ ልህቀት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በአንደኛነት  ደረጃ ያጠናቀቀ፣ 2, የመከላከያ  ኮማንዶ ዩኒት ወንጀል መሪማሪ ደረጃ አንድ መሪ ! 3, በሰሜኑ ጦርነት በኮማንዶ ሀይል ውስጥ ከጅማሯ አስከ ፍፃሜው ከፍተኛ ተጋድል ያደረገ ሲሆን ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድን ባለፉት ሁለት አመታት እየመራ፦ 1, ሁለት ከረኔሎች (ኮረኔል ያሬድና ኮረኔል አባተን የማረከ፣ የገደለ)፡ 2,  ሁለት ድሽቃዎችን ከ10 በላይ ብሬንና 6 ስናፐር የማረከ፡ 3,  ዘጠኝ ሺ አለቃ መሪና መቶ አለቃዎችን ያስወገደ፡ 4,  አንድ  የመከላከያ ኮር ታዝዞበት በብቃት መመከት የቻለ፡ 5,  ብዛት ያላቸዉ ምርኮኞችንና መሳሪያ፣ ተተኳሽ፡ መገናኛ ሬዲዮ፣  31ሚ የጠላት ገንዘብ ጨምሮ የማረከ። 6, ከፉነተሰላም ማንኩሳ ቲሊሊ አሽፋና ዋካኒ ዳንግላ እንጅባራ ሰከላ ግምጃ ቤት አካይታ ምርክታ አምሳልታ ፋግታ አሽፋ መገንጠያ ደንስላሴ ዡጋ ውንድይ አዲስ ቅዳም ... በተደጋጋሚ  በተደረጉ ከ65 ጊዜ በላይ  አውደ ውጊያዎች ታላቅ ድል የተጎናፀፈ የዘመናችን ጦረኛ የጀግኖች መጠሪያ ነዉ። ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድን በልዩነት ከማዋቀር አስከ ሺዎች ጦር በማሰልጠን የሚያታግል፣ የሚመራ... የአገዉ ሸንጎን ምንነት ገና በእንጭጩ ተረድቶ እግር በእግር ተከታትሎ የእግር እሳት ሆኖ ዘወትር እየጠዘጠዘ ማጥፋት ማዳከም የቻለ! ለድፍን ሁለት አመታት ቲሊሊ ወረዳን ባጠቃላይ ከከተማ እስከ ገጠሩ ቀበሌ የፋኖ መዋቅር ተሰርቶ  ያለ ምንም ኮሽታ ያለምንም ባንዳ ዘራፊ ሌባ የፀዳ አድርጎ ማስተዳደር የቻለ!! ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድን አሰልጥኖ ጋናታና ሻምበል መሪነት ሆኖ እስከ ጦር አዛዥነት በወታደራዊ ዲሲፕሊ የታነፀ በችሎታው ያስመሰከረ ። በየ አወደ ዉጊያ በሮ እየደረሰ ስንቱን የወገን ሀይል ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ ያወጣ፤ የብረት አጥር ሁኖ ስንቱን ጠላት ውጦ ያስቀረ ታማኝ ፊት አውራሪ የዘንገና መሪ ነው .....‼ ሁለት ጉምቱ ኮረኔሎችን አንዱን ማርኮ ሌላዉን የገደለ ጀብደኛ ብላቴና መሪ...‼ ኮረኔል ያሬድ ኪሮስን መስከረም 29/2017 ዓ.ም ደን ስላሴ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ የብረት አጥር ሆን ማለፊያ መውጫ አሳጥቶ አስደማሚ ዉጊያ መርቶ መማረክ ሲችል፤ አለ የተባለዉን ኮረኔል አባተ ማሞ የተባለ ግዙፍ አገልጋይ  አሽፋ ዋካኒ ተራራ ላይ ከበባ ፈፅሞ በአፍ ጢሙ በመድፋት ቤተ መንግስት ድረስ ያናወጠ ጀብድ የፈፀመ፤ ብዛት ያለዉን የመከላከያ ሰራዊት ማርኮ ከ23,73,75ኛ ክፍለ ጦሮችን ድምጥማጣቸዉን ያጠፋ ታዛዥ ቅን መሪ። ከህዝቡ እስከ ጦሩ የሚከበር የሚታፈር ግርማ ሞገስ የተጫነው የአማራነት መለኪያ አምድ። መናገር መክለፍለፍ የማይወድ፤ እዩኝ እዩኝ የማይል፤ ንዋይና ስልጣን ማያታልለው፤ ለወጣለት አላማ ለአማራ ህዝብ ፍፁም የተገዛ፤ በማንነቱ ማይደራደር የሰው ልክ ከተባለ በቁጥር አንድ የሚጠራ፤ የቀጠናው ሚዛን አስጠባቂ ሸማቂ ኮማንዶ ነዉ። ማንም ያወራል እሱ ይሰራል💪 አማራ ጀግናህን እወቅ‼ እንደ ጀኔራል ተሾመ "አይዞህ አምበሳየ" በማለት ጦሩን እያበረታታ በሞራል በማዋጋት የሚታወቀው ብላቴናው ጦር አዛዥ ኮማንዶ አብርሃም መብራት (ዝምተኛው ሚሳኤል) #ያልተነገረለት_የቲሊሊ_ዘንገና_ብርጌድ_ጦር_አዛዥ‼ © በፋኖ አለበል አወቀ

ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም የማህበረሰብ ውይይቶች ቀጥለዋል የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር ሰዴ ወረዳ ሁለት ቀበሌወች ከሚገኘው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል። ድርጅታችን አሁን ላይ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ በማስረዳት ከሰዴ ወረዳ አዲስአለም ቀበሌ እና ሂወተ ሰላም ቀበሌ ካሉት ህዝብ ጋር ያለፉ ስራወችን በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ በፋኖ እና በህዝቡ መካከል ያለውን መስተጋብር ቀጣይነት ያለው ስራ ለመስራት ከውጊያው ጎን ለጎን ስርአት በመዘርጋት የወረዳ እና የቀበሌ አስተዳደሮችን በህዝብ በማስመረጥ ስርአት የመትከል ስራ ተሰርቷል። በሌላኛው መንገድ የ54ኛ ክ/ጦር በውስጡ ያሉትን ተወርዋሪ ሀይሎችን እና በውስጡ ካሉ የሰራዊት አባላት ጋር የቴድሮስ ዕዝ አማራሮቾ በተገኙበት ከሰራዊቱ የተነሱ መሰረታዊ ጥያቄወችን በመቀበል ለተነሱት ጥያቄ በቂ ምላሽ በመስጠት ከዚህ በፊት የነበረውን የሰራዊት እና የአመራር የስራ አፈፃፀም ገምግሞ የቀጣይ ምዕራፍ ስራወችን አቅጣጫ በመስጠት ለግዳጅ ዝግጅ ማድረግ ተችሏል።     ሐብታሙ የሱፍ ቴድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት      ጥቅምት28/2018 ዓ.ም

የአብይ አሕመድ ጨፍጫፊ ቡድን ዛሬ በሸዋ ደራ ገብሮ ቀበሌ በሪሳ ጎጥ የደረሰ አዝመራ በከባድ መሳሪያ አቃጠለ‼️ ትናንት ጥቅምት 27 እና ዛሬ 28/02/2018 ዓ.ም  በአፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ አፄ ዘረያዕቆብ ፩ኮር በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ የቃኝ ቡድን አገዛዙ ከሰፈረበት ድረስ ገብተው የተኩስ እሩምታ የተከፈተበትና የነበልባሎቹን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ኃይል ዲዳ አፋፍ ሆኖ በከባድ መሳሪያ  በማስወንጨፍ የደረሰ አዝመራ ላይ በመጣል  እየታጨደ የነበረ ጤፍ አቃጥሏል። በሌላ በኩል በከራባ ቀበሌ በወረወረው ቅንቡላ 3 ፍየሎች ላይ በማረፉ ገበሬ ቀን ያወጡኛል ብሎ እየለፋ ያረባቸውን በበቀል ጥሞኞች ተገድለውበታል። ይሔ ዘር አጥፊ የኦነግ ምልምል በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማራን እና የአማራን የሆነ ሁሉ ማውደም ማጥፋት ነው እና ተግባሩ ሁሉም አማራ ከፋኖ ጎን በመቆም እራሱንም ንብረቱንም ሊያድን ሊጠብቅ  ይገባዋል ሲሉ የአሳምነው ፅጌ ብርጌድ አናብስቶች ለንስር አማራ በላኩት መልዕክት ገልፀዋል‼️ ድል ለአማራ ፋኖ ድል ለአማራ ሕዝብ 28/ዐ2/2018 ዓ.ም

#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️ ከደብረ ማርቆስ ወደ ስናን ረቡዕ ገብያ አሁን ምሽት ላይ 4 ካሶኒ፣ 2 ሲኖ፣ 1 ኦራል ፣1 ፓትሮል መከላከያ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል አሁን ጭራወንዝ መሊትን አልፏል በፍጥነት ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት አስተላልፉ ፍጠኑ እባካችሁ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች መልዕክት አስተላልፈዋል‼️ ከምሽቱ 2:30 ሼርርርርርርር ይደረግ 28/ዐ2/2018 ዓ.ም

