ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多4 378
订阅者
-424 小时
+2487 天
+1 44230 天
帖子存档
⚫️ምስራቅ አርሲ የክርስቲያኖች የግፍ መሬት ናት ተባለ‼️
ሽርካ በሚባለው ወረዳ ብቻ ከሚገኙት 37 አብያተ ክርስቲያናት 17 ወይ ሙሉ በሙሉ ፈረሰዋል ወይም በጭፍጨፋው ምክንያት አገልግሎት አቁመዋል ብለዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ዐመታት ብቻ በሚታና ቀበሌ የ118 ኦርቶዶክሳውያን አባወራዎች ቤት ፈርሷል፣ ንብረታቸው ተወርሷል፡፡
አጥቢያዎቹን በተመለከት ዲያቆን አብርሃም ተስፋዬ የሚከተለውን ዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ደግሞ አስተያተ መስጫ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡
ሙሉ በሙሉ በአክራሪ ኀይሉ የፈራረሱና ከጥቅም ዉጪ የሆኑ ቅጽራቸው ሳይቀር የፈራረሰ፦
፩ አኖሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
፪ ላሉንጮ አማኑኤል
፫ ሰንጎ እግዚአብሔር አብ
አገልግሎት ያቆሙ
፩ ጮጫ እግዚአብሔር አብ
፪ ጪሳ ተክለሃይማኖት
፫ ጎሮ ሥላሴ
፬ ሄላ ሴሮ ማርያም
፭ ዘምባባ አርሴማ
፮ ዲገሉ መድኅንዓለም
፯ ኮኔ እግዚአብሔር አብ
፰ ሚታና ዮሐንስ
፱ ባቦ ማርያም
፲ ሰቄ ገብርሄል
፲፩ ጠሬታ በዓለ ወልድ
፲፪ ሽፎ ተክለሃይማኖት
፲፫ ያያ ዮሐንስ
፲፬ ሸንኮራ ቀርሳ ጊዮርጊስ
ፍትሕ በአርሲ እየተጨፈጨፉ ላሉ ኦርቶዶክሳውያን!
12/ዐ3/2018 ዓ.ም
አንድ አስገራሚ የሙስና ታሪክ በፕሬዝዳንት ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ የስልጣን ዘመን ይፈፀማል!
ጊዜውም ከ1930-1997 ዓ.ም ነበር።ይህ ፕሬዚዳንት ወደር የማይገኝለት ሙሰኛ እና አምባገነን መሪ ነበር።በዚህ አምባገነን ስርአት ውስጥ የኮንጎ ህዝብም ይሁን የኮንጎ የተፈጥሮ ሀብት የአምባገነኑ መሪ ጥሪት ሀብቶቹ ነበሩ።ትንሽ አለፍ ሲል ደግሞ የፕሬዝዳንቱ ጋሽአጃግሬዎች ንብረት ነበሩ ።በዚህ አምባገነን እና ሙሰኛ ስርአት የተማረሩት የኮንጎ ወጣቶች የትጥቅ ትግል በካንታንጋ ክፍለ ሀገር ጀመሩ።
እናም የትጥቅ ትግሉ መሪ ሎረንት ካቢላ ይባላል።ይህ ትጥቅ ትግል በሎረትት ካቢላ እየተመራ ድፍን 30 አመትና ከዚያ በላይ አስቆጠሩ።በዚህ 30 አመት የትጥቅ ትግል ዘመን የኮንጎን ህዝብ የስቃይ ዘመን ከማራዘምና በሁለቱም በኩል ስል በሆነ ካራ ከማሳረድ ውጪ አንድም ጠብ የሚልና ተስፋ የሚሰጥ ነገር ጠፋ።