በባሕር ዳር ከተማ 4 ስፔሻሊስት ሐኪሞች  በፀጥታ ኃይሎች ታፋነው ተወስደዋል! 1. ዶ/ር መኩ ዳምጤ (የጠቅላላ እና የሚኒማል ኢንቬሲቭ ስፔሻሊስት ሃኪም፣ እኒህ ታዋቂ ሃኪም የባህርዳርን እና ከባቢውን ህዝብ ለ 20 አመት ያገለገሉ እና  አሁን ያሉትን የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቶች በሙሉ ያስተማረ መንገድ ያሳዬ ታላቅ ዋርካ የሆነ፤ እጁ ፈውስ የሆነ ሃኪም፣ መምህር፣ መሪ የሆነ 2. ዶ/ር ስመኘው (የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) 3. ዶ/ር ይበልጣል (የነርቭ እና የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ስፐሻሊስት) 4. ዶ/ር ዘላለም ስመኘው (የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) የመጀመሪያ ሶስቱ የታፈኑት በ 24/02/2018 ሰኞ እለት ሲሆን 4ኛው ዛሬ ሃሙስ  27/02/2018 ጥዋት ላይ ነው። የታሰሩበት ቦታ መጀመሪያ ሶስቱ ባህር ዳር ከተማ ጣቢያ 8 እና 4ኛው ጣቢያ 9 ነው። የእስር ምክንያት ጽንፈኛ አክማችኋል፡፡ እባክህ ድምጽ ሆናቸው ሌሎቹም ከስደት የተረፉት ተመሳሳይ እጣ በመፍራት ተገቢውን አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት ተቸግረዋል ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ በበርካታ ቀጠናወች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠነ ራሱን በሰው ሀይል እያጠናከረ ያለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ በመደራጀትላይ ያለችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን በቀን 27/2/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን ይታወቃል:: ይህን ሁኔታ ያየው የደሴ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና እና የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በቀን 28/2/2018 ዓ.ም በደሴ ዙሪያ ወረዳ የሚቀሳቀሰውን ፋኖ አጠፋለኩ ብሎ የመጣው የመከላከያ ሰራዊት ተብየውና የአድማ ብተና ሚኒሻና ፖሊስ ጥምር ጦር በሁለት አቅጣጫ መነሻውን ከደሴ አዲርጎ በጉጉፍቱና ከደሴ የተነሳው በአስግዶ በኩል በሁለት አቅጣጫ መቶ ፋኖ በሚቀሳቀስባቸው ቦታወች የገባው ጥምር ጦር አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃና አዲስ ተመራቂ ሰልጣኖች በምርቃት ማግስት የመጣውን ጥምርጦር ቀድሞ መረጃው ስለደረሰን አጥትመስበሪያና እሁዲት ተብለው የሚጠሩ ቦታወችላይ ደፈጣ በመያዝ የመጣውን ጥምርጦር በላጎ ተወርዎሪ ሻለቃ ሙትና ቁስለኛ አርጎ መልሶታል በዚክም መብረቃዊይ ጥቃት ሁለት መኪና እሬሳውንና ሶስት አቡላስ ቁስለኛውን ከደሴና ኮምቦልቻ ከኩታበር ወረዳ ተጨማሪ ሀይል አምጥቶ ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ እግሬአውጭኝ ብሎ ወደ ደሴ ከተማ ተመልሶ ገብቷል:: መዳረሻችን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልወና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ህልውናችን በተባበረ ክዳችን አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ከ/ጦር ‼️              በዛሬዉ የአዲስ ቅዳሙ  ልዩ ኦፕሬሽንየአድማ ብተና  ሻለቃ መሪዉ በቆንጆዎቹ ተቀንድሾል‼️                                                  የግምጃ ቤት ተወላጁ የአድማ ብተና ሃላፊ ሻለቃ አለማየሁ(ጃፍር) በአፋብኃ ቴዎድሮሰ  ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር በኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ነበልባሎች እና በክ/ጦሩ ተወርዋሪ (መች ሃይል) በተሰራ ሰርጅካል ኦፕሬሽን ወደ ላይኛዉ ተልኮል። ይቀጥላል ገና.......

አዲስ ቅዳም 💪💪💪 ዛሬ #ከአሽዋ_እስከ_አዲስ_ቅዳም ከተማ የጦር ሜዳ መገናኛዉን ጨምሮ ክላሽ እንደቆሎ ታፍሷል‼️ በአንድ በኩል የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ሊያደርግ ያሰበዉን ዉይይት ለማስተጓጎል በሌላ በኩል ኬላ ዘርግቶ ማህበረሰባችንን ለመዝረፍ አሰፍስፎ ዛሬ ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም ከአድጓሚ ተራራ እስከ አሽዋ ተዘርግቶ  የነበረዉ የብልፅግና ታጣቂ በፋኖ ሰይፍ እየተበላ  በወጣበት ቀርቷል። በዚህ እረመጧ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ እና ቁጡዎቹ  የክ/ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ ሀይል በሰሩት አስደናቂ ኦፕሬሽን የአድማ አዛዡን እና ዲሽቃ ተኳሹን ጨምሮ 22 የጠላት ታጣቂ ሲደመሰስ _ከ29 በላዩ ቁስለኛ ሁኗል። በምርኮ በኩልም _23 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ _1አንድ የጦርሜዳ መገናኛ ሬዲዮን _5 የእጅ ቦንብ                                                                   _328 የክላሽ ተተኳሽ ገቢ ተደርጓል። አዲስ ቅዳም ከተማ የተሰገሰገዉ ሆድ አደር ካድሬ በእየጊዜዉ የሚወገድበትን በመቶወች የሚቆጠር ታጣቂ "የድሀ ልጅ መተካት" በሚለዉ ፀረ ፍጥረት ፍልስፍናዉ ከላይ ከላይ  እየተካ ስልጣኑን ለማቆየት ቢጥርም ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ዉጭ ሁነዉበት  መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ እየፈራረሰ ይገኛል። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም ፋኖነት አሸናፊነት‼️

ጀምበር የጠለቀችበትና ተስፋ የቆረጠው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በብሔር እና በሐይማኖት ምክንያት የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት ጊዜ ለመግዛትና ዙፋኑን ለማፅናት በበጀትና በመዋቅር የተደገፈ ስራ እየሰራ ይገኛል:: የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በፋኖ የህልውና ተጋድሎ ተንኮታኩቶ ጀምበር እየጠለቀችበት ያለ ሲሆን ይህንን ሁኔታ በኢትዮጵያውያን የእርስ በርስ ግጭት ለመቀየርና ጊዜ ለመግዛት ሐይማኖትን እና ብሔርን መሰትረት ያደረገ ግጭት ለመቀስቀስ በበጀትና በመዋቅር የተደገፈ ስራ እየሰራ እንደሆነ በርካታ ጉዳዮችን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም በተለይ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሚንቀሳቀስበት አጠቃላይ በቤተ-አማራ ቀጠና የሃይማኖት ግጭቶች እንዲነሱና በህዝብ መጠፋፋት ዙፋኑን ለማፅናት በከፍተኛ ሁኔታ ስራ እየሰራ ያለ ሲሆን በቅርቡ ካየናቸው ተጨባጭ ምልክቶች በተጨማሪ ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ልዩ ስሙ ሮቢት አካባቢ ከባድ የጥፋት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የደህንነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል:: ስለሆነም