ይህ አልበቃ ብሎ አማፅያኑ የፕሬዝዳንት ሞቡቱን ምት መቋቋም እየተሳናቸው መጣ።ይህንን ምት ተከትሎ የአማፅያኑ መሪ ሎረንት ካቢላ በ1965 ዓ.ም ለአለማቀፉ ማህበረሰብና የነፃነት ታጋዮች የድጋፍ ጥሪ አደረገ።ይህንን የሎረንትን ጥሪ ተከትሎ መቼም የአፍሪካን ጭቁኖችን ማገዝና መርዳት የሚያስደስተው በአለማቀፍ ዘንድ ዝነኛ የሆነውና የፊደል ካስትሮ የቅርብ ወዳጅና የትግል አጋሩ የሆነው እንዲሁም የኩባን አብዮት ዳር ያደረሰው ቼ ጉቬራ ከፊደል ጋር በመነጋገር አንድ መቶ የሚሆኑትን ኮማንዶዎችን ይዞ አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጦ በታንዛኒያ ድንበር በሚገኘው ፊዚ ባራክ በተሰኘው ኮረብታማ አካባቢ ይገኝ በነበረው የማዘዣ ጣቢያው ሲቀበለው ሻምፓኝ፥ውድ ውስኪ እና ቆነጃጅት ሴቶችን በማቅርብ ነበር። ያኔ! ነበር ቼ ጉቬራ በመገረም አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠን የመጣነው ልንሞሸር ነው ? ወይስ ልንታገል ? ብሎ የአማፂያኑን መሪ ሎረንት ካቢላን ሸንቆጥ አደረገው።ቼ! በኮንጎ እየቆዬ ሲሄድ የአማፅያኑ ባህሪ ተስፋ እያስቆረጠው ሄደ።አማፅያኑ ከተራው ተዋጊ እስከ አመራሩ ድረስ ምንም አይነት ድሲፕሊን ወይም ስርዓት የሚባል ነገር ፈፅም የሌላቸው ሆነው አገኛቸው።
ለምን 30 ዓመት ሙሉ በጫካና በዋሻ ውስጥ እንደኖሩ በግልፅ ገባው። እነዚህ አማፅያን ውድ መጠጦችን እና ሴቶችን ከከተማ እያመጡና እያስመጡ በዋሻቸው ውስጥ እየጠጡ እና እየጨፈሩ ጊዚያቸውን ማሳለፍ የዘወትር የማያቋርጥ ተግባራቸው ነበር።ቼ ጉቬራም እንዲህ ሲል ታዘባቸው።
አማፅያን በነጠላማ ጫማ፥ የውጊያ እና መሰል እቅድ የማይነድፍ አማፅያን እና የአማፅያን መሪ እና አመራር ፥ በመጠጥና በወሲብ ፍቅር አይናቸው የታወሩ የአማፅያን መሪ እና አመራር የት ይደርስ ይሆን ብሎ ትዝብቱን በውስጡ አስቀመጠ። እናም ወደ ሀገሩ ለመመለስ ወሰነ።ተመለሰም።ከተመለሰ በኋላ ለአለማቀፍ ጋዜጠኞች እንዲህ ሲል አስታወቀ፤እነኛ ላግዛቸው ብዬ ውቅያኖስ አቋርጬ የሄድሁባቸው አማፅያን ምንም አይነት አላማ የላቸውም።
ስራና ተግባራቸው በሙሉ ዳንስ ፥መጠጥና ወሲብ ነው። እናም እግዚአብሄር ረድቷቸው ስልጣን ቢይዙ እንኳ ህዝባቸውን ወደ ባሰ ድህነትና ጉስቁልና የሚወስዱት ይመስለኛል ብሎ ቼ! የታየውንና የታዘበውን ለአለማቀፉ ማህበረሰብ አጋራ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጣም የሚገርመው ነገር የእነሎረንት ካቢላ የትጥቅ ቡድንና የነፃነት ተዋጊዎች አብረዋቸው ሊታገሉ ጫካ የወጡትን የኮንጎ ሴቶችን ለወሲብ ተግባር ይጠቀሙባቸው ስለነበር አንዳንድ ዕድለኛ ሴቶች እመቤቶች ለመሆን በቅተው ነበር።
እናም አንድ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተወለደ ልጅ የኮንጎ ፕሬዚዳንት መሆኑ ነው።ስሙም ጆሴፍ ሎረንት
ካቢላ ይባላል።አይገርምም? አስባችሁታል? ይህ ፕሬዝደንት ለህዝቡ ምን ሊሰራ እንደማችል?ብቻ ዝም ነው!አባትዮው ዳኛ! ልጅዮው ቀማኛ! ማለት እንዲህ አይነቱን አይደለም ወይ?