መላው ህዝባችን ይህንን የብልፅግና አገዛዝ ፀረ-ህዝብ ድርጊትና እንቅስቃሴ በመረዳትና በመገንዘብ አንዳንድ ሁኔታዎችን ከመፈጠራቸው በፊት ተገቢውን ጥንቃቄና ክትትል በማድረግ ብሎም ችግሮች ቢፈጠሩም ድርጊቱ የፋሽስቱ አገዛዝ ተግባር መሆኑን በማወቅ ህዝባችን ሽ ዘመናትን የኖረና የተሻገረ አንድነትና አብሮነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ኃይሉን እየገነባ ይገኛል። https://youtu.be/1xG4AodrTYE?si=C8jgwOGX_PzHQo58

#አፋብኃ_እንደ_ንስር_ከፍብሎ_በመብረርላይ_ይገኛል የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ምስረታ ተጠናቋል። በስሩ ያሉት ክፍለ ጦሮች 54ኛ ክ/ጦር 64ኛ ክ/ጦር 74ኛክ/ጦርን በማቀፍ ምስ
+2
#አፋብኃ_እንደ_ንስር_ከፍብሎ_በመብረርላይ_ይገኛል የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ምስረታ ተጠናቋል። በስሩ ያሉት ክፍለ ጦሮች 54ኛ ክ/ጦር 64ኛ ክ/ጦር 74ኛክ/ጦርን በማቀፍ ምስረታው ተጠናቆ የኮሩ አመራሮችም በጋራ ትውውቅ በማድረግ ለቀጣይ ስራወች እራሳቸውን ዝግጅ በማድርግ ተልዕኮወችን በመስጠት በአዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ወደተግባር ተገብቷል። ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም የኮሩ አመራሮች በከፊል 👉

አዲስ ቅዳም 💪💪💪 ዛሬ #ከአሽዋ_እስከ_አዲስ_ቅዳም ከተማ የጦር ሜዳ መገናኛዉን ጨምሮ ክላሽ እንደቆሎ ታፍሷል‼️ በአንድ በኩል የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ሊያደርግ ያሰበዉን ዉይይት ለማስተጓጎል በሌላ በኩል ኬላ ዘርግቶ ማህበረሰባችንን ለመዝረፍ አሰፍስፎ ዛሬ ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም ከአድጓሚ ተራራ እስከ አሽዋ ተዘርግቶ  የነበረዉ የብልፅግና ታጣቂ በፋኖ ሰይፍ እየተበላ  በወጣበት ቀርቷል። በዚህ እረመጧ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ እና ቁጡዎቹ  የክ/ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ ሀይል በሰሩት አስደናቂ ኦፕሬሽን የአድማ አዛዡን እና ዲሽቃ ተኳሹን ጨምሮ 22 የጠላት ታጣቂ ሲደመሰስ _ከ29 በላዩ ቁስለኛ ሁኗል። በምርኮ በኩልም _23 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ _1አንድ የጦርሜዳ መገናኛ ሬዲዮን _5 የእጅ ቦንብ                                                                   _328 የክላሽ ተተኳሽ ገቢ ተደርጓል። አዲስ ቅዳም ከተማ የተሰገሰገዉ ሆድ አደር ካድሬ በእየጊዜዉ የሚወገድበትን በመቶወች የሚቆጠር ታጣቂ "የድሀ ልጅ መተካት" በሚለዉ ፀረ ፍጥረት ፍልስፍናዉ ከላይ ከላይ  እየተካ ስልጣኑን ለማቆየት ቢጥርም ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ዉጭ ሁነዉበት  መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ እየፈራረሰ ይገኛል። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም ፋኖነት አሸናፊነት‼️