የአማፅያኑ መሪ ሎረንት ካቢላ ጫካ በወለደው ልጁ ጆሴፍ ሎረንት ካቢላ ሲተካ ምኑ ነው ለውጡ ያላችሁኝ እንደሆነ መልሱ የጊዜ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ለኮንጎ ህዝብ ምንም ጠብ የሚል ነገር ያለለት ነገር የለም።
ምክንያቱም በጫካ ውስጥ እና በዋሻ ውስጥ ሽርሙጥናና መጠጥ የለመዱ አእምሮዎች ቤተ መንግስት ሲገቡ ምኑን ከምን ያድርጉት?! ይኸው ዛሬም ድረስ ያቺ የዩራኒዬም ማዕድን ባለቤት የሆነች ሀገር፥ያቺ የአልማዝ ማዕድን ባለቤት የሆነች ሀገር፥ያቺ የኮባልት ማዕድን ባለቤት የሆነች ሀገር፥ያቺ የወርቅ ማዕድን እንደድጋይ የሚታፈስባት ሀገር ዛሬም ድረስ በጦርነት እና በችግር እንዲሁም በድህነት አዙሪት ውስጥ ትገኛለች።ይህ የሚያሳየን አንዳንድ የነፃነት ትግል ተብለው የተጀመሩት እና ብዙ ዋጋ የተከፈለላቸው ትግሎች የተነሱለትን አላማ ግብ ሳይመቱ ህዝባቸውን ወደባሰ ድህነት እና ጉስቁልና እንዲሁም ውርደት ይከታሉ።በሌላ በኩል የምስራቅ አፍሪካው ተገንጣዩ ሻበያ በኤርትራ ሰማይ ስር ለ30 ዓመታት እንዲሁ የነፃነት ትግል አድርጊያለሁ ይለናል።
ለካ! ነፃነት ማለት ድንበር ከልሎ ወንዝ ላይ ታንክና መድፍ አጥሮ ህዝቡን ወደየትም እንዳይንቀሳቀስ እና በድህነት አረንቋ እንዲማቅቅና እንዲሁም ከአለማቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሲነፃፀር ኋላ ቀር ሆነው ለአንድ ግለሰብና ለአንድ ፖርቲ ታማኝ መሆንና እንዲያም ሲል
በባህር እየገቡ የሻርክ ቀለብ መሆን ነው ለካ!!ድንቄም!ተመረቀች አሉ አያ አቡሀይ!እና ምን ይሁን ነው የምትለኝ? አንዴ የኮንጎ አማፅያን ታሪክ እያነሳህ ታወራኛለህ?አንዴ የሻበያን ታሪክ እያነሳህ ታወራኛለህ? ወያኔስ ቢሆን አስራ ሰባት አመት ሙሉ ሲዘርፍና ሲቀማ አይደለም እንዴ የኖረው? ይህ የጫካ ባህሪው 4 ኪሎ ድረስ ተከትሎት መጦ ከመርከብ እስከ አውሮፕላን አልሸጠም ወይ? ኢትዮጵያን ለጊዚያዊ ጥቅም ሲል አንገቷን ቆርጦ የባህር በር አላሳጣትም ወይ?! ኧረ ስንቱ?!!! የሁቱ አማፅያን በየመንስ ለነፃነት ብሎ ወጦ አገሩን ወደ ፍርስራሽነት አልቀየራትም ወይ?!ዜጎቿን ጠቅልሎ አገር አልባ አላደረጋትም ወይ?!ብቻ! ሆድ ይፍጀው?! ይብቃን አይደል?! ኧረ?! አንድ የረሳሁት የአሳማዎችና የሁሉ ኬኛ ድርጅትስ ለ62 ዓመት ጫካ ውስጥ ሲደንስ እና ሲዘርፍ እንዲሁም ያገኛትን ሴት ሁሉ ሲደፍር አልኖረም ወይ?!
አያችሁ ! የጫካ ውስጥ ልምምድ ምን ያህል አደገኛ መሆኑን!? በሰባት ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያን መቅኒዋን መጠው! አጥንቷን ግጠው! ህዝቦቿን ገለውና አፈናቅለው እንዲሁም ወንዱንም ሴቱንም ደፍረው እርካታ የሌላቸው የኦነግ ጭራቆች አይደሉምን?! እናም አንዳንድ የነፃነት ትግሎች ነፃነትን ገድለው በምትኩ ጭቆናን ሲያስፋፉና አምባገነንነትን ሲወልዱ ስታይ !? እኛም ከዚህ መማር አለብን እያልሁ ነው ወዳጄ!!!?
፨፨፨በመጨረሻም፨፨፨
እንድህ ስል የግል ሀሳቤን ለወንድሞቼ፥ለእህቶቼና ለትግል ጓደኞቼ መልዕክት አስተላልፋለሁ።
፨የነፃነት ትግሎች ሁሉ መጨረሻቸው ነፃነትን ማፅናት እንጂ ጭቆናን መውለድ የለባቸውም!
፨ነፃነት የሌለው የነፃነት ታጋይ ነፃነትን ሊያመጣና ነፃነቱ ቢመጣ እንኳ በዘላቂነት ሊያስጠብቀው አይችልም!
፨በጫካም ቢሆን በስርዓትና በአላማ ውስጥ ነፃነት ለነፃነት ታጋዮች ሁሉ ያስፈልጋል !!
በሌላ ጊዜ ጓዶቹ ሌላ ይጠቅማል የምለውን መሳጭ የትግል ታሪክ ይዤላችሁ እመጣለሁ። እስከዛው ቸር እንሰንብት?!
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር የ44ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
የመልሶ ማደራጀት ስራው በዶክተር ጋሹ ክንዱ እና አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
የአገዛዙ ወታደሮች ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን ሲያሸብሩት ዉለዋል።
ዛሬ ህዳር 12/2018ዓ.ም
ቂሊንጦ ማረሚያ ዞን ሁለት በሽብር ተከሳሾች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመዋል።
አገዛዙ ሜዳላይ የገጠመዉን ሽንፈት ከሁለት አመት በላይ ያለፍትህ አስሮ በሽብር ከሶ በሚያሰቃያቸዉ የግፍ እስረኞች ላይ በበቀል ስሜት እያሰቃያቸዉ ይገኛል።
አገዛዙ በደነገጠ ቁጥር በሽብር ተከሳሾች ላይ ድብደባ እና ማዋከብ እየፈፀመ ይገኛል።
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ዞን ሁለት ላይ ከዚህ በፊትም በሽብር ተከሳሾች ላይ ከፍተኛ ድብደባ እና ዛቻ ተፈፅሟል።
ዛሬ ህዳር 12/2018 ዓ.ም በማረሚያ ፖሊሶች እና በፌደራል ፖሊሶች ከተደበደቡ የሽብር ተከሳሾች መካከል...
1, ሔኖክ ዋለ
2, አሸናፊ መለሰ
3,ዳዊት እባቡ
የተባሉ በማንነታቸዉ የታሰሩ ግለሰቦችን ከታሰሩበት ክፍል አስወጥተዉ በማናለብኝነት በአገዛዙ ወታደሩች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።
በከፍተኛ ድብደባ የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ ቢሆንም ህክምና ተከልክለዉ አሁንም በከፍተኛ ህመም ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸዉ ለሚዲያችን ተናግረዋል።
የሰባዊ መብት ተሟጋቾች እና ገለልተኛ ተቋማት ጉዳዮን እንዲከታተሉ እና ጉዳት የደረሰባቸዉ ህክምና እንዲያገኙ ጫና እንዲያደርጉ ቤተሰቦቻቸዉ ጠይቀዋል።
‼️ደምበጫ የጠላት መቅጫ‼️💪💪💪
ዛሬ ደምበጫ ላይ ሬቻውን የበላ የነሽመልስ አብዲሳ መልዕክተኛ ነው፡፡
አብይ አህመድ ለተባለ ቀውስ የግል ስልጣን የድሃ ልጅ በመላው አማራ ምድር የአሞራ ሲሳይ እየሆነ ይገኛል። በተለይ የኦሮሞ እና ደቡብ ወጣት ምንም ባልገባው ጦርነት የእሳት እራት እየሆነ ነው ያሳዝናል መካሪ ትልቅ ሰው ማጣት።
ሰበር ዜና!
ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት በተደረገ የአጭር ሰዓት ማጥቃት ከ20 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ!
ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን መናገሻ ከሆነችው ከወልድያ ከተማ በውስን ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ጃርሣ ቀበሌ ዛሬ ህዳር 12/2018 ዓ/ም አመሻሹን ባካሄደው የአጭር ሰዓት ማጥቃት፡ በጠላት ኃይል ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ድርብ ድል ተቀዳጅቶ ማምሸቱን ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
ዕዙ፡ በሦስት ክፍለጦሮች ስር ከሚገኙ ሻለቃዎች የተወጣጡ ውስን የፋኖ ቃኚዎችን ብቻ በማሰለፍ በጥቂት የሰው ኃይልና በአጭር ሰዓት ባካሄደው ፈጣን ማጥቃት፡ ከ20 በላይ የብልፅግና ቡድን መከላከያ ሰራዊት አባላትን ሲገድል በርካቶችን ለከፋ ጉዳት ዳርጓቸዋል።
ፀረ አማራው ኃይል በዚህ ምሽት ቁስለኛና አ*ስ*ከ*ሬ*ኑን በበርካታ ተሽከርካሪ ጭኖ ወደ ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አል አሙዲን ስታዲየም እያጓጓዘ ነው።
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት እየከዳና እየኮበለለ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ መሆኑ ይታወቃል::
በዚህም ሰባት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት አባላቶች ስምንት ክላሽ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመያዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዙ23 ማራኪዎቹን ካላኮርማ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
እነዚህ ከኮበለሉት ሰራዊቶች መካከል አንደኛው ሁለት ክላሾችን በመያዝ ፋኖን የተቀላቀለ ሲሆን አጠቃላይ ሰባቱ አባላቶች ስምንት ክላሽ፣ 1260 የክላሽ ተተኳሽ፣ 9 F1 ቦምብ፣ እና 7 የወገብ ትጥቅ ይዘው ካላኮርማ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 13/2018 ዓ.ም
የካላኮርማ ክፍለጦር አሳምነው ክፍለጦር እና ዞብል አምባ ክፍለጦር የሻለቃ ቃኞች በጥምረት ወልድያ ጃርሳ ላይ ታላቅ ጀብድ ፈፀሙ::
ከወልድያ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ጃርሳ ከተማ ህዳር ሚካኤልን እያከበሩ በነበሩ የሶስቱ ክፍለጦር ማለትም የካላኮርማ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ቃኝ፣ የአሳምነው ክፍለጦር 4ኛ ሻለቃ ቃኝ እና የዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ቃኝ፣ አሃዶች ላይ ተኩስ የከፈተው የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከንስሮቹ በተሰጠው ምላሽ ከ20 በላይ አስከሬን ይዞ ወደመጣበት ተመልሷል::
ተጋድሎው ዛሬ ህዳር 12/2018 ዓ.ም ማምሻውን የተደረገ ሲሆን ከወልድያ ከተማ በመኪና ተጉዞ የመጣው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ፋኖዎች በዓል እያከበሩ ባሉበት ተኩስ ቢከፍትም በአጭር ሰዓት ውስጥ ከባድ ምት የተመታ ሲሆን ከ20 በላይ ሙትና ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛም ይዞ ተመልሷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
ዛሬ ነው ደንበጫ ላይ የተደመሰሰ!
አብይ አህመድ ለተባለ ቀውስ የግል ስልጣን የድሃ ልጅ በመላው አማራ ምድር የአሞራ ሲሳይ እየሆነ ይገኛል። በተለይ የኦሮሞ እና ደቡብ ወጣት ምንም ባልገባው ጦርነት የእሳት እራት እየሆነ ነው ያሳዝናል መካሪ ትልቅ ሰው ማጣት።
+4
ህዝባዊ ዉይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ጀግና የጦር ገበሬ ለሆኑት በኮሩ ጦር መሪ በኮረኔል አደመ የሰንደቅ አላማ ሽልማት ተበረከተላቸው።
በቢቡኝ ወረዳ ኮረፍታ ነዋሪወች ጋር ድረጅታችን በየቀኑ አሰራሩን እያዘመነ አደረጃጀቱን እያስተካከለ የጠላትንሀይል እያፈራረሰ የጉዞ ፍጥነቱን አስተካክሎ መራመዱን ቀጥሏል።
አሁን ያለንበትን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በቢቡኝ ወረዳ ኮረፈታ አካባቢ ከሚገኙ ከገበሬ ጦሩ ጋ ሰፊ ዉይይቶችን አድርገናል
በዚህ መድረክም ይህን ጨካኝ ስርዓት ከስሩ ነቅለን እስካልጣልነው ድረስ እንቅልፍ አንተኛም በሄዳችሁበት እንሄዳለን ሜዳውም ተራራውም የኛነው አለንላችሁ የጀመርነው እኛነን የምንጨርሰውም እኛነን ሲሉ በወኔ አርበኝነታቸውን ገልፀዋል።
እስካሁን ድረስ በነበረው ትግል ጀግና የገበሬ ጦር አመራር ለሆኑት በኮሩ ጦር አዛዝ በኮረኔል አደመ አማካኝነት የሰንደቅ አላማ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የ201ኛ ኮር አስ/ር የ54ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የግዜዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት የቀጣይ አቅጣጫወችን በመስጠት ተጠናቋል።
የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 11/2018 ዓ.ም
መብረቁ እውነትም መብረቅ ሆነዋል ‼️
#ሞጣከተማ_ኮሊሳ_ላይ_ጠላት_ተቀጥቅጧል
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
አይበገሬወች በተግባር አስመስክረዋል ስም እና ምግባር ማለት ይኸ ነው በዛሬው እለት ጠላትን ሲያስለፈልፉት የዋሉ ሲሆን ሽንፈቱን ማረጋገጥ ያቃተው የጁላ ጦር የጀግኖችን ቀየ መድፈር አልቻለም።
በ201ኛ ኮር በ54 ክ/ጦር ውስጥ ከሚገኙት ወረዳወች መካከል በሞጣ ኮሊሳ ዙሪያ ተንቀሳቅሶ ለመክበብ ቢሞክርም ነገሩ ተገልብጦ በቆንጆወቹ ከበባ ውስጥ ለመውደቅ ችሏል።
#መብረቆቹ_ጠላትን_መውጫ_መግቢያ_አሳጥተው የብርሀኑ ጁላ ጦር በየቦታው ሲያዝረከርኩት የዋሉ ሲሆን ከ ከ11 በላይ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኞችን በአንቡላንስ ሲያመላልስ አርፍዷል። የኖወችን ብትር መቋቋም ሲያቅተው አስክሬን እና ቁስለኞችን ለማንሳት ከከበባው ለመውጣት ከሞጣ ተጨማሪ ሀይል ዙ= 23 በማስመጣትና ለማምለጥ ቢሞክርም የተማረከው ተማርኮ ሙትና ቁስለኛውን አስታቅፈው ሸኝተውታል።
የምርኮ ፎቶወች እንደደረሰን እናጋራቹሀለን..?!
የአፋብኃ ቴድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
+2
የድል ዜና ከወለጋ ምድር!!
ለመጨረሻ ግዜ የአማራ ፋኖ በወለጋን አጠፋለሁ ብሎ ከዬአቅጣጫው ተሰባስቦ ተማምሎ የገባው የኦሮሚያ ጥምር ጦር በድሮንና በሊኮፍተር ቢታገዝም ከሞት አልተረፈም።
በአሁኑ ስዓት ውባንጭ ቀበሌን በመልሶ ማጥቃት ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠው የአማራ ፋኖ በወለጋ በአይነቱ ለየት ያለ ድል አስመዝግቧል ጦርነቱ ከጀመረበት የሁለት ስዓት ምንገድ እያራዎጠ እዬነዳው ይገኛል ጫካዎቹ በሙትና ቁስለኛ ተሞልተዋል።
የተረፉት ቀዬጫካው እዬተለቀሙ ይገኛሉ።
አርበኛ አደም ተፈራ የዋዛ አደለም💪💪✊✊ አርበኛ አለፈ💪💪💪
+1
አሁን ጎጠኝነት ካልሆነ በስተቀር በላስታው ግዙፍ ኮር አማራ የሆነ ሰው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ይሰራል ?
እውነት በናንተ ተልካሻ ቅርሻት የአሳምነው ልጆች ሸብረክ የሚሉ መስሏችሁ ነበር ?
የአሳምነው ልጆች እዚህ የደረሱት ዝም ብሎ መሰለህ ?
👉ሰው ናቸውና እርስ በርስ ሲጋጩ እርስ በርስ #ሽማግሌ ሆነው ነገሩን በማብረድ
👉ሰርጎ ገብ ጎጠኛ ሊከፋፍላቸው ሲሞክር እንደ አንድ #ቤተሰብ እጂለጂ ተያይዘው ሴራውን በማክሸፍ
👉የአብይ አህመድ ወራሪ ወታደር አደገኝነታቸውን በመረዳት ብዙ ሰራዊት እና ድሮን ሲያሰልፍባቸው #በጀግንነት ተዋግተው ዋጋ በመክፈላቸው
😁በጥቅም እና በውሸት ሳይሸነፉ #የአባታቸውን አደራ ጠብቀው በመቆየታቸው
በዚህ ሁሉ መከራ መሀል አልፈው ልምድ ስላካበቱ በተራ ወሪ ሊረቱ አይቻላቸውም
ይህንን ግዙፍ ኮር ማበረታታት ከዚህ በላይ ከፍ እንዲል ማገዝ እንጂ በሀሰት ወሬ ጀግኖችን እየነጠሉ መምታት ለማዳከም መሞከር ቅሺምና ብቻ ሳይሆን ባንዳነትም ነው
❗️ ዳግማዊ አሩሲ በጎጃም ደምበጫ😭😭😭😭
አመታታዊ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ ባዕል በሚያከብሩ ሁለት የሀይማኖት አባቶች(ካህናትን ) በደምበጫ ወረዳ የደገራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመግባት በነፍሰ በላው ዙፋን ጠባቂ የመከላከያ ሰራዊት በግፍ መረሸናቸውን የአይን እማኞች ገለፁ።
ቀን 12/3/2018 ዓ.ም 👈
#ስናይፐር_ይዞ_ፋኖን_ተቀላቅሏል!
የመዋጋት ሞራሉ የላሸቀው የብልፅግና ሰራዊት በየቀኑ እየከዳ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ይገኛል።
##ምክትል_አስርአለቃ_መልካሙ_ስማቸው 22ኛ ክፍለጦር ውስጥ የሚገኘው የጠላት ካምፕ የነበረ ሲሆን 01 ስናይፐር በመያዝ የ105ኛ ኮር 66 ክ/ጦር አባይ መተከል ሻለቃን ተቀላቅሏል።
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 12/2018 ዓም
#ስናይፐር_ይዞ_ፋኖን_ተቀላቅሏል!
የመዋጋት ሞራሉ የላሸቀው የብልፅግና ሰራዊት በየቀኑ እየከዳ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ይገኛል።
##ምክትል_አስርአለቃ_መልካሙ_ስማቸው 22ኛ ክፍለጦር ውስጥ የሚገኘው የጠላት ካምፕ የነበረ ሲሆን 01 ስናይፐር በመያዝ የ105ኛ ኮር 66 ክ/ጦር አባይ መተከል ሻለቃን ተቀላቅሏል።
አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 12/2018 ዓም
የአረመኔው ጡት ቆራጭ የብልፅግና መቶ መሪ የደባይ ጮቄ የፋኖ ኃይሎችን ተቀላቀለ
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል/አፋብኃ/ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦ ፲ አለቃ #ማስረሻ_አሰማ_መሠሉ የተባለ የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ በአማራ ህዝብ ላይ እየደሰሠ ያለውን አረመኔያዊ ሰቆቃ በመረዳት በዛሬው ዕለት ደባይ ጮቄ ሻለቃን ከነ ሙሉ ትጥቁ ቸቀላቅሏል።
፲ አለቃ ማስረሻ አሰማ መሠሉ በመከላከያ ሰራዊት
6ኛዕዝ 52ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻምበል ውስጥ ጋንታ መሪ የነበረ ሲሆን በዛሬው በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ ፋኖ ናችሁ ትግፋላችሁ በሚል በሙሉ የአማራ ተወላጅ መከላከያ ሰራዊት አባላትን ትጥቃቸውን በማውረድ በማሰርና በማሰቃየት ላይ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ዛሬ ላይ ከአማራነቴ ማማ ላይ ከምወዳቸው ጓዶቼ ጋር በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ ሲል ደስታውን በመግለፅ ለቀጣይ ይህንን አረመኔያዊ ስርዓት ከወንድሞቹ ጋር በመሆን ትግሉን እንደሚቀጥል አውስቷል!!!!
አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋአዲስ አስተሳሰብ
Hailemariam Kiber Temesgen
አